• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ከኢትዮጵያ ስለመጣችሁ ታሰራችሁ”

December 17, 2012 09:02 am by Editor 1 Comment

አገር ቤት ያሉትን ወገኖች ለጊዜው መታደግ ካልተቻለ ቢያንስ ከማንም ተጽዕኖ ወጪ በስደት የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያኖች ለመርዳት ለሚቀርብ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ የሚያሳዝን እንደሆነ አቶ ሳሙኤል አለባቸው በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር ሊቀመንበር ገለጹ። አቶ ኦባንግ ሜቶን ማህበሩ በተለይ መጋበዙን አስታወቁ።

ከሚያሳዝን መከራ ተርፈው እስራኤል ከደረሱ በኋላ እስር ቤት እንዲቆዩ የተደረጉት ታዳጊዎች መፈታታቸውን አስመልክቶ መግለጫ ያሰራጩት አቶ ሳሙኤል በተለይ ለጎልጉል እንደተናገሩት “በተለያዩ አገራት መከራ እየተቀበሉ ያሉትን ወገኖች መታደግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሰው፣ በተግባር ግን ይህንን ማየት” እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

አቶ ሳሙኤል አለባቸው

በእስራኤል እየደረሰ ያለውን የወገኖች ስቃይ አስመልክቶ ለቀረበ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ግንባር ቀደም እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሳሙኤል “በየአገሩ የተበተኑ ወገኖች እንደሚሉት በእስራኤል ያሉ ኢትዮጵያዊያን በአቶ ኦባንግና በድርጅታቸው አኢጋን ላይ ታላቅ እምነት አላቸው” ብለዋል።

“አቶ ኦባንግን ብቻ ሳይሆን አብረዋቸው ለሚሰሩት ሁሉ ልዩ ክብርና ፍቅር እንዳለን የምንገልጸው ዝም ብለን አይደለም” ያሉት አቶ ሳሙኤል “በጠላት ላይ ትኩረት አድርጎ በህብረት ከመስራት ይልቅ እርስ በርስ በመጠላለፍና ባለመተማመን በሚፈጥሩት ውዝግብ ጊዜያቸውን ከሚያባክኑት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይልቅ ኦባንግ የሚመሩት ድርጅት ውጤታማ ስራ ሲሰራ ይስተዋላል። ይህ እውነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ በገሃድ የሚታወቅ ነው…” ሲሉ ተናግረዋል። ከህዝብ በቀረበ ጥያቄ አቶ ኦባንግ እስራኤል እንዲገኙ ጥሪ ማቅረባቸውንም አስታውቀዋል። ያስመዘገቡት ስኬት፣ የህይወት ተሞክሯቸውና ትምህርት ሰጪው ልምዳቸው፣ እንዲሁም የሚመሩት ድርጅት የገነባው ስም ለግብዣው ዋና ምክንያት መሆኑን አስታውቀዋል።

ለአንድ አገር ወዳድ የዜጎቹን ህይወት ከመታደግ በላይ ታላቅ ክብር የሚያሰጠው ጉዳይ እንደሌለ ያመለከቱት አቶ ሳሙኤል አድማሱ፣ “በህዝብ መወደድ እንዲሁ የሚገኝ ቀላልና ተራ ጉዳይ አይደለም። ቀናነትና መልካምነት እያደር በሁሉም ዜጎች ልብ ውስጥ የሚነደው በቀስታ ነው። ቀስ ብሎ የሚገነባ ክብር በቀላሉ አይናድም። ይህን የመሰለው ፍቅርና ክብር አቶ ኦባንግ ለሚመሩት ድርጅት አለን። ከተደረገው ነገር አንጻር ብዙ መናገር ቢገባኝም ለጊዜው ከዚህ በላይ የምለው የለም” ብለዋል፡፡

በተቃራኒው “አምላክ ይማርህ/ሽ የማይባልለት በሽታ ይዞናል። ብዙ ስራ አለብን። ብዙ ጉዳዮች ከፊታችን ተቀምጠዋል። አላማችን ኢትዮጵያ ናት ግን አንስማማም። ከመከራ፣ከግድያ፣ ከእስር፣ ልንማር አልቻልንም። ኢትዮጵያን ፊትለፊት በማሳየት ውስጥ ውስጡን ለግል ጥቅም የምንሰራ አለን። እንዲህ ያለው ድርጊት ሊያበቃ ይገባዋል” ብለዋል።

በእስር ላይ የነበሩት ታዳጊዎች ዛሬ ተፈተው ወደ ተለመደው የህይወት እንቅስቃሴ እንዲዛወሩ ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል የተሳካ ስራ ለመስራቱ ታዳጊዎቹን በመጎብኘትና በማነጋገር ያሰራጨው በምስል የተደገፈ ምስክርነት ያረጋግጣል። (ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት እዚህ ላይ ይገኛል) አሁን ትልቁ ጥያቄ እስር ላይ ያሉትን ተጨማሪ ከ300 በላይ ሰዎች ከእስር የማስለቀቁ ተግባር ነው። እነዚህ ወገኖች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከትና ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር አቶ ኦባንግ ሜቶ ወደ ስፍራው የማምራት እቅድ አላቸው። ማረጋገጫ እንዲሰጡ ለተጠየቁት “ስንቋቋም ለወገን ነው።የምንሰራውም ለወገኖቻችን ነው። በተደረገው ተደስተናል። ለወደፊቱም የምንችለውን እናደርጋለን። አሁንም ውጤቱን መግለጽ ባልችልም ስራዎች እየተሰሩ ነው። እስራኤል ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቦታዎች” የሚል መልስ ሰጥተዋል። በእስራኤል ከ2500 እስከ 3000 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ባልተሟላ የስደት ህይወት እንደሚገፉ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ሳሙኤል የሚመሩት ማህበር ይፋ ያደረገው በምስል የተደገፈ ቃለ ምልልስ በታዳጊዎቹ ውጫዊ አካል ላይ የደረሰ ጉዳት የሚታይበት ባይሆንም፤ ስራ እናስገባችኋለን በሚል አፍነው እንዴት እንደወሰዷቸውና ሲና በረሃ አስኪገቡ የደረሰባቸውን መከራ፣ ከዚያም በሲና በረሃ ቆይታቸው፣ እኒህ ህጻናት ይፋ ያላደረጉት ምን ደርሶባቸው ይሆን የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

ቀደም ሲል ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ስለ ሲና በረሃ ባወጣው ዘገባ የአካል ክፍልን መሰረቅ፣ መደፈር፣ መሰቃትና ጉሮሮ ለማርጠብ እንኳን አረብኛ አለመናገራቸው ወገኖቻችንን እንዴት እንደሚጎዳቸው ጠቅሰን ነበር። በተመሳሳይ አሁን በተለቀቀው የቪዲዮ መረጃ “የታሰራችሁት ከኢትዮጵያ ስለመጣችሁ ነው” በማለት የእስራኤል ፖሊስ እንደገለጸላቸው የምትናገረዋ ታዳጊና ሌላዋ ጓደኛዋ የሚናገሩትን በጉልጉል ቲዩብ ይመልከቱ። ያቺ ስሟን የሰማናትና አካላዊ ግፍ የተፈጸመባት ታዳጊና ሌሎች ተበዳዮች ወደፊት ሰፊ ዘገባ ለማቅረብ እንሞክራለን።

የኢትዮጵያን እናድን በእስራኤል ማህበር ሊቀ መንበር አቶ ሳሙኤል አድማሱ በማህበሩ ስም ያሰራጩትና ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ በአድራሻ የላኩት ደብዳቤ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል።

ቀን 14/12/2012

የማያባራው የኢትዮጵያውያን ፈተና

ፍትህ ሰላም ዴሞክራሲ ስርአት የራቃት አገራችን ለብሔራዊ ዳር ድንበሯ መከበርና ለዜጎቿ የመኖር ዋስትና የሚሰጥ ወይም የሚታደግ መንግስት በማጣታችን የተነሳ በየጊዜው የሚገጥመን ሰቆቃ ማባሪያ አጥቶ ከዛሬው እለት ላይ ደርሰናል።

ይህ ዘገባ የሚያጠነጥነው ከጎንደር ክፍለ አገር በደላሎች አሳሳችነት ከደባርቅ፣ ከማክሰኝት፣ 50 ፍጭ እና አጅሬ ከተባሉ አካባቢዎች ወደ መተማ በመወሰድ ከመተማም ስራ እንሰጣችኋለን በሚሉ ግለሰቦች አማካኝነት እድሜያቸው ከ14 እስከ 16 የሆኑ ታዳጊዎችን በበረሃ ውስጥ ባዘጋጁት የመጠለያ ስፍራ ቀደም ሲል በተለያየ ጊዜ ያሰባሰቧቸውን 14 ወንዶችንና 46 ሴቶች ከሚገኙበት ቦታ በመውሰድ በጠቅላላው 60 ታጋቾችን ወደ ሲናይ በርሃ በማስተላለፍ “እስራኤል እንልካችኋለን ሰርታችሁ ገንዘብ ታገኛላችሁ” በማለትና ከዚያ በፊት ኢትዮጵያ ያሉ ቤተሰቦቻችሁን ስልክ ቁጥር አምጡ በማለት ወደ ኢትዮጵያ ስልክ በመደወል በእያንዳንዳቸው 60,000 /ስልሳ ሺህ የኢትዮጵያ ብር/ እስካልተከፈለ ድረስ እንደሚገሉን የሚያመለክት የማስገደጃ ትእዛዝ ለቤተሰቦቻችንን በመናገር የተጠየቀውን ገንዘብ ሊቀበሉ ችለዋል። ከዚያም የሲናን በረሃ በተሽከርካሪና በእግር በማቋረጥ ላይ እንዳለን ከመሐከላችን ከወሎ ክፍለ አገር ራያና ቆቦ ከሚባል ስፍራ የተሰደደች ሰሚራ ሲሳይ ወይም ቤተልሄም ሲሳይ እድሜዏ በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ወጣት መንገድ በሚመሩ ግለሰቦች በመደፈሯና በመደብደቧ የደረሰባት በደል ፅኑ ስለነበር ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል። እኛም በእድሜያችን ልጆች በመሆናችንና አካባቢው ላይ ስርአተ ቀብሯን ለመፈፀም አቅም በማጣታችን ከሜዳ ላይ ጥለናት ልንሄድ ሲሉ ቃላቸውን ከመስጠታቸውም ባሻገር እነሱ ራሳቸውን በረሃ ላይ ታግተው ከቆዩባቸው ቀናትና በጉዞው ላይ ባሳለፉት 14 ቀናት ውስጥ ከመደብደባቸውም ባሻገር በቂ ምግብ የተነፈጉና ለመጠጥ ውሃ በሚጠይቁበት ጊዜ ከቤንዚን ወይም ከናፍጣ ጋር የተቀላቀለበት ስለነበር በጤናቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር ገጥሟቸው ስለነበር ልንጠይቃቸው በሄድንበት ሰአት ገልፀውልናል።

እነዚህ በእድሜአቸው እጅግ በጣም አነስተኛ የሆኑ ታዳጊዎች ከአገራቸው የኑሮ ዋስትና በማጣታቸው በእግዚአብሔር ቸርነትና ከቤተሰቦቻቸው በተከፈለ 60000 ብር በሲናይ በረሀ ከሚፈፀም የተለያየ ወንጀሎች ተርፈው ወደ እስራኤል ብሔራዊ ድንበር በተሻገሩበት ወቅት በእስራኤል የጠረፍ ጠባቂ ፖሊሶች ተይዘው ለ1 ወር ከታሰሩ በኋላ በአገሪቱ መሀል አገር በሚገኝ ራምሌ በሚባል እስር ቤት በተጨማሪ 7 ወራት በጠቅላላው 8 ወራት ከቆዩ በኋላ ከእስር ተለቀው የእስራኤል መንግስት ባዘጋጀላቸው አዳሪ ት/ቤት መደበኛ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ከአዳሪ ት/ቤት ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ሞግዚታቸው ወ/ሮ ምካኤል አነጋግረን የልጆቹ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከመሀከላቸው ያለምወርቅ ሲሳይ የኔነህ የምትባል ታዳጊ ያለባትን የጥርስ ህመም በተመለከተ ተገቢው ተከታታይ ህክምና እየተደረገላት እንደሚገኝ ከመግለፃቸውም ባሻገር ተማሪዎቹ ከእስር እንደተፈቱ ለእያንዳንዳቸው 500 የእስራኤል ሼቅል ተሰጥቷቸው እለታዊ አስፈላጊ ነገር የተሟሉላቸው ሲሆን በቋሚነት በየወሩ ለእያንዳንዳቸው 150 ሼቅል የኪስ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ገልውልን መደበኛ ትምህርታቸውን በተመለከተ በሳምንት 5 ቀናት ከጠዋቱ 8 ሰአት እስከ ቀኑ 1፡30 እንደሚከታተሉና በትምህርት ቤት ቆይታቸው እድሜአቸው 18 አመት እስከሚሞላ መሆኑን ገልፀውልናል። ከ18 አመት በኋላ የታዳጊዎቹ እጣ ፋንታ ምን እደሚሆን አላወቅንም።

የእስራኤል መንግስት የእነዚህን ታዳጊዎች ህይወት በመታደግ ረገድ ላደረገው መልካም ትብብር በታዳጊዎቹ ስም ምስጋናችንን እያቀረብን እስራኤል አገር ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን በተመለከተ በመላው አለም ለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ለችግራች የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡን ጥሪ አቅርበንላቸው ምላሽ ለሰጡን የድህረ ገፅ ባለቤቶች ምሥጋናችንን እያቀረብን በተለይ ለእስራኤል መንግስትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የተለያዩ ክፍሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የመብት ጥሰት በመግለፅ ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎችን ከእስር ነፃ እንዲያደርጋቸው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግርና ም/ቤትና ከአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ለተፃፉ ደብዳቤዎችና ሁለገብ ድጋፎች በኢትዮጵያ አንድነት ማህበር ስም ምጋናችን ለማቅረብ እንወዳለን።

እነዚህን ታዳጊዎችና አሁን በእስር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ በመላው አለም የምትገኙ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎች የሲቪክ ማህበራት የሀይማኖት መሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለእስራኤል መንግስት በማሳዋቅ ረገድ የበኩላችሁን እገዛ ታደርጉልን ዘንድ በታሳሪዎቹ ከእስር ከተፈቱትና ቧልተሟላ የስደተኛ መብት በሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስም የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ የኢትዮጵያ አንድነት ማህበር በእስራኤል ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ከእስር ከተፈቱት መሐከል

ተቁ ስም እድሜ የመጣችበት ክ/ሀገርና ልዩ ቦታ መግለጫ
1 ዘርፌ ጌዴ እንደሻው 14 ጎንደር /ደባርቅ/
2 ለቄ ደጀን መለሰ 15 ጎንደር /ደባርቅ/
3 ባንቺ ባዜ በላይ 15 ጎንደር /ማክሰኝት ወረዳ/ ልዩ ለፍሬው ባህር ግንብ
4 ወደር ገብሬ ጫኔ 16 ጎንደር /ባሪ ግንድ/
5 ገበያነሽ ተስፋ አማረ 14 ጎንደር /ማክሰኝት ወረዳ/ ልዩ ቦታ 50 ፍጭ
6 አለምወርቅ ሲሳይ የኔነህ 14 ጎንደር /አጅሬ/

ከዱሪም ከሚባል ስፍራ የእርሻና የወጣቶች መንደር ታዳጊዎቹን በአንድ አዳሪ ት/ቤት አግኝተን ተገቢውን መሰረታዊ ቁሳቁስ እርዳታ ልናደርግላቸው ችለናል። ቀሪዎቹ 4 ታዳጊዎች ማለትም

ተቁ ስም እድሜ የመጣችበት ክ/ሀገርና ልዩ ቦታ መግለጫ
1 ሸዋዬ ሹመት
2 ድንቄ መብራት
3 ወርቅዬ ማሞ
4 ስለእናት ጥላዬ

የተባሉት ከእስር የተለቀቁ ሲሆን የተመደቡበትን አዳሪ ት/ቤት አድራሻ በትክክል እንዳወቅን በተመሳሳይ መልኩ ተገቢውን የአልባሳት ስጦታና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ መጠቀሚያዎችን ለማዳረስ ቅድመ ዝግጅት ያደረግን ሲሆን በዚህ የእርዳታ ማሰባሰብ ስራ ላይ ከማህበሩ አባላት በተጨማሪ የእስራኤል የአካባቢ ም/ቤት አባላትና ሌሎች ግለሰቦችም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

በአጠቃላይ በረሀ ከነበሩት 60 ታጋቾች እስካሁን በህይወት ያገኘናቸው አስር ያህሉን ሲሆን የተቀሩት 50 ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

ከእስር የተፈቱት ታዳጊዎች የመደበኛ ትምህርት በተመለከተ ከ3ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል በአገር ቤት የተማሩ ሲሆን አንዷ ግን ምንም አይነት የትምህርት እድል እንዳላገኘች ለማወቅ ችለናል፡፡

የሁሉም አስተያየት ተመሳሳይ ሲሆን ስራ ፍለጋ እንደተሰደዱና የቤተሰቦቻቸው አቅም በሐብት ያልደረጁ በመሆናቸው ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ መሰደዳቸውን ገልፀዋል።

በአንፃሩም በበረሀና በእስር ቤት ያሳለፉትን ስቃይ በማሰብ ሌሎች ወገኖቻችን ስደትን የመፍትሔ አማራጭ አድርገው እንዳይወስዱ የበኩላቸውን አስተያየት በመስጠት የቆይታ ጊዜያችንን በዚህ መልክ ያጠናቀቅን ቢሆንም አሁንም የነዚህን ታዳጊዎች የወደፊት እድል በተመለከተ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊተባበራቸውና አቅሙ በፈቀደ ሁሉ ይረዳቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ከሰላምታ ጋር

ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ

የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ሊቀመንበር

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Fedlu says

    December 17, 2012 12:17 pm at 12:17 pm

    Ethiopiawi kibrun ata tesekayen…yesew fit gerefen min yishalal?wetatu bechatina beshisha denziual ke eskindirena keandualem yilek sile runey new miawkew ebakih yehagere wetat nika….nika….wegen tesedo 1tiwelid bado lihon new

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule