ትናንትና (እሁድ) የከተማ መለስተኛ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠናቆ ለአገልግሎት ተመረቀ፡፡ አሄሄሄ! ውስጡን ለቄስ! አሉ፡፡ ይሄ የባቡር ሥራ ብቻ ሳይሆን በወያኔ እጅ የሚሠራ ሥራ ሁሉ ከፍተኛ ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛና አሳሳቢ የጥራት ችግር እንዳለባቸው በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ቢሊዮኖች ዶላር (ብልፎች ዶላር) ልብ በሉ ቢሊዮን (ብልፍ) ነው ያልኩት ሚሊየን (አእላፋት) አይደለም ፈሶበት ቴሌ ላይ የተሠራውን ሥራ እና ውጤቱን ዐይተናል፣ መብራት ኃይል ላይም አሁንም እንዲሁ በቢሊዮኖች (ብልፎች) ዶላር ወቶበት ከህንድ እንዲገባ ያደረጉት ትራንስፎርመር (ማስተላለፊያ) በሙስና ምክንያት ከጥራት ደረጃ በታች እንዲሠራ የተደረገ በመሆኑ በተገጠመ ቁጥር እየተቃጠለ ምን ዓይነት ችግር ላይ እንዳለን ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ በዚህ በባቡር ሥራው ላይም የጅብነታቸው ጅብነት የሸክላ ሀዲድ ዘርግተው ገደል እየከተቱ ሊጨርሱን ከማለቁ በፊት የበሉትን ገንዘብ ሲከፋፈሉ ቅር ያለው ነበር መሰለኝ አንዱ የዘረጉት ሀዲድ የሸክላ ሀዲድ መሆኑን በማጋለጡ እንደገና እያነሡ አሁን በትክክለኛው የብረት ሀዲድ ቀየርን፤ ይሄንን ያደረጉትንም አባረርን አሉ፡፡ ሲሉ ሰማን እንጅ በትክክልም የሸክላው ሀዲድ ተነሥቶ በትክክለኛው የብረት ሀዲድ ስለመቀየሩ ያረጋገጥነው ነገር የለም፡፡ መቸስ ሰው አስቀርበው?
እነዚህ ሥራዎች የሚወጣባቸው በብድርና በእርዳታ የተገኘ ገንዘብ ዓለማቀፋዊ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሊያሠራ የሚያስችል ቢሆንም ከሙሰኞቻችን ባለሥልጣናት ጅብነት የተነሣ 10 በመቶውን እንኳን እንዲሠራበት ስለማይፈቅዱ እንዲህ እንዲህ ዓይነቶች ከባባድ የጥራት ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ ባጠቃላይ በዚህ አገዛዝ የሚሠራ ሥራ ሁሉ ወይ ገንዘቡ አልዳነ ባለ ዕዳ ሆነን ወይ ብድሩ መጥቶም ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ተሠርቶበት ተጠቃሚ የማንሆንበት ሁኔታ ስለ ሆነ ያለው ነገር በዚህ የገማ አገዛዝ እጅ ምንም ነገር ባይሠራ ሽ ጊዜ ተመራጭ ነው፡፡ እስኪ አስቡት ለእነኝህ የማይረቡ ብላሽ ቆልኮሌ ሥራዎች ሀገሪቱ በትውልደ ትውልድ ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ውስጥ እየሰጠመች እኮ ነው!
እንግዲህ ያው በሸክላ ሀዲድ እየተጓዝን ለማለቅ እንኳን አደረሰን ልበል ይሆን? ባለሥልጣኖቻችንም በዚህ ስንት ጉድ በታየበት የባቡር ሥራ ምረቃ ላይ “ቢያንስ በአዲስነቱ ምንም አይል” ብለው ነው መሰለኝ በድፍረት ሲጓዙበት ሳይ በጣም ነበር የገረሙኝ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
በለው ! says
“ስኳር ቀምሶ የማያውቅ ገበሬ ስኳር እንዳመረውና እንዳማረረው የሱኳር ፋብሪካ ቁጥር ሲቆጥር ሞተ”አባይ ፀሐይ የስኳር ሚኒስትሩ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ተወጥረው ነበር…
“ጤፍ ቀምሶ የማያውቀው ብሔር ብሔረሰብ ከመጠን በላይ መብላት በመጀመሩ ዕድገቱን አቀጨጨው ሲያንገሸግሸው በከተማ ጤፍ ሲወደድ በጎረቤት ሀገራት ጤፍ እረክሶ ሰው የብረት እጥረቱን አሟላበት…”
” የኢትዮጵያ መብራትና ኅይል ባለሥልጣን….” በሻማና ጧፍ ኮርፖሬሽን’ ከተቀየረ ጀምሮ የአካባቢው ሥልጣን አስተባቂ ወዳጅ ሀገሮች መብራት በቀላል ዋጋ ሲሸጥላቸው ውሃ በነፃ ሲቸራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳቦ ሰልፍ ወደ ውሃ ጀርካን ሠልፍ ተሸጋገረ…
” መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ጎን ለመሠለፍ የዩኒቨርስቲ እንጂ ብቁ የተማረ ኅይል የማይፈልቅበት ጥሩ አጫፈሪ ካድሬ ሆድ-አደር ፣ አደር-ባይ መፈልፈያ ወታቦ ሆኖ ያልተማረ እየመራው የተማረ ያለደሞዝ እየተባረረ ዘልቋል…
“ይህ ሙስና መር ኢኮኖሚ…በብድርና በልመና የሞላው ካዝና በቀለበትና በአሳላጭ በፈጣን መንገድ ለመክበር የሚደረገው ፉክክር…በልቶ እያባላ የሚያኖራቸው መካከለኛና ከፍተኛ ትቅማጥቅመኞች አነስተኛና ትቃቅኖችን በባርኔጣ ከልለው..በካኒተራ አስውበው..በአንገት ልብስ አፍነው…ያስጨፍሯቸዋል..ዕድገትና ውድቀትን እንዴት ያውቁታል?
“ትምህርት፣ ጤና ፣ፍትህ፣ የኑሮ መሻሻል፣የመናገር መፃፍ ነፃነት ገና በልመና ሲሆን የምረጡኝ አስገድዶ ማሳመን የተለመደው ተግባርና ‘አውራው ፓርቲ’ አለኝ በሚለው የአምስት ዓመቱ የትዳር(ኮንትራት) ባለፈው ቅንጅትን መንታ ሲያደርግ ዘንድሮ ከምርጫው ጫጉላ ላይ …ሜንጫ ቦንድን ዋስ እድርጎ… መኢአድን እና አንድነት ፓርቲን ጥንድ የማድረጉ ጉዳይ “አውራው ፓርቲ ምንኛ የተዋጣለት አጥቂ ቢሆን ነው!?
** እንግዲህ እናንት በሻቢያህወአት የተፈጠራችሁ በኢህአዴግ ጥላ ሥር ብቻ ለመኖር በመፈቃቀድና በመፈቃቀር ቃል ገብታችኋል! ለእኛ በእኛ ብቻ የምትኖሩ መሆናችሁን አምናችኋል! ትናንት ያልነበራችሁ እኛ ስንፈጥራችሁ ማንነታችሁን አታውቁም ቀድሞ በባዶ እግራችሁ ትሄዱ ነበር አሁን ባቡር አይተው የማያውቁ መሳፈር ጀምረዋል…በጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የህወአት ጉዳይ አስፈፃሚ አቶ ኀይለመለስ ደስአለኝ….”
http://www.youtube.com/watch?v=aU0vyc6X57A