• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል

November 30, 2016 11:16 pm by Editor 5 Comments

የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።

በዛሬው እለት ፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በታጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስርዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሆኑን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።

በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ ገለጻ አድርገዋል። ከዚያም በሆላንድ፣ በጀርመን እና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ ሃገሪቱ ሁኔታ መወያየታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኛል ብለው በምርጫ እና በሰላማዊ አግባብ ሲታገሉ የነበሩት ፕ/ር መረራ ጉዲና ለምን እንደታፈኑ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር በአውሮፓ ህብረት ተጋብዘው መገኘታቸው ወንጀል መሆኑን የገዥው ፓርቲ ልሳኖች ሲያረግቡት እንደነበር አይዘነጋም። (ፎቶ: Simona Foltyn)

ክንፉ አሰፋ
30 ኖቬምበር 2016

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Aklilu says

    December 1, 2016 12:54 pm at 12:54 pm

    Friends, I sow and greeted Prof. Merara Gudina a day before here in one of Europe city.
    Pleas correct your information.

    Reply
  2. በለው! says

    December 1, 2016 09:53 pm at 9:53 pm

    » ዶ/ር መረራም ሆነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጋር የተጋበዙት በአውሮፓ ሕብረት መሆኑን እያወቀ ሆን ብሎ ልማታዊ ወዶ ገብ ጋዜጠኛ ቢኒያም ከበደ ዶ/መራራ ጉዲና የኮማንድ ፖስቱ አንቀጽ 2. ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ (1). በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶች እና ከጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር ግንኙነት ማድረግ፡ የሚለውን በመጥቀስ “ቀይ መስመር አለፉ ሲል በቀይ ፅፏል።”
    >> ይህ የሚያሳይው የመረጃ መቀባበልን መሽቀዳደምን እንጂ ይህ አዋጅ ‘አስቸኳይ’ ከሚለው ቃለ አጋኖ በቀር የአሸባሪው ህግ ስለሆነ ለእሱ ብርቅ ሆኖበት ነው። እኔ የማደንቀው “የአውሮፓ ኮሚሽን የአሸባሪ ቡድን ጠርቶ ስላነጋገረ ጽ/ቤቱ ከሀገራችን በአስቸኳይ ይውጣ ንክኪ ያላቸውም ኤምባሲዎች ይዘጉ! ከዛሬም ጀምሮ ምንም ዕርዳታ እንዳትልኩብን ብሎ በጥቁር ቢጽፍ ጥሩ ነበር።

    **የኢህአዴግ ካድሬ፡ጋዜጣ በሎች፡ተደጋፊዎች፡አድርባዮች(አዜብ ጎላ እንዳሉት) የሚያቀነቀኑት “ዲያስፖራው ለድሃ ወገኑ የምግብ እርዳታ እንዲቆም ማድረጉ..ጸረ ሕዝብነት ነው።”ይላሉ በተጓዳኝ በምግብ እራሳችንን ችለናል…ከአፍሪካ አንደኛ..ከዓለም ሁለትኛ ተብለን የዓለም መንግስታት ፈነደቁ ይሉና…ርሃብ ሳይሆን የምግብ ዕጥረት ከ9-15ሚሊየን ሕዝብ ላይ ተከሰተ ብለው እህሉን ደፍተው ጆንያውን ሸጠው የኢኮኖሚ ኢምባየር የሚገነቡ ናቸው። ቢኒያም ከበደ ካናዳ ቀለም መቀየጥ እንጂ የህወአት የፖለቲካል ቅወጣና ቅየጣ አልገባውም ጭራሽም አይገባውም። ግን አንዳንዶች በሕገመንግስታዊ (ማኒፌስቶ) ጥቅማጥቅማችን ካልተተገበረ ለንብረት መውደምም፡ ለግልበጣም፡ መሐላችሁ ገብተናል እናፈርሳልን!..እንበታትናለን! ሲሉ ምነው ድምጻቸው አልተሰማ?ይህ መፈክርና ቻርተር በነጭ መስመር ጉዞ ሆኖ ነው? አረንጓዴ ይለፍ ተሰጥቶት? ወይንስ የራሱ የታላቁ መሪና የአስቸኳይ አዋጁ ራዕይ ስለሆነ!? ታዘብኩሽ አለ እንዲህ ብስ ስ ስ ስ ስትል ሳይሰማት..ይሁን እስቲ። November 13, 2016
    ********************!
    »…” የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” መራራ ጉዲና….” በቁጥጥር ሥር ዋሉ!”
    ___በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የታሪክ ቁርሾ እንዲቀጥል የሚፈልገው ቡድንና ኅይል ነውን? ምንም እንኳ የሽብርተኛ አዋጁ አብሮ የተቀምጠ፡ ሻይ ቡና ያለ ቢልም …የአስቸኳይ (የችኮላና የችከላ) አዋጁ ግን ስድስት ወር ለብሔር በሔረሰቦች ደህንነት ሲባል ብሔር ብሔረሰቦች..እንዳይናገሩ..እንዳየፅፉ…ዓይነ ስውራን እንኳ ቢሆኑ በምልክት እራሳቸውን እንዳይገልጹ …ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ እንዳይከፍቱ የሚከለክል..ሕገ ጠርንፍ ሲታወጅ ለሕዝቦች (ለውጭ ዜጎችና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቀም ላላቸው ከ፳፭ ኪሎ.ሜ ወጭ እንዳይጓዙ የሚለውን ዕገዳ ሲዘርዝ ሌላውን አጠናክሮ ቀጥሏል። አንዳንዶችም ቀጥልበት ሲሉ ሌሎች አሳጥረን የሚመጣው ይታይ ብለው የሚያደፋፍሩም አሉ።
    ___በዚህ አጋጣሚ ህወአት/የኢህአዴግ ጥልቅ ተሃደሶ ምስክር የሚሆነው ለመጀመሪያ ግዜ ሰው ከሀገሩ ሲከዳ የአዕምሮ በሽተኘ ነው ብሎ ሰው ነጻ ሳያደረግ ጭራሽ በዓለም ፊት የተቃወመን ስፖርተኛ ሌሊሳ ፈይሳን “ጀግናችን ነው የጀግና አቀባበል እናደርግለታለን ኢህአዴግ ደሞክራሲያዊ ነው ተቃወሞ ይደግፋል ያበረታታል” ብሎ ነበር።
    ____ አሁን መራራ ጉዲናን ሲያስር “የጀግና አቀባበል ይህን እንደሚመስል ሕዝብ ለአለም ስብሰባውን ለመሩት ማሰተዋወቁ ነው? በመራራ መታሰር ሌሊሳ ፈይሳ ነፃ ወጣ በለው! ምን አልባትም በአዲሱ ጥልቅና ምጥቅ የምሁራን ካቢኔ ተሃደሶ…የወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ (ገበየሁ) ሥምና ክብር ማጉደፍ የኦሮሞ ዜግነት ለኤርትራዊው ለተስፋዬ ግብረእባብ (ገዳ) የተሰጠ ለምን ለትግሬው ወርቅነህ ገበየሁ (ነገዎ) ይከለከላል።
    ችግራችን ጀመረ እንጂ አላለቀም እንዳይጨርሰን እንጠቀቅ…በመፈቃቀርና በመፈቃቀድ ፰ ከመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ(ገበሬ)የህወአት/ኢህአዴግ የግል ንብረቴ ነው ብሎ በረከት ስምኦን ከነገረን አማራጭ ሶስተኛ ሐሳብ (በመደናነቅና በመሞጋግስ) ልደቱ አያሌው (ጠንካራ ተፎካካሪ) አዲስ ፓርቲም ከወዲሁ ሚዲያው በቡዳ በልቶት ሌት ተቀን ያስጓራዋል ። የቸኮለው አዋጅ ራዕይ ወደታች ለማስረጽ፡ አዲስ የመግባባትና ለነውጥ ማበረታታት እንጂ ለውጥ ተስፋ የለውም!! አንገት አልባ እራስ በለው!! በቸር ይግጠመን

    Reply
  3. Tesfa says

    December 2, 2016 06:26 pm at 6:26 pm

    ፕ/ር መራራ ጉዲና ትላንት የተፈጠሩ ፓለቲከኛ አይደሉም። ከንጉሱ ጀምሮ እስከ ደርግ ከዛም በዘር ሃገሪቱን ለራሱ ጥቅም የከፋፈለውን ወያኔ በፊት ለፊት በሃገር ውስጥ ከሚጋፈጡት ጥቂት ምሁራን መካከል አንድና ቀዳሚው ናቸው። ባጭሩ ፕ/ሩ የሃገራችን ሃብት ናችው። ወስላቶቹ የወያኔ አሽቃባጮችና ነገር ቶሎ የማይገባቸው በውጭ ሃገር ተሰግስገው የሚገኙ ጠባብ የኦሮሞ ብሄተኞች የመራራ ጉዲናን ስም ጭቃ ለመቀባት ትላንትም ዛሬም ይሞክራሉ። ህዝባችን ግን ገለባውን ከፍሬው ለይቶ ያውቃል።
    በአንድ ወቅት ዛሬ አስመራ ላይ የበርበሬና ነጋዴና የግማሽ ቀን የሻቢያ ሰላይ የሆነው ተስፋዪ ገ/አብ በዋሽንግተን የኦሮሞ ጥናት ማህበር ላይ ተገኝቶ ንግግር ሲያደር እንዲህ ብሎ ነበር። “መራራና ሃወኒ” አንድ ናቸው ሲል የስብሰባው ተካፋይ ሁሉ ሳቁን ለቀቀው። ላሰበበት የሚያስቅ ሳይሆን የሚያስለቅስ ነገር ነው የተናገረው። ሃወኒ ማን ናት? የስደተኛ ማስታወሻ በተሰኘው መጽሃፉ ላይ እንደ አድርባይና ወላዋይ አድርጎ ያቀለማት ናት። አድርባይ ተስፋዬ። ወላዋይ ተስፋየ ነው። አላማው ግን ኢትዮጵያዊነትን ለማምከን በሻብያና በወያኔ የተላከ ደላላ ስለሆነ ለመኖር የማይለፈለፍ የማይሰራ ወንጀል የለም።
    እውቁ ፕ/ር መራራ ጉዲና በቅር ቀን ከተናገሩት አንዷን ብቻ ወስደን እንይ። “የታሪክ ሂሳብ ማወራረድ አቁሙ”። ይህች ቃል ብቻዋን የወያኔን ህልውና ትዋጋለች። ወያኔ የሆነ ያልሆነው ታሪክ እየፈጠረ እኛን ሲያተራምስ ያስተዋሉና ሊጋፈጡት የቃጡ ዛሬ አፈር የተመለሰባቸው፤ በእሥር የሚማቅቁ እዕላፍ ናቸው። መራራ ጉዲናን ማፈን የማን አለብኝነቱን የወያኔ ባህሪ በይፋ ያሳያል። በመሰረቱ ጥሪው ከአውሮጳ ህብረት የመነጨ እንጂ ወያኔ እንደሚለው ግንቦት 7 ጋር ራት ለመብላት የተጠሩበት ግብዣ አልነበረም። ሰውን በጉድጓድ ውስጥ በጭስ አፍኖ የሚገል ድርጀት (ወያኔ) ስብዕና የኖረዋል ብሎ መጠበቅ ከቀይ ባህር የሚጠጣ ውኃ እንደመሻት ነው። ይታየኛል ቤተሰብ ተሰብስቦ ቦሌ ሲጠብቃቸው። የወያኔ አንጋችዎች አፈነው ሲያዋኩባቸው። ሻንጣቸው የያዙት ነገር ወደ ቤተሰብ ከመላክ ይልቅ የወያኔ ሾቶሎች ክፍተው ሲፈትሹትና ደስ የሚላቸውን ለራስ ሌላውን ቆሻሻ ሲወረውሩ። በቻይና ሃይል የቆመው የኤሌክትሮኒክስ የስለላ መረብ ስልካቸውንና ሌላውንም ንብረታቸውን ሲጎረጉርና ለክስ እንዲያመቸው የራሱ የሆነ የፈጠራ ነገርን ሲከትበት። በእውነቱ እቤት ቁጭ ብሎ በወያኔ አጋዚ ጦር ሌት ተቀን አንድ በአንድ እየተለቀሙ ሃበሳ ከመቁጠርና ብሎም ከመሞት ራስን እየተከላከሉ መሞት ይመረጣል። ወያኔ ትላንትም ዛሬም ወደፊትም ዘረኛ፤ የሃገር አንድነትና የህዝባችን ጠላት ነው። መታገል ምርጫ ሳይሆን ግድ ነው።

    Reply
  4. Mulugeta Andargie says

    December 3, 2016 04:43 am at 4:43 am

    Guys!! Dr Mererra Gudinna broke the law of the State of Emergency. No one can’t be above the law. We are under the rules and regulations of the country where we live. Gudina lost and broke the law. The State of Emergency is not being exercised only on him. It is to all natives. To all citizens!!! To all men and women who live in!!! He did it purposely This guy is guilty He shouldn’t be a leader of political organization at all. Whether it is bad or good, the law should be respected!! Additionally, the State of Emergency which is applied is temporary and couldn’t affect only him.He broke the laws!! He must go to court!!!

    Reply
  5. Adam says

    December 4, 2016 06:46 pm at 6:46 pm

    Tesfaye’s last sentence says it all. As long as the enemies of Ethiopia, the Tigre Woyanes will stop at nothing including mass murder, incarceration, torture, to break our will, why not die fighting.

    What has sparked in Gondar, should be replicated elsewhere.

    Reply

Leave a Reply to Tesfa Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule