• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዶ/ር መረራ የፍንዳታውን ዜና “እንጠራጠረዋለን” አሉ

October 22, 2013 06:39 am by Editor 3 Comments

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ “አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና አጠጥሎታል።

በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች “የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውም አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ ለሌላ ተግባር መዋሉን እንቃወማለን” በማለት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በማሳየት ዜናውን ለማጀቢያነት ተጠቅሞበት ነበር።

በግል አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው “ብዙዎች፣ እኔም ጓደኞቼም በጥርጣሬ ነው ያየነው” ሲሉ ከተቆረጠው ንግግራቸው ተደምጧል። ዶ/ር መረራ “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ ራሱን አያጠፋም” ካሉ በኋላ “ስለዚህ እውነት ተደርጓል?” የሚለው ትልቁ ችግርና የጥርጣሬው መነሻ እንደሆነ አመልክተዋል።
ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ የሚነሳውና በታጣቂ ሃይሉ ፈርጣማነት የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  /ትህዴን/ በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች አይደሉም ሲል ከሁሉም ወገን የተሰራጨውን ዜና በዜሮ አጣፍቶታ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል።የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችኋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን በመግለጽ የሶስት እስረኞችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 በራሱ ኦፊሳላዊ ድረገጽ ላይ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ይህ ዜና እስከተጻፈበት ቀን ድረስ በሰነድ አስደግፎ አላቀረባቸውም።

በሌላ በኩል ኦክቶበር16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 3ቀን 2006ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን ዘግቧል።

Bomb-Blast-Addisየአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሶማሊያውያኑ መካከል፣ አንደኛው ከ20ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን ያመለከተው ሪፖርተር ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያኑ ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጂ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ጠቁሟል፡፡ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሏል በማለት ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ አድማስ በበኩሉ አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት መውሰዱን አድራሻው አልተመዘገበ የትዊተር ማረጋገጫ በማመላከት ከዚህ በታች ያለውን ዜና አስነብቧል።

ባለፈው እሁድ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ሁለት ተጨማሪ የፍንዳታ ጥቃት ለማድረስ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ቡድን እንደዛተ የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የዛቻው ተአማኒነት ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ የሚገኙ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዳይለያቸው ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ዜናውን የከፈተው አዲስ አድማስ፣ “የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ቡድኖች ግጥሚያ በሚካሄድበት ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጅና ሽብር ለመፈፀም በመዛት የሚታወቀው አልሸባብ “ድርጊቱ በኔ አባላት የተፈፀመ ነው” ብሏል በማለት አልሸባብ በቦሌ ሚካኤል ለተከሰተው ፍንዳታ ሃላፊነት እንደሚወስድ በትዊተር እንዳስታወቀ ማሰራጨቱን፤ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አካባቢ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እንደዛተም ገልጿል፡፡

በቦሌ ሚካኤል በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ ሁለት የሶማሊያ ተወላጆች መሞታቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ ከሟቾቹ አንዱ የኢትዮጵያ ማሊያ በመልበስ ከኳስ ተመልካቾች መሃል የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደነበር መጠቆሙን አዲስ አድማስ በዜናው አውጇል። አዲስ አድማስም ሆኑ ሪፖርተር ፖሊስ የነገራቸውን ከመዘገብ ውጪ ከሌሎች ሚዲያዎች፣ በተለያዩ ማህበረ ገጾችና በቅርበት ከህብረተሰቡ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመለክቶ ዜናውን ላቀበላቸው ክፍል አላቀረቡም።

የኢህአዴግ አንደበትና የንግድ ድርጅት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩን ጠቅሶ አስታውቋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳለው ፍንዳታው የደረሰው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ቀበሌ 01 በተለምዶ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በአንድ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ፖሊስ ፍንዳታው ፈንጂ መሆኑንና በጥቅም ላይ የዋለው ቲ ኤም ቲ የተባለ የፈንጂ ዓይነት መሆኑን እንደደረሰበት አረጋግጧል። ፍንዳታውንም ሁለት ሶማሊያውያን ማቀነባበራቸውን ፖሊስ እንዳረጋገጠና ግለሰቦቹ የአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ አባል መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን ጄኔራል አሰፋ አብዩ መናገራቸውን የጠቆመው ፋና ከሁለቱ አሸባሪዎች መካከል አንደኛው ወገቡ ላይ የታጠቀና ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር የተዘጋጀ መሆኑን ያመላክታል ብሏል።

ሌላኛው አሸባሪ በሻንጣ ፈንጂ የያዘ ሲሆን፥ የፈነዳውም ፈንጂ በሻንጣው ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው ጀነራል አሰፋ ያስረዱት። ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር ሲዘጋጅ የነበረው ግለሰብ የታጠቀው ፈንጂ ግን እንዳልፈነዳ አመልክተዋል። አሸባሪዎቹ በአጠቃላይ ሶስት ፈንጂዎችንም ይዘው ነበር። አሸባሪዎቹ ህዝብ ባለበት ስፍራ አደጋ ለማድረስ ተከራይተው በነበሩበት ቤት ውስጥ ሲዘጋጁ ፍንዳታው ደርሷል ብሎ ፖሊስ እንደሚጠረጥር ነው የጠቆሙት። ከአሸባሪዎቹ ጋር ፖሊስ የእጅ ቦምቦችንና ሽጉጥ ከነጥይቱ አግኝቷል።

የፋናን ዜና ተንተርሶ የተሰነዘሩ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ሪፖርተር በፈነዳው ፈንጂ ህይወቱ ያለፈው አንደኛው ሰው ሰውነቱ መበታተኑና የአይን እማኞችን ገልጾ መዘገቡን ያስታውሳሉሉ። ፈነዳ የተባለው ፈንጂ ከፈነዳ በሁዋላ አጥፍቶ ለመጥፋት የተዘጋጀው ሰው የታጠቀው ፈንጂ አለመፈንዳቱ መገለጹ ከሙያ አንጻር ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ድርጊቱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጋር ለማገናኘት የብሔራዊ ቡድን መለያ ሹራብ ተገኘ መባሉ ድርጊቱን ድራማ ያስመስለዋል ባይ ናቸው። (ፎቶ: ሪፖርተር)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tsinat says

    October 22, 2013 11:50 pm at 11:50 pm

    Why don’t they give the choreographic part of the movie trailer to those “Limatawi” artists?. I believe they would act more professionally than this.

    Reply
  2. በለው! says

    October 23, 2013 07:02 am at 7:02 am

    ፩) ኦክቶበር ፲፫/፳፻፲፫ ኢቲቪ ዜና ሲሰብር “የፈንጂ ፍንዳታ” በለው!
    “የተጠመደ ወይንም ሌላ ቦታ እንዲፈነዳ የተዘጋጀ ፈንጂ ባልታወቀ ምክንያት መፈንዳቱ ተሰማ” ከፈነዳ ሲፈነዳ አጠገቡ ቆመው ሲመለከቱ የነበሩ ሰዎች ነበሩ ማለት ነው። ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ በቦታው የተገኘ ጋዜጠኛ ወይም አጣሪ እራሱ እንዳስቀመጠው አድርጎ ክስተትን መዘገብ በጣም ቅሌት ነው!። **የሀገር ውስጥ ቅጠር ጋዜጠኛች ለጠ/ሚኒስትር ኀይለማርአም ደስአለኝ ማብራሪያና መልስ ካቀረቡ በኋላ ግለሰቡ ከመልሱ ላይ ጥያቄ ለማውጣት ሲታገሉ ሳይ ያሳዝኑኛል። በቴሌቪዥን መሰኮት የሚታየው በጥሩ የተግባረዕድ ምሩቅ ኤሌከትሪሺያን ሙያተኛ ለፎተግራፍ የዘረጋው ይመስላል፡ ይህ ገመድ እንኳን ቦንብ ተቀጣጥሎበት ሊፈነዳ የተገጣጠመበት ፕላስተር እንኳ አቧራ አልነካውም። ሁለት ሕፃናት ፍራሽ ሥር ተኝተው እያሳዩ ተበታትነው ተገኙ? አንደኛው ፈንጂውን እንደታጠቀ ሳይፈነዳ ሞተ? ማለትም የሌላውን ቦንብ ፈንድቶ ቁጭ ብሎ ሲሞቅ ይሆን የሞተው? ይህ አሮጌ ሽጉጥ ምንድነው? ግለሰቦቹ እራሳቸውን በቦንድ ከአፈነዱ በኋላ ለደስታ መግለጫ የሚተኩሰት ነው?ወይንስ ከማፈንዳታቸው በፊት ሰው እንዲሮጥ ወይንም ተሰብስቦ ድምቀት እንዲሰጥ የዳመራ ችቦ መሆኑ ነው? ዘይገርምዩ አለ… ፈንጂው ዶሮ ቤት እንኳን ለማፍረስ አቅም የለውም! ግን አቶ ኅያለመልስ በላፈው ሳምንት “በኢትዮጵያ አንድም ቦንብ አይፈነዳም!” ብለው ሲፎክሩ አልነበረምን?ሰሞኑን እናፈነዳለን ጠብቁን ማለታቸው ይሆን? ምን አልባት የአልሸባብ ምርኮኞች ቃሊቲ(ቅሊጦ) ነበሩን ሁለቱን አምጥተው ሞክረውባቸው ይሆናል?
    ** ህወአት/ወያኔ ገድሎ ለመርዶና ለቀብር አንደኛ ነው ስንት ንፁሕ ትግሬ አልቋል!?ግን ተስፋዬ ግበረእባብንና ጃዋር መሐመድ እየቀወቱት አለው በቅርብ ጥርግ ብለን እነገባለን መከላከያውን ኢኮኖሚውን ልንይዘው ነው የሚሉትን መንግስት ምነው ዝም አለ! እነሱን በመካከለኛና ከባድ ደረጃ አቅፈአቸው ይሆን? ጠርጥር በለው! ..ምን አልባት ሙስሊም የኦሮሞ ፈርስት ጆሌ ብሸፍቱ! ከሆኑስ? እነሱ ናቸው በአውሮፓ፣ ካናዳ ፣አሜሪካና ደቡብ አፍሪካ፣ እስካንድኒቪያን ሀገሮችን ጨምሮ የሚደነፉት!አለ ነገር!

    ፪) ኦክቶበር ፲፬/፳፻፲፫ ነገሩን ባለሙያ ሲያጣራው “ፈንጂ ፍንዳታ አፈንጂዎች ሱማሌያውያን ሆኑ!
    በአካባቢው የሚኖሩ ሱማሌያውያን ጉዳዩን አውግዘው መረጃ በመስጠት ከመንግስት ጋር ተባባሩ። በለው! የሚተባበሩት ሱማሌያውያን ለምን ቀደም ብለው ጥቆማ አላቀረቡም? ግን ህወአት/ወያኔ ሱማሌን ነጻ ሲያወጣ ሀገሩን እስወረረ ማለት ነው? “ኢትዮጵያን የሚመሩ ባለሥልጣን ኤርትራውያን አሉ እኔም ኤርትራዊ ነኝ” ስብሃት ነጋ…ታዲያ ለዚያች ለበሬ ግንባር ለምታክል መሬት ፸ሺህ ወጣት ያስበላነው ለማን ነበር? ማንን ነበር?ለምን ነበር? ሁሉም ዜሮ ዜሮ..ቅንደባም! የኢትዮጵያ ብሐራዊ ቡድን ማሊያ አድረገው ነበር ምን ለማለት ነው? ኢትዮጵያ የሱማሌ ዜግነት ያላቸውን ለእግር ኳስ አሰልፋለች ማለት ነው? አሃ..ግጥሚያው የቦንብ ነበር ማለት ነው? ይህ ቦንብና ሽጉጥ ከዚህ በፊትም ታይቷል መሰለኝ!?። ለመሆኑ ይህ ሁሉ ገመድ በቦርሳ ነው? በጆንያ ነው?በወዛደር አሸክመው ነው?በጋሪ ፈረስ አሰጭነው ነው?በካቻማሊ ነበር ? ሊያጓጉዙት የነበረው ለእስፖርት ደጋፊው ለማሳየት ይሆን? ። ምንም ይሁን ምን እንኳንም በድሃ ሕዝብ ላይ አደጋ አልደረሰ። አላህም አምላክም ይክበር ይመስገን!!! የሆነ ሆኖ ኢህአዴግ የሽብርን መፈክርና ጥላቻን የሚነዙትን ከወስጥም ከውጭም ማጽዳት ከፍተኛ ኀላፊነት አለበት። የሚጽፉት መፅሐፍ፣ የሚሰጡት ቃለመጠይቅና፣ የሚለጥፏቸው ማስታወሻዎች፣ ሁሉ ብዙ ይጠቁማሉ… ኢህአዴግ ለህዝብ እውነቱን በአስቸኳይ ማሳወቅ አለበት!። የሽብርተኛ አዋጁ መጠናከር አለበት የሚሉት አሽቃባጭ አድርባዮች ሆድአደሮች ናቸው!ዋናው ጉዳይ ሌባንና ሽብርተኛን ትቶ በጉያ አቅፎ፣ አልሰማሁም፣ አላየሁም፣ አላውቅም ማለትና አንድነት! ሰማያዊ! እና መድረክ! እያሉ እጅ መቀሰር ጠረጴዛ ምምታት በባርላማ መደንፋት እራስን ማታለል፣ በእውነቱ መጃጃል ነው!! ካድሬዎቻችሁን ፈትሹ!ሹማምንቶቻችሁ ንክኪ አላቸው!!
    ፫) ኦክቶበር ፲፮/፳፻፲፫ የተሰበረው ዜና ጭራሽ ወለቀ!
    *የኢህአዴግ አንደበትና የንግድ ድርጅት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩን ጠቅሶ አስታውቋል።
    “አሸበረ ማለት!” ቀወጠው ጮኽ (አቀለጠው )እረበሸ ፣አስደነገጠ፣ ማለት ነው” ድርጊቱን የሚፈጽመው “አሸባሪ ይባል” እዚህ ሊደረግ የነበረው ንፁሃን ዜጎችን በደስታቸው መካከል ሠርገው ገብተው ሕይወት ማጥፋት ነው። *ስለዚህ “ከቤት ንበረት ከይዞታ ቦታ ቀዬ አባሮ ማፈናቀል አደለም ማስፈር ነው” የሚባለውም እንዱ የእውቀት ጉድለትና ማጭበርበር ነው።**ባለፈው ሶማሌያውያን ነበሩ የእስፖርት ማሊያ አጥልቀው ነበር እሺ…ከቀን በሗላ ኢትዮጰያውያን ሆኑ…በሚቀጥለው ሳምንት ቻይና ይሆናሉ። ወይ እነኝህ ድሃሆች እሳት አቀጣትለው ሲሞቁ ጋዝ ፈንድቶባቸው ሞተው ይሆናል። አለዚያም ከሰል አቀጣጥለው እንቅልፍ ወስዷቸው ጭስ ገድሏቸዋል። አለበለዚያ ሀገሪቱ ባለቤት የላትም ማ ምን መሥራት እንዳለበት በውል አልታወቀም!፣ ሠራዊቱ ንግድ ሲያጧጡፍ ሥራውን ዘንግቷል፣ምንአባቱ ብሏል፣ ወይንም ድራማው አልተሳካም! እጅግ አስጊና የህዝብ ማጫረስ ተልዕኮ ከኢህአዴግ አባላት ውስጥ በሻቢያ ጋር ግንኙነት ተፈጥሯል በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ ጦር መሥበቅ ሰማያዊ ፓርቲና አናድነት ፓርቲን መተናኮል የውሸት እባብን በጉያ ይዞ ማደርና የዋህ እርግብ ማብረር ነው…..አዎን! “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አይጠፋም” “አጣፍቶ የሚያጣፋው አጥፊ ጠፊ “ግን አደገኛና ተሞክሮ ያለው ህወአት ነበር! ነው! ይሆናልም!። ግን እግዝሐብሄር ለድሃው ሕዝብ ጥላ ከለላ ይሁነው ክፉን ያርቅልን አሜን! በቸር ይግጠመን

    Reply
  3. Truly says

    October 25, 2013 02:08 am at 2:08 am

    Woyane is the master mind of this dirty bombing of Addis Ababa and Nairobi.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule