• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?

April 29, 2014 08:10 am by Editor 3 Comments

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉዞ በርካታ ጉዳዮች የሚከናወኑበት እንደሆነ ተጠቆመ። የዘወትር የጎልጉል ምንጭ አንዳሉት የኬሪ አዲስ አበባ ጉዞ አስቀድመው የተሰሩ ስራዎች ውጤት ነው። ጥቁሩ ሰው “ውሻ ምንም ሳይመለከት አይጮህም” ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ብቃት ያላቸው አማራጮች መሆናቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ኢህአዴግ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እንደለመደው “ከሶማሊያ ጦሬን አወጣለሁ” በማለት መደራደሪያ ከማቅረብ ውጪ ሌላ አቅም እንደሌለው ተገለጸ። ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች “አገር በማተራመስ” ወንጀል ክስ መሰረተባቸው።

የድረገጽና የማህበራዊ ገጽ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚ አባላት ባይዋጥላቸውም አሜሪካና ኢህአዴግ የነበራቸው ግንኙነት እየሻከረ መሔዱን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የዋሽንግቶን ዲፕሎማት ምንጩን በመጥቀስ እንደዘገበው አሜሪካ ኢህአዴግን “የምስራቅ አፍሪካ ስጋት” አድርጋም ፈርጃለች። የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተለውና በስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ የተቋቋመው የቀውስ መከላከልና ዕርቅ ቢሮ ሃላፊ ከጥር ወር ወዲህ ባሉት ጥቂት ወራት ውስጥ አራት ጊዜ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።

ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ፍትሃዊነት የጎደለው አገዛዝ ኢትዮጵያን ወደ ቀውስ እንዳመራትና ይኸው ቀውስ እልባት ካልተበጀለት የምስራቅ አፍሪካን የሚያዳርስ እንደሚሆን በአሜሪካ በኩል አቋም መያዙ ኢህአዴግን እንዳስበረገገው ተንታኞች እየገለጹ ነው። የምስራቅ አፍሪካ “የሰላም አባት ነኝ የሚለው ኢህአዴግ በውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ ስለሚገኝ የመወላለቅ ችግር ሳይገጠመው በፊት አሜሪካ አስቀድማ ስራዋን መስራት መጀመሯ ከራሷ ጥቅም አንጻር ነው” ሲሉ ዲፕሎማቱ እንደቀድሞው ሁሉ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። የኬሪ ጉዞም የዚሁ አካል እንደሆነ አስታውዋል። “ኢህአዴግ” አሉ ዲፕሎማቱ “የቀለም አብዮት እያለ እንደሚደነፋው ሳይሆን በመጪው ምርጫ በሩን ከፍቶ ለመወዳደር ከተስማማ ብቻ የለመደው ርጥባን ይሰጠዋል የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።

በ97 ምርጫ ወቅት እንዳደረገው በሶማሊያ ያለውን አለመረጋጋት እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም ጦሩን የማስወጣት ርምጃ ቢወስድስ? በሚል ለተጠየቁት “ኢህአዴግ የመጫወቻ ካርዶቹ ያለቁበት ይመስለኛል” በማለት የግሌ ያሉትን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በምርጫ 97 ተደራደር ሲባል ጦሩን ሰብስቦ ለመውጣት በዝግጅት ላይ እንደሆነ መግለጹን የተለያዩ የውጪ አገር ሚዲያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም።

obang-o-metho-hearingየአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ “ውሻ ከጮኸ የሆነ ነገር አለ ማለት ነው” ሲሉ ለጎልጉል አስተያየት ሰጥተዋል። ኦባንግ አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህንን ጩኸት ሰምተው ህዝብን በማስቀደም ራሳቸውን አማራጭ አድርገው እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል። አማራጭ የለም የሚለውን ፍርሃቻ በመስበር ወቅቱን ለህዝብና ለአገር ጥቅም ለማዋል እንዲተጉ አሳስበዋል። የሚመሩት ድርጅት በቅርቡ በዚህ ዙሪያ የሚለው ነገር ስላለ ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ ከመግባት ተቆጥበዋል።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በመጥቀስ የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው ኬሪ፤ ሃይለማርያም ደሳለኝን፣ ቴድሮስ አድሃኖምንና የሚመለከታቸውን ባለስልጣናት በሰብአዊ መብት አያያዝና በዲሞክራሲ ትግበራ ዙሪያ እንደሚያነጋግሩ ማረጋገጫ መሰጠቱን ጠቁሟል። በዚሁ ዜና ላይ ቃላቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ኬሪ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጋር ይነጋገራሉ የሚል ስጋት እንዳለባቸው የሚያሳብቅ መልስ ሰጥተዋል። ኬሪ የዞን9 ድረገጽና ማህበራዊ ድር ጦማሪዎች እስርን አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ጆን ኬሪ ስለ ዞን9 አባላት እስር ሊያነሱ እንደሚችሉ ተጠይቀው “እንደምናከብረው መሪ ጥያቄውን ካቀረቡ አስፈላጊውን መልስ እንሰጣለን” ካሉ በኋላ “የዞን9 ጦማሪዎች በጋዜጠኛነታቸው አልታሰሩም” በማለት ከገጀራና ከስርቆት ወንጀል ጋር በማዛመድ ለማቃለል ሞክረዋል።

getachew
ጌታቸው ረዳ

አገዛዙ ዝም ማለቱን አስመልክቶ “የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረገ ሴል ቢኖር መግለጫ እናወጣለን” ሲሉ የመለሱት አቶ ጌታቸው፣ ጆን ኬሪ የእስረኞቹን ጉዳይ እንዲያነሱ ያሳሰበውን ሂውማን ራይትስ ዎችን “ልማዱ ነው” ሲሉ ዘልፈዋል።

የዞን9 አባላትን ታፍኖ መወሰድና በአገር ማተራመስ ወንጀል መከሰሳቸውን የሰሙ “ኢህአዴግ ማንንም ለአገር ተቆርቋሪ ሆኖ የመወንጀል ሞራላዊ ብቃት የለውም” በማለት ነው አስተያየታቸውን የሚጀምሩት። ኢህአዴግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አሁን አስከደረሰበት ደረጃ ድረስ ዜጎችን በአገር ክህደት የመፈረጅ ብቃት ከቶውንም እንደሌለው ራሱም ጭምር የሚያወቀው እውነት እንደሆነ የደረሱን አስተያየቶች ያመላክታሉ።

ያለፈው እሁድ አራዳ ምድብ አንደኛ ችሎት የቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማሪዎች በሶስት የተለያዩ መዝገቦች መከሰሳቸው የጀርመን ሬዲዮ ይፋ አድርጓል። ከታሰሩ በኋላ ከቤተሰብና ከተመልካች ተሰውረው ምርመራ ሲደረግባቸው የነበሩት የዞን9 ጦማሪዎች አስመልከቶ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የራሳቸው በሆነው የዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ክስ ከመመስረቱ በፊት ስለተከሰሱበት ጉዳይ የፖሊስ ምንጭ ጠቅሰው መናገራቸውን ቪኦኤ ተናግሯል።

ወ/ሮ ሚሚን ጠቅሶ የዞን9 ጦማሪዎች አርቲክል 19 ከሚባለው ተቋም ጋር ግንኙነት ያላቸውና የተለያዩ አገራት ሄደው የሰለጠኑ መሆናቸውን፣ በአገሪቱ ትርምስ ለመፍጠር በሻዕቢያና በግብጽ በገንዘብ እንደሚረዱ ቪኦኤ በዘገበ ማግስት ነው ፖሊስ በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የተጨማሪ ቀጠሮ ቀን የጠየቀባቸው። የዞን 9 ጦማሪዎች ኢህአዴግ ላይ ጠንካራ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ ናቸው።

“አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ በበነጋው ደግሞ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስም በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ታሳሪዎቹን ለመያዝ የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን መስማታቸውን በዚሁ አጭር መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

zone9“ዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 15፣2006 ባወጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ” በማለት በራሳቸው የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ዜና አሰራጭተው ነበር።

በተመሳሳይ ዜና ቻይናን “ቃል የገባሽውን ብር አምጪ” ብሎ የሙጥኝ የያዘው ኢህአዴግ “ቀለም ይፈራል” ሲሉም በቅርብ የሚከታተሉ እየተቹት ነው። “ሆድ በባሰው ቁጥር የቀለም አብዮት ” በማለት ቅስቀሳ የሚያዘወትረው ኢህአዴግ አሁን ያስፈራው የትኛው ቀለም እንደሆነ በይፋ ባይገልጽም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትን ኢንጂነር ይልቃል “ተስፋ የተጣለባቸው ወጣት መሪዎች” በሚል ተመርጠው ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አሜሪካ ለስልጠናና ለልምድ ልውውጥ መጋበዛቸው፣ ወደ ስፍራው እንዳያመሩ መደረጉ፣ እንዲሁም አሁን በድፍረት የሚንቀሳቀሱና የሚያስተባብሩ መሆናቸው አንዱ የስጋት ምንጭ ሊሆን አንደሚችል ግምት አለ።

“የቀለም አብዮት ሰለባዎች” በሚል ርዕስ ኢህአዴግ ዩክሬንን አስታኮ ያሰራጨው ቪዲዮ አሜሪካንን በሽብር ስራ የማሰልጠን ክህሎት ያላት፣ ሽብርተኞች አገርን አንዲያተራምሱ በመደገፍ የሚታወቁ ተቋማት ባለቤት የሆነች አገር ብሎ መፈረጁ አይዘነጋም። ኢህአዴግ ተንታኝ አድርጎ ያቀረባቸው ጎረምሶች አሜሪካንና የምዕራብ አገሮችን ሲዘልፉ የሚያሳየው ፊልም መጨረሻው “ከፊል የዩክሬን ህዝብ ራስን በራስ በመወሰን መብቱ ተጠቅሞ የቀድሞ አካሉን ሩሲያን ተቀላቀለ” በሚል መሆኑና ጉዳዩ ከአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ተዛምዶ መቋጨቱ የኢህአዴግን በተለይም የህወሃትን ስጋት እንደሚያጎላው የሚያሳይ እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠበት ነው። በሕገመንግሥቱ አገር እንድትበታተን በአንቀጽ 39 በግልጽ አስቀምጦ እስካሁን ኢትዮጵያን በ“ነጻ አውጪ ግምባር” ስም የሚመራውና “የነጻ አውጪ ግምባሩን” መሪ ወደ ተባበሩት መንግሥታት በመላክ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል ዓለምን የለመነው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “የቀለም አብዮት ሰለባዎች” በማለት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ከሶቪየት ህብረት የተገነጠለችውና የዩክሬን አካል የነበረችው ክሬሚያ ወደ እናት አገሯ ሩሲያ መመለሷን አብሮ ማሰራጨቱ ዘጋቢ ፊልሙን ዋጋቢስ የሚያደርገው መሆኑን አለማስተዋሉ በራሱ ሌላ ዘጋቢ ፊልም የሚያሰራ ነው፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. jonny says

    May 18, 2014 08:35 am at 8:35 am

    it is finishing time for this dictatorship party!!we all need new party leader!we pray god split this [OPDO]party?

    Reply
  2. EZEDIN MIFTAH says

    May 18, 2014 08:40 pm at 8:40 pm

    THIS SHOWS US SOMETHING WHICH MEANS NEXT YEAR AMERICA WILL MAKE BLUE REVOLUTION AND TIGRAY WILL JOIN ERITREA LIKE CRIMEA

    Reply
  3. Mahlet says

    May 21, 2014 09:13 pm at 9:13 pm

    Hello Golgul, I am forwarding a link Teshome sent me this morning. Thanks.
    http://erecycler.wordpress.com/2014/05/21/bloggers-of-the-world-unite

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule