• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምርጫ ሲባል፣

June 9, 2015 08:17 am by Editor 1 Comment

ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ።

ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል ይሆናል፤ አንድ የሁለት ጓደኞች የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ፤ አንዱ ስሙ መሳይ ነው፤ ፊታውራሪ ነው፤ ሌላው ስሙ በፈቃዱ ነው፤ ሀኪም ነው፤ አንድ ቀን በፈቃዱ መሳይን ሲያገኘው በፊታውራሪነቱ ለማሾፍ ፊታውራሪ መሳይ አለ፤ መሳይን ጫን ብሎ፤ መሳይም ሲመልስ በዶክተርነቱ እያሾፈ ዶክተር በፈቃዱ ብሎ ዶክተርን ጫን ብሎ መለሰለት! የኛን ምርጫ-መሳይ ምን ብለን፣ እንዴት ብለን እናሹፍበት? ያውም ማሾፍ ከተፈቀደ! በባህላችን በጣም የተወደደ ምግብ አለ፤ ያንን ምግብ አቅርበው መሣሪያው ሲነፍጉ ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን መንሣት ይባላል፤ ንፉግነት ብቻ አይመስለኝም፤ ክፋትም አለበት፤ የደርግና የወያኔ ምርጫ-መሳዮች በአለማወቅና በንፉግነታቸው ይመሳሰላሉ፤ በክፋት ግን አይመሳሰሉም።

ደርግም ሆነ ወያኔ ከሌኒን ለመማር አልቻሉም እንጂ አስመስለዋል፤ ምርጫ-መሳዩንም ያገኙት ከዚያው ነው፤ ሌኒን ጉሮሮን ግጥም አድርጎ በብረት ሰንሰለት አስሮ ነጻ ነህ ይላል! መገንጠል ትችላለህ! ይላል፤ ወያኔም ሲሉ ሰምቶ መገንጠል-መሳይ ሕግ-መሳይ አወጣ!

ችግር ነው ጌትነት! ዱሮ ተረት ነበር፤ ዛሬ ግን በእውነት ሲቸግር እያየን ይመስለኛል፤ አንድ ሰው ራሱ ባፈራው ሀብትና በደረሰበት የጌትነት ደረጃ ችግር አይሰማውም፤ ሀብቱ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት እንደመጣ፣ ምን ያህል ልፋት እንዳስከተለ መገመት ይቻላል፤ በተዘረፈ ሀብት ጌትነት ሲመጣ ግን ችግርን አዝሎ ነው፤ አንድ ሰው አራት ሚልዮን ብር ወድቆ ቢያገኝ አራት መቶ ካሬ ሜትር መሬት ቢገዛበት አያስደንቅም፤ የገንዘብ አያያዝን ስለማያውቅና በስጋት ስለሚከሳ መሬቱ ላይ መቀመጥ አስተማማኝ መስሎ ይታየዋል፤ ከካስትሮ በፊት የነበረውን የኪዩባ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን የሚያውቅ በዛሬው ጊዜ በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነቱን ለመረዳት አያዳግትም፤ በኪዩባም ሆነ በኢትዮጵያ በተዘረፈ ሀብት ጌትነትን ያስፋፋው አሜሪካ ነው፤ ሕዝብ የሚደኸየውና የሚከብረው በጉልበትና በዝርፊያ ብቻ በሆነበት አገር ጊዜውን ጠብቆ ከሁለት አንዱን አርግዞ ይወልዳል፤ ወይ ዘራፊዎችን ሁሉ ዘርፎ ሙልጭ የሚያወጣቸው ጉልበተኛ ይመጣል፤ ወይ በሕጋዊ መንገድ ከዘራፊዎች እየገፈፈ ሀብትን ለሕዝብ የሚያደላድል ሕጋዊ ሥርዓት ይመሠረታል፤ ሁለቱንም በማስረገዝ ላይ ያሉት በግፍ ሀብታም የሚሆኑት ናቸው።

ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ምርጫ መሳይ አለ፤ ሕዝብ የሀብት ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ግን ትንሽ ያስቸግራል፤ በኮንዶሚንየም ለማስመሰል ቢሞከርም አልሆነም፤ ለሎሌዎች ሹሞችም አልተዳረሰም!

በምርጫ መሳዩ ማሸነፍ ቀላል ነው፤ እንዲያውም መቶ በመቶ ማሸነፍ ይቻላል፤ ችግሩ የሚመጣው ከዚያ በኋላ ነው፤ ደካሞች የፖሊቲካ ቡድኖችንና ደካማውን ሕዝብ ማሸነፍ እንደሚቻል ጉልበተኛው አስመስክሯል፤ ሌላው ቀርቶ “የኔ” የሚላቸውን ቡድኖችም አፈር ላይ ሊያስተኛቸው ይችላል፤ እንዲያውም አፈሩ ምቹ ፍራሽ ነው ብለው በደስታ እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው ይችላል፤ አሁን የጉልበተኛው መድረክ እየጠበበ መጣ፤ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ የጠበበው መድረክ ውስጥ ባሉት ጉልበተኞችና ጉልበተኛ መሳዮች ነው፤ በአንድ በኩል በጉልበተኞች መሀከል፣ በሌላ በኩል በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፤ በሌላ በኩል በጉልበተኞችና በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፣ ይህ ትግል ደካማዎች የፖሊቲካ ቡድኖችን እንደማሸነፍ ቀላል አይደለም፤ በአጥር ላይ እየተንጠለጠሉ የጣሉትን ለመልቀም እየተሻሙ ነው፤ በጉልበተኞቹ መሀከል ክፉ የሥልጣን ችጋር ገብቷል ማለት ነው፤ ጦር መማዘዝ ኪስን እንደሚያራቁት ያውቃሉ፤ ያለሥልጣን ኪስ ሙሉ እንደማይሆንም ያውቃሉ፤ ታዲያ ምን ይሻላል?

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ዓለሙ says

    June 12, 2015 11:52 pm at 11:52 pm

    ፕሮፌሰር ጉዳዩን በትክክል አስቀምጠውታል፤ ለእርስዎም ዕድሜውንና ጤናውን ይስጥዎት፣ እኛንም ያቆየንና ወያኔን ኮቴ በኮቴ እየተከታተሉ ገና ብዙ ይነግሩናል፣ “አባት የልጆቹን ሥራ አያጣው” እንዲሉ። “ቁጭ ብለው የሰቀሉት፣ አቤት! ሲቸግር ተቁሞ እንኳን ሊያወርዱት።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule