• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር

September 16, 2016 11:58 pm by Editor 2 Comments

የአፍሪካ ነፃነት አብሪ ኮከብና  በጀግና ህዝቧ አኩሪ ተጋድሎ ባለክብር የነበረቺው ኢትዮጵያ ዛሬ  በከፋ ፈተና ውስጥ ገብታለች። በብርቱ ትግልና ጥንቃቄ መወገድ ያለባቸው ያገርና የህዝብ ደህንነት ስጋቶች ከፊቷ ተጋርጠዋል። የርስ በርስ ጦርነት ስጋት፣ የአስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እጦት፣ የማእከላዊ መንግስት አቅጣጫ ብዥታና የውጭ ጠላት ስጋት፣ ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህንና መሰል ያገርና ህዝብ ደህንነት ስጋቶች ለማስወገድና ጤናማ የፖለቲካ ድባብ ለመፍጠር ባስቸኳይ መንቀሳቀስና ሀገርና ህዝብን ካሳፋሪ ውድቀት ማዳን ያስፈልጋል።

በኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ ያንዣበቡትን  እነዚህን  አደጋዎች ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? በእርግጥስ ይቻላል?

እነዚህን ያገርና የህዝብ ህልውና ፈተናዎች በማስወገድ የኢትዮጵያን ሁኔታ ሰላማዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ማድረግ የሚችለውስ ማነው? የሁሉም ጥያቄዎች መልስ አዎንታዊ ነው፤ መሆንም አለበት። ሃላፊነቱም የሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎችና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ነው። በዚህ ፈታኝ የታሪክ ወቅት በየጎራው የተሰለፉት የኢትዮጵያ ልጆች የገዛ ሀገራቸውንና  ህዝቧን የማዳን ታሪካዊ ሃላፊነት መሸከም አለባቸው።

ስራው መጀመር ያለበት መቼ ነው?

ኢትዮጵያ በሰላምና ፀጥታ ፈተና ላይ ወድቃለች፤ ግጭቱም ከሯል፤ በየለቱ የሰው ህይወት እየጠፋ ነው። እናም ችግሩ አጣዳፊ ነው። ጊዜ የሚሰጥ አይደለም። ቀናት በተቆጠሩ ቁጥር አደጋዊ እየሰፋና መልኩን እየለወጠ ችግሩን ለመፍታት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል። ስለሆነም ስራው ዛሬ  ነገ ሳይባል ባስቸኳይ መጀመር አለበት።

ኢትዮጵያና ህዝቧን ካደጋ የማዳን ስራው  እንዴት ሊጀመር ይችላል? ስልትና ብልሃቱስ ምንድነው?

ኢትዮጵያን ከገጠማት የወቅቱን ጭንቅ ለማውጣት መንገዱ አንድ ብቻ ነው። ይሄውም መነጋገር ነው። በየጎራው ያሉት የኢትዮጵያ ልጆች ተሰባስበው መነጋገር አለባቸው። ከዚህ ስብሰባ የሚቀር ወገን ወይም ቡድን ሊኖር አይገባም። በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሃይሎች ሁሉ በዚህ የምክክርና ክርክር መድረክ ላይ መገኘት አለባቸው። የትኛውም ወገን ምንም አይነት የፖለቲካ አቋም ወይም ሃሳብ ይኑረው በዚህ ፋታ በማይሰጥ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይሳተፍ ዘንድ ወቅቱ የግድ ይላል። እናም ጥሪው ያለምንም ልዩነት ለኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ሃይሎች ሁሉ ነው። ኢትዮጵያን ለማዳን መፍትሄው ባስቸኳይ መሰባሰብና መምከር ነው። አማራጭ መንገዶችን በጋራ ለመፈለግና በሚያዋጣው መንገድ ላይ ለመስማማት መነጋገር ያስፈልጋል። ባጠቃላይ ኢትዮጵያን ለማዳን ከመነጋገር የተሻለ መንገድ የለም። የኢትዮጵያ ቀጣይ መንገድ ምንድነው በሚለውም ሆነ አሁን ከገባችበት ማጥ ማውጣት የሚቻለው እንዴት ነው በሚሉት ጥያቅዎች መልስ ላይ ለመስማማት መመካከር ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ነው።

የምክክሩና ክርክሩ ፋይዳ

1. ሳይነጋገሩ ሰላም ማምጣት አይቻልም።

2. ሳይነጋገሩ ችግሩን መፍታት አይቻልም።

3. ሳይነጋገሩ  ወደፊት መራመድ አይቻልም

4. ሳይነጋገሩ፣ ሳይከራከሩና ሳይስማሙ መፍትሄ ማምጣት አይቻልም። ስለሆነም የምክክሩና ክርክሩ መድረክ ከወቅቱ ጭንቅ መውጫ በር የሚከፍት ስለሆነ ወሳኝ መድረክ ነው።

መድረኩን የሚፈጥረው ማነው? ስፍራውስየት ነው?

ይህን ታላቅ ሃላፊነት ለመውሰድ የተዘጋጀው ፥ሰላምና ፍትህ ለአፍሪካ፥ የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ከኢትዮጵያ ህዝብ ወዳጆችና የሰላም ሀይሎች ጋር በመተባበር ነው። ስፍራውም በዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ይሆናል።

“ሰላምና ፍትህ ለአፍሪካ” ማነው?

ሰላምና ፍትህ ለአፍሪካ (peace and Justice for Africa) የአፍሪካ አህጉር የሰላም ምድር እንዲሆንና የህግ የበላይነት የበለፀገ የህዝብ ባህል እንዲሆን ለመታገል በአሜሪካ ህግ መሰረት የተቋቋመ ገለልተኛ ግብረሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ሰላምና ፍትህ ለአፍሪካ እድገት ብቻ ሳይሆን ለህልውናዋም ወሳኝ ቅድመሁኔታዎች ናቸው የሚል እምነት ባላቸው ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያን የተመሰረተ ነፃና ገለልተኛ ድርጅት ነው። ዋና ፅህፈት ቤቱ በዋሽንግተን ዲሲ ሲሆን በየአህጉሩ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶችን ከፍቶ ለመንቀሳቀስ ሰፊ እቅድ ይዟል። የመጀመርያውን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በካናዳ  ከፍቷል። ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የገጠማትን ከባድ የሰላምና ጸጥታ ችግር በመመልከት ለጉዳዩ ቀዳሚ ትኩረት በመስጠት መፍትሄ በማፈላለጉ ሂደት የበኩሉን እገዛ ለማድረግ ሌት ተቀን ያለረፍት እየሰራ ነው። ለጥረቱ ስኬት የኢትዮጵያንና ህዝቧን  ደህንነት የሚሹ አካላትን  ሁሉ ድጋፍ ይሻል።

የታቀደው ውይይትና ክርክር መድረክ  ይዘትና ቅርፅ ምን ይመስላል?

በዚህ ወሳንና ሰፊ መድረክ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሀይሎች ሁሉ እንዲሳተፉ ይጠበቃል። ታዛቢዎችና የልማት አጋሮችም ተሳታፊ ናቸው። የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአሜሪካና የሌሎችም መንግስታት ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የውይይትና ክርክር መድረኩ አላማ ምንድነው?

መድረኩ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ይመክራል።

ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት አጣብቂኝ መውጫው መንገድ ምንድነው? ምን መደረግ አለበት?

ቀጣዩ ጉዞስ ወዴት ነው?

አማራጮች ምንድናቸው?

ከገባንበት አጣብቂኝ እንዴት እንውጣ?

ያለግጭት ገደሉን እንዴት እንሻገር?

የእርስ በእርስ ጦርነት ስጋት ማስወገጃው ስልት ምንድነው?

ሁሉንም የሚያስማማው መንገድ ምንድነው?

ሁሉንም የሚያስማማስ መንገድ አለ?

ኢትዮጵያን ለማዳንንና ጦርነትን ለማስወገድ ከመነጋገር ሌላ ምን መንገድ አለ?

እነዚህ ጥያቄዎች ለመነሻነት የቀረቡ ናቸው። ተሳታፊዎች የራሳቸውን አካሄድና አጀንዳም ሊቀርፁ ይችላሉ። ከላይ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ የሚሰጡት መልሶችም የተለያዩ ናቸው። ሁሉም ወገኖች የሚሰጡት መልስና የሚያቀርጉት ሃሳብ ይለያያል። የመፍትሄ ሃሳቦችም ይለያያሉ። ልዩነቱ ከሃይል ሌላ ለኢትዮጵያ ሰላም ሊያመጣ አይችልም እስከሚል ድረስ ይዘልቃል። የመድረኩ አዘጋጅ ሰላምና ፍትህ ለአፍሪካ በየትኛውም አማራጭ የፖለቲካ መፍትሄ ላይ የራሱ አቋም የለውም። ሆኖም በየትኛውም አማራጭ ስልት ላይ ለመስማማት ከመነጋገር ሌላ መንገድ እንደሌለ በፅኑ ያምናል። ከዚህም ሌላ መቼም ቢሆን ሰላምን በሰላም ለማምጣት እስከተቻለ ድረስ ለሰላማዊ ንግግርና ክርክር ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል የሚለውን ሃሳብ በሙሉ ልብ ይደግፋል። በመጨረሻም ይህ መድረክ የትግል ጥሪ ሳይሆን ኢትዮጵያን ከአደጋ ለማዳን የሁሉም ፖለቲካ ሀይሎች አማራጮች የሚመረመሩበትና የሚሞገቱበት በማጠቃለያውም ተስማሚ ነው የተባለው የሰላም እስትራትጂ ተግባራዊ የሚሆንበት አቅጣጫ የሚነደፍበት መድረክ እንደሚሆን ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል።

ስለዚህ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ የመድረኩን አስፈላጊነት በውል በማጤን ለስኬቱ ከጎናችን እንዲቆሙ፣ ማንኛውንን ትብብርም እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በታቀደው የሰላም መድረክ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ አቋማችሁን ብታሳውቁን ለዝግጅት ይረዳናል። አማራጭ መፍትሄም ሆነ ምክር ወይም አስተያየት ያላችሁ ወገኖች ሁሉ ከዚህ በታች በተገለፀው የድርጅታችን አድራሻ ብትልኩልን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው። ስለመድረኩ ዝግጅትና ይዘትም የተሻለ አማራጭ አለን የምትሉ ሃሳባችሁን ብትልኩልን ለእቅዱ ስኬት ይበጃልና በደስታ እንቀበላለን።

ሰላምና ፍትህ ለአፍሪካ (Peace and Justice for Africa)

840 First Street NE,
Washington DC, 20002
Email: Peaceafrica16@gmail.com
Telephone: Office: 202-380-3600
Fax: 202 2896539
Direct mobile phone: 703-798-1156
Website: www.peaceandjusticeforafrica.org

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    September 23, 2016 11:00 pm at 11:00 pm

    Please say no to the fascists from TIGRAI. We are not short of organizations but we need unity and action to dismantle the home grown fascists.

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    September 25, 2016 03:24 am at 3:24 am

    ጓዶች!! ያልሆነ ህልም አታልሙ!! ቅዠት!!ቅዠት! ሃገሪቱ ደህና ናት!

    Reply

Leave a Reply to Mulugeta Andargie Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule