ኦሮሚያ ብቻ ሳትሆን ድፍን አገርን ማቅ ያለበሰው የጅምላ ጭፍጨፋ እያደር አጥንት የሚያደቅ መረጃ እየወጣበት ነው። ህወሃት የእርቅ መንገዶችን በሙሉ አሟጦ የቀበረበት ይህ “ይቅርታ የሌለው ወንጀል” እስካሁን የ678 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል። የትዳር ጓደኛውን አስከሬን በግል ተሽከርካሪ ጭኖ እያነባ ወደ ቤተሰቡ የወሰደ አለ። ገንዘብ ተዋጥቶለት የሚስቱን አስከሬን ጭኖ ወደ ሱሉልታ የተጓዘ መኖሩ ተሰምቷል። እናትና ልጅ ባንድነት ቀብራቸው ተከናውኗል። በአንድ ቀን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወገኖች ከቤተሰባቸው ጎድለዋል። አስከሬን አሁን ድረስ እየተቆፈረ እየወጣ ነው። ሃይቅ ላይ የተንሳፈፉ አስከሬኖች እየተለቀሙ ነው። ህዝብ ቁጣው ገንፍሎ በተለያዩ ስፍራዎች እምቢተኛነቱን እየገለጸ ነው። ህወሃት ግን አሁንም ይዋሻል።
በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ በታጣቂዎች እስከታዘዙበት ድረስ የታዘቡትን ለቪኦኤ ሲያስረዱ ሁሉም ነገር ሰላማዊ ነበር። ህዝብ ተቃውሞውን ሲገልጽ የነበረው በሰላማዊ መንገድ ነበር። ምንም ዓይነት ትጥቅ ያልያዙ የኦሮሚያ ፖሊሶች ከህዝቡ ጋር በኦሮሚኛ እየተነጋገሩና ህዝብም “የእኛ” ሲላቸው ይደመጥ ነበር። ታዲያ ሰላማዊ ተቃውሞ ከነበረ ለምን በአየር፣ በታንክና፣ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ተፈጸመ? የሚለው ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሕዝብ ላይ ጦር ሠራዊቱ ጭፍጨፋ እንዲፈጽም ትዕዛዝ የሰጠው ሃይለማርያም ደሳለኝ በህወሃት ቴሌቪዥን ቀርቦ “እስካሁን ባለኝ መረጃ 52 የሚጠጉ ሞተዋል” በማለት ጸቡን ያስነሱትን ህግ ፊት እንደሚያቀርብ ዝቷል። ምንም ዓይነት የጥይት ድምጽ ሳይሰማ ህዝብን በመጠበቅ ከፍተኛ ትጋት ላሳዩት የጦር ሠራዊት አባላት ብሎ ለጠራቸው የአጋዚ ታጣቂዎች ምስጋናውን አሰምቷል። ሃይለማርያም በትዕዛዝ እርቅ በጠየቅ ባጭር ጊዜ ውስጥ ህዝብ ላይ ክተት መታውጁን አብሳሪ ሆኖ “አማራ ክልል” ሰላማዊ ዜጎች እያስጨረሰ ነው። አሁን ደግሞ የህወሃት አንጋቾች ለፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋ እውቀና መስጠቱ ከሃዘኑ በላይ ህዝብን ያቆሰለ ጉዳይ ሆኖ እያነጋገረ ነው።
እልቂቱ በደረሰበት ዕለት ዜና ያነበበችው የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃዬ “በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ” ያለቻቸው፣ “የአማጺ ባንዲራ በመያዝ ነጻነት እንፈልጋለን የሚሉ ነበሩ” ስትል አወላግዳና አሳንሳ ያቀረበችው የተንሸዋረረ መረጃ የሃይለማርያምን ያህል ባይሆንም ትዝብት ውስጥ የሚጥል እንደሆነ አስተያየት የሰጡ አሉ። ወዲያው አዳነች ይህን ብላ ስትጨርስ የተቀበላት ሌላው የቪኦኤ ባልደረባ የኦሮሚያ ክልልን ጠቅሶ እስከ 4 ሚሊዮን ህዝብ በበዓሉ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆን አመልክቶ ነበር።
ከዚህ አስዛኝና ዘግናኝ ዜና በኋላ በሟቾችና በቆሰሉ ዜጎች አኻዝ ዙሪያ ለተፈጠረው ሰፊ ክፍተት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ “ህወሃት በቁጥር ማምታታቱ የተለመደ ነው። አይገርምም። የሚደንቀኝ የዓለም ሚዲያዎች እነሱን አምነው የሚዘግቡት ነው” ሲሉ ህወሃት ቀጣፊ እንደሆነ የታሪክ ሪኮርዱ እንደሚመሰክርበት ያመለክታሉ። ምርጫ ሲባል 100 ከ100፣ ኢኮኖሚ ሲባል የድርብ አሃዝ ዕድገት … በማለት የሚጠቀሱት አቶ ኦባንግ “ህወሃት ከግድያ ውጪ ችግርን የሚፈታበት እውቀት የሌለው፣ እምነቱም፣ ፍጥረቱም፣ ዕድገቱም፣ ዕቅዱም ንጹሃንን መግደል ብቻ ነው። የሚጠቅመው ሲሆን ድሮ እንደሚያደርገው ነጻ አወጣችኋለሁ የሚለውን የራሱንም ሰዎች ያጠፋል” ሲሉ ጊዜው የተራራቁ አካላት ተሰባስበው አንድ አካል የሚሆኑበት ጉዳይ ላይ ቅድሚያ የሚሰጥበት እንደሆነ አመልክተዋል። አያይዘውም “ቀደም ብለን አካል ሆነን ቢሆን ኖሮ እየነጣጠሉ አይገሉንም ነበር። ምክንያቱም አካል አንዱ ክፍል ሲጎዳበት ሁለመናውን ያመዋልና” ብለዋል፡፡ በቀናነትና ህዝብን ባስቀደመ መልኩ አንድ አካል መሆን፣ ከዘር ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ መስጠት፣ እንደ ጎሣ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ማሰብና መሰባሰብ፣ መታገል ግድ መሆኑን አስመረውበታል።
ሃይለማርያም “ጥቂት ጸረ ሰላም ሃይሎች” ሲል አሳዳሪዎቹን ለማስደሰት እንዲህ ባለው መሪር ሃዘን ቢሳለቅም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ እንዳለውና ኦፌኮ ለቪኦኤ እንዳረጋገጠው በኦሮሚያ ህዝባዊ እምቢተኛነቱ ተፋፈሞ ቀጥሏል። በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች የአገዛዙ መዋቀሮች ላይ ጉዳት ደርሷል። በምዕራብ ሃረርጌ የህወሃት ንብረት የሆኑ የሰላም አውቶቡሶች ወድመዋል። በወለጋ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በጅማ፣ በጉጂ፣ አርሲና በሌሎችም ስፍራዎች ህዝብ በህወሃት ንብረቶች ላይ የበቀል ርምጃ ተወስዷል። የአምቦ ውሃና የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ስራ አቁመዋል። እንደ ዜናው የህዝባዊ እምቢተኛነቱ አራማጆች “ቀጣዩ እርምጃ ሕዝብን እያስገደሉና እየገደሉ ያሉትን ግለሰቦችን ያጠቃልላል” ማለታቸውን ይፋ አድርጓል።
ህዝባዊ እምቢተኛነቱ እየከረረ እንደሚሄድ የሚጠበቅ ሲሆን በዛሬው እለት (ሰኞ) በአምቦ 4 ንጹሃን፣ በቢሾፍቱ 2 በአጋዚ ሠራዊት መገደላቸውን የአይን ምስከሮች ለጎልጉል ተናግረዋል። ህዝብ ሃዘኑ ሳያጠግለት ዛሬም ነፍስ ማጥፋት ላይ የተጠመደው ህወሃት ላለፉት 25 ዓመታት የፈጸመውና ያደረሰው በደል አንድ ላይ ተዳምሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሊስማማ የሚችልበት አማራጭ ሁሉ መዘጋቱን ብዙዎች እየተናገሩ ነው።
የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ከህወሃት የቀረበላቸውን የእርቅ ጥያቄ አንቀበልም ማለታቸው የዚሁ የቆየው ሰቆቃ ውጤት ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። ለዚህም ይመስላል ህወሃት በገሃድ እየገደለ በጓሮ የለመነው እርቅ የተዘጋበት። በቤተ እምነት ሰዎች በኩል የእርቅ ጥያቄ የቀረበላቸው እኒህ ሁለት ግንድ ህዝቦች ህወሃት ላለፉት 25 ዓመታት እርቅንና ፍቅርን እንደገደለ አመልክተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህወሃት ያደረገውንና እያደረገ ያለውን፣ በተለይም በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የፈጸመውን “አረመኔነት የተሞላበት፣ የታቀደና ዝግጅት የተደረገበት” የተባለውን የጅምላ ጭፍጨፋ የተመለከቱ “ህወሃት/ኢህአዴግ ራሱን ለመጨረሻ ጊዜ ገደለ። ምን አልባትም የመጨረሻ እድሉ የሆነውን የባለአደራ መንግስት የማቋቋም ተስፋ የማግኘት ዕድሉም ሊኖረው አይችልም” ሲሉ እየተደመጡ ነው።
የኦሮሞ ህዝብ የኢሬቻን በዓል ሲያከናውን ከተፈጸመበት የጅምላ ጭፍጨፋ በፊት ህወሃት በሃይለማርያም ደሳለኝ አማካይነት የተለያዩ ቤተ እምነት ሰዎችን ስለ ዕርቅ ተማጽኖ ነበር። በሃይለማርያም የጥሪ ደብዳቤ መነሻ በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ የየእምነቱ የወንጌል አገልጋዮች አዲስ አበባ ተገኝተው ነበር። እነዚሁ ሰዎች ኦሮሚያና አማራ ክልል በመሄድ ህወሃትን ከህዝብ ጋር እንዲያስታርቁ ተጠይቀዋል። በጥያቄው መሰረት እያንገራገሩ የእምነት አባቶቹ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በመሄድ አግባብ ያላቸውንና ለሕዝብ ቅርብ ከሆኑት ጋር ተወያይተው ተመልሰዋል። ምላሻቸውንም ይዘው ሃይለማርያም ቢሮ በመገኘት ህዝብ የሰጠውን ምላሽ አስረድተዋል። የጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ በስብሰባው “ተገኝቻለሁ” ካሉ ያገኘውን መረጃ ጠቀሶ እንዳለው የሰዎቹ ምላሽ ሃይለማርያምን አስደንግጦ ነበር።
“በመጀመሪያ በትህትናና በህግ እንዲሁም በልመና ለረዥም ጊዜ ጥያቄ አቅርበናል። ዕርቅ ጠይቀን አልተቀበሉንም። አሁን ደም ተቃብተናል። ሰዎች ሞተዋል። ሌላ ሳይከተል ይልቀቁን ነው የሚሉት” ሲሉ የአማራዎችን አቋም አንደኛው መልዕከተኛ አቀረቡ። “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” ሲሉ ጠቀለል አድርገው ኦሮሞዎች የመለሱት መልስ ምን እንደሆነ ሌላኛው መልዕክተኛ አስረዱ። ይህ በጓሮ ሲደረግ ህወሃት የሚመራው ሚዲያና የህወሃት መሳሪያ የሆኑ ክፍሎች የነጻነት ጥያቄ የሚያቀርቡትን የኅብረተሰብ ክፍሎች አሸባሪ፣ የጥፋት ኃይሎች፣ ተላላኪዎች፣ ጸረ ልማቶች፣ አተራማሾች … ወዘተ እያለ እያወገዙ ነበር፤ አሁንም ነው።
ገና ከጅምሩ ሃይለማርያም “ህዝብ ይሰማችኋልና ዕርቅ አውርዱልን” ብሎ ሲጠይቅ አንድ ትውልዳቸው ከኦሮሞ የሆነ አንጋፋ የወንጌል ሰባኪ “እግዚአብሔር ይህ ‹አገዛዝ› እንደሚወድቅ የተናገረው ከ10 ዓመት በፊት ነው። ልጄ ለምን እዚህ ውስጥ ገባህ? እጅህን አንሳ፣ ውጣ፣ መንግስት ከአንተ እጅ አይደለችም፣ የብዙ ሰዎች ደም በእጅህ አለ። ይህ ቦታህ አይደልም። ልቀቅ…” ብለው ማሳሰቢያ እንደሰጡ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የመረጃ ሰው በመናገር የሃይለማርያምን ምላሽ ሳያብራሩ አልፈውታል። ዘጋቢው ማብራሪያ ቢጠይቅም “ቢሰማ ኖሮ ኢሬቻ ሲያከብሩ በነበሩ ወገኖች ላይ አንድም የጥይት ድምጽ አልተሰማም” ብሎ አያወራም ነበር ሲሉ የመጠየፍ ስሜት እየተሰማቸው ተናግረዋል።
ላለፉት እጅግ በርካታ ዓመታት ስለ ዕርቅ መላ ሲቀርብ ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ እያሾፈ ይህ የባልና ሚስት ጠብ አይደለም በማለት ብዙ ሲቀለድ ኖሯል፡፡ በ97ቱ ምርጫ ወቅት ይኸው መለስ ከሰማይ በታች በማንኛውም ጉዳይ ላይ እደራደራለሁ በማለት የሕዝብን ቁጣ እንዲበርድ ካደረገ በኋላ የድርድሩን ምላሽ የተቃዋሚ መሪዎችን ወኅኒ በመወርወር ንቀቱን አሳይቷል፡፡ ከዚያም በተደጋጋሚ የቀረቡ የብዙዎች የዕርቅ ጥያቄዎች የፈሪ ልመና ተደርገው የተወሰዱባቸው ጊዜያት ጥቂት አይደሉም፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ከዚህ በኋላ የሚያቀርበውም ሆነ የሚቀርብለት የዕርቅ ጥያቄ እንደሌለ በርካታዎች የሚስማሙበት ሃቅ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይልቁንም ኢትዮጵያ የወላድ መሃን አለመሆኗ እንደገና የሚታይበት ወቅት ላይ መሆኑ አገር ወዳድ የሆኑና በሕዝብ ዘንድ ታማኝነት የሚጣልባቸው አገርን የማዳን ሥራ የሚሠሩበትና ከተደበቁበት የሚወጡበት ጊዜ ነው፡፡ ጥቃቱ እስከ መቅኔያችን የተሰማን በሙሉ በተለያዩ መጠሪያዎች ሳንከፋፈል በኅብረት የተቃውሞ ድምጽ የምናሰማበት ጊዜ ነው የሚለው አስተሳሰብ የበርካታዎች እየሆነ መጥቷል፡፡ (መግቢያ ፎቶ: Reuters, ሌሎቹ ከማኅበራዊ ገጾች የተገኙ)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Tesfa says
Hammered by a constant stream of patriotic songs and ethnically charged political propaganda none of the TPLF sadistic killers see life as a normal person sees it. For them, life is to take another person’s life to make a living. It is a full time job! Country, boundary, nationalism can only be interpreted and seen from a regional point. Ethiopianisim is colonialism in their eyes. To sustain their dominance in all sectors of Ethiopian society, they must divide us along ethnic lines while reinforcing their home base the state of Tigray. TPLF is led by people who gain pleasure by inflicting pain and humiliation on others for the continuity of their leisure survival. Ruthlessly, they dehumanize the living and the dead.
Whatever meager gains were achieved in the last twenty five years of their control of the country, they do not care preserving or enhancing it. They think temporary, now not the future. If they are not in control they tell us nothing will work. The country will fall apart. Oh well, I hate to tell you the country has been falling apart the day you took power. No other power including the Italians two attempt of colonizing Ethiopia did so much harm to its people and identity than the Tigray led power mongers of the TPLF. People born and raised within Ethiopia are dismembering the country and its people. What was not achieved by foreign powers is fulfilled by the sadistic acts of the TPLF. That is the irony of the situation we all Ethiopians are facing.
Wake-Up says
ውድ ጥራዝ-ነጠቅ ፖለቲከኞቻችን መጀመሪያ ነገር ፖለቲካ መቼ እንደተጀመረ በትክክል ተረዱ፡፡ከዚያ በኋላ የምትሞነጫጭሩትን ትንተና እና አስተያየት አትኩሮት ሰጥተን እናነባለን፡፡
መፍትሄ የማያመጣ የበሽታውንም መንስኤ የማይጠቁም ተመሳሳይ አሰልቺ ነገር ማንበብም ሰለቸን እኮ፡፡ፖለቲካ የጀመረው የዛሬ ሃምሳ ዓመት በተማሪዎች ንቅናቄ የሚመስለው የፖለቲካ ህፃን ለዚህች ሀገር መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም፡፡እስኪ ስለፖለቲካ ታሪክ ወሳኝ ክስተቶች ትንሽ ፍንጭ እንስጣችሁ፡፡የመጀመሪያው ፖለቲካ የተጀመረው ሉሲፈር በእግዚአብሄር ላይ አመፅ ወይንም አብዮት ያካሄደ ለት ነው፡፡ሁለተኛው ፖለቲካ ሉሲፈር አዳምና ሄዋንን አስቶ ሌላ ሁለተኛ አብዮት አካሂዶ ከገነት ሲያባርራቸው ነው፡፡ከዚያ ቀጥሎ ቃየን አቤልን ሲገድለው ነው፡፡የቃየን ዘር የሚባለው ማነው?የቃየን ዘር በአለም ላይ በሌሎች ዘሮች ላይ የበላይ ሆኖ ሌሎቹን ዘሮች እያሳደደ ለማጥፋት ለምን ተነሳ?የቃየን ዘር ከሌላ ጋር ተዋህዶ ኔፊሊም የተባሉትን የተለዩ ድብልቅ ዘሮች ፈጠረ፡፡በዚህ የተነሳ የጥፋት ውሃ መጣ፡፡ሶስተኛው ዋና ፖለቲካ እግዚአብሄር ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደዚህ ምድር በመምጣት ሰይጣንን በመስቀል ላይ ድል ሲነሳውና በሰይጣን ባርነት ስር ለሚማቅቀው ለአዳም ዘር በሙሉ ነፃነትን ሲያውጅ ነው፡፡የቃየን ዘር እንደሌላው የሰው ዘር በአለም ላይ ተበትኖ ያለ ነው፡፡ይህ የቃየን ዘር ከጥንት ጀምሮ አለም አቀፋዊ ህብረት የፈጠረ ሰይጣናዊ ሃይል ነው፡፡በዓለም ታሪክ ውስጥ ሱመሪያ ባቢሎን ሮም ወዘተ ወሳኝ ታሪካዊ ክስቶች ናቸው፡፡ከዚያ በዓለም ታሪክ ውስጥ እስራኤል(Hebrew) እና ጂው(Jew) የሚለው ስያሜ ወሳኝ ቦታ አለው፡፡እስራኤል(Hebrew) እና ጂው(Jew) የሚለው ስያሜ ብዙ ሰው ስለሚምታታበት የአለም ፖለቲካውም እንደዚሁ ተምታቶበታል፡፡እየሱስ ክርስቶስ ጂው(Jew) እየመሰለው የሚሳሳት ብዙ ሰው ነው፡፡እርግጥ ነው ክርስቶስን የሰቀሉት ጂው(Jew) ናቸው፡፡ጥንት አቤልንም የገደለው ቃየን ነው፡፡ወደድንም ጠላንም ጂው(Jew) የሚለው ነገር የዓለምን ታሪክ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተቆጣጥሮ ያለ ነገር ነው፡፡የእኛም ሀገር የሺህ ዘመን ታሪክና ፖለቲካ ከዚህ ውጪ አይደለም፡፡የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት እየሱስ ክርስቶስ ከሄሮድስና ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡እውነት ነው ኢትዮጵያ ሀገራችንን እና መላውን የሰው ዘር በዓለም ላይ እየበጠበጠ ያለው ይኼው ሰይጣናዊ እርሾ ነው፡፡ከሙዚቃ ግጥሞችና ክሊፖች ጀምሮ እስከ ዋና የመንግስት ስልጣን እና የሃይማኖት መሪዎች ድረስ ይህ ሰይጣናዊ እርሾ አለ፡፡ከዚያ ቀጥሎ አዲሱ የዓለም ስርዓት የሚባለው አለ፡፡ይሄም በቅዱስ መፅሀፍ በእየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ የተገለፀ ነው፡፡ሰባት የባቢሎን ኢምፓየሮች አሉ አምስቱ ወድቀዋል ስድስተኛው አሁን ያለው የሮም ኢምፓየር ነው፡፡ሰባተኛው ወደፊት ይመጣል ብሎ እየሱስ ክርስቶስ በዘመኑ ተናግሮ ነበር፡፡ሰባተኛው ባቢሎናዊ ኢምፓየር ወይንም አዲሱ የዓለም ስርዓት የሚባለው 666 እንደሆነ በዮሀንስ ራእይ ተገልጧል፡፡ይህንን ያህል ካልናችሁ የኢትዮጵያን ሁኔታ በዚህ መንገድ ማየት ትችላላችሁ፡፡በአሜሪካ በእንግሊዝ በእስራኤል እና በተቀረው ዓለም ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ጂው(Jew) ከሚለው ወሳኝ ነገር ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡በእኛም ሀገር ያለውን የወያኔ ምንነት ለማወቅ ጂው(Jew) የሚለውን ጠንቅቃችሁ እወቁ፡፡ከዚያ ሁሉም ነገር ይገለጥላችኋል፡፡ኢዝም(-ism) የሚባሉትን አስተሳሰቦች ሁሉ ጂው(Jew) የፈጠራቸው ናቸው፡፡የፈረንሳይ አብዮት የአሜሪካ አብዮት የሩስያ አብዮት ወዘተ የማን እጅ ነበረበት?የአንደኛው የዓለም ጦርነት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና ሶስተኛውም የማን ስራ ነው የሚሆነው?በኢትዮጵያችን ከነበረው የተማሪዎች ንቅናቄ እና አብዮት በስተጀርባ ማን ነበረ?አሁንስ እያተራመሰን ያለው የዘር ፖለቲካ ምንጩ ምንድን ነው?በሀገራችን እና በተቀረውም አለም የሚካሄደው ባህልና ታሪክን የመበረዝና የማፍረስ ስራ የማን ተንኮል ነው?ፈፅሞ ማብቂያ የሌለው የማይረካ ቁሳዊ ሀብት ማግበስበስ እና ሌሎችን እየጨቆኑና እየበዘበዙ በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ የመስፋፋት ባህሪ የማን ባህሪ ነው?የዓለምን አጠቃላይ ሀብት ተቆጣጥሮ የያዘው እና ከዚህም በላይ ተጨማሪ ለመቆጣጠር እየጣረ ያለው ማነው?አብዛኛውን በዓለም ያሉትን የየሀገራቱን መንግስታት(አሜሪካንን ጨምሮ) ከበስተጀርባ ተቆጣጥሮ እየዘወረ ያለው ማነው?ከእርሱ ዘር ውጪ ያለውን የአዳም ዘር ሁሉ ለማጥፋት እየጣረ ያለው ማነው?ሌላውን ዘር እርስ በርስ እያናከሰና እያጫረሰ ያለው ማነው?በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እየተደረጉ ያሉ አውዳሚ ጦርነቶችና ግጭቶች በማን ምክንያት ነው የሚቀጣጠሉት?ከአሸባሪነት ጀርባ ማነው ያለው? የተለያየ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘዴ በመጠቀም የዓለምን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ሰይጣናዊ ጥረት እያደረገ ያለው ማነው? ጂው(Jew) የሚል ስም ለራሱ ያወጣው የቃየን ዘር አይደለም እንዴ?ይህ እራሱን በሀሰት ጂው(Jew) ሳይሆን ጂው(Jew) ነኝ የሚል ዘር በቅዱስ መፅሀፍ ዮሀንስ ራእይ 2፡9 ላይ ተገልጧል፡፡ኢትዮጵያም ዛሬ በዘር ፖለቲካ እየታመሰች ያለችው የዚህ ጂው(Jew) የሚባል ሰይጣናዊ እርሾ መንፈስ በኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ስለመጣ ነው፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የውጪና የሀገር ውስጥ ተብሎ ለሁለት የተከፈለችው ለምን ይመስላችኋል?ቤተ-ክርስቲያኒቷ በሄሮድስና በፈሪሳዊ እርሾ እየተበከለች ስለሆነ ነው፡፡የጂው(Jew) መንፈስ ፀረ-ክርስትና እና ፀረ-ክርስቶስ ስለሆነ ነው፡፡በህግ ጥላ ስር ያለን እስረኛ ከነህይወቱ ማቃጠል ሊያመልጥ ሲል ደግሞ በጥይት መግደል የዚህ የጂው(Jew) ሰይጣናዊ መንፈስ ተግባር ነው፡፡በነገራችን ላይ የጂው(Jew) ሃይማኖት መመሪያው የባቢሎን ታልሙድ ነው፡፡በዚህ የባቢሎን ታልሙድ ህግና እምነት መሰረት ከጂው(Jew) ውጪ ያለው ሰው ጎይም(Goyim) ተብሎ ይጠራል፡፡ጎይም(Goyim) እንደ ሙሉ ሰው አይቆጠርም፡፡ስለዚህ አንድ ጂው(Jew) ሌላውን ጎይም(Goyim) መግደል፣ማታለል፣መስረቅ፣ማፈናቀል፣ማሰደድ፣ሀገር-አልባ ማድረግ፣ ማደህየት፣ማስራብ፣ማሰቃየት፣ህክምና መከልከል፣ፍርድ ማዛባት፣እና ሌላም ብዙ አይነት አ-ሰብዓዊ ተግባር መፈፀም ይቻላል እንደሁኔታውም ይህንንም ማድረግ አለበት፡፡ህገ-መንግስት እና ዲሞክራሲ የሚባለው ነገር ዝም ብሎ ማታለያ ነው፡፡የጂው(Jew) ዘር በብዛት ጥቂት ቢሆንም የራሱን ህቡእ አለም አቀፍ ኔትወርክ በመፍጠር አለም አቀፍ አሊያንስ ወይንም ትብብር አለው፡፡ጎይም(Goyim) የሚባለው አብዝሃው ቁጥር ግን ይህንን ለማድረግ ስላልቻለ በጥቂቶቹ በጂው(Jew) ሰይጣናዊ ተንኮል እየተጠቃና እየተሰቃየ ነው፡፡የሚገርመው ነገር ጂው(Jew) ተቀናቃኙን ጎይም(Goyim) ለማጥቃት በዋናነት እየተጠቀመ ያለው እራሱን ጎይም(Goyim) ነው፡፡ወያኔዎች የሚያደርጉት የዚህን ግልባጭ ነው፡፡የዓለም ፖለቲካ ኢኮኖሚና ሌላውም አጠቃላይ ስርዓት በዚህ ተፅእኖ ስር እየወደቀ ነው ያለው፡፡በኢትዮጵያ ከዛሬ 1100 ዓመት በፊት የነበረውን የዮዲት ጉዲትን ዘመን የሚያስታውስ ካለ መረዳት ያለበት ወያኔ የዘመናችን ዳግማዊ ዮዲት ጉዲት እንደሆነ ነው፡፡ከላይ በአጭሩ በጠቀስቁት መንፈሳዊ እይታ ስትመሩ ፖለቲካውና ሌላውም ይገባችኋል፡፡ሁለ-ገብ ትግሉ ዛለቂና አስተማማኝ ውጤት የሚኖረው ሁኔታውን በዚህ መንገድ ጭምር ስንረዳው ነው፡፡የዛሬ 120 ዓመት አፄ ምኒሊክ አድዋ ሲዘምቱ ታቦት ይዘው የሄዱት የሚዋጉትን ሰይጣናዊ ሃይል ምንነት ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው፡፡ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር የመጣችው ከበስተጀርባ በሮም ቫቲካን ተገፋፍታ ነው፡፡ሮም ቫቲካን ደግሞ ማን እንደሆነች የሚያውቅ ያውቃታል፡፡የዘመኑ ትውልድ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ ብዙ መማር ሲችል እንደዚህ መሆኑ ግን በጣም ያሳዝናል፡፡ለነገሩ ኢትዮጵያ አዲስ ምእራፍ ችግር ውስጥ መግባት የጀመረችው የኢትዮጵያ ምሁር መፅሀፍ ቅዱስን ወርውሮ ሲያበቃ ከቆየው የቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮት ጋር ተለያይቶ በምትኩ የማርክስን ዳስ-ካፒታል እና ሌላውንም አለማዊ እውቀት እንደ መፅሀፍ ቅዱስ መቀበልና ማመን ሲጀምር ነው፡፡የመንፈሳዊውን ዓለም እውቀት ከአለማዊ እውቀት እና ስልጣኔ ጋር አስተባብሮና አስማምቶ ለማየት ቢቻል እንደ ሀገር አሁን ያለንበት ምስቅልቅል ውስጥ ላንገባ እንችል ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ፖለቲከኞቻችን ለማንኛውም ቅዱስ-መፅሀፍን ልትተኙ ስትሉ እንኳን ትንሽ ገልበጥ እያደረጋችሁ አንብቡት፡፡ያለበለዚያ አሁን እየሄዳችሁበት ባለው አካሄድ ለሀገራችን ትርጉምና ፋይዳ ያለው መፍትሄ ልታመጡ አትችሉም፡፡
ቸር እንሰንብት፡፡
Paulos says
Bravo wake-up
ሃሳብህን እጋራለው ዋናው ከዚሁሉ ነገር ማን እንዳለ ፖለቲከኞች ተብየዎቹ አያውቁም።
Paulos says
Bravo wake-up
ሃሳብህን እጋራለው ዋናው ከዚሁሉ ነገር. በስተጀርባ ማን እንዳለ የኛ ፖለቲከኞች ተብየዎቹ አያውቁም።
Markos says
TPLF-Tigres have a satanic bacground.
They even do not belong to the Axumites.
They are Jews who migrated to Ethiopia during the time of king Kaleb.
There was Christian masacre in Yemen Nagra by Jews.
Jews by the leader of Phinhas in Nagra killed and burned Christians and churches.
King Kaleb waged war against Jews leader Phinhas to save Christians in NAgra.
He defeated the Jewsish leader Phinhas and the Jewish there.
He made them captives and brought them to Axum.
Then they lived there under the rule of Christian Axumite kings.
During Yodit Gudit they became so powerful to revenge Axumite Christians.
Now they made a name Tigre and claim all Axumite Civilization.
They belive in JUdaism of Babylonian TAlmud.
They are inherently against Christianity and Christians.
That is why they hate Amhara,Orthodox Christianity and the Monarchy.
TPLF is a mask for the Nagra Jewish conspiracy.
The nature of TPLF is same as the nature of satanic Jewish.
World Jewery used to disposes every nation it controls.
The same is true of TPLF.
They use fake names the same way Jews do.
The total war against Ethiopia is the war waged by international satanic Jewery.
TPLF is the agent of Illuminati.
TPLF is part of satanic world jewry and illuminati.
THey have formed satanic alliance.
TPLF exploits the sp called Tigres the same way satanic world jewry exploits ordinary Jews.
TPLF and Illuminati want to deliberately create chaos and dismantle Ethiopia.
Then they want Tigre republic to be created out of chaos.
They are creating chaos to achieve independent Tigray.
Additional referces for my views.
SOURCE:http://www.rense.com/general66/rosen.htm
http://www.satenaw.com/amharic/archives/21224
Mulugeta Andargie says
ያልበላንን ብታክልን!
ወይ ባንቀልባ ብታዝለን
እሹሩሩ ብትለን!
ቋት አይሞላ ቃል!
ቢንዠረገግ ይበቃል!?
የገደል ማሚቶ ጫጫታ
እንዲያው! ብቻ! ሁካታ!
ቃል ኪሎ ይመዝናል!?
የበርበሬ ወይ የጌሾ ያህል ይደፋል!?
ይገርማል! ይገርማል! ይገርማል!