• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!

September 1, 2017 06:38 pm by Editor 3 Comments

  • “ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተለቀቁ ፍትሕ ይበየናል”
  • “ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ውሳኔውን በመቀበል ለአገራቸው አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል” ኦባንግ ሜቶ
  • “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ራይላ ኦዲንጋ

በኬኒያ በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በርካታ ችግሮች የገጠሙትና በአገሪቱ ሕግጋት መሠረት ያልተካሄደ ነው ሲል የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ከመጀመሩ በፊት የኬኒያን ፖለቲካ በቅርቡ የሚከታተሉት ኦባንግ ሜቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማድነቅ “ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተደረጉ በምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን አፍሪካም የሕግ የበላነይትና ፍትህ ይሰፍናል፤ ሁለቱም ተወዳዳሪዎች፤ ራይላ ኦዲንጋ ከአመጽ ይልቅ በሥርዓት ጥቄያቸውን ለፍትሕ አካል በማቅረባቸው፤ ኡሁሩ ኬኛታ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ እገዛለሁን ማለታቸው የሚደነቁ ናቸው፤ ለአገራቸውም አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል” ብለዋል፡፡ ተቀናቃኙ ተወዳዳሪ ራላ ኦዲንጋ ውጤቱን አስመልክተው “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ብለዋል፡፡

ዜናውን አስመልክቶ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያጠናቀረው ዘገባ እንዲህ ይነበባል፤

ነሐሴ 2 / 2009 ዓ.ም. በተካሄደው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ማሸነፋቸው በምርጫ ኮሚሽኑ ቢታወጅም የተመራጩ ፕሬዚዳንት ተቀናቃኝ የሆኑት ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ ውጤቱን እንደማይቀበሉ በማሳወቅ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገብተው ነበር።

የዛሬውን የፍርድ ቤቱን ውሣኔ ያስተላለፉት ዳኛ ዴቪድ ማራጋ የሃገሪቱ የምርጫ ቦርድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ህገመንግሥቱና የሃገሪቱ የምርጫ ሕግ በሚያዝዙት መሠረት ባለማካሄዱ ውጤቱ ውድቅ መደረጉን አስታውቋል።

“ነኀሴ 2/2009 ዓ.ም. የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፤

“አንደኛ፤ የሀገሪቱ ህገመንግሥትና ሌሎች የሀገሪቱ የምርጫ ህጎች በሚያዝዙት መንገድ ባለመካሄዱ የምርጫ ውጤቱ ተሽሯል።

“ሁለተኛ፤ የምርጫው ውጤት በዚህ አዋጅ በመሻሩ “ተመራጭ ፕሬዚዳንት” ተብሎ የታወጀው በይፋ እንዲነሳ ተወስኗል።

“ሦስተኛ፤ የሀገሪቱ ህገመንግሥት አንቀፅ 143 ና የሀገሪቱ ምርጫ ህግ በሚያዝዙት መሠረት የመጀመሪያው ተከሳሽ በ60 ቀናት ውስጥ አዲስ ምርጫ በጥንቃቄና ሂደቱ ሊረጋገጥ በሚቻልበት መንገድ እንዲያካሂድ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል።

“የምርጫውን ማካሄጃ ወጭ በተመለከተ እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ የራሱን ወጭ የሚሸፍንበትን መንገድ ይፈልግ” ብለዋል ዳኛው።

ዳኛው ማራጋ አክለው ስለዛሬው ውሣኔ የኬንያ ህግ በሚያዝዘው መሠረት ሙሉ መረጃ በ21 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ነኀሴ 2 ተካሂዶ የነበረው የኬንያ ምርጫ በተለይ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ድምፅ ቆጠራና ውጤቱንም ይፋ የማድረጉ አሠራርና ሂደት ተቃውሞ ገጥሞት የነበረ ሲሆን የኡሁሩ ኬንያታ ተቀናቃኝ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ የፕሬዚዳንታዊው ምርጫ ውጤት እየተገለፀ በነበረ ጊዜ በሃገሪቱ ዋና የምርጫ ማዕከል እየተላለፉ የነበሩት ውጤቶች ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ካሉት ውጤቶች ጋር እየተስተያዩ አልነበረም ሲሉ ቅሬታ አሰምተው ነበር።

ሚስተር ኦዲንጋ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ዛሬ ውሣኔውን ከሰጠ በኋላ ባደረጉት ንግግር “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ብለዋል።

“ዛሬ በአፍሪካ ዴሞክራሲ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ፍትሃዊ ያልነበረን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እንዲሻር ወስኗል። ይህ ውሣኔ በጣም ታሪካዊ ነው። ይህንን ፍትሃዊ ብያኔ ለኬንያ ህዝብ የሠጡትን ዳኞች በጣም ላመሰግን እወዳለሁ። የህግ ጠበቆቻችንንና መረጃ በመሰብሰብ የተባበሩትን የኬንያ ወጣቶችንም በዚህ አጋጣሚ በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። እኛ በምርጫ ቦርዱ ላይ አሁን ባለበት አቋሙ ምንም እምነት የለንም። እንዲያውም ብዙዎቹ ከፍተኛ ወንጀል ስለፈፅሙ በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን። ስለዚህ እነዚህ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ህግ ፊት ቀርበው በኬንያ ህዝብ ላይ ለፈፀሙት አስፀያፊ ተግባር እንዲከሰሱ እንጠይቃለን” ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ ኡሁሩ ኬንያታ የዛሬውን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ውሣኔውን በግል ቢቃወሙም ለመቀበል ግን ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኡሁሩ ኬንያታ

“ዛሬ በተሰጠው ውሳኔ በግሌ አልስማማም፤ ግን አከብረዋለሁ። ፍርድ ቤት የራሱን ውሣኔ አሳልፏል፤ ማክበር አለብን። በተጨማሪም ኬንያዊያን አሁንም ደግሜ በሰላም እንድትነጋገሩ እጠይቃችኋለሁ። እናንተ ዘንድ አንዳች ጥፋት የለም። ስለዚህ ጎረቤቶቻችሁ ሁሌም ጎረቤቶቻችሁ ናቸው። ሁሌም የሚያስፈልጓችሁ ሰዎች ቢኖሩ እነርሱ ናቸው። እኔና የኔ ምክትል ወደ ህዝብ ተመልሰን ለመወዳደር ዝግጁ ነን” ብለዋል። (የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)

የኬኒያን ፖለቲካ በቅርብ የሚያውቁትና በተለይ ምርጫውን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጎልጉል ጋር ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መርካታቸውን ገልጸዋል፡፡ “ምዕራባውያን ለኦዲንጋ ውጤቱን እንዲቀበል ሲገፋፉት ነበር፤ ለአፍሪካ ምርጫ ይህ በቂ ነው፤ ወደፊት በሒደት ይስተካከላል፤ ሽንፈትህን ተቀበል፤ ህዝቡን ለዓመጽ አታነሳሳ፤ … ሲሉት ነበር፤ ሆኖም ኦዲንጋ በሰላማዊ መንገድ ለፍትህ አካላት ጉዳዩን አቅርቦ ውሳኔውን ለመቀበል በመወሰኑ በጣም አደንቀዋለሁ” ብለዋል፡፡

“ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተጽዕኖ ነጻ ሆነው በነጻነት እንዲሠሩ ከተደረጉ ፍትህ መስፈኑ፤ የሕግ የበላይነት በአፍሪካም እንኳን ቢሆን መረጋገጡ የማይቀር ነው” ያሉት “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ “ፍትሕ በምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም መተግበር ይችላል፤ እንዲያውም ምዕራባውያን ከአፍሪካ ላይ ዓይናቸውን ቢያነሱ ለራሳቸው የሚሆን ትምህርት ከአፍሪካ ሊያገኙ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘው የዛሬ 17ዓመት አካባቢ በአሜሪካ በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አል ጎር ማሸነፋቸው እየታወቀ ጠቅላይ ፍርድቤቱ አሸናፊነቱን ለጆርጅ ቡሽ አሳልፎ መስጠቱ አስታውሰዋል፡፡

ራይላ ኦዲንጋ

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የተባሉት አሜሪካዊውውን ጆን ኬሪን ጨምሮ ሌሎችም በጣም ሰላማዊና ፍትሐዊ ምርጫ ያሉትን የኬኒያውን የምርጫ ሒደት የራሷ አገር ፍርድቤት “በምርጫ ሕግ መሠረት ያልተከናወነ” በማለት ውድቅ ማድረጉ ዓለምአቀፍ ታዛቢ እየተባሉ ምርጫ የሚከታተሉትን ታላቅ ትዝብት ውስጥ ከትቷቸዋል፡፡

በዓለማችን የተለያዩ አገራት ማለትም በኦስትሪያ፣ በማልዲቭ፣ በዩክሬይንና በሌሎች አገራት በፍርድቤት ምርጫ ውድቅ ተደርጎ የሚውቅ ቢሆንም በአፍሪካ በዚህ መልኩ የምርጫ ውጤት ውድቅ በማድረግ የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠች አገር በመሆን ኬኒያ ቀዳሚነቱን ወስዳለች፡፡ ይህ የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንደ ሰሜን ኮሪያ ኮሙኒስት ፓርቲ የራሱን የምርጫ ቦርድ አቋቁሞ፣ ራሱ ለብቻው ተወዳድሮ፣ እንደ ሚኒስትሪ ውጤት መቶ በመቶ አሸንፌአለሁ ለሚለው ህወሓት/ኢህአዴግ ቅስም ሰባሪ፤ አንገት አስደፊ ውሳኔ ነው ተብሏል፡፡ (ፎቶ @Public Domain)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Ali says

    September 2, 2017 06:50 am at 6:50 am

    Disgrace & shame for the so called international (UN?) observers. Kenyans made African history.

    Reply
  2. Aytalnew Newzendro says

    September 2, 2017 02:23 pm at 2:23 pm

    Donot expect that the fascists from Tigray will learn from Kenya. No fascist in world history transferred power freely and willingly. Neither Hitler nor Mussoloni transferred power freely and willingly. Unite and dismantle these home grown fascists who are tainted with millions of Ethiopian blood whom they killed in the name of liberation.

    Reply
  3. Alem says

    September 2, 2017 09:52 pm at 9:52 pm

    The court ruling is perhaps meant to quell disturbances; that is all. Uhuru Kenyatta is still going to be pronounced the winner. To use the laws for lawless ends is a common practice everywhere. The US and UK are in favor. The US and UK are also in favor of Tplf.

    Reply

Leave a Reply to Aytalnew Newzendro Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule