• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ

January 22, 2020 12:19 am by Editor 1 Comment

ለቀረበለት ሕጋዊ ደብዳቤ ዛቻን አስቀድሟል

ከለውጡ በኋላ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የመጠጋጋት ህልምና ውጥን እንደሌለው ሲወተውት የነበረው ጃዋር በቅርቡ ኦፌኮን መቀላቀሉን ተከትሎ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ሊልክለት በዝግጅት ላይ መሆኑ ትላንት በመረጃ ገልጸን ነበር። ዛሬ (ማክሰኞ) የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳመለከተው ጃዋር የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ እጁ ገብቷል፤ ፈርሞ ተቀብሏል። ደብዳቤው እንዳይዘጋጅ ያደረገው ሩጫ ሳይሳካ በመቅረቱ ዛቻ እየሰነዘረ መሆኑም ታውቋል።

በተደጋጋሚ የሕግ የበላይነትን በማንሳት ዲስኩርና ማብራሪያ የሚሰጠው ጃዋር፣ ምርጫ ቦርድ በጻፈለት ደብዳቤ መቆጣቱና ወይዘሪት ብርቱካን ላነሱት የሕግ ጥያቄ መልስ ከመመለስ ይልቅ ዛቻን መመረጡን የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ይፋ አድርገዋል።

በሚያስተዳድራቸው ሠራተኞቹና አበል በሚከፍላቸው ጭፍሮቹ ዘንድ የተለያዩ የማዕረግ ስሞች ባለቤት የሆነው ጃዋር፤ ከግራኝ አሕመድ ቀጥሎ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ልዩ ክስተትና ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆኑንን ደጋግሞ ይገልጻል። ከዚህም በተጨማሪ የሚያሳድማቸውና ለሚፈልገው ዓላማ በቅጽበት የሚያሰማራቸው፣ “ደማቸውን እኔ አወራርዳለሁ” ሲል የሚማግዳቸው የጎዳና ላይ ነውጥ ፈጣሪዎች ስላሉት ራሱን መንግሥት አድርጓል። ፈላስፋ ነኝ ባይልም አዋቂ መሆኑንን በተደጋጋሚ ይናገራል፤ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ ሲልም ተደምጧል። ከዚህ ስሜቱ በመነሳት “እንዴት ደብዳቤ ይጻፍልኛል?” በሚል ለሕግ ተገዢ እንደማይሆን የጎልጉል ዘጋቢ መረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሕግን በማስከበር ረገድ በተግባር ተፈትነው ያለፉት ወይዘሪት ብርቱካን ለጃዋር ዛቻና ምልጃ ጆሮ ሳይሰጡ የአሜሪካ ዜግነት ይዞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መፈትፈት እንደማይችል ጠቅሰው፤ ቀነ ገደብ አስቀምጠው፤ ጥርት ያለ ምላሹን ሕጋዊ ሰነዶችን በማያይዝ በሕጋዊ ወኪሉ ወይም ራሱ በአካል ተገኝቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ ካካበቱት የሕግ ዕውቀታቸው በተጨማሪም አሜሪካ በቆዩበት ወቅት የአሜሪካንን የሕግ አሠራር በቅርብ አውቀው በመምጣታቸው ወ/ሪት ብርቱካን ሊቀርቡ የሚገባቸውን ሰነዶች አስቀድመው የሚውቁ መሆናቸው ይታወቃል።  

በለውጡ ማግስት ሜኔሶታ ጠቅላይ ግዛት ጣምራ ዜግነትን የሚከለክለው የኢትዮጵያ ሕግ እንዲቀየር ሲወተውት የነበረው ጃዋር፣ የአሜሪካ ዜግነቱን ለመመለስ የሚያስችለውን ሂደት ማከናወኑንና በቀናት ውስጥ ጉዳዩ እንደሚያልቅ በኤል ቲቪ የጭውውት ክፍለ ጊዜ መናገሩ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ ሕጋዊ ሰነድ አላቀረበም። አስፈላጊውን ሕጋዊ ፎርማሊቲ ሳያሟላ “ዜግነት፤ ኢትዮጵያዊ” በማለት መታወቂያ የሰጠው ዶ/ር መረራ የሚመሩት ኦፌኮ ነው።

ምርጫ ቦርድ ከጃዋር በጊዜ የተገደበ ደብዳቤ ምላሽ በኋላ ኦፌኮን በይፋ ሕግ ፊት እንደሚያቆመው የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች ሰምተዋል። ኦፌኮ ምን ይዞና በየትኛው መመዘኛና የሕግ መሥፈርት ይህንን መታወቂያ ሊሰጥ እንደቻለ ማብራራት፣ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የከረረ ሕግን የመተላለፍ ቅጣት እንደሚጠብቀውም ለመረዳት ችለዋል።

ዳጎስ ያለ ገንዘብ እየከፈለ ከቦታ ቦታ በማዘዋወር በሚያሰማራቸው ውስን ጭፍሮቹና የሚዲያ አውታሮቹ አማካይነት ጫና በማድረግ በሰላማዊ ትግል የሚታወቁትን አክራሪ ማድረጉ፣ በተለይም በሰላሌ በቅርቡ በእሱ አቀነባባሪነት ያሰራጨው የውክልና ቅስቀሳ በርካታ ሰላም ወዳድ የኦሮሞ ልጆችን እንዳሳዘነ ጎልጉል ያነጋገራቸው የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናግረዋል። እነዚሁ ክፍሎች እንዳሉት “ኦፌኮ በጃዋር አማካኝነት ካርዱ ተበላሽቷል”።

ዜግነትን ስለመመለስ ወይም ስለመቀየር ሰፊ ትንታኔ የሰጡት የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣንና የዓለም ዓቀፍ ህግ ባለሙያ አቶ ባይሳ ዋቅ-ወያ፤ “ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች” በሚል ርዕስ ለጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ በላኩት ዘገባ ችግሩ “… ዜግነት የሚባለውን እሳቤ እንደ ሰብዓዊ መብት ከመቁጠር የተነሳ ይመስለኛል” ሲሉ በሰፊው ማብራሪያቸው ይጠቅሳሉ። አያይዘውም “ዜግነትን የመስጠትም ሆነ የመንሳት መብት ያለው መንግሥት ስለሆነ ዜግነት የሰብዓዊ (መብት) ሳይሆን የሕጋዊ መብት እንደሆነ ማወቁ ተገቢ ነው” በማለት ጉዳዩ የሕግ እንጂ በእብሪትና በጎዳና ነውጥ የሚታደል የማንነት ማረጋገጫ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። በተለይ ከአሜሪካዊ ዜግነት ስለመቀየር የጻፉትን ሕጋዊና ሙሉ ትንታኔ እዚህ ላይ ይገኛል።

ወ/ሪት ብርቱካን ቀነ ገደብ ቆርጠው ለጃዋር የላኩት ደብዳቤ በተሰጠው ቀን ምላሽ ካልተሰጠበት የሕግ ጥያቄው ጃዋርን ብቻ ሳይሆን ኦፌኮንና የፓርቲውን አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት ይሰጣሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: birtukan midekssa, Election Board, Full Width Top, jawar, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ሙኒክ says

    January 24, 2020 01:23 pm at 1:23 pm

    ምርጫ ለምን ያስፈልጋል?
    እያደር እየተቀየረ ከመጣው የአለም ታሪክ እና ተጨባጭ እውነታ የምንረዳው ይህን አለም የሚገዛው የዚህ አለም ገዥ (prince of this world) የተባለው ዲያብሎስ ነው።በአለም ላይ ያሉ መንግስታት ከሞላ ጎደል በቁጥጥሩ ስር ወድቀዋል?ዲሞክራሲ እና ምርጫ የሚባለው በህዝብ መቀለጃ ፌዝ ነው።
    በአለም ላይ እንደልምድ ምርጫ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ህገወጥ ስርአትን ህጋዊ ሽፋን መስጠት የተለመደ ስለሆነ ብቻ ነው።ህዝብ ለውሸት የይምሰል ዲሞክራሲ ምርጫ እንዲመርጥ ግድ የሆነበት ዋና ምክንያት በዋናነት ዲያብሎስን የሚያገለግለው መንግስት የተባለውን አካል(necessary devil) በራሱ በህዝብ ጫንቃ ላይ ሆኖ ህገወጥ ስራ እንዲሰራበት ህጋዊ ፈቃድ ወይንም ላይሰንስ መስጠት ስላለበት ነው።አሁን ባለው የአለም ተጨባጭ ሁኔታ መንግስት የሚባለው አካል ሁለት ፊት (double face) ያለው አካል ነው።ውጪያዊው ገፅታው ለህዝብ የቆመ ቅዱስ መስሎ ይታያል።ውስጣዊ ገፅታው ግን ሰይጣንን በአለም ላይ የተዘረጋውን ሰይጣናዊ ስርአት የሚያገለግል ነው።በአለም ላይ ሰይጣንን የሚያገለግል Global Deep-State እየተፈጠረ ያለው በዚህ ምክንያት ነው።መንግስት ውጪያዊ ገፅታውን በምርጫ ሽፋን የህዝብ ይሁንታን በማግኘት በቀጣይ ያለውን ህገወጥ ሰይጣናዊ ተግባሩን ያከናውናል።ምርጫው ያስፈለገው ህዝቡ በራሱ ጫንቃ ላይ የሚዘረጋበትን ህገወጥ የማፍያ ሰይጣናዊ ስርአት ተስማምቻለሁ ብሎ በምርጫ ዲሞክራሲ አካሄድ ህጋዊ ሽፋን እንዲሰጥ ግድ ስለሚል ነው።በመላው አለም ምርጫ የሚደረገው በዚህ ስሌት ነው።ከጥቂቶቹ በስተቀር አቅም ያለው በየሀገሩ ያለው አብዛኛው ኤሊቱ ታማኝነቱና አገልጋይነቱ ለሀገሩና ለህዝቡ ሳይሆን ለግሎባሊስት ሳታኒስት ሲናጎግ ኦሊጋርኬው ነው።በምርጫ ሽፋን ኤሊቱ ስልጣን ላይ እየተቀያየረ ቢወጣም ሁሉም የሚሰራው ለግሎባሊስት ሳታኒስቶቹ ነው።በሰለጠነው የውጪው አለም የነቃው አስተዋይ ህዝብ ይሄን ድራማ ነቅቶና አውቆ የራሱን አማራጭ የትግል ከቀየሰ ቆይቷል።ስድስት ወር ባልሞላው አዲስ ፓርቲ ምረጡን ህዝብ እንምራ ብሎ ምርጫ ማካሄድ በህዝብ ማሾፍ ነው።ኢትዮጵያ ሱሴ ናት እንደተባለው ምርጫ ሱሴ ነው መሆኑ ነው።እርግጥ ነው የምርጫ ዲሞክራሲ ለሜንስትሪም የኢትዮጵያ ኤሊት በህዝብ ደምና በሀገር ሀብት እየተገበረ የሚቀለድበት አዋጪ የስራ እድል ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ምስኪኑ ገበሬ እስከመቼ ነው ሲቀለድበት የሚኖረው? ምርጫ ለኢትዮጵያ ሜንስትሪም ኤሊት ሱስ ሊሆን ይችላል።ለተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለገበሬው ግን እዳ ነው።የዚህ ደጋፊ ነህ የእገሌ ተቃዋሚ ነህ እየተባለ ህዝቡ ከዚህ ምርጫ የሚተርፈው ነገር ቢኖር እስራት አፈና ግድያ ስደት መፈናቀል ከስራ መባረር ወዘተ ነው።የኢትዮጵያ ሜንስትሪም ኤሊት ወይንም ልሂቃን ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ነገር ግልፅ አድርጓል።ይሄውም ስልጣን እና ጥቅም ከሀገር እንደሚበልጥ ግልፅ አድርጓል።የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን ኤሊት ማስተማር አለበት።እንዴት? ህዝቡ በምርጫ ባለመሳተፍ እና ማንንም ባለመምረጥ ሀገሩን ምርጫን ሽፋን አድርጎ ከሚመጣ ብጥብጥና ቀውስ መታደግ አለበት።ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ስሟን ዥግራ ይሏታል እንደሚባለው የሀገራችን ብሂል እንደሚወራው ከሆነ ኢትዮጵያ Failed-State ቀዳሚ ዝርዝር ውስጥ እንድትገባ ተደርጓል።በሌላ በኩል የሀገራችን መሪ የኖቤል ሽልማት ተቀብለዋል።ይሄ ሁለቱ እውነታ የሚቃረን የሚመስል oxymoron paradox ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱን እና የሀገሩን እጣፈንታ ስልጣን ጥቅም እና ጥላቻ ላሰከራቸው ለሜንስትሪም የውጪ ሃይሎች ቅጥረኛ ልሂቃኑና ፓለቲከኞች ብቻ መተው የለበትም።በቅርቡ ሀገራት በግሎባሊስት ሳታኒስት ሲናጎጉ ተግባራዊ እየሆነ ባለው order out of chaos ሴራን መመሪያ በመከተል በዲሞክራሲ ሽፋን እየፈራረሱ ወደ ጥንታዊ ጋርዮሽ (dark ages) ተመልሰዋል።ከላይ እንደተጠቀሰው የምርጫ ዲሞክራሲ በአለም አቀፍ ደረጃ ጊዜ እያለፈበት የመጣ ወይንም phase-out እያደረገ ያለ አሰራር ሆኗል።እያገለገለ ያለውም ለግሎባሊስት ሳታኒስቶቹ ህገወጥ ስርአትን ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ብቻ ነው።ህዝቡ በራሱ ጫንቃ ላይ ሰይጣናዊ ማፍያ መንግስታትን በምርጫ ሽፋን ፈቅዶ ተስማምቶ ስልጣን ላይ እንዲያወጣ ነው እየተደረገ ያለው።ማንም ይመረጥ ማን ስልጣን ላይ የሚወጣው ሃይል ቅድሚያ ሀገሩን እና ህዝብን ሳይሆን የሚያገለግለው ቅድሚያ የራሱን የግል ጥቅምና ስልጣን ላይ ከበስተጀርባ እንዲወጣ ያደረገውን ግሎባሊስት ሳታኒስት ሲናጎግ ነው።የምርጫው ዋናው ተቀዳሚ ትርጉምና ፋይዳው ይሄው ስለሆነ ህዝቡ ማንንም ባለመምረጥ ሀገሩን ከሚመጣው ቀውስ የመታደግ ሃገራዊ የዜግነት ግዴታውን መወጣት አለበት

    Reply

Leave a Reply to ሙኒክ Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule