• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ሲተረጎም

January 28, 2018 08:57 am by Editor 2 Comments

ኦቦ ለማ መገርሳ ህወሃት ያጎራቸውን 2,345 እስረኞች ነጻ አወጡ የሚለውን ዜና በቀኝ እየሰማን፣ የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ደግሞ በግራ በኩል ብቅ አለ። ሰበር ጋዜጣዊ መግለጫ። በርግጥም “ወገብ የሚሰብር”። ልዩ መግለጫው ተከባብዶ ሲነገረን “ገዱ ደግሞ ስንት ሺህ አማሮችን ከእስር አስለቀቀ” እያልን በጉጉት ባንጠብቅም “የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሕዝቦች ሆይ በወልድያ እና በቆቦ ለተፈጸመው እልቂት ተጠያቂው እኔ የምመራው ብአዴን ነው” ብሎ አረፈው።

ይህቺ ሃላፊነት የመውሰድ ዲስኩር ደግሞ አዲስዋ ቅኝት መሆነዋ ነው። ለትርጓሜዋ ቱርጁማን የማያሻት ቅኝት። ማራቶን ያሉት የአራቱ ድርጅቶች ስብሰባ እንዳበቃ አይቴ ደብረጽዮን ገብረ-ሚካኤልም ረገጥ ዓድርጎ ብሏታል። የናቴ  ቀሚስ አድናቅፎኝ … ምናምን የምንለው ነገር የለም። ለጠፋው ጥፋት ሁሉ ሃላፊነቱን ወስደናል። ብሎ ተነግሯል። ይህንን የተናገረው በህልም ሳይሆን በውን ነበር። በአለም መገናኛ ስንሰማ ያደግነው፤ ሰላማዊ ዜጋ ላይ እንዲህ አይነት አደጋ ሲደርስ ሃላፊነት የሚወስዱት እነ ሙጃህዲን፣ እነ አልቃይዳ እነ አይሲስን ነበሩ።

ደብረጽዮን በኢቢሲ ቀርቦ ለእልቂቱ እና ለውድመቱ ተጠያቂዎቹ “እኛ ነን” ብሎናል። የጥልቅ ተሃድሶው ጥልቅ ድፍረት! ንቀትም ነው። ታድያ የፍትህ ስርዓቱን እነ ዳኛ ዘርዓይ ባይይዙት ኖሮ፣ ለጥፋቱ ተጠያቂ መሆናቸውን ያመኑት ሁሉ ማእከላዊ (ሙዝየም) ገብተው በሕዝብ ይጎበኙ አልነበር?

ገዱ አንዳርጋቸውስ ይህን ለማለት ምን ያንሰዋል? ቅርቃር እንደገባች አይጥ እየተቁለጨለጨ ሃላፊነቱን እወስዳለሁ ብሎ ሲናገር ሰማነው። በእርግጥ  የደብረጽዮን እና የገዱ አገላለጽ የተለያዩ ናቸው። የደብረጽዮን “ገድለናል። ምን አባክ ታመጣለህ” አይነት ቅኝት ያለ የተረገጠ አነጋገር ሲሆን ገዱ ግን እየረገጠ ሳይሆን እየተረገጠ የሚናገር ነው የሚመስለው። ከካሜራ ጀርባ ወይ ላውንቸር፣ አልያም የስኳር ደብተር ያለመኖሩንስ ማን አየ?

ቴሌቭዝኑ ላይ ወጥቶ እንዲህ አይነት አስገራሚ መግለጫ የሚሰጠው “ገዱ ነው ወይንስ ደብረጽዮን?” ብሎ ያልተጠራጠረ  ቢኖር፣ የፍራንስ ፋነንን “black skin white mask” የሚል መጽሃፍ ያነበበ ብቻ ነው። ሃብትና ንብረቱን፣  አለፍ ሲል ደግሞ አካሉን እና አእምሮውን የተሰለበ ሰው ስነ-ልቦና።

ይህ የመግለጫ ገቢር፣ ገዱ አንዳርጋቸው ከ”በላይ” አካል ተጽፎ የተሰጠውን ይህን መግለጫ ለማንበብ ሲጨናነቅ በግልጽ ያሳየናል። ወረቀቱ ሲዝረከረክበት የሚያሳየውን ቦታ እንኳን ሳያርሙ ነው የለቀቁት። ምንም ያህል ስኳር ቢልስ፣ ምንም ያህል ያልተከፈለ እዳ ቢኖርበት፣ ሰውዬው በዚህ ደረጃ ይጃጃላል ብሎ ማሰብ ግን ይከብዳል። ለእልቂቱ ሃላፊነቱን ይውሰድ፣ ግን ጽላት ላይ በድፍረት የማስተኮስ ሃላፊነትን መውሰድ ከጤነኛ ሰው ይጠበቃል?

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለሰራተኞቹ በለቀቀው የውስጥ መልእክት ግድያውን “የትግራይ ወታደሮች” መፈጸማቸውን በግልጽ አስቀምጦታል። የወልድያው እልቂት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መወገዙ ሰዎቹን ብርክ አንዳስያዛቸው ቢታወቅም፣ ይህንን “የኒዮ ሊብራሎች ሴራ” ለማፍረስ፣  ገዱ አንዳርጋቸው ለመስዋእትነት እንደቀረበ ከብት በአደባባይ ወጥቶ ሂሱን ውጧል። ገዱ ያለ ሃጥያቱ የወንጀለኞቹን መስቀል ለመሸከም የመፍቀዱ ምስጢር ግን ግልጽ አይደለም። አንዱ የበላውን ሌላው እንዴት ይውጠዋል?

እኚህ ሰው ልብ ገዝተው ከህወሃት ሰዎች ጋር እኩል መናገር ሲጀምሩ፣ “ወፌ ቆመች…” ብለን ሳንጨርሳት፣ ይኸው ደግሞ ሃሞት እንደሌለው ሰው ሲልፈስፈሱ አየን።

ደብረጽዮን፣ “ሁሉንም ሳይሆን ትምክህተኛውን አማራ፣ ሁሉንም ሳይሆን ጠባቡን ኦሮሞ እየነጠልን መምታት ነው ያለብን!” ብሎ በትግርኛ ትዕዛዝ ካስተላለፈ ወር አልሞላውም።

ከዚህ ቀደምም በአማራው ላይ ጦርነት ሲያውጅ እንዲህ ነበር ያለው “… መከላለያ ሃይላችን እንኳንስ ለ30 ሚሊዮን (የአማራ) ሕዝብ አይደለም፤ መላው አፍሪካን ለመደምሰስ አቅም እንዳለው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያረጋገጡት ሃቅ ነው። … የመከላከያ ኃይላችን በሙሉ ትጥቅ በመሆን ብጥብጡ ወደከፋባቸው አካባቢዎች በመሄድ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንዲወስድ በጠቅላይ ሚኒስትራችን ታዟል።”

አካባቢው የተጠራቀሙ ችግሮች አሉ ተብለናል። ችግሩን ለመፍታትም ልማታዊው መንግስት ብዙ ይሰራልም ብለዋል። “ይሰራል” የሚለውን  ቃል የተናገሩት ተሳስተው ካልሆነ በቀር ከደብረጽዮኑ ድንፋታ ጋር የሚጋጭ ነው። እናም ድርጅታቸው ብዙ ይሰራል የሚለው ቃል ብዙ “ይገድላል”  ነው የሚሆነው። ለችግሮች እና ለጥያቄዎች ሁሉ መፍትሄያቸው አፈሙዝ ስለሆነ!

ገዱ ሃላፊነቱን ወሰደም አልወሰደ፣ በነባራዊው እውነታ ላይ  የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ያልበላውን ማከኩ ግን ራሱን ምን ያህል ለህወሃት ተገዥ እንዳደረገ ያሳየናል። በወሎ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂው ማን እንደሆነ ወንዙ ላይ ስንደርስ እናወራዋለን። የመከላከያ ሚኒስትሩን የሚመራው ሲራጅ ፈርጌሳ እና አዛዥ ነኝ የሚለው ሃይለማርያም ደሳለኝም ቢሆኑ በዚያን ግዜ “ግድያውን እኛ አላስፈጸምንም። በቦታው እንደ አሻንጉሊት ነው የተቀመጥነው… እትት እትት” ቢሉ ማንም አይሰማቸውም። የኑረንበርጉን ችሎት ያስተውሏል!

ግን አንድ ነገር ልብ እንበል። ወያኔ ፊቱን ወደ ወሎ ሲያዞር የተሳሳተ ቁልፍ ነው የነካው። ሰላም ባስ ዛሬ ከአዲስ አበባ በአፋር ዞራ ትግራይ ትገባ ይሆናል። ነገ ደግሞ በሱዳን…

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: eprdf, Left Column, tplf, Woldiya Massacre

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    January 29, 2018 03:13 pm at 3:13 pm

    መቼም ሰዎች!! ወፍ ስትጮህ ንጋትን ታበስራለች ይባል ነብር። ሌሊት ማለቴ ነው!!! የቁራ ጩኸት ግን ግራ እያጋባን ወፍ ትሆን?? ኧረ ሌቱ ነጋ እያልን ነው!!!ቂቂቂቂቂቂ!!!!!!

    Reply
  2. በለው ! says

    January 31, 2018 12:16 pm at 12:16 pm

    * ህወሓት/ኢህአዴግ ተሰብስበው ለጦመሩም ይሁን፡ ለዘመሩ፡ ወይም ድማፃቸውን ላሰሙ ‘ተመጣጣኝ እርምጃው’ ግንባርና ደረቱን በአልሞ ተኳሽ ማስበርቀስ ነው።ድሮስ የተናቀ ሠፈር..!የመጀመሪያ ሞታችን ወደብ አልባ እንደከብት ስንከለል።
    *የአማራና ኦሮሞ ወጣት ወንድምና እህቱ ከጎኑ እንደቅጠል ሲረግፍ የሚሰጠው ተመጣጣኝ እርምጃ …የካድሬና የክልል(ባንዳ) ተላላኪ ጣራ በድንጋይ ደበደቡ ነው። ቢያንስ ድሃ ተቀጠሮ የሚሰራበትን አቃጥሎ ዓመድ ከመታቀፍ፡ በሕገወጥ የሚዘዋወር የሙሰኛና ልዩ ተጠቃሚ ንብረትን ወርሰው ለድሃ አከፋፈሉ የሚለው እጅጉን ይመረጣል!።
    የሁለት ታዛዦች ወግ….
    *የአማሮች ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው በወሎ ከፍለ ሀገር ወልዲያ ከተማ “የተፈፀመው ጥፋት ነው” “ከሕዝብ ጋር ተወያይተናል፣ ችግሮችን በየደረጃው እንፈታለን” የጭፍጨፋው ምክንያት ባሻገር ሕዝብ በርካታ ችግር እንዳለበት፣ እሱም በየደረጃው መፈታት እንደሚገባው ገልፀዋል።”
    * የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አማረ ጎሹ “ያጠፋነው አጥፊዎችን ነው፣ አሁንም እናጠፋቸዋለን” “ጦር እየተጨመረልን ነው፣ አሁንም እንገድላቸዋለን” አይነት መግለጫ ይሰጣል። የችግሩ ምንጭ የፖለቲካ አላማ ያላቸው አካላት ናቸው። መፍትሄው “መደምሰስ” ነው።
    *******************
    “ወልዲያ ውስጥ የተፈጠረው የከተማዪቱን ማኅበራዊ ስብጥርና ግንኙነቶች የማያንፀባርቅ አሣዛኝ ሁኔታ መሆኑን በሰሞኑ ግርግር የንግድ ተቋማቸውና መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደሙባቸው በጓደኛቸው ልጅ ሞት ያዘኑት “ከእኔ ንብረት የሰው ሕይወት ይበለጣል” የኃይላይ ሕንፃ ባለቤት አቶ ኃይላይ ንጉሴ።
    __________________________________________
    ”ተገዳይ ወንድሜ ገብረመስቀል ጌታቸው እንዳይተርፍ ነው ፭ ጊዜ በጥይት የመቱት” ሲል በምሬት ይናገራል። ኪዳኔ ዕለቱን ሲያስታውስ ”ግርግር እንደተነሳ ደጋግሜ ስልክ ደወልኩለት አያነሳም። ብጠብቀውም መልሶ አይደውልም። በጣም ስለተጨነኩኝ ወደ ሆስፒታል ልፈልገው ሄድኩኝ፡ አንገቱ ላይ፣ ደረቱ ላይ፣ ሆዱ ላይ እና ብልቱ ላይ አምስት ጊዜ በጥይት የተመታ እና በደም የተሸፈነውን የወንድሜን አስከሬን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁ”ኪዳኔ ጌታቸው
    —————————————————
    “የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሕዝቦች ሆይ(!?) በወልድያ እና በቆቦ ለተፈጸመው እልቂት ተጠያቂው እኔ የምመራው ብአዴን ነው” ብሎ አረፈው።”ገዱ አንድ አድርጋቸው
    ** በመጀመሪያ መታሰር ያለበት የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አማረ ጎሹ ነው::
    (፩) የወጣቱን ነባር ችግሮች እያወቀ ለክልሉ መስተዳድር ጉዳዩን አቀርቦ አልፈታም።
    (፪) ደንገተኛና አነስተኛ የችግር አፈታት እና ማረጋጋት ብቃት የለውም።
    (፫)ችግሮችን በማባባስ ወጣቱ እንዲበረግግ መሳሪያ የታጠቀ ወታደር አሰማርቷል።
    (፬) ልዩ ኅይል በማያስፈልግበት ሁኔታ የፌደራል ጦር ጠርቶ ሰው እንዲሞት ፈቅዷል።
    (፭)ሕዝቡ ችግር አልነበረም እያለ የሰው ሕይወት እንዲቀጠፍ መመሪያ ሰጥቷል።
    (፮) ለዘመናት የሚከበር ዓመታዊ የጥምቀት ክብረበዓል በውጭ ሀገራት በተሽከርካሪ ሞተር የፖሊስ አጃቢ የሚፈቀድለትን ታቦት አዋርዶ በአስለቃሽ ጭስ እንዲረከስ፡አድርጓል።
    (፯) ከሙሰኛ፡ አድርባይ፡ አወርቶአደር፡ ጓዶቹ ጋር በመመሳጠር የሌሎችን መብትና ልዩ ጥቅም ለማስከበር፡የተመደበበትን ሥራ የቆመለትን የአማራ ሕዝብ ማንነትና ክብር አስደፍሯል፡ የአማራን ደም በከንቱ እንዲፈስ አስደርጓል። ይቀጣል! ይወገዳል!
    ስለዚህ አንድአርጋቸው ይህንን አርሞ ካልተገኘ ‘በትናቸው’ ነው ማለት ይቻላል።አራት ነጥብ።

    Reply

Leave a Reply to በለው ! Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule