• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር (ክፍል 1)

June 11, 2014 05:14 am by Editor 5 Comments

የሰው ልጆች አብረው በማህበረሰብ ለመኖር ይቻላቸው ዘንድ ለአብሮ መኖር ፀር የሆኑ ምግባሮችንና ባህሪዎችን ማስቀረት መቻል አለባቸው። አለበለዚያ ማህበራዊ ኑሮ ሊታሰብ አይችልም። ሰውን ከእንሰሳ የሚለየው ከስሜት ባሻገር የማሰብና የማመዛዘን ክህሎቱ ነው። ህሊና አንድ ሰው በጎና ክፉውን፤ መጥፎና ጥሩውን፤ ትክክለኛና ሃሰተኛውን ነገር ለይቶ እንዲያውቅ የሚያስችለውን ችሎታ ወይም ክህሎት አመልካች ነው። የሰው ልጅ የማሰብና የማሰላሰል ልዩ ችሎታ ስላለው በሚኖርበት ማህበራዊ ስፍራ የሚከሰቱትን ነገሮች ሊገነዘብና ሊዳኝ ይችላል። ልጅ ሲያድግ በጎውና ክፉውን እየለየ የሚያውቀው ከአሳዳጊ ቤተሰቦቹ፣ ከጎረቤቱ፣ በሚኖርበት አካባቢ ከሚገኙ ሰዎች፣ ተቋሞች፣ ትምህርት ቤት፣ መስጊድ፣ ቤተ ክርስቲያን ወዘተ ነው። የህሊና ዳኝነትና ለሱ መገዛት መቻል የአንድን ሰው ነፃ መሆንና በራሱ ነፃነት በጎና ክፉውን የመወሰን ችሎታን ያሳያል።

በጎሳ ብሄርተኝነት የተለከፈ አንድ ሰው አንደ ራስ-በቅ (self reliant) ሰው በራሱ ሀሳብና ፈቃድ ተመርቶ ማህበራዊ ህይወቱን ሊመራ አይችልም። በዚህ አይነት በጎሳ ብሄርተኝነት አይምሮአቸው የተመረዙ ሰዎች የግል ማንነታቸው መገለጫ የሆነውን እንደ ሰው የማሰብ ችሎታቸውን ለጎሳ መሪዎቻቸው አሳልፈው ስለሚሰጡ የአንድ በጎሳ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በሙሉ የጎሳ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን እየሰሙና እየተከተሉ እንደ አንድ ሰው ወይም እንደ ጎሳ መሪያቸው ማሰብ ይጀምራሉ። ይህ ፈረንጆች “group thinking” የሚሉትና የአንድ አክራሪ የጎሳ ድርጅት ተከታዮች አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ (homogenization of thought) ተሸካሚዎች የሚሆኑበት ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት በአክራሪ የጎሳ አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በጎሳ መሪዎቻቸው ትዕዛዝ(ውሳኔ) ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል። የጎሳ መሪዎቹ የወደዱትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ። የጎሳ መሪዎቹ የመረጡለትን ነገር ሁሉ አንድ ሰው ለመቀበል ይገደዳል። ምን እንደሚያስብ፤ ከማን ጋር ቡና መጣጣት እንዳለበት፤ ከማን ጋር መወያየት፤ ማንን ማፍቀር ማንን መጥላት፤ በየትኛው የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ እንደሚገባው ወዘተ የጎሳ መሪዎቹ ይነግሩታል። በዚህ አይነት የግል ማንነቱን ያጣ ሰው ይሆናል።

በአለም ላይ ሰዎች የጎሳ ብሄርተኝነትን፣ አክራሪ የሃይማኖት ፍልስፍናን ወዘተ በመሣሠሉ መርዘኛ አመለካከቶችን በሚያራምዱ ፍልስፍናዎች ምክንያት የህሊና ዳኝነት ችሎታቸውንም ሆነ ክህሎታቸውን አሽቀንጥረው የጣሉበት ሁኔታ እንደነበረ ታሪክ ዘግቧል። ለምሳሌ በናዚ ጀርመን ውስጥ ሰዎች እንደ ሰው ለህሊናቸው መገዛትን አቁመው ህሊና ቢስ በመሆን በጥላቻ የሰከሩ መሪዎቻቸውን እነ ሂትለርን፤ በጣሊያን እነ ሞሶሎኒን በጭፍን የተከተሉበት ሁኔታ እንደነበር በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አይተናል። በዚህ ወቅት በናዚ ፍልስፍና መስፋፋት የተነሳ ብዙ ጀርመኖች ህሊናቸውን ስተው የሂትለር ፓርቲ ደጋፊና አጫፋሪ ሆነው ስለነበር አብዛኞቹ የጀርመን ተወላጆች ሰው የሚያሰኛቸውን የህሊና ዳኝነት ክህሎት አሽቀንጥረው በመጣል የግል ማንነታቸውን አጥተው የናዚን ፋሽስት የፖለቲካ ፍልስፍና ስርዓት ተከታዮችና አቃፊ ደጋፊዎች ሆነው ነበር።

የናዚም ሆነ የፋሽስት አክራሪ የጎሳ ብሄርተኝነት ተከታዮችን ከሰውነት ተራ በመውጣት የግለሰብ ማንነታቸውን አጥፍቶ እንደ እንሰሳት መንጋ የአንድን የጎሳ ድርጅት መሪዎች በጭፍን እንዲከተሉ ያደርጋል። እነዚህ በመሪዎቻቸው ሀሳብና ትዕዛዝ በጭፍን የሚመሩ ህሊና ቢስ የተደረጉ በጎሳ ብሄርተኝነት ስሜት የሰከሩ የአንድ ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ጀሌዎች መሪዎቻቸው አድርጉ ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ ካለ አንዳች ማወላወልና ማንገራገር ይፈፅማሉ። በዚህ አይነት ህሊናቸውን ያጡ ጀሌዎች በበዙበትና ስልጣን በተቆናጠጡበት ሃገር ውስጥ ሊከሰት የሚችለው አደጋ የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት ሊቀጥፍ ይችላል፤ ሀገርን ያፈርሳል፤ ህዝብን ይበትናል። ትላንት የናዚ ጀርመኖች ፍልስፍና ገዥና ዋና አስተሳሰብ (dominant ideology) በነበረበት ግዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዳዊያን፣ እስላሞች፣ ጂፕሲዎች ወዘተ በገፍ እየተነዱ ሲፈጁ አብዛኛው የጀርመን ህዝብ ድርጊቱን ሳይቃወም እንዲያውም ሲደግፍ ታይቶ ነበር። በዛን ጊዜ በርካታ ጀርመናዊ በናዚ ጭፍን የጀርመን የበላይነት ፍልስፍና (Deutschland ueber alles) ወይም ጀርመን ከሁሉ በላይ በሚለው የአርያን የዘር የበላይነት በሚያንፀባርቅ አስተሳሰብ አይምሮው ተመርዞ ነበር። በዚህ ምክንያት የጀርመን ህዝብ በጎውና መጥፎውን የሚለይበትን ህሊናውን አሽቀንጥሮ በመጣል የራሱን ማንነት አሳልፎ ለናዚ መሪዎች በገፀ-በረከትነት ሰጠ።

ዛሬ በኢትዮጲያችን ተመሣሣይ ሁኔታ እየታየ ነው ብዬ እሞግታለሁ። የወያኔ ድርጅት ትግል ሲጀመር የዚህን ድርጅት እኩይ አላማ በመቃዎም የተገረፉ፣ የተገደሉ፣ የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉና ለነዚህም ከፍተኛ አክብሮት እንዳለኝ ልገልፅ እፈልጋለሁ። ለሀገራቸው ያደረጉትንም ውለታ አልረሳም። ይሁን እንጂ ለ17 አመታት በጦርነት እንዲሁም ላለፉት 38 አመታት ወይም 39 አመታት በፀረ-ኢትዮጵያ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ በተለይም ቀለም ቆጠረ የሚባለው ክፍል በዛሬው ወቅት የመርዘኛው የትግራይ ብሄርተኝነት ሰለባ በመሆን የዚህ ያለው ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ የወያኔ አገዛዝ ደጋፊና አቃፊ ከሆነ ውሎ አድሯል።

tplf addis mexico squareበዚህ ምክንያት የወያኔ ስርዓት በሌሎች የኢትዮጵያ ጎሳዎች ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ከመቃወም ይልቅ በርካታ የትግራይ ተወላጅ ይህንን የወያኔን ስርዓት በፅናት ከሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን በተቃራኒ ጎን መቆምን መርጧል። ይህንን ገደምም ጠመምም ሳላደርግ ባለፉት 21 አመታት ስናገር እንደቆየሁት ዛሬም በናንተ ፊት በአደባባይ እናገራለሁኝ። የዚህንም አደገኛ አዝማሚያ አውዳሚ ፍፃሜ አመለክታለሁኝ። እስቲ በቅድሚያ የቀድሞ የወያኔ ትግሬዎች መሪ መለስ ዜናዊ ለትግራይ ህዝብ ካደረገው እጅግ እብሪትና የማን አለብኝነት ከተጠናወተው ንግግሩ አንዱን ጠቅሼ የትግራይ ብሄርተኝነት ከምን አደገኛና ወደ ኋላ ሊመለስ ከማይችልበት ጫፍ እንደደረሰ ማስረጃ አቅርቤ ላስረዳ ልሞግት። ይህ ከዚህ በታች የምጠቅስላችሁ ንግግር መለስ ዜናዊ መቀሌ ውስጥ የወያኔን የድል በዓል ሲያከብር በመቶ ሺዎች ለሚቆጠር የትግራይ ህዝብ ካደረገው ንግግር ነው፦

“ይህ ህዝብ እንኳን የሌሎች ባዕዶች ያልሆነ። እንኳን ከእናንተ ተፈጠርን። ይህ የእያንዳንዱ ታጋይ እምነት ነው። እንኳን ከእናንተው ማህፀን ተፈጠርን። እንኳን የኛ ሆናችሁ። እንኳን የሌላ የባዳ አልሆናችሁ። እንኳን በማዶ እያየናችሁ የምንቀናባችሁ አልሆናችሁ።”

በዛው እለት በተያያዘ ንግግሩ መለስ ለትግራይ ወጣቶች እንዲህ ብሎ መልዕክቱን አስተላልፎ ነበር፦

“እናንት ወጣቶች እዚህ ያላችሁበት መድረክ እንድትደርሱ ሲባል ታላላቆቻችሁ ላባቸውንና ደማቸውን አፍስሰዋል። ታላላቆቻችሁ በየጉራንጉሩ በየሸለቆውና በየተራራው ቀርተዋል። ታላላቆቻችሁ አጥንታቸው በየተራራው ተበትኗል። አጥንቶቻቸው በየተራራው የተበተነበት ምክንያት ትግራይ እንድትለማ በሚል ነው። እነኚህን አጥንቶች እንዳትረግጧቸው እንዳታረክሷቸው፤ ሁኔታውን ካመቻቹላችሁ በኋላ እንዳትከዷቸው ሌት ተቀን መጣር ይኖርባችሗል።”

ይህ ንግግር አንድ በብሄርተኝነት የሰከረ እነ ሂትለር ካደረጓቸው የእብሪት ንግግሮች የላቀ ነው። ዛሬ በዚህ የተቀሰቀሱ ልባቸው ያበጠ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ተፈጥረዋል።

ዛሬ የወያኔ ትግሬዎችና በስራቸው ያሰለፏቸው የጎሳ ተከታዮቻቸው በአብዛኛው ህሊና እንዳለው ግለሰብ በጎውንና ክፉውን አመዛዝኖ ፍርድ ከመስጠት ይልቅ በወያኔ ድርጅት ትዕዛዝ እንደ መንጋ በጀሌነት የሚመሩ ፍጡራን ሆነዋል። የአንድ ጎሳ ተወላጆች የራሳቸው ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች በሌሎች ከነሱ ጎሳ ውጪ ባሉ ተወላጆች ላይ የሚፈፀሙትን ማናቸውንም ህሊና ያለው ሰው ማየት የሚችለውን ጥፋትና ግፍ ለማየት ይሳናቸውና የጎሳ መሪዎቻቸው የሚሏቸውን እየሰሙ ይህን ግፍ ለሚፈፅሙት የጎሳ መሪዎቻቸው ጭፍን ድጋፋቸውን ሲሰጡ ይህ ሁኔታ ለአንድ ሃገር ታላቅ አደጋን ይጋብዛል። የጎሳ ፍጅት (Genocide) መነሾም ይሆናል። በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የታጠቁ የትግራይ ተወላጆች በሃይል ከጎንደር ተቆርሶ ወደ ትግራይ ክልል የተጠቃለለውን ለም መሬት ይዘው፤ አሻፈረኝ ያለውን ነባሩን ህዝብ ገድለው፤ ከፊሉን የተወለደበትንና ያደገበትን ቀዬ ጥሎ ወደ ሱዳን፣ አዲስ አበባና ጎንደር እንዲሰደድ ማድረጋቸው የወያኔ ትግሬዎች የተፀናወታቸውን ህሊና ቢስነትና አመለካከታቸው በጎሳ አስተሳሰብ የተመረዘበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

በቅርቡም የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ታሪካዊውን የዋልድባን ገዳም «የትግራይ ክልል አካል ነው» በማለት በገዳሙ ውስጥ የነበሩትን የትግራይ ቀሳውስትና መነኮሳት በጎሳ ስሜት ቀስቅሶ ከጎኑ በማሰለፍ የወሰደው ገዳሙን የመቆጣጠር እርምጃ ይህንኑ ህሊና ቢስነትና የአንድ አናሳ የጎሳ ተወላጆችን እብሪት የሚያሳይ ድርጊት ነው። እንደ ኢትዮጲያ ግፍ ሞልቶ በፈሰሰበት ሀገር ውስጥ ይህ አይነቱ ጭፍንነት ኋላ ጎሳን መሠረት ላደረገ ከፍተኛ ፍጅት(Genocide) የሚዳርግ ነው። ዛሬ የአማራን ህዝብ ከሶማሌ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከደቡብና ከኦሮሚያ ክልል እንዲዎጡ የተደረገበት በፋሽስቱ የጣሊያን የወረራ ግዜ እንኳን ያልተፈፀመ ዘግናኝ ድርጊት ሲፈፀም የዚህን የአማራ የጎሳ ጥቃት እያስፈፀሙ ያሉት የወያኔ ትግሬዎች፣ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ከላይ እስከታች የዘረጋው የስለላ መረብ አዛዦችና የወታደራዊ ጭፍሮቻቸው እንደሆኑ አንዘንጋ።

በክፍል ሁለት የወያኔ መንግስት አንዳንድ ፋሽስታዊ ጠባዮችን እንመለከታለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. solomon says

    June 15, 2014 08:01 pm at 8:01 pm

    eroso belo doctor tebabenet eyetakawumu zeren bejemela yesadebalu. Enderso ayenet bezer tilacha yetelekefe eyale yetegray yetemare endet bechefen weyanen aydegef.

    Reply
  2. semagne says

    June 16, 2014 12:20 pm at 12:20 pm

    pleas,depends on witteness

    Reply
  3. semagne says

    June 16, 2014 12:25 pm at 12:25 pm

    any one like you and others seems like this talking and writting the insult on other this not the way of the developemnt trigger.This one of the evile way.not poltical idology.wo do have knowoledg one we benefite from the coming to the present.please designe other good way of moblization of poltics!!!

    Reply
  4. gud ayehu zendro says

    June 16, 2014 09:22 pm at 9:22 pm

    Mr Solomon, It is not difficult to identify you as one of the member of woyane fascism. What was written in this article is true. In the history of the world people killed people based on politics, ethnicity, religion etcetera. Most of woyane syupporters are Tigreans and other hodam bandas from different clans. The writer wanted to tell you that don’t follow some morons just because they are from your clan. We need to set aside our differences and try to build a new Ethiopia where all ethnic groups are treated equally. In this regime, all the privileges are to the members of woyane fascism. This is true and if you’re not insane, you wouldn’t deny it.

    Reply
  5. Hasab says

    June 16, 2014 10:51 pm at 10:51 pm

    Dear Sir, with your respect you need to slow down your tone. Don’t forget the ones who are real Ethiopians and isolated and/or punished by Woyane/tplf just because of their belief. In Amaric, “Newur new.” I understand your pain but let’s don’t generalize. How about ONEG and Juhar Mohammad follower Oromos doing in Ethiopia now? They are attacking Amharas and burning down their properties again, same as they did 20 years ago. They are following same path as woyane; they are hateful, misplacing and killings, hate Ethiopian interest and Amharic language and claiming fighting for Oromo peoples’ right. They are also trained by shabya and funded by Arabs. Since they are not representing all Oromos, we cannot generalize and say bad things about Oromos. TPLF and ONEG members are evils as they trained; but not the ordinary citizens of these ethnic groups.

    Reply

Leave a Reply to semagne Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule