• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት/ኢህአዴግ የራሱን ሪፖርት ይፋ ማድረግ ፈርቷል!

November 5, 2016 03:13 am by Editor Leave a Comment

ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በምንም ዓይነት መልኩ የማይተዋወቀው፤ መተዋወቅና መግባባትም የማይችለው ህወሃት “የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን” ብሎ ባቋቋመው ጽ/ቤቱ አማካኝነት በሰኔ 2008ዓም “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት ዘገባ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ይህ በቃል “ለፓርላማው” የቀረበው ሪፖርት እስካሁን ድረስ ይፋ አልተደረገም፡፡ የሂውማን ራይት ዎችም እስካሁን በተደጋጋሚ ኢህአዴግ ሪፖርቱን “እንዲያወጣ” ጥሪ ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡ ጌታቸው ረዳ ከሂውማን ራይትስ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን ጋር በአልጃዚራ ላይ በቀረበ ጊዜ ሰብዓዊ መብት ድርጅቱን በመወከል ሚ/ር ሆርን ኢህአዴግ ሪፖርቱን ይፋ እንዲደርግ በይፋ ጠይቀዋል፡፡ አሁን ደግሞ የመብት ድርጅቱ በወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” በኩል ለህወሃት/ኢህአዴግ በጻፈው ግልጽ ደብዳቤ “የራሱ ፓርላማ ሰዎች ያላነበቡትን ሪፖርት” ይፋ እንዲያደርግ ኢህአዴግን ተገዳድሯል፡፡

ለዓመታት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት – ሂውማን ራይትስ ዎች – ላይ የስድብ ናዳ ሲያወርድ የነበረው ህወሃት ከሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ግልጽ ደብዳቤ ደርሶታል፡፡ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ህወሃት/ኢህአዴግን ለምታደርሱት ወንጀል ያለንን ማስረጃ ይዘን ቤታችሁ ድረስ መምጣት እንችላለን ወይም ከተወካያችሁ ጋር ሌላ አገር ላይ መገናኘት እንችላለን ብሏል፡፡

felix-horne
ፊሊክስ ሆርን ስለኢትዮጵያ ጉዳይ በአውሮጳ ፓርላማ

የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ግልጽ ደብዳቤውን የላከው አሁን ለተሾመው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ሲሆን የደብዳቤው ሃሳብ ትኩረት ያደረገው ቴድሮስ አድሃኖም ከቀድሞ ሥልጣኑ ከመነሳቱ በፊት ስለ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ምርምር ስለሚያደርጉት ፊሊክስ ሆርን ነው፡፡ በOctober 22, 2016 (ጥቅምት 12፤2009) ስለ ፊሊክስ ሆርን በተለቀቀው ረጅም ጽሁፍ ላይ ህወሃት በተመራማሪው የሚቀርቡትን የጽሁፍ፣ የቪዲዮ መረጃዎችና መግለጫዎችን በሙሉ ኮንኗል፤ ማስረጃ ሳያቀርብም ሃሰት ናቸው ብሏቸዋል፡፡ ከዚህም አልፎ “ሂውማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ የተውቃውሞ አመጽ እንዲነሳ ያደፋፍራል” በማለት ድርጅቱንም ዘልፏል፡፡

ለዚህ የህወሃት ዘለፋ ምላሽ ይሆን ዘንድ ዛሬ November 4, 2016 (ጥቅምት 25፤2009) ድርጅቱ በላከው ግልጽ ደብዳቤ በቴድሮስ አማካኝነት የተለቀቀውን የህወሃት ክስ ዕርቃኑን አስቀርቶታል፡፡ የመብት ድርጅቱ ሥራውን “በዓለም ዙሪያ በ90 አገራት ውስጥ” እንደሚያከናውን በመጥቀስ በሌሎች አገሮች እንደሚደርገው በኢትዮጵያ ላይ ማንኛውንም አቢይ ሪፖርት ለሕዝብ ይፋ ከማድረጉ በፊት የግኝቶቹን ማጠቃለያ፣ የተሰጡትን የእርምት ሃሳቦችን በተመለከተ አስተያየት በመጠየቅ ኢትዮጵያን በግፍ እየገዛ ላለው ህወሃት ሲያቀርብ እንደኖረ ገልጾዋል፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል ቀጥተኛ የሆነ ይፋዊ ምላሽ ከህወሃት/ኢህአዴግ እንዳላገኘ በደብዳቤው አውስቷል፡፡

ድርጅቱ ባለው አሠራር መሠረት መረጃ የሚያቀብሉትን ግለሰቦች ማንነት ይፋ እንደማያደርግ የገለጸ ሲሆን ይህ ደግሞ የአሠራር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን መረጃ ሰጪዎቹ በህይወታቸው ላይ አደጋ እንደሚደርስ በግልጽ በመናገራቸውና ህይወታቸው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስረድቷል፡፡ የጥቃት hrwሰለባዎችን ብቻ በማነጋገር ዘገባ እንደማያቀርብ የተናገረው ድርጅት ከእነርሱ ከሚገኘው መረጃ በተጨማሪ የራሱን የሆነ ምርመራ እንዴት እንደሚደርግና ዘገባ እንደሚያጠናቅር በየጊዜው በሚወጣው ሪፖርት ላይ በግልጽ እንደሚያሰፍል ተናግሯል፡፡ ሆኖም ግን ማስተካከያዎች ካሉ ዘገባው እንዲሻሻል ማረሚያ መቀበያ ገጽ ከቀድሞ ጀምሮ አዘጋጅቶ ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን ህወሃት ለስድስት ወር ባወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ለማንኛውም ድርጅት መረጃ ማቀበል እንደ ወንጀል በመታየቱ የመረጃ አቀባዮቻችን ማንነት በምሥጢር እንድንይዝ ያስገድደናል በማለት የመብት ድርጅቱ ህወሃትን በራሱ ህግ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል፡፡

ካለፈው ህዳር 2008ዓም ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አስመልክቶ ዓለምዓቀፋዊ ምርመራ እንዲደረግ የተጠየቀ መሆኑን ያስታወሰው ደብዳቤ በሰኔ 2008ዓም ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ “ፓርላማ” በቃል የተናገረውን ዘገባእስካሁን ይፋ አለማድረጉን በድጋሚ አስረድቷል፡፡ “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት በህወሃት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበው ዘገባ ማንም የጽሁፍ ሪፖርቱ እንዳልደረሰው ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል፡፡ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ያነጋገራቸው “የፓርላማ” አባላት የጽሁፍ ሪፖርቱ ያላዩትና ያልደረሳቸው መሆኑን የጠቀሰው ደብዳቤ ሌሎች ተመሳሳይ የመብት ጥሰቶችን የሚዘግቡ ድርጅቶች ከሚያወጡበት የአዘጋገብ ስልት ehrcበተለየ መልኩ በህወሃት/ኢህአዴግ “የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ” በሚል በዘገባው የተሰጠው የተዛባ ድምዳሜ በዘገባ አቀራረብ ስልት ልዩ እንደሚያደርገው ጠቁሟል፡፡ ስለዚህ ይላል ደብዳቤው፤ “በጽሁፍ የታተመ ዘገባ በእርግጥ ካለ ለሕዝብ ይፋ እንድታደርጉት አጥብቀን እናስገነዝባችኋለን” በማለት ሂውማን ራይትስ ዎች በድጋሚ ህወሃት/ኢህአዴግን እጅግ የሚገዳደር ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ዓለምአቀፋዊ ምርመራ እንዲካሄድ አሁንም ጥያቄውን ያቀረበው ድርጅት እንዲህ ዓይነቱ ምርመራ በኤርትራ፣ በቡሩንዲና በደቡብ ሱዳን እንዲካሄድ ድርጅታችን ይፋ ሲያደርግ ህወሃት/ኢህአዴግ በፍጥነት ድጋፍ መስጠቱን በማስታወስ አሁንም የሺዎች ሰዎች ላይ የደረሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፍትህና ተጠያቂነት እንደሚያስፈልገው በግልጽ አስረድቷል፡፡

በመጨረሻም ይህ በአውሮጳ ኅብረት የሂውማን ራይትስ ዎች ዳይሬክተር የተላከው ደብዳቤ እየተፈጸ ስላለው የመበት ረገጣ በሌላ አነጋገር ህወሃት እየፈጸመ ላለው ወንጀል ያለንን ማስረጃ ይዘን ቤታችሁ ድረስ መምጣት እንችላለን ወይም ከተወካያችሁ ጋር ሌላ አገር ላይ መገናኘት እንችላለን በማለት ደብዳቤው ተግዳሮቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በጄኔራልነት ማዕረግ የፖሊስ ኃላፊ በመሆን ከዚያም በፊትም ሆነ በኋላ የሰብዓዊ መብቶችን ሲጨፈላልቅ ለመጣው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ይህ ደብዳቤ “ሹመት ያዳብር” እጅ መንሻ አይደለም በማለት ቅድመ ግምት አስቀማጮች ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ እንዲያውም ሂውማን ራይትስ ዎች በዚህ መልኩ ህወሃት/ኢህአዴግን በመገዳደር የላከው ደብዳቤ ግፍ በመፈጸም ለከፍተኛ ሹመት የበቃውን የወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ”ን “ዘንዶ” ቀን ጠብቆ የሚያወጣ “አሣ ጎርጓሪ” ደብዳቤ እንዳይሆን በማለት እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ለጎልጉል አስረድተዋል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule