• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ወደው አይስቁ”

January 19, 2014 11:22 pm by Editor 3 Comments

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።

የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”

በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል።  የሚናገሩትን አያውቁትም። የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ። እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።

anole3ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣  የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም። “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል።  ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል።  እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም።  እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…

በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ።  የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው። ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።

“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው።  “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።

አጼ ምኒሊክ አምስት ሚሊዮን ጡት ቆርጠዋል ሲሉን ግን፤ ስሌቱ ላይ የቤት ስራቸውን በደንብ የሰሩት አይመስልም። በአጼ ምኒሊክ ዘመን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ቁጥሩ ስምንት ሚሊዮን ነበር። የአምስቱ ሚሊየን ህዝብ ጡት ከተቆረጠ፣ በዘመኑ ወንዶቹም ጡት እንደነበራቸው ያመላክታል። ግን ያንን ሁሉ ጡት እንዴት ሊቆርጡት እንደቻሉ ተናጋሪው አላብራሩም።  ስልጣኔን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት አጼ ምኒሊክ በመጀመሪያ ያደረጉት የጡት መቁረጫ ማሽን ማስገባት መሆኑን ከጉግል ላይ በቅርቡ ሊገኝ ይችላል።

ጉግል፣ ጉግል፣ጉግል፣ጉግል፣ … እያለ መነጋገርያውን ለቆ ወረደ – የምኒሊክን አዲስ ታሪክ የሚያስተምረው።

“ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል።… ይህንንም በቅርቡ ይፋ በሚሆነው ጥናት ታገኙታላችሁ… ።”  የሚል ሌላ ተናጋሪ መድረኩን ይዞ ሲናገር ከማርስ የመጣ ፍጡር ነበር የመሰለን።

ጨርቁን ጥሎ እርቃኑን መንገድ ለመንገድ የሚሄድ፤ ወይንም ደግሞ እጅና እግሩ በሰንሰለት የታሰሩ ሰው ስናይ፤  በተለምዶ ይህ ሰው አብዷል እንላለን – ውጭውን ብቻ አይተን። ጥሩ ልብስ ለብሰው በስነልቦና እና በአእምሮ መታወክ የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ እብዶች እንዳሉ ብዙውን ግዜ እንዘነጋለን።  እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች በቀን ቅዠት የሚሰቃዩ፣ የስነምግባርና የሞራል እስረኞች በመሆናቸው አእምሯቸው ይታወካል። በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የአጼ ምኒሊክ ጣእረ ሞት እየመጣ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነው።

ፓልቶክን ከሰባት አመታት በኋላ መስማቴ ነው።  ይህን ትልቅ መድረክ፣  አንዳንዶች ታሪክ ሰርተውበታል። ሌሎች ታሪክ ሲያወሩበት ሰንብተዋል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ታሪክ የሚያጎድፉ ጉዶች ይዘውታል። ከሰባት አመታት በኋላ የኛ ፓልቶክ ሽቅብ ሳይሆን ቁልቁል አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ቢገርመኝም፤ በአንጻሩ ግን እንደ አዝናኝም እየሆነ መምጣቱን አልጠላሁትም።

እንደሰማነው የፓልቶክ ርእሱ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አልተቀየረም። የዛሬውም መነጋገርያ ርእስ ዳግማዊ ምኒሊክ ናቸው። እኚህ መሪ ካለፉ እነሆ መቶ አመት ሆናቸው። “የሞኝ ለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ!”  እንዲሉ አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ስለ አጼ ምኒሊክ አውርተው ሌሊቱንም ይመለሱበታል። ዛሬ ግን ወሬውም፣ ስድቡም ያለቀባቸው ይመስላል። ዛሬ ስለጀኖሳይድ እያወሩ አይደለም። ይልቁንም ጀኖሳይድ እያወሩ ነበር። ወንጀሉን ራሳቸው በቃል እየፈጸሙት…።

ሌላኛው ተናጋሪ ተራውን ጠብቆ መነጋገርያውን ያዘ። የተለመደውን የአጼ ምኒሊክን አጽም ከመቃብር እየጠራ ካወገዘ በኋላ፤ እንዲህ ሲል ተናገረ። “… አበበ ቢቂላን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ አድርገው ታላቅ በደል ፈጽመውበታል።”

መቼም ወደው አይስቁ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች እንኳ አይፈረድባቸውም። ገና ሃገር ሲለቅቁ የለቀቁ ስለሆኑ ለክርክርም አይመቹም።  “አበበ ቢቂላ በሮም እና በቶክዮ ላይ የሮጠው በአጼ ምኒሊክ ዘመን ነው።” ብሎ ከሚከራከር ሰው ጋር ሙግት መግጠም እብደት ይሆናል።

“የቁቤ ትውልድ ነን።” የሚል ሌላ ታናጋሪ ደግሞ መጣ። ይሄኛው ደግሞ የቆሪጥ መንፈስ የሰፈረበት ሳይሆን አይቀርም። የሚያወራው ሁሉ ስለ መቁረጥ ብቻ ነው። ሚኒሊክ ጡት፣ እጅ፣ ቆለጥ፣ እግር፣ ጥፍር … ቆርጠዋል አለን። እንደታናጋሪው ከሆነ እኚህ መሪ ያልቆረጡት ብልት የለም። ሃገር ማስተዳደሩን ትተው አስራ ሁለቱንም የሰውነት አካል ሲበልቱ ኖሯል!

አርፍደው የሚገቡት ተሳዳቢዎች ከአፋቸው የሚወጣውን ጸያፍ ስድብ ለመድገም ይዘገንናል።  በ”ምሁሮቻቸው” ገለጻ መሃል እንደ አዝማች ጣልቃ እየገቡ በአማራው ህዝብ ላይ ይወርዱበታል።  በዚህ ሁሉ መሃል ትንሽ የገረመኝ አንድ ክስተት ነበር።  የክፍሉ መሪ በስድድቡ መሃል ገብቶ በኦሮምኛ እንዲህ ሲል ተናገረ።

“ጀሪን ወል አኛተኑ። ማይኪ ኢቲ ኬኒ። ኑ ሂንደጌኛ”።

ወደ አማርኛው በግርድፉ ሲመለስ፣ “ማይኩን ስጣቸው። እነሱ እርስበርስ ይባሉ። እኛ እንሰማለን።” እንደማለት ነው።  ዋናው ጨዋታ እዚህ ላይ ኖሯል። ምክንያቱም ይህንን ውግዘት እና ውርጅብኝ ሜንጫዎቹ ያለምክንያት በዚህ ሰዓት አላነሱትም። ነብሳቸውን ይማርና  አፄ ምኒሊክ ካረፉ 100 አመት አለፈ። የሙት አመታቸው መከበር ከጀመረ ደግሞ 70 አመት ሆነው። ይህንን ወቅት ጠብቆ በአማራ እና በክርስትና እምነት ላይ ለመዝመት የሚደረገው ሙከራ፣ ግብታዊ ሳይሆን በጥናት የተደረገ ስለመሆኑ ያመላክተናል። ግርግር በመፍጠር እና ዜጎችን እርስበርስ በማባላት፣ ትንሽ የፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚፈጸም የፖለቲካ ዝሙት መሆኑ ነው።

ልብ በሉ! የዚህ የሜንጫ ዘመቻ መሪዎች ኦሮሞዎች አይደሉም። አብዛኞቹ በግማሽ ከሌላ ዘር የሚወለዱ ናቸው። በእምነታቸውም ሆነ በዘራቸው የተቀላቀሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ።

ስድስት ሚሊየን አይሁዶችን የፈጀው አዶልፍ ሂትለር ግማሽ አይሁድ እንደነበር አንዘንጋ።

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tezebtu says

    January 21, 2014 08:10 am at 8:10 am

    Woy…wayane dagmo bezeh meta be ‘Ye Burka Zemita’ alesaka bilaw.dagmo kasamonu yeset belet hawult yesaral…kkk.kk
    enya oromowoch mogn aydalanem woyane kaya beher beherasabu leyagachan yemifalegaw egnan ansto hawlet teklo oromo yehen yemaslal lemalat naw.nuti oromo loon miti kan wayanen nuti taphatu taphni isa kan amma kun immo nu saba sablamota ethiopia wajjin waliti nu naqee gar gar nu baasudhaaf .

    Reply
  2. በለው! says

    January 22, 2014 01:55 am at 1:55 am

    >>> አሁን ባለንበት የቁቤ (የዕቁብ)ትውልድ እያሉ እራሳቸውን የሚያጃጅሉ የሞቀ ውሻ(ሆት ዶግ)ተጠቃሚ አካላት “ሜንጫ የሙስሊም ኦሮሞ አብዮት አራማጆች ሀገርና ትውልድ አምካኝ የፖለቲካ ተንታኝ ህብረተሰብ በታኝ ሆነው፡ አንዳንዶች ባንዳ (ሹምባሽ) በክቡር ገብረመድክን አርዓያ መዝገበ ቃል (የባእድ ወራሪ ዶሮና እንቁላል አቅራቢ) …በፋፋና በዱቄት ወተት የተሸጡ…ከሻቢያ በጉዲፈቻ ኦሮሞ ቤት ጮጮ ልሰው ያደጉ (ጆሌ ቢሸፍቱ)”የኦሮሞ ዝምታ!” የሰላቢው ማስታወሻ” “የሰላዩ ጉዞ” በተሰኘ በኦሮሞ ሊሂቃን ተረቆ በትግሪኛ ተሻሽሎ በአማርኛ በነፃ ብሔርና የትውልድ ማጥፊያ የተረጨ መርዝ…ዙሪያውን እንዳበደች ውሻ ያቅበዘብዛቸዋል። የኦሮሞ ሕዝብ በራሱ ቋንቋ ነግሯቸው አልገባቸውም…ከአልቅት የፀዳ ንፁህ ውሃ፣ለወገቡ አልጋ፣ ለልጆቹ ሕክምናና ትምህርት፣ለሆዳቸው ዳቦ…እናቶቻቻው በኩበት ጭስ ዓይናቸው እንዳይጠፋ …በጉልበት ተንበርኮ ወፍጮ እንዲያበቃ…ከጠላና አረቄ ጠመቃ አልፈው.. የፀዳ ለብሰው የአማራቸውን ጎርሰው በሃይማኖታቸው ፀልየው በሰላም መኖርን ይለምናሉ። ያደመጣቸው የለም!

    ***ሎሎች በቀን አሥር ግዜ እየጋጡ…ደረቅ ጫት እየመጠጡ…የሻቢያህወአት የሙስና ሻንጣ ተሸካሚ ሆነው…ከአህያና ፈረስ ወርደው በሹፌር እየሄዱ የህዝብ ማስለቀሻ…የትውልድ ማናካሻ..የሀገር ሰላም ማደፍረሻን ሴራ በህወአት ጥላ ተከልለው ፳፪ዓመት ያልተገባቸውን መሬትና ሀብት ዘርፈው ባንዲራ ቀርጸው የክልል ካርታ ሠርተው ያናፋሉ። ጭራሽም የብሔር ጥያቄያችን “ከመገንጠል” በቀር ተመልሷል ብለው ጧፍ ዕጣን አጭሰው ቄጠማ ጎዝጉዘው ይዘምራሉ። ለመሆኑ ይህ ሥራ ዕድል መክፈት ከአፍ መክፈት ነፃነት ጋር እንዴት አንድ መሰላቸው። አላግባብ አፍ ሲከፈትም…ምን ይታያል እነጂ የፖለቲካ ትርፋማነት አያስገኝም።ባለፈው ሰሞን ከተስፋዬ ግብረእባብ የነፃ መፅሀፍት እደላ በኋላ ከደቡብ አፍሪካ፣አስካንዲኒቪያን ሀገራት፣ አሜሪካ፣ ካናዳ…አውሮፓና አውስትራሊያ…ያሉ ፅንፈኛ፣ፀረሕዝቦች፣ አሸባሪዎች…በግብጽ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ሲቃወሙ…በደቡብ አፍሪካ ማንዴላ ኦሮሞ ነው ሲሉ…ተስፋዬ በኢሬቻ በዓል በፈረንጅ ውሃ ዳር ሲመረቅና የጀግናው ደራሲ ቅቤ ሲቀባ፣ በቅርብ ቀን የኢትዮጵያን ፖለቲካን ኢኮኖሚ፣ መከላከያን ጨምሮ ለመቆጣጠር ከእያለንበት እንገባለን እኔም የኦሮሞ ዜግነት አለኝ ሲል ደነፋ…እንግዲህ ከአቶ ሌንጮ ለታና ከህወአትሻቢያ ጋር የነበረው የውስጥ ስምምነት አስቀድሞ ደርሶት ታላቁ ትንቢት ፋላስፋ ሆኖ ነበር። **ግን ተመልሰን ገብተን እንታገላላን ሲሉ ትግሉ ምንድነው? ከማነው? ምን ለመጨመር ነው? አንድ ባንዲራ አንገበው ‘ኢትዮጵያ ከኦሮሞሚያ ትውጣ ሲሉ…ይህን ሁሉ መብት ያጎናፀፏቸው ትግራይና ሻቢያን የትኛው ባሕር ሊጨምሯቸው ነው? እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አደለንም ሲሉ ከርመው ኢህአዴግ ጥላ ሥር የተሸጎጠው ቀኝ ክንፋቸው አማራዎችን በመንደራቸው እየገደሉ፣ እየዘረፉ፣በመርዝ እየጨረሱና እያፈናቀሉ ሁሉን ነገር አመቻቹላቸው…። የኦሮሞ ፅንፈኞች ያልተረዱት ይህ ከአማራ ተነጥቆ የተሰጣቸውን መሬት(ኤርትራውያንም ተመልሰው መጥተው አባቶቻችን እናቶቻችንና ልጆቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን የከሰከሱበት መሮት ነው ብለው የመጠየቅ ሙሉ መብት እንዳላቸው አያውቅምን? በማን ልጅ ደምና አጥንት የሙስሊም ኦሮሞ ዲያስፖራ ያናፋል!?)አንዳንድ አልኩ ባይ የህወአት ጡረተኞችም እምዬ ምንይልክን ሲያንቋሽሹ ብሔር ብሔረሰብ ራስን አድል በራስ መወሰን ነፃነት ተረጋግጦ የአማራ የበላይነት ወድቆ ኢትዮጵያን መበተን በሕገመንግስታችን(በማኒፌስቶአችን)ተረጋግጧል ኦሮሞ ‘የጡት ሀውልት’ ደቡብና ትግሬም ‘የቆለጥ’ ተረስተውና ማንንታቸውን የማያውቁ ‘የቂጥ ሀውልት’ አቁመው(የዝሙት) ሴክስ ቱሪዝምን ለሚሽነሪስት አለቆቸቀቸው ወጣት ሴቶችን ለአረብ ሀገር የሸጧቸው ስላከሰራቸው አሁን በሀገር ውስጥ ለመነገጃ ማስተዋወቂያ ማድረጋቸው እጅግ በጣም የወረደና የዘቀጠ የከብት የአዕምሮ የትውልድ ክስረት ማፈሪያዎች ናቸው።

    **ነጮች አለቆቻችው የሚያፍሩበትን ሎሌዎቻቸው ፀጋ ብለው ማቅረባቸው አካባቢያቸውን ማርከሳቸው ባህልና ሀይማኖታቸውን መፃረራቸውን አልገባቸውምን? ወይንም ግብረሰዶምን ተገንጥለው ሊቀውጡት ያሰቡ ዲያስፖራዎች(ፈላሾች) በዚያ አካባቢ ክልል ሊመሰርቱ ኢንቨስት እያደረጉ ነው።የአማራ ሥም ያስጠላት ጫልቱ …ሊሊ፣ ቡኪ፣ ሱኪ፣ቡቺ፣ ፊፊ፣ልትሆን ቋመጠች ጠርጥር ድሮም የነጭ ጉዲፈቻ ማደጎ ምን ተምሮ ይመጣል?ትርፍ የለም ኪሳራ ብቻ ነው በለው! ሌላው የተበላበት ቁማር ብአዴን.. ኦፌዴን.. የሚባለውንና ሌሎችንም የወሮበላ ቡድንን ጨምሮ ለሚያጠፉት ታሪክና ትውልድ ኦነግ ኦብነግን አሰማርተው ኤርትራ የቀጠናው አተራማሽ ህወአት መሪዎች ናቸው የኢትዮጵያ ጠላቶችና አጥፊዎች ማለቱ አያዋጣም እንደ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ መልስ ሁሉም በእየፊናው ሀገር ለማጥፋት ህወአት(ትግሬዎች) እያለ ጣቱን ይቀስራል። ዞረውም በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈው ይበትናሉ>>>ኦፌዴን የአፄ ምኒልክን ሀውልት ለማፍረስ ተሰልፎ አቅም በማጣቱ ብቻ አልተሳካልንም የሚሉት ነጋሶ ጊዳዳ አንቀፅ ፴፱ ከማያከብሩ ጋር አብሮ ለመሥራት አስቸጋሪ ሆኖ በገዳ ደሞክራሲ መሠረት በ፵፰ ዓመት ሥልጣን መልቀቅ ሲገባኝ ሕገመንግስቱ በ፸ ዓመቴ ድረስ ያሰረና ያስቀመጠኝ አላግባብ ነው ከፖለቲካ እርቄአለሁ ግን አልጠፋም! የኢህአዴግንና፣ የአንድነትና የመድረክን ፓርቲ አባላትንና ብዙ ውስጠ ሚስጠር አወጣሉ፣ እተቻለሁ፣ መፅሐፍ እሸጣለሁ፣ብዙ ቃለምልልስና ለ፴፭ኣመት እድሜ ባለፀጋው ሌንጮ ለታ ከቡልቻ ደመቅሳ ጋር በመሆን ከአባልነት ውጭ ሆነን ያለንን ሚስጥር እንመክራለን ብለዋል።” ታዲያ ማን? ከማን? እንዴት? የት? ልዩና የተሻለ ነበር? ተልዕኮአቸውን የፈፀሙ ወደ ሀገር ሲገቡ ሀገር ውስጥ የነበሩ ይሸሻሉ…አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀን ግለሰብ ወይም ቡድን(ድርጅት) ጋር የተነጋጋረ አብሮ የተሰበሰበ ሻይ ቡና ያለ…(በሕግ ተጠያቂ ይሆናል)። በትክክል በተረጋገጠዉ በበደኖ እና አርባ ጉጉ፣ በተፈጸመ ግፍና ጭካኔ ዙሪያ ማስታወሻ ሃዉልቶች ሳይሰሩ፣ በጀዋሪያን ተስፋ በተፈበረከው የውሸት ታሪክ በሕዝብ መካከል ጥላቻና አመፅ ሊያሰፍን የሚችል፣ፀረ ሰላም ዓላማ የሴት ልጅን ጡት የሚያሳይ ሃዉልት በአርሲ መሰራቱ ። በበደኖ በኦነግ ታጣቂቶች ነፍሰ ጡር ሴቶች ሁሉ ሳይቀሩ፣ በሕይወት አይኖቻቸውን ተሸፍነዉ ተጠቅልለው ገድል ዉስጥ እንዲወረወሩ መደረጉ የሚታወቅ ነዉ። በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ.ኢሕአዴግ ታጣቂዎች አቀነባባሪነት፣ በአርባ ጉጉ አርሲ በርካታ ዜጎች በተኙበት ቤታቸው እንዲቃጠል ተደርጎ አልቀዋል።የክርስቲያን ኦሮሞ ቤተክርስቲያንም ፖሊስ ባለበት አቃጥለዋል። ከአሸባሪነት ነፃ ለመሆን ሳያመለክቱ ጥፋተኛን ሳያጋልጡ ምሕረት ሳይደረግላቸው የጡት ሀውልትና የቆለጥ ሐውልት በማቆም የአማራን መሬት ለሥልጣን ማስጠበቂያ ለባዕድ አከራይቶና ሰጥቶ በመቀበል ሽብርተኝነትን ማወራረድ አለን!?
    **ለምርጫ መወዳዳር ምሕዳሩ አሁን እንዴት ሰፋ!? ምን አልባት ማንዴላ ስለሞተ ይሆን!? ወደው አይስቁ አለ…የ፻ዓመት ትዝታ…የ፶ ዓመት ትግል…የ፳፪ዓመት ውዥንብር ለአንድ የጡት ሀውልት ያረጁትም ደነቆሩ ወጣቱም ደነቆረ መልሶ መላልሶ ማልቀስ ሆነ በለው!>>>>ሠላምና ልብ ለሁሉም።

    Reply
  3. kie says

    January 24, 2014 01:14 am at 1:14 am

    You guys what the hell you talk about. Both bible & quaran are salvages that are imported. The very very narrow guys like celebrate their stupidity.

    Reply

Leave a Reply to በለው! Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule