• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግን በጓሮ ድርድር የጠየቀበት ሰነድ ተተረጎመ!

April 18, 2013 06:41 am by Editor 3 Comments

በልማትና ኢንቨስትመንት ስም ኢህአዴግ ለውጪና ለራሱ ሰዎች እየቸበቸበ ያለውን መሬት አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ አማርኛ ትርጉም በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ ይደረጋል ተባለ። የመሬት ነጠቃ ዜጎችን እያፈናቀለና ውድ የተፈጥሮ ሃብትን እየበላ ነው።

እመራቸዋለሁ ለሚለው ህዝብና አገር ደንታ የሌለው ኢህአዴግ፣ በመረጃ ለሚያጭበረብራቸው ዜጎች የተሟላና የተመጣጠነ ዘገባ እንደሚያቀርብ የተነገረለት ይህ ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ይፋ እንደሚሆን የገለጸው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዴስክ ነው።

የጋራ ንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ዴስክ በተለይ ለጎልጉል በሰጠው መረጃ በጥናቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት የተገኙ መረጃዎች፣ መንግስት ራሱ ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎችና ለጥናቱ አስፈላጊ የተባሉ አኻዞች ተካተውበታል።

በዚሁ መሰረት ኢህአዴግ በልማትና በኢንቨስትመንት ስም “ጥቅም ላይ ያልዋለ መሬት” በማለት ለንግድ ማቅረቡና፣ ይህም በመደረጉ አገሪቱ ውስጥ ልማት እንደሚስፋፋ የሚሰብከው ስብከት ያለ አንዳች ማስተባበያ እርቃኑን የሚያስቀረው ሪፖርት በዋናነት የተዘጋጀው መረጃ ለጠማው ህዝብ እንደሆነ ዴስኩ አስታውቋል።

አገራቸውን፣ መሬታቸውንና መንግስትን አምነው የሚኖሩ ዜጎችን በገንዘብ በመለወጥ ያፈናቀለውና እያፈናቀለ ያለው ኢህአዴግ፣ ምትክ የሌላቸውን እድሜ ጠገብ የተፈጥሮ ደኖች ጨፍጭፏል፤ አቃጥሏል፤ አውድሟል። ሰፊ መሬት ምድረ በዳ አድርጓል። ያለ አንዳች ምክርና ውይይት ዜጎችን አፈናቅሎ ለመከራ ዳርጓል። ንብረታቸውንና ማሳቸውን እንደ ባዕድ በዶዘር ጠርጎባቸዋል። ለመቃወም በሞከሩ ወገኖች ላይ የባዕድ ወራሪ ሃይል ይፈጽመዋል ተብሎ የማይገመት ወንጀልና መከራ አድርሷል። የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ እንዳለው ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ሲፈጽም ጎን ለጎን ዜጎችን በመረጃ እያጭበረበረና እያስራበ በመሆኑ አሁን ይፋ የሚደረገው ሪፖርት ታላቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

ለጋሽ ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብና አበዳሪ ድርጅቶች አቋማቸውን እንዲመረምሩ ለማስቻል ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ያወሳው የጋራ ንቅናቄው “የመሬት ወረራው መቆሚያ የሌለው፣ እንዲያውም በቀጣይነት የሚከናወን በመሆኑ ይፋ የሚደረገው ይህ መረጃ አገር ቤት ገጠር ሳይቀር ዘልቆ እንዲገባ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል” በማለት አስረድቷል። ይሁን እንጂ መረጃው እንዴት እንደሚሰራጭ ዝርዝር ማብራሪያ አላቀረበም።

ወደፊት ጥናትና ምርምር የሚያካሂዱ ተቋማትም ሆነ ግለሰቦች ሊጠቀሙበት እንዲችሉ ተደርጎ በዝርዝር የቀረበው ይህ ሪፖርት፣ በእንግሊዝኛው ጥቅል ጥናት ውስጥ በሰባት የአፍሪካ አገራት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ሲሆን ወደ አማርኛ በተቀየረው ትርጉም ውስጥ ሙሉ ትኩረት የተደረገው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንደሆነ ተመልክቷል።

congress briefings
አቶ ኦባንግ በም/ቤቱ ውይይት ወቅት ማብራሪያ ሲሰጡ

“በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በሦስት ዓቢይ ምዕራፎችና በበርካታ ንዑሳን ክፍሎች ተከፋፍሎ የተዘጋጀው ከ110 ገጽ በላይ የሆነው የአማርኛው ጥናታዊ ሪፖርት “የሰከነው” ትግል ውጤት እንደሆነ የመረጃ ዴስኩ አስታውቋል። በቅርቡ የጋራ ንቅናቄው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ህንድ በመሄድ ያነሳሱት የትግል አብሮነት ስሜት ያነሳሳ ነበር፡፡ ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ ሰኞ ዕለት በአሜሪካው ምክርቤት ለውይይት በመሬት ነጠቃ ጉዳይ ላይ የቀረበውና ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠውን ይህንኑ የመሬት ነጠቃ ጉዳይ በምክርቤት ተገኝተው ገለጻ ከሰጡት መካከል አቶ ኦባንግ አንዱና ዋንኛው መሆናቸውን የሚዲያ ክፍሉ ጨምሮ አስታውቋል፡፡ ይህም ለመሆን የቻለውና ጉዳዩ በከፍተኛ ደረጃ ተደማጭነት እያገኘ የመምጣቱ ሁኔታ ከፍተኛ ድል እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ኢህአዴግ የሚተማመንባቸውንና ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ የሆኑ አገራትንና ተቋማት እጅ የማስጠምዘዝ ሁኔታ ሊያስከትልበት እንደሚችል በመገንዘብ ካድሬዎቹን በየቦታው በማሰማራት ከፍተኛ የውስወሳ ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ በዚህ ረገድ የጋራ ንቅናቄው እጅግ ከፍተኛ ሥራ ላይ የተጠመደ መሆኑን ጨምሮ ተገልጾዋል፡፡

የጋራ ንቅናቄው አክሎ በሰጠው ማሳሰቢያ አደራም አስተላልፏል። በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ የሚደረገው ይህ ጥናታዊ ሪፖርት ምንም እንኳ የጋራ ንቅናቄው ንብረትና የኮፒ ራይት ያለው ቢሆንም “ሪፖርቱን ለማራባትና ለማሰራጨት የሚፈልጉ ሁሉ ለሪፖርቱ ባለቤትና አዘጋጆች ጨዋነት የተሞላው እውቅና ሊሰጡ ይገባል” ሲል ጥሪውን አቅርቧል። በማያያዝም በሚቻላቸው መንገድ ሁሉ ሪፖርቱን ለማራባት ለሚተባበሩ ወገኖች ከወዲሁ ምስጋናውን አቅርቧል። ሪፖርቱ እንዲደርሳቸው ለሚፈልጉ ሁሉ በኢሜል ለመላክ ፈቃደኛ በመሆኑ በሚከተለው አድራሻ media@solidaritymovement.org ጥያቄ ቢያቀርቡ እንደሚተባበር አመልክቷል። የመሬት ነጠቃን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚያካሂደውን እቅድን መሰረት ያደረገ ትግል አጠንክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Teshale says

    April 19, 2013 04:37 pm at 4:37 pm

    Wonderful job. This is the kind of job that those opposing the government should do. This proactive action will put TPLF government on the defensive. For the most part, those opposing the TPLF government are reacting when it does something. We need to keep TPLF busy defending itself and have no time to brew yet another disaster in Ethiopia and its people. What SMNE is doing on the land issue is clearly a proactive job that is a step ahead of TPLF and forcing it to react than act. Thank you SMNE.

    Reply
  2. gelam says

    April 20, 2013 01:54 am at 1:54 am

    If people want to talk, they always have some thing to say regardless of the rationality of their topic. When the country was in drought and famine, they used to say ‘Green drought’ to mean that the country is poor while having fertile land. And now, when the country started to utilize its resources, they made a U-turn and they are telling us to stop farming our fertile land. for an average Ethiopian, it is not hard to imagine what some outsider groups/individuals/or countries would benefit if the country remains always poor. But for the opposition diaspora and the like, shame on you! study history and politics before you open your mouth.

    – “for the betterment of the country, the feudal system must be removed” …. Derge
    -“for the betterment of the country, the military dictator must be removed”…..Woyane
    -“for the betterment of the country, Woyane must be removed”…..opposition Diaspora.
    -“for the betterment of the ……….”

    When do you think this cycle will have an end?
    In my opinion, it will never end unless we are aware of our outside enemies. Ethiopia’s enemy’s are always enemies. They do not care about the governments. They help a certain group to come to power and the time that group becomes stronger, they train another group in order destroy the former one. In this situation, the countries always remains between RAISE and FALL states.Political game. I think the opposition diaspora are playing a political game without knowing the rules of the game. The rules of the game are in the hand of other masters (the outsiders).

    Reply
  3. andnet berhane says

    May 16, 2013 04:46 pm at 4:46 pm

    አንድን ሕዝብ አንድን ሃገር በመወከል ተጨባችና ተአማኒነት ያለው ተግባርና የትግል ርብርቦሽ በማድረግ ጉዳዩን ለዓለም ሕብረተሰብ በይፋ ወያኔን ማጋለጥ ለደረጉት ታአልቅ አስተዋጽኦ አቶ አቦንጋ ሜቶን እንዲሁም አኢጋን አባላትንና ድርጅጀት እንዲሁም የኦክላንድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ዳይረክተርና የትምሕርቱን ተቋም ታላቅ ምስጋና ይድረሳቸው ።
    የመሬት ነጠቃው ስውርና የሃገርና የሓዝቦችን ኑሮና መሰረት ያናጋ የዘመናችን ፋሽሽታዊ ስራአት ለመሆኑ ለዚህም ተወቃሾች ያለጥናትና በጥቅምና በፖሊሲ መዛባት የሚሰሩትን የምእራብ ሃገራት አመራሮች ጭምር የሚያስወቅስና እሚያስጠይቅ ፡ ከመሆኑ ባሻገር ለወደፊቱ ከዓለም ሕብረተሰብ ተአማኒነት የሚያሳጣ ስራ በመስራት የዓለምን ሰላምና ከመረጋጋት እንደሚያደፈርስ ያለመመልከት በጥቂት እበላ ባዮች ዘራፊ ሃብታሞች ዓለምን ወደከፋ የጦርነት አውድማ የሚያደርስ ደርጊት ካሁኑ ካልቆመ አሳሳቢነቱ ካለንበት ዘመን የከፋ ለመሆኑ ማውወቅ ያስፈልጋል፡ በኢትዮጵያ ያለው የማፈናቀልና የመሬት ዝርፊያ እንዲሁም በሌላው አፍሪካ ሃገራት የተረጋጋ ሰላምና እድገት እንደማያመጣ እየተወቀ በህዝቦችና በሃገሮች የተሰነዘረ የጥፋት ሽብር ለመሆኑ ሁሉም ያገባኛል የሚል በጥብቅ ማውገዝና በዚህ የትግል ሰልፍ ያቅሙን ማበርከት ሃገራዊ ኃላፊነት አለበት፡
    መረት የአንድ ዜጋ መታወቅያው መግላጫው ነው ፡ መንግስት የህዝቦችን ጥቅም ለማስጠበቅ በምርጫና በተሰተው ሃገራዊ መተዳደርያ ሕግ ከሌላው ዓለም ግንኙነት ባማድረግ በመደራደር ለሃገር ጠቃሚና የሕዝብን ኑሮና የእውቀት እጤናና የእርሻን የመገናኛን በመዘርጋት የተሰጠውን አደራ በተግባር ተርጉሞ ኃላፊነቱን መወጣት እንጂ፡ እንድ ኢኅዴግ ሃገርና ሕዝብን መሸጥና መዝረፍ አስነዋሪና ሕገወጥ ስራ በድፍረት መሬት የመንግስት የሚለው ዓለም አቀፍ ወንጀልና (በጅምላ ጭፍጨፍ )ለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ጠንቅቆ ማወቅና ይህንን ተግባር ሩቅ ሳይሄድ ለማምከን ጽናታዊ ሞራላዊ አይምራዊ የሆነ ትግል አማራጭ የሌለው በመሆኑ ሁሉም ይተባበር ፡

    Reply

Leave a Reply to gelam Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule