• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ

February 26, 2014 06:12 am by Editor 4 Comments

ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ በረዳትነት የሚያበረውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ስዊዘርላንድ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ካሳረፈ ወዲህ የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛውን ትኩረት ይዞ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ድርጊት በኋላም በሁለቱም ጎራ ያሉ አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በተመለከተ የተለያየ መላምት ትችትና ነቀፋ ሲሰነዝሩበትና ሲሰናዘሩበት ሰንብተዋል፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን ጀግና ነው አርበኛ ነው ሲለው “መንግሥት” እና ደጋፊዎቹ ደግሞ ከሀዲ ነው ብለውታል፡፡

እነኝህ ሁለቱም አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በየበኩላቸው ያሉትን ለመሆኑ የየራሳቸውን ማስረጃ የሚሏቸውን ነገሮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ክፍል ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ጀግና ነው የሚሉበትን ምክንያት ሲጠቅሱ በአገዛዙ ተማሮ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁን፣ ይሄንን ድርጊት ከመፈጸሙ በፊትም ለወያኔ ባለመመቸቱ አሜን ወዴት ባለማለቱ እኅቱ በፌስ ቡክ (በመጽሐፈ ገጽ) በሰጠችው ገለጻ መሠረት ስልኬን ጠልፈውብኛል ይል እንደነበር፣ “መንግሥት” በተለያየ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች እየተከሰሰ እንዳለው የተለያዩ ግለሰቦችን በኮምፒውተራቸው (በመቀምራቸው) መሰለያ በመጫን እየሰለለ እንደሆነ እንደሚነገረው ሁሉ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅንንም የግል ኮምፒውተሩን (መቀምሩን)  ካሜራ (በመቅረጸ ምስል) በመጠቀም እያንዳንዱን እንቅስቃሴየን ይከታተሉኛል ይል እንደነበር ኮንፒውተሩን (መቀምሩን) ሲጠቀም ካሜራውን (መቅረጸ ምስሉን) ለመሸፈን ይገደድ እንደነበር፣ መኖሪያ ቤቱንም በሌለሁበት እየገቡ ይፈትሹብኛል ይል እንደነበር፣ የሚያስፈራሩት አካላት እንደነበሩ፣ አልፎም ለቤተሰቦቹ እንደሚሠጋ ባጠቃላይ ደኅንነቱ በሚያሳዝን ሁኔታ አደጋ ላይ የወደቀ እንደነበር፣ ይህ ሁሉ ውክቢያና ማስፈራሪያ እየደረሰበትም ለእነሱ ቡድናዊ የፖለቲካ (እምነተ አሥተዳደር) ፍላጎት ባለመንበርከኩ ባለማደሩ ባለመገዛቱ እንደነበር ይህ ሁኔታ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ችግር መሆኑንና አዲስ ነገር አለመሆኑን በሁሉም ዜጎች ላይ እንደሚደርስ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የጋራ ችግር መሆኑን ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ግን እንደ ብዙዎቻችን ሁሉ በእነዚህ ግፎች ሁሉ ተንበርክኮ ባለመሸነፉና አሻፈረኝ ብሎ እራሱን ነጻ በማውጣቱ ለዚህ ለደረሰበት ሰላም ለሚነሳ ውክቢያ እጅ አለመስጠቱን በመጥቀስ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ጀግና እንደሆነ ያረጋግጣሉ፡፡

“መንግሥት” እና ደጋፊዎቹ ደግሞ ምንም እንኳን እስከአሁን ከቦታው በተገኘው መረጃ መሠረት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን የፖለቲካ ጥገኝነት እንዳቀረበ በግልጽ የታወቀ ጉዳይ ሆኖ ያለ ጉዳይ ቢሆንም በማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛው የ“መንግሥት” ደጋፊዎች የሆኑቱ የረዳት አብራሪውን የኃይለ መድኅንን ጉዳይ ኢሳትን በመሳሰሉ የብዙኃን መገናኛዎች ፖለቲካዊ ገጽታ ተሰጥቶት በማየታቸው ስሕተት መሆኑን በመኮነን ሲናገሩ ተስተውለዋል፡፡ ማስተዋል ካለመቻላቸው ይሁን የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ካለማወቃቸው ሊገባኝ አልቻለም፡፡

ጥቂቶት የመንግሥት ደጋፊዎች እና “መንግሥት” ግን ይህ ጉዳይ ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ገብቷቸዋል፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድም የሠጉት ትርጉም እንዳይወሰድና ስማቸው አሁን ካለበት ደረጃ ይብስ እንዳይጠፋ ያደረጉ መስሏቸው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ይህንን እርምጃ በወሰደበት ወቅት በደኅና በትክክለኛ (normal) የአእምሮ ጤና ላይ እንዳልነበረና ሱሰኛም እንደሆነ በዚህም ምክንያት ድርጊቱን እንደፈጸመ በማስረዳት ለመከላከል እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ድርጊታቸው ከድጡ ወደ ማጡ መሆኑን አልተረዱም አልተገነዘቡም፡፡ ድርጊታቸው ፈጽሞ ኃላፊነት የጎደለውና አርቆ ማሰብ የተሳነው፣ አየር መንገዱንም ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርግ የደነቆረ ማስተባበያ ነው፡፡ ምክንያቱም ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን እንዲህ እንዳሉት ዓይነት ሱሰኛና ሥራውን በትክክል ለመሥራት በማያስችል የመንፈስ ጭንቀትም ሆነ የሥነ ልቡና መታወክ እንዳለበት እየታወቀ ሥራ ላይ በማሠማራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ደንበኞቹን ደኅንነት ለአደጋ አጋልጧል የሚል ትርጉም እንደሚያሰጠውና አየር መንገዱ ለደንበኞቹ ደኅንነት የማያስብ የማይገደው የማይጠነቀቅ ኃላፊነት የማይሰማው እንደሆነ ተቆጥሮ ለዘመናት በብዙ ድካም የገነባውን መልካም ስም እንደሚያጠፋው ደንበኞቹንም እንዲያጣ እንደሚያደርገው ያልተረዱና መረዳት የማይችሉ ሰዎች የደነቆረ አርቆ ማሰብ የተሳነው ስም ማጥፋት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሥራየ ብለው ይህንን ስም ማጥፋት ያደረጉትና እያደረጉም ያሉት ደናቁርት አየር መንገዱ ለሚደርስበት ጉዳትና ኪሳራ ኃላፊነቱን የሚወስዱ ይሆናሉ፡፡

በሌላ በኩል በእርግጥም እንደተባለው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን የአውሮፕላኑን አቅጣጫ መቀየር ሳያስፈልገው በራሱ በግሉ በፈለገው ሀገር ላይ በሔደበት ጥገኝነት ጠይቆ መቅረት የሚችል ሰው ነበር፡፡ እንደኔ ግምት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ይህንን ያደረገበት ምክንያት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት፡፡ የአውሮፕላኑን አቅጣጫ ከሮም ወደ ስዊዘርላንድ ማድረጉና ጥገኝነቱን እዚያ መጠየቁ ሲጠይቅም አውሮፕላኑን መያዙ መውሰዱ ምክንያቱ አንደኛው ሽንት ቤት ሲገባ የቆለፈበት ዋናው አብራሪ ጣሊያናዊ በመሆኑ ለሚያቀርበው የፖለቲካ ጥገኝነት በቂም ምክንያት እንቅፋት እንዳይሆነው በመሥጋቱ ሲሆን ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን በሄደበት ቀርቶ ብቻውን መጠየቅ ሲችል ይሄንን ያላገረገበት ምክንያት ጉዳዩ የሱ የግሉ ጉዳይ ሆኖ እንዲቀር ስላልፈለገ፣ ይህ እሱን ያሰቀቀውና ያንገላታው ችግር የሱ ችግር ብቻ አይደለምና አውሮፕላኑን በመውሰድ የኢትዮጵያን ሕዝብ አቤቱታ በአደባባይ አጉልቶ በማሰማት እንዲያቀርብ አድርጎታል፡፡

ይህ ሰው እንደሌሎቻችን ሁሉ ሆዳም ቢሆን ኖሮ የያዘው የሙያና የኑሮ ደረጃ አይደለም በኢትዮጵያ በየትኛውም ሀገር ቢሆን ተንደላቆ ተንቀባሮ መኖር የሚያስችለው ደረጃ ነበረው፡፡ ነገር ግን ልጁ ሰው ነውና፣ ባለ ሕሊና ነውና፣ ጭንቅላት ያለው ዜጋ ነውና፣ አስተዋይ ነውና ሕዝቡ ወገኑ በችጋርና በሰብአዊ መብቶች እጦት እየተሰቃየ እያየ የሚበላውና የሚጠጣው ሊዋጥለት አልችል አለው፡፡ ምቾቱ ሊደላው አልቻለም፡፡ በአፍንጫየ ይውጣ አለ፡፡ አለና ድሎት ያለውን ሕይዎቱን መሥዋዕት አድርጎ በአስደናቂ ብቃትና አፈጻጸም የሕዝብን አቤቱታ በተገቢው ቦታና ሁኔታ ለዓለም ሕዝብ አቀረበ አሰማ፡፡

አዎ ይሄም እውነት ነው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ከሀዲ ነው፡፡ ግፈኛ አገዛዝን አላገለግልም ብሎ የግፍ አገዛዙን ክዷልና፡፡ ይህ አሁን እሱ ያደረገው ሥራ የሰላማዊ ትግል መሐንዲስ የሆነው ጋንዲ ለስኬት የበቃበት የሰላማዊ ትግል አንዱ ዓይነት እርምጃ ነው፡፡ ከተጠቀምንበትና ሁላችንም ከተባበርን የረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅንን አርአያነት ከወሰድን፡፡ ወያኔን በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ብቻ እጅ እንዲሰጥ ማድረግ አቅሙን ጨካኝ ጉልበቱን ማሽመድመድ ይቻላል፡፡ እስከመቸ ነው እሽሩሩው? እስከመቸ ነው ትዕግሥቱ? እስከመቸ ነው መቻሉ? መጨረሻ የለውም እንዴ? ልክ የለውም እንዴ? በዚህ ሁኔታ ትውልድ እያለፈ ትውልድ መተካት አለበት እንዴ? ሁሉም ነገር ቢሆን እኮ ልክና መጨረሻ ገደብም አለው፡፡ ትዕግሥታችን እሽሩሩአችን መቻላችን መጨረሻ ገደብና ልክ ካለው ጊዜው አሁን ነው ጊዜው ዛሬ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የምንጨምራቸው ጊዜያት የሚባክኑ ብቻ ሳይሆኑ ህልውናችንን የሚያስከፍሉ የሚበሉ የሚያጠፉ የጥፋት የመዓት ቀናት ጊዜያት ዘመናት ናቸው፡፡

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

በተናጠል የሚወሰዱ እርምጃዎች የትም አያደርሱንም፡፡ የዚህን ጀግና እርምጃ ዐይተን አድንቀን መቀመጡ ምንም አይጠቅመንም እሱ ትልቁን እርምጃ ተራምዶ ጀምሮልናል የግድ መከተል ይኖርብና፡፡ ይሄኔ ሀገርን ሕዝብን እራሳችንን ነጻ እናወጣለን፡፡ ነጻ ነጻ ነጻ እንሆናለን እኛም ወግ ይደርሰንና ለሥልጣኔ ሽምጥ እንጋልባለን፡፡ የነጻነት ፍሬዎችን ልማትን፣ ሰላምን፣ አስተማማኝ ደኅንነትን፣ ምቾትን፣ ጤናን፣ ፍቅርን እናጣጥማለን እንኮመኩማለን፡፡ ሥጋትን፣ ፍርሐትን፣ ጭቆናን፣ እንግልትን፣ አፈናን፣ እረገጣን፣ መብት መነፈግን፣ ረሀብን፣ ችጋርን፣ ጉስቁልናን፣ አንገት አስደፊውን አዋራጁን ድህነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቶሎ እናሰናብታለን እንቀብራለን፡፡ ይህች ሀገር ከራሷ አልፋ ለስንት የሚበቃ ሲሳይ በረከት አላት፡፡ ሕዝብ የተቸገረው የተራበው የሚጠማው ስለሌለን አይደለም፡፡ በጨካኝና አንባገነን አገዛዙ ተዘግቶብን፣ ተይዞብን፣ ተቆልፎብን፣ ተከልክለን፣ ተነፍገን ነው እንጂ፡፡ እውነት እንዳይመስላቹህ ድሆች አይደለንም በፍጹም ምንም የሚቸግረን ነገር አልነበረም፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

amsalugkidan@gmail.com (ፎቶ: ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Matebe Melese says

    February 27, 2014 02:57 pm at 2:57 pm

    ተባረክልኝ ወንድሜ ስአሊ አምሳሉ፡
    እናት ሃገር ኢትዮጵያ፡ እየተገዛች ያለችው በእነዚህ፡
    ሕዝብንም፣ ታሪክንም፣ ፈጣሪንም፣ በካዱና በናቁ፣
    ደናቁርትና፡ታሪካቸውን ለጥቅማቸው፣ ስብናቸውን ለሆዳቸው፡
    አሳልፈው በሰጡ ጄሌዎቻቸው ስለሆነ እነሱ እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል
    አለች እንደመትባለዋ እንስሳ፡ ሁሉ እንኳን ለአየር መንገዱ ታሪክ ይቅርና
    ለራሳቸው፡ የነገ ምንነትንና የልጆቻቸውን ህይወት እንኳን አሻግረው የሚያዩበት፡
    አይነ ህሌናቸው የታወረና በነገ ተሰፋየቆረጡ ድኩማን ናቸው።
    ለማነኛውም ሐይለመድህን ጀግናችን ነው፡ ፈጣሪ ለታሪክ ሰሪነት ከሚፈጥራቸው፡
    ሰዎች አንዱ ነው፡ ኮርተንበታል፡ ሌላ ሀይለመድህን፡ ደግሞ ፈጣሪ ይላክልን አሜን፡

    Reply
  2. Moghes Zewdie says

    February 27, 2014 03:09 pm at 3:09 pm

    for me Hailemedhin is a leading actor

    Reply
  3. ETHIOPIAN GHION says

    February 27, 2014 11:10 pm at 11:10 pm

    WOYANIE, YOU ARE THE STUPIDEST DOG EVER WHO HAS ALREADY SOLD ERITREA & MADE ETHIOPIANS LANDLOCKED!!
    LOVE U AMSALU!!

    Reply
  4. ezra says

    February 28, 2014 03:33 am at 3:33 am

    Seali Amsalu… Many many Thanks ! it is really a nice article

    Reply

Leave a Reply to Matebe Melese Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule