• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሕዝባዊ ተቃውሞው ኢኮኖሚውን እየጎዳው ነው!

August 27, 2016 04:51 am by Editor 1 Comment

በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰ መሆኑ ተሰማ፡፡ የአመጹ ሒደትና ብርታት ያሳሰበው ህወሃት ከመግደል በላይ እንዴት እንደሚያጠብቀው ባያሳውቅም “ጥብቅ እርምጃ” መውሰድ እንደሚጀምር ተናገሯል፡

ህወሃት ለማመን ባይፈልግም ለአስር ወራት የዘለቀው የኦሮሞ ተቃውሞ በክልሉ የንግድና ሌሎች ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ ከክልሉ ወደሌሎች የሚደረገው የንግድ፣ የዕቃ፣ የገበያ፣ የሰው ኃይል፣ የገንዘብ፣ … ዝውውር በተቃውሞው ምክንያት በርካታ መስተጓጎሎች ደርሰውበታል፡፡ ከዚህም አልፎ አገሪቱ ለውጭ ንግድ በምታቀርበው ምርትና በምትሰበስበው ግብር ላይ የሚያስከትለውን ጫና ከክልሉ ስፋት አኳያ እጅግ ሰፊ እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በአማራው ክልል የተነሳው ተቃውሞ ችግሩን በይበልጥ እያባባሰው እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተለይ የቤት ውስጥ አድማ በሚመታበት ጊዜ የዜጎች እንቅስቃሴ ይገታል፤ ንግድ ይቀዘቅዛል፣ በየዕለቱ ለመንግሥት የሚሰበሰበው ግብር (ቫት) ይቀንሳል፤ የንግድ ተቋማት ሽያጭና ትርፍ ይቀንሳል፤ በዚህ ምክንያት መንግሥት ከንግድ ተቋማት የሚሰበስበው የትርፍ ግብር ይቀንሳል፤ … እንዲህ እያለ ተጽዕኖው በራሱ እየተቀጣጠለ ሌሎች ችግሮችን በመውለድ ኢኮኖሚውን እስከ ማሽመድመድ ይደርሳል፡፡

bure4
ቡሬ ጎጃም

ነውጥ አልባ የትግል ስልት የሚከተለው የኦሮሞ ተቃውሞ በትግሉ መርኽ መሠረት ሰሞኑን በኢኮኖሚ ላይ ያነጣጠረ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይፋ አድርጓል፡፡ ጳጉሜን 1 ይጀመራል የተባለው እርምጃ በምን መልኩ እንደሚደረግ ዝርዝሩን እንደሚያሳውቁ አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በየትኛውም መልኩ ይደረግ የኢኮኖሚ ተቃውሞ ሥርዓትን በማሽመድመድ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር በኢኮኖሚ ላይ ያነጣጠረው የኦሮሞ ተቃውሞ የህወሃትን ኮሮጆ አደጋ ላይ እንደሚጥለው ካሁኑ እየተገመተ ነው፡፡ ተጽዕኖው ደግሞ በአንድና በሁለት ሳምንታት ብቻ የሚቋጭ ሳይሆን የበርካታ ጊዜያት ተደራራቢ ውጤት ማስከተሉ የማይቀር ሐቅ እንደሆነ በሌሎች አገራት የተካሄዱት ተቃውሞዎች ምስክር ናቸው፡፡

በሙስና እና በዝርፊያ ለ25 ዓመታት ብቃቱን ያዳበረው ህወሃት/ኢህአዴግ በውጭ ንግድ (ኤክስፖርት) ከሚያገኘው የውጭ ምንዛሪ ይልቅ ዳያስፖራው ከሚልከው ዶላር የሚያገኘው እንደሚበልጥ የራሱ የገንዘብ መ/ቤት ይመሰክራል፡፡ ከ2003 ዓም በኋላ ባሉት አምስት ዓመታት የውጪ ንግዱን በእጥፍ አሳድጋለሁ ብሎ ቃል የገባው ህወሃት/ኢህአዴግ አሁንም ያኔ ከነበረበት የ3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አለመነቃነቁን አዲስ አድማስ ዘግቧል፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን በዓመት ከዳያስፖራው የሚያገኘው የውጭ ምንዛሪ የዛሬ አራት ዓመት 2.5ቢሊዮን ዶላር የነበረው በአሁኑ ጊዜ በዓመት 4ቢሊዮን ዶላር መድረሱ አብሮ ተዘግቧል፡፡ ከዚህ አንጻር ቀጣዩ የኢኮኖሚ ተቃውሞ በዚህ ዙሪያ ያጠነጠነ ቢሆን የህወሃትን አከርካሪ በመምታትና ዕድሜውን ወደማሳጠር በቶሎ ይደረሳል በማለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡

እንደ አዲስ አድማስ ዘገባ ከሆነ ከአራት አመት በፊት፣ የኢትዮጵያ ጠቅላላ የውጭ እዳ ወደ 9 ቢሊዮን ገደማ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የዕዳው ክምችት 20.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ለዕዳ ክፍያ የውጭ ምንዛሬ የግድ አስፈላጊ በመሆኑ ዕቃ ከውጭ ለማስመጣት የሚሰጠውን የዱቤ ፍቃድ እንዲቀንስ በማድረግ ወይም ረጅም ጊዜ እንዲወስድ በማድረግ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ በኢኮኖሚው ላይ ያሳድራል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ የተጠራው ተቃውሞ ሰልፍ አገዛዙን ለከፍተኛ የገንዘብ ወጪ እንደዳረገው ተሰምቷል፡፡ ቁጥሩን ለማረጋገጥ ባይቻልም እስከ 30 እና 40ሺህ ፖሊስ፣ ወታደሮችንና የስለላ ሰዎችን ያሰማራው ህወሃት ለእነዚህ ሁሉ ከአምስት መቶ ብር ጀምሮ የውሎ አበል ከፍሏል፡፡ ይኽም እስከ 10ሚሊዮን ብር ለሚሆን ወጪ እንደዳረገው ስሌቱ ያሳያል፡፡ የአዲስ አበባው ሰልፍ በተለያዩ ምክንያቶች እንደታሰበው ባይሳካም atnafበሥርዓቱ ላይ ጉዳት ከማስከተል አንጻር ዓላማው ግቡን እንደመታ ይነገራል፡፡

ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል በሚል ፍርሃት ውስጥ የገባው ህወሃት አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የቁጥጥር ሸክም መጫኑ ነዋሪዎች ይመሰክራሉ፡፡ በአማራ ክልል የተነሣው ብረት አከል ተቃውሞ ወደ አዲስ አበባ ይዛመታል በሚል ፍርሃቻ ሆቴሎች ቁጥጥሩ ጠብቆባቸዋል፡፡ የዞን 9 ጦማሪ የሆነው አጥናፍ ብርሃኔ በትዊተር በለቀቀው መልዕክት “ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ መጥቶ የሚያርፍ እንግዳ ካለ በ24 ሰአት ውስጥ ለፖሊስ እንዲያሳውቁ ትእዛዝ ለየሆቴሎቹ ተላልፏል” በማለት ትላንት መልዕክት አስተላልፎ ነበር፡፡

በየማኅበራዊ ድረገጹ ላይ አፍቃሪ ህወሃቶች አሠራሩ በቀድሞ አገዛዞችም ሲሠራበት የኖረና የተለመደ ነው ብለው ለማስተባበል ቢፈልጉም ሁኔታው ግን ከዚያ የተለየ ነው፡፡ በእርግጥ ሆቴሎች እንግዶቻቸውን ለፖሊስ ማሳወቅ የተለመደ አሠራር ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች  የአሁኑ ትዕዛዝ ግን ለየት ያለ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በአገር ውስጥ የሚያሰጋ ነገር ሲከሰት ህወሃት ተመሳሳይ ትዕዛዝ ሲያስተላልፍ መቆየቱን የሚናገሩ ወገኖች ከዚህ በፊት በኦነግ ሰዎች ላይ ተመሳሳይ ፍርሃቻ በነበረበት ጊዜ ትዕዛዙ መተላለፉን ያስታውሳሉ፡፡ ከዚያም በሶማሌ ክልል ተመሳሳይ አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት ከክልሉ የሚመጡ ተስተናጋጆችን ወዲያውኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ መታዘዙን የሆቴል ባለቤቶች ይናገራሉ፡፡ ያሁኑ ደግሞ ከአማራው ክልል በሚመጡ ላይ መደረጉ በክልሉ የተነሳው ተቃውሞ በህወሃት ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ ያሳያል፡፡

ethflagበተያያዘ ዜና ለዘመናት የኦሮሞንና የአማራን ወገኖች በመከፋፈል እርስበርስ እንዲናቆሩ በሰፊው የሰራው ህወሃት የሁለቱ ጥምረት ኅልውናውን አደጋ ላይ መጣሉን የራሱ ሰዎች መናገራቸውን ባለፈው ጎልጉል ዘግቦ ነበር፡፡ እነ አባይ ጸሃዬ ወደ አሜሪካ መጥተው ጥምረቱ ስጋት እንደሆነባቸው ለጌቶቻቸው አስረድተዋል፡፡ አሁንም ይህ ጥምረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በሚደረጉት ሰልፎች እና በየማኅበራዊ ድረገጾች ላይ በሚጻፉት እየተንጸባረቀ ነው፡፡

በኦሮሚያ ከህጻናት እስከ አዛውንት በደም ኩሬ ሲጠምቅ የነበረው ህወሃት ሰሞኑን እየከረረ የመጣውን ተቃውሞ ለማክሸፍ “ጥብቅ እርምጃ” እወስዳለሁ ብሏል፡፡ ሲገድል፣ ሲረሽን፣ ሲያስር፣ ሲያሰቃይ፣ … ወዘተ የቆየው ህወሃት አሁን ከዚህ የተለየ ምን “ጥብቅ እርምጃ” እንደሚወስድ ግልጽ አላደረገም፡፡ ስቃይና ሞት በተለያየ መልኩ ሲፈጸምበት የኖረ ሕዝብ ከዚህ በላይ ምንም እንደማይመጣበት በማወቅ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከአስተባባሪዎችና ከአገር ቤት ከሚሰሙት ድምጾች ለመረዳት ይቻላል፡፡

በመለስ ሞት ፊታቸውን ያዞሩት ምዕራባውያኑ የህወሃት አንጋሾች ይህንን የህወሃት አካሄድ ካለመደገፍ ጀምሮ እስከ ጀርባ መስጠት እያደረሳቸው መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. NW_Group Agency says

    August 29, 2016 04:45 pm at 4:45 pm

    የዚህ ኔት ወርክ አላማ፡

    ህወሓት/ኢህአዴግ የወቅቱን የሀገራችንን የፖለቲካ አለመረጋጋትን ተከትሎ የፖለቲካ ራስ እንደሆነ ለማስቀጠል በመንግስት መ/ቤቶች ጠንካራ መሰረቱን ለመጣል በመንግስት መ/ቤቶች በተለይም ተላላቅ ተቋሞችን እንደ ትራንስፖርት መ/ቤቶች፣ በኢትዮዽያ አየር መንገድና አ/አ ቀላል ባቡር ኮርፖሪሽን ለመቆጣጠር እንዲያስችለው ባወጣው ዕቅድና ስትራተጂ መሰረት በመዋቅር ለውጥ ሰበብ የህወሓት አባላቶችን በፖለቲካ ታማኝነታቸው ብቻ ታሳቢ በማድረግ ያለ በቂ ችሎታ የአመራሩን ቦታ እንዲይዙ በማድረግ በተለይ የህወሓት ደጋፊ ባልሆኑት ላይ ኃላፊነት እንዳይኖራቸው በማድረግ በንፁህ ዜጎች ላይ የሚደረግባቸው ግፍና በደልን በማጋለጥ ለህብረተሰቡ በማቅረብ የህወሓት ባለስልጣኖችን በጋር ለመዋጋት በተወሰኑ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡

    ውድ አንባቢዎች በዘህ አይነት በደል ያደረሱትን መ/ቤቶችን ለህብረተሰቡ ለማጋለጥ እንዲያስችለን በአድራሻችን ፃፉልን፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule