• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ

May 14, 2016 02:45 am by Editor 3 Comments

ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የጀርመን ኤምባሲ የትግርኛ ቋንቋን ቁልፍ ቅድመ መስፍርት የሚያደርግ ክፍት የስራ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ለሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አወጣ። ትግርኛ ዋና መስፈርት የሆነበት ምክንያት ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የኤምባሲው ተግባር የኢትዮጵያውያንን እኩልነትን ከህወሃት በላይ ያንቋሸሸ ነው ብለውታል፡፡ ኤምባሲው ማብራሪያ እንዲሰጥ ይጠበቃል።

ኢምባሲው በድረገጹ ሜይ 4 ቀን 2016 ያወጣው  ማስታወቂያ የሚፈልገው ባለሙያ የቪዛ ማመልከቻ ስራን የሚያመቻች፣ የሚያረጋግጥ፣ ቪዛ ነክ ጉዳዮችን አስመልክቶ የቃልና የጸሁፍ መረጃዎችን የሚሰጥ፣ የቪዛ ክፍያን የሚፈጽምና የመዝግብ አያያዝ ስራን የሚያከናውን እንደሆነ ያረጋግጣል። የስራው ቦታ ከአዲስ አበባ ውጪ ስለመሆኑ የሚለው ነገር የለም። ማስታወቂያውን የተመለከቱ ወገኖችን ያነጋገረውም ይኸው ጉዳይ ነው።

መመዘኛ (requirements) በሚለው የማስታወቂያው አንድ ክፍል ላይ በቀይ ቀለም “Good knowledge of Tigrinya is a precondition/የትግርኛ ቋንቋ በቂ እውቀት የስራው ቅድመ መስፈርት ነው” ይላል።

ዝቅ በሎ የቋንቋ ችሎታ በሚል የሚፈለገውን ሲዘረዝር እንግሊዝኛና ጀርመንኛ አቀላጥፎ የሚናገር ይላል። አክሎም ትግርኛና አማርኛ መናገር አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክታል።

ዲግሪ፣ የኮምፒውተር ችሎታ፣ ተባበሮ የመስራት ተነሳሽነትና በአስተዳደር አገልግሎት በቂ ልምድ ያላቸው ተመራጭ እንደሚሆኑ የሚያስረዳው የኤምባሲው ማስታወቂያ የማመልከቻው ጊዜ የሚጠናቀቀው ሜይ 20 ቀን 2016 መሆኑን ይጠቁማል።

ለጎልጉል ዝግጅት ክፍል አስተያየት የሰጡ ወገኖች እንደሚሉት የኤምባሲው ማስታወቂያ “ሸውራራ ነው፤ ዜጎችን በእኩል አያስተናግድም፤ ፍትሃዊነት የጎደለው ነው፤ ዘረኝነትን የሚያበረታታና የአገሪቱን የስራ ቋንቋ ያናናቀ፣ ወገናዊ፣ የኢትዮጵያውያንን እኩልነት ከገዢው ህወሃት በላይ ያንቋሸሸና ክብር የነካ…” ሲሉ ነቅፈውታል። በማከልም “ኤምባሲው ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ሆኖ ሳለ ትግራይ ክልል ቢሮ ወይም የቆንስላ ጽ/ቤት የከፈተ ይመስል ትግርኛን ለመቀጠሪያ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ አድርጎ በአንደኛነት ማስፈሩ ምዕራባውያን ኤምባሲዎች እንዴት ለህወሃት አጎብዳጅ እንደሆኑ የሚጠቁም ነው” ብለዋል፡፡

ማስታወቂያውን ሲያወጣ ኤምባሲው በግልጽ የትግርኛ ቋንቋን ቅድመ መስፈርት ያደረገበትን ምክንያት ሊያስረዳ ይገባው እንደነበር ያመለከቱት ወገኖች የዝግጅት ክፍላችን ኤምባሲውን ጠይቆ ምላሹን እንዲያሳውቃቸው ጠይቀዋል። በዚሁ መሰረትና ዜናውን ማመጣጠን በሚለው ሙያዊ እሳቤ ኤምባሲው ማብራሪያ እንዲሰጥ የዝግጅት ክፍላችን መጠይቅ ልኳል። ይህ ዜና እስከታተመበት ጊዜ ኤምባሲው ምላሽ አልሰጠም፡፡

በሌላ በኩል አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች የቪዛ ጉዳይ ከደህንነት/ስለላ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የህወሃት ሰዎች ባላቸው ትሥሥር ይህ እንዲደረግ ጫና ከማሳደር እንደማይታቀቡ ይናገራሉ። አያይዘውም ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ በሆነ “ታላላቅ” ኤምባሲዎች ውስጥ በብዛት የሚቀጠሩት የህወሃት ሰዎች ስለሆኑ የስለላው ክፍል መረጃ ለማግኘትና ኤምባሲዎች ውስጥ የሚከናውኑ ተግባራትን በቅርብ በመከታተል እንደሚቻለው ጠቁመዋል። (ፎቶው ከኤምባሲው ድረገጽ ላይ የተወሰደ ነው)።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    May 15, 2016 04:23 pm at 4:23 pm

    U fools !
    It is intended to give asylum to Eretrians

    Reply
  2. Sofiya says

    May 20, 2016 05:26 am at 5:26 am

    Amharic and Amhara people is not easily desroyed. Those that tried to do that fall before Amara or Amharic . Recently Ahmed Nasir, President of the Benishangul Gumuz State, Died at age 51 on Thursday May 18, 2016 he is remembered among many crimes for his ethnic cleansing especially in 2013 he was responsible for so many crimes against the Amara ethnicity members. He also made it a rule noone speak Amharic in his office. The whole idea and talk about oppression of nations and nationalities, as they call them, was propagated only to patronize the ethnic elites and facilitate their cooperation in the Bantustanization of Ethiopia and reduce the country to units manageable to rule. That was how you could manufacture surrogate ethnic parties. This was the reason the multiethnic Ethiopian People’s Democratic Movement (EPDM) was forced to become an ethnic Amhara party overnight, though it is obvious that none of it looks like a party created to help Amharas.

    Folks, whether you like it or not, this is the vision that will definitely challenge Ethiopia’s survival as a nation in the future. And this is the vision that all of Ethiopia’s officialdom and party cadres are swearing to preserve. Be afraid not only for the Amhara, this poison embedded in the philosophy of our government’s ethnic policy can destroy Ethiopia if left unreformed. This fire will catch more forests. You ain’t seen nothin’ yet, as my American friends would say.

    Yes, we are witnessing a painful tragedy in progress and I understand why many of you are crying. I myself did shade some tears when listening to the voices of the unfortunate. But don’t let your tears cloud you from seeing the real reason. There is a need for a huge change in Ethiopia.

    http://nazret.com/blog/index.php/ethiopia-behind-the-ethnic-cleansing-in-benishangul-gumuz?blog=15

    http://www.ethiomedia.com/14store/5578.html

    http://ethsat.com/freed-blue-party-officials-ordered-to-leave-benishangul/

    Chief Administrator of Benishangul Gumuz Regional State, Ahmed Nasir, has passed away yesterday at the age of 51.
    According to the regional state communication affairs office, Ahmed had been chief administrator of the state for the past 7 years.
    He was also a deputy chairman of Benishangul Gumuz People’s Democratic Party (BGPDP), the ruling party in the regional state.
    The late Ahmed earned his first degree from Haremaya University in agricultural engineering and his second degree from the Chinese Hohai University in water engineering.
    He also served as state minister of agriculture and as head in various government offices.
    He will be laid to rest in the regional state’s capital, Assosa, in the presence of his family, relatives and residents of the town.
    He is survived by his wife and a son.

    GET UPDATES FROM THOSE THAT MADE IT THEIR LIFE MISSION TO SAVE ETHIOPIA.

    Prof. Berhanu Nega Patriotic Ginbot 7 Chairman will be in Seattle, Join Us FOR THIS HISTORIC TOWN HALL MEETING OPEN TO PUBLIC ON SUNDAY MAY 22ND AT 8323 RAINER AVENUE S. , SEATTLE , WASHINGTON 98118

    http://ecadforum.com/2016/05/18/berhanu-nega-patriotic-ginbot-7-chairman-will-be-in-seattle/

    OR IN DC ON 5/29/16

    Prof. Berhanu Nega Patriotic Ginbot 7 Chairman will be in DC, Join Us FOR Ethiopia: Public Meeting with Prof. Berhanu Nega in Washington, DC –

    GEORGE TOWN MARRIOT 1221 22ND STREET , NW , WASHINGTON , DC 20037

    ON SUNDAY MAY 29TH 2PM ENTRANCE FEE ONLY $20.00 DOLLARS

    See more at: http://www.zehabesha.com/ethiopia-public-meeting-with-prof-berhanu-nega-in-washington-dc/#sthash.gnqK5nMH.dpuf

    Reply
  3. zamed says

    May 21, 2016 12:02 am at 12:02 am

    ይህ ዜና የሚያሳየን ትልቁ ነገር ትግሬ መሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት ጉዳይ ለማስፈፀምና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚያስችል ፈረንጆቹ ማወቃቸውን ነው።
    ዓይን ያወጣውና ለከቱን ያለፈው ዘረኝነት በዲፕሎማሲው ማህበረ ሰብና በግብረ ሰናይ ድርጅቶችም ግንዛቤ አግኝቱኣል። ዛሬ የጀርመን ኤንባሲ ግልፅ ያርገውና ያደባባይ ሚስጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አለም ዓቀፍ ድርጅቶች የሚለማመዱት የዕለት ከዕለት ጉዳይ ነው።
    ፈረንጆቹ ከመንግስት ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ከትግሬ በላይ አገልጋይ እንደማያገኙ ያውቀሉ።

    Reply

Leave a Reply to gud Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule