• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት

October 14, 2018 01:50 pm by Editor 8 Comments

የኦሮሚያ ክልላዊ ምክርቤት ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. የበርካታ አዲስ የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች አደረጃጀትን ሲያጸድቅ የአዳዲስ ተሿሚዎችን ሹመትም አጽድቋል። ከእነዚህ መካከል የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር እንዲሆን የተሾመው መሐመድ አዴሞ ነው። የአቶ ለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” የሚለው ልብ የሚያረካ አባባል ከመሐመድ አዴሞ ለዓመታት የዘለቀ ፀረ ኢትዮጵያዊነት አቋም ጋር የሚጋጭባቸው ወገኖች የሹመቱ ጉዳይ ትልቅ ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ መሐመድን ብቃት ካለው ባለሙያ አንጻር የሚመለከቱት ሹመቱ ትክክለኛ ብቻ ሳይሆን ገጣሚም ነው ይላሉ።

ለሃያ ሰባት ዓመታት በግፍ ቀንበር ሥር የነበረውን ሕዝብ በለውጥ ማዕበል ውስጥ በማስገባት “እንቁላሉን ከውስጥ የሰበሩት” የለማ ቡድን (ቲምለማ) አባላት በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ብቻ ሳይሆን ሞተ፣ አበቃለት የተባለውን ኢትዮጵያዊነትንም እንደገና እንዲያንሠራራ አድርገዋል። ከዚህም አንጻር በአንድ ወቅት አቶ ለማ “የኢትዮጵያ ህዝቦችን ያስተሳሰረው የደም ሐረግ ብርቱ ነው። ድልድያችን ሻማ፣ ከዘራችን ቄጤማ አይደለም፤ ዘመን ባስቆጠረ አብሮነታችን ወደላቀ ደረጃ እንደምንሸጋገር እናምናለን” ማለታቸው ይታወሳል። ከዚያም ሲያልፍ የእርሳቸው ቡድን አገር ያዳነ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ይህንን ያህል ከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት በሕዝብ ዘንድ እንዲሰርጽ ያደረጉ ታላቅ ሰው እንደ መሐመድ አዴሞ ዓይነት ፀረ ኢትዮጵያዊ አቋሙን በገሃድ ለዓመታት ሲሰብክ የቆየ ሰው የኦሮሚያን ሚዲያ እንዲመራ እንዴት ፈቀዱ ሲሉ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ይጠይቃሉ። አቶ መሐመድ አዴሞ በርግጥ በባለሙያነቱ ብቃት ያለው ሰው ነው በማለት የሚናገሩ በፖለቲካ አቋሙ ግን ፍጹም ለቦታው የማይመጥን ነው በማለት ያለፈውን ታሪኩን በማንሳት ይዘረዝራሉ።

ጎልጉል ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሚዲያ ሰው እንደሚሉት “መሐመድን በቅርብ ባላውቀውም ከሥራ ጋር በተያያዘ ለመገናኘት ችለናል፤ በተደጋጋሚ በማንኛውም ሚዲያ ላይ ቃለምልልስ እንዲያደርግ ሲጠየቅ በእንግሊዝኛ ወይም በኦሮሚኛ ካልሆነ አልቀርብም በማለት መልስ የሚሰጥ ሰው እንደነበር አውቃለሁ፤ ለራሴም ይህንኑ መልስ ሰጥቶኛል” በማለት ይናገራሉ።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ለበርካታ ዓመታት መሐመድን በማኅበራዊ ሚዲያ ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸውን በመጥቀስ ሲናገሩ፤ “እኔ እስከማውቀውና በኔ አመለካከት መሐመድ አዴሞ በፀረ ኢትዮጵያዊነት ከጃዋር የሚበልጥ ጽንፈኛ ነው ለማለት እችላለሁ፤ ጃዋር የፖለቲካ ቁማር የሚጫወት ጥቅመኛ ስለሆነ አንዳንዴ እንኳን ሰዎች ደስ የሚላቸውን በመናገር የሚደልል ቁጭ በሉ የሚባል ዓይነት ነው፤ መሐመድ ግን ተሳስቶ እንኳን ይህንን የሚያደርግ አይደለም፤ ጥላቻውን ባገኘው መስመር ያለልክ የሚናገርና የሚጽፍ ነው” ይላሉ።

መሐመድ አዴሞ ከአስራስድስት ዓመት የስደት ኑሮ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የለማን ቡድን የተቀላቀለው ከበርካቶች አስቀድሞ ነው። ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የአቶ ለማ መገርሣ አማካሪ ሆኖ ሲሠራ ቆቷል። ድምጻቸው ጎልቶ ባይሰማም የመሐመድን በፍጥነት የአቶ ለማ አማካሪ መሆን የጠየቁ ግን ጥቂቶች አልነበሩም። በተለይ እርሱ ለዓመታት ሲያራምደው የነበረው አቋም፤ የለማ ቡድን ከሚከተለው የኢትዮጵያዊነት ትርክት ጋር በቀጥታ የሚጋጭ በመሆኑ መሐመድ ለአቶ ለማ ሊሰጠው የሚችለው ምክር ምን እንደሚሆን ለመገመት የሚከብድ ሆኖ ቆይቷል። ከዚህ አልፎ ግን የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር ሆኖ መሾሙ አቶ ለማ መሐመድን አጠመቁት ወይስ መሐመድ አቶ ለማን “በምክሩ” አሸነፋቸው ብሎ የሚያስጠይቅ ሆኗል።

መሐመድ አዴሞን በቅርብ የሚያውቁትና በኦሮሚያ ውስጥ በጋዜጠኝነት የሚሠሩ ለጎልጉል የሰጡት አስተያየቶች መሐመድን የሚጠራጠሩት ከሰጡት በሌላው ጥግ የሚመደብ ነው። “መሐመድን ልንለካ የሚገባው ከለውጡ በፊት ባለው አቋሙ ሳይሆን ከዚህ በኋላ ባለው ነው፤ እኔ እስከማውቀው ከለውጡ በኋላ ከዚህ በፊት የነበረውን አቋም የማያራምድ መሆኑን ተመልክቻለሁ፤ ጽሁፎቹን ስከታተል ስለነበር እንደበፊቱ ዓይነት ምንም ዓይነት ነገሮችን ሲጽፍ አላነበብኩም” የሚሉት ኦቢኤንን ሲያገለግሉ ቆይተው አሁን በግል ሥራ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሙያ ናቸው።

ስለ ኦቢኤን በቅርብ የሚያውቁ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ደግሞ በፓርቲው (ኦዴፓ) በተወሰነው መሠረት ከፓርቲው ውጪ ያሉ ሰዎች ወይም ባለሙዎች በአመራር ላይ ብቃታቸው እየተመዘነ ይመደቡ በሚል በተወሰነው መሠረት መሐመድ ይህንን መስፈርት የሚሟላ ሰው ነው። ፓርቲውም ቃሉን በመጠበቁ ሊመሰገን ይገባዋል ይላሉ።

ጎልጉል ከተለያዩ ባለሙያዎችና በኦሮሚያ ላይ በሚዲያው አካባቢ የሚሠሩ ሰዎችን አነጋግሮ ባገኘው መረጃ መሠረት አብዛኛው በፖለቲካው ዙሪያ ያለ ሰው የመሐመድን መሾም እንደሚደግፍ ነው። አንዳንዶች እንደተናገሩት ደግሞ ከስድስት ወር በፊት ጽንፈኛ አቋም መያዝ የመሐመድ ብቻ ሳይሆን የበርካታ ኦሮሞዎች አመለካከት ነበር፤ አሁን ግን ለውጥ ከመጣ ወዲህ በርካታዎቹ ለዘብተኛ ወደመሆንና የጋራ የሆነች አገር ለመሥራት ፍላጎትም ፈቃደኝነትም እያሳዩ ነው፤ መሐመድም በዚሁ መታየት አለበት የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያዊነት አቋማቸው የበርካታዎችን ቀልብ የሳቡት አቶ ለማ መገርሣም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች አንዳንዶች በዓይነቁራኛ ይመለከቱታል። ከዚህ ጋር ተያይዞም አንዳንዶች አልፈው ተርፈው የትግራይ የበላይነት በኦሮሞ እየተተካ ነው የሚል የድፍረት አስተያየት በመስጠት ይሞግታሉ።

የመሐመድ አዴሞን ሹመት በርካታ በሙያው ላይ ያሉ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቲች በተለይ ደግሞ የህወሓትን አቋም በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት የሚሰብኩ “ታጋዮች” ደግፈዋል፣ ሙያዊ ብቃቱንም አሞካሽተዋል። ፍጹም መቀበል የከበዳቸው ደግሞ ከፓርቲ ውጪ ያሉ ሰዎች ይሾሙ ቢባልም ለቦታው የሚመጥን ሌላ አወዛጋቢ ያልሆነ ኦሮሞ ጠፍቶ ነው አቶ ለማ ይህንን ሹመት የፈቀዱት ብለው በመጠየቅ ቀጥሎስ የጃዋርንና የፀጋዬ አራርሣን ሹመት እንጠብቅ ሲሉ ይሳለቃሉ።

መሐመድ አዴሞ በትዊተር ገጹ ላይ ኦቢኤን የሕዝብ ሚዲያ መሆኑን በመግለጽ የግል አመለካከቱ በሙያዊ ሥራውና (በሹመቱ) ላይ ተጽዕኖ እንደማያስከትልበት፤ ሥራውንም የሕዝብን ጥቅም በማስጠበቅ እንደሚያከናውን ተናግሯል። ይህንን የተመለከቱ አንድ አስተያየት ሰጪ እንዳሉት “ቅዱሱ መጽሐፍ ‹በሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ› እንዳለው እንግዲህ ወደፊት በሥራው እናየዋለን” ብለዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Kalacha Boku says

    October 15, 2018 01:05 am at 1:05 am

    The funy thing is ,that you are poisened by Oromo hatrade. You better ask yourself what you are thinking and your ansisters were doing. Oromo was feeding your anisters and now feeding you. Beggers became colonizers, they don’t know equality. Niw no way out to live in equality or ….

    Reply
  2. girma says

    October 15, 2018 03:53 am at 3:53 am

    አንተን ብሎ ፀሀፊ ፡አፀያፊ

    Reply
  3. Sergute Selassie says

    October 15, 2018 03:47 pm at 3:47 pm

    ህም።

    Reply
  4. Sergute Selassie says

    October 15, 2018 03:48 pm at 3:48 pm

    ህም።
    https://sergute.blogspot.com/

    Reply
  5. Gi Haile says

    October 16, 2018 04:09 am at 4:09 am

    ይህ ሰው የሆሮሚያ ክልል የሚዲያ ኃላፊ እንጂ የፌደራሉ አይደለም ። ይህ ሰው የሆሮሚያን ሕዝብ በተመለከተ የሚያስተላልፈው ማንኛውም መልዕክት ክልላዊ ተፅህኖ እንጂ የፌዴራሉን ጁርስዲክሽን ሰለመፃሩ ምንም ፍንጭ የለንም ሰለዚህ የክልልን ሥራ ከፌደራል ጋር በናጋጨዉ ጥሩ ነው የዚህ የዚህ አገላለጽ ካላችሁ የትግራይ ሚዲያ መቶ በመቶ ለትግራይ ጠቀሜታ የቆመ ሚዲያ ነው ሌላውን ክልሎች ሚዲያ የሚያጥላላ ልቅ የሆነ ነው በእውነት ሚዛናዊ የሆነ ጽሑፍ ብታቀርቡ ብዙ አንባቢ ሊኖራችሁ ይችላል ። ፌዴራሉን ክክልሎች ለዩ ለሕዝቡ ግልጽና መረዳት በሚችለው መልክ አቅርቦት ብታደርጉ ጥሩ ነው ።

    Reply
  6. yuya jamal says

    October 18, 2018 03:27 pm at 3:27 pm

    anti oromo and phobia team! Mohammad best educated and excperinced man!! your intenetion is to attack nknown oromo intelagenices!!!!!!!! Gim ahyiya

    Reply
  7. Takele M . says

    October 25, 2018 04:34 pm at 4:34 pm

    ሕዝብ ይወቅባቸው
    አቤቱ ጌታዮ ለእምዮ ኢትዮጵያ
    ካለአንት ማን አላት ሊበታትኗት ነው አንተ ካልረዳሃት
    ልትቆራረስ ነው አንተ ካልቆምክላት
    በአንድ መንደር ተወልደን
    አንድ ሆነን በሰፈር ስንጫወት አድገን
    አንድ ወንዝ ጠጥተን በነንድ ማእድ በልተን
    አንተ እኮ መጤነህ አንተ ሰፋሪ ነህ እኔ ነኝ ባለሃገር
    ሂድ ውጣ ሂድ ከዚህ እያሉ ወገንን ማሸበር ወንድምን ማባረር
    ከየት የመጣ ነው እንዲህ አይነት ነገር
    በኢትዮጵያ ተወልደው ከህዝቡ ጋር ኖረው
    ሃገሬ እሷ ማለት ያቃታቸው
    ኢትዮፕያ ብለው መጥራት ያስጠላቸው
    የድንግል ማያም ልጅ አንተ ድረስላት ልትበታተን ነው
    በውሸት ትርክታ ሕዝኑን ከሕዝብ ጋር እያጫረሱት ነው
    በቅዱስ መጽሐፍ ነብዮ ኤርሚያስ አንድነታችንን ዘርዝሮ ነገረን
    ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉሩን አይለውጥም አለን
    ለባእድ ስንታይ አንድ ነው መልካችን
    ወዴት ሄዶ ይሆን መተዛዘናችን
    ወዴት ነው የጠፋው መፈቃቀራችን
    ፈጣሪ ይመልስ የቀድሞ ክብራችን እንድሁም ፍቅራችን
    መለያየታችን ለምንስ ይበጃል
    መጫካከናችን ለማንስ ይጠቅማል
    ዓለም ልታልፍ ነው ለሃገር ሳንሰራ ወንድሙን ሊያባርር አንዱ አንዱን ሲገድል
    ቅዱስ መጽሀፍ እንዲህ ይነግረናል እግዚአሔር አምላክ ከነገሮች ሁሉ6 ቱን ይጠላል
    7 ተኛውን ግን ነፍሱ ይጠየፈዋል ጠብን የሚዘራ በሰዎች መካከል
    እናውቃቸዋለን ይህን የሚሰሩ በእውቀት በጥበብ የተመራመሩ
    አንዳንድ ምሁራኖች ወደ ውጭ ልከን እኛያስተማርናቸው
    ሐገርን ማሳደግ ህዝብን ማስተባበር ነበረ ስራቸው
    ታዲያ እነሱ ግን እንኳን ሊሰሩበት በተማሩት እውቀት
    ሆንዋል ተግባራቸው አንዱን ዘር ካንደኛው በክፋት መለየት
    ይሄ ነው እንግዲህ ትልቁ ስራቸው
    የማይታዘዙ ለወላጆቻቸው
    እርቅን የማይሰሙ ገንዘብ የሞወዱ ትእቢተኛ ናቸው
    መጥፎ ግብራቸውን የህዝብ ይወቅባቸው
    ሃገር ያበላሹ የሰው ደም የጠጡ ነፍስ ገዳይ ናቸው
    ከዚህ ስራቸው የማይፀጸቱ
    እኔ ረግሜአለሁ በቆፈሩት ጉድጓድ እነሱ ይግቡበት የቁም ሞት ይሙቱ
    የኢትዮጵያን ትንሳኤ ፈጣሪሊያሳዮን
    እንዘምራለን እንፀልያለን በአንድነት ሆነን
    እናት ኢትዮጵያ ጨለማሽ ተወግዶ ብርሃንሽ ይበራል
    አምላካችን ቸር ነው ሁሉን ያሳየናል
    ይልማሰው ባገሩ መታሰቢያነቱ እናት ኢትዮጵያ እንዳትበታተን ሕዝብ እንዳይለያይ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ሃብቷን ንብረቷን በዘርፉ የህዝቡን አንድነትና ፍቅር ባጠፉ በእነዚህ የእናት ጡት ነካሾች ህይወታቸውን ለገበሩ ሰውነታቸውን ለጎደለ ለታሰሩ ለተገረፉና ለተሰደዱና ትንሳኤዋን ለሚመኙ ሁሉ የሁንልን መስከረም 2011

    Reply
  8. Roba says

    October 28, 2018 04:12 pm at 4:12 pm

    ይህ ሰው የተሾመው ለኦሮሚያ ክልል እንጂ ለፌደራል አይደለም፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ በላይነት የሚባለው ምኑ ላይ ነው?

    Reply

Leave a Reply to Gi Haile Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule