• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?

October 28, 2013 07:12 am by Editor 1 Comment

በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት “ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።

ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።

አንጋፋ እድሜ ጠገብና ረዣዥም የተፈጥሮ ደን በመጨፍጨፍ ጣውላ እያመረተ ሲቸበችብ የነበረው ኩባንያ ሙሉ ንብረቱና ከፍተኛ መጠን ያለው የጣውላ ምርት ከተለያዩ ማሽኖች ጋር ወድሞበታል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኩባንያው ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለመሰብሰብ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ማሳ አጋይቶታል።

በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን፣ በጎደሬ ወረዳ በጉማሬና በካቦ ቀበሌዎች የሚገኝ 5000 ሄክታር በደን የተሸፈነ መሬት በኢንቨስትመንት ስም እንዲሸጥ መወሰኑን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን “በባዕድ ወራሪ ሃይል እንኳን የማይፈጸም” በማለት የተቹና ቅሬታቸውን የገለጹ ነበሩ።

ሙሉ በሙሉ በደን የተሸፈነ 3012 ሄክታር ድንግል ለም መሬት በሄክታር111 ብር ሂሳብ ለ50 ዓመት የሊዝ ኮንትራት የተሸጠለት ይህ ኩባንያ ጥብቅ ደኑን ከማውደሙ በፊት ውሳኔው እንዲጤን የአካባቢው ህዝብ በወኪሎቹ አማካይነት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጥያቄ አቀርበው ነበር። በወቅቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን በመቃወም የሚከተለውን ጽሁፍ አትሞ ነበር። ሰሚ ባለመገኘቱ የተፈራው ደረሰ።

ጡረተኛው ፕሬዚዳንት ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የተፈጥሮ ደኑ ከመጨፍጨፉ በፊት ውሳኔው እንዲመረመርና እንዲጠና ሚያዚያ 28 ቀን 2002 ዓ ም ለክልሉ ደብዳቤ ልኮ ነበር። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በወቅቱ የአፍሪካ የተፈጥሮ ጥበቃና የአየር ንብረት ተሟጋች ነኝ ያሉበት ወቅት መሆኑንን በማስታወስ፣ የፕሬዚዳንቱን መመሪያ በመጠቆም ባለስልጣኑ የጻፈውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የክልሉ ፕሬዚዳንት ህዳር 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ ደመሰሱት። ከላይ የተጠቀሰው ኩባንያ የ50 ዓመቱን ውል ቅድሚያ ክፍያ የአንድ ዓመት 19 ሺህ ዶላር ስለከፈለ ቦታውን እንዲረከብ ዞኑንን አዘዙ።

የበላይና የበታቹ በማይታወቅበት የመለስ አወቃቀር ጥብቅ ደኑ ያለበት መሬት ለህንዱ ኩባንያ ተላለፈ። ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ እስከ ፕሬዚዳንቱ ያደረሱት ሊቀመንበር እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ከሃላፊነታቸው ተባረሩ። ህዝብ የኑሮው መሰረትና የህይወቱ ያህል የሚንከባከበው ደን ተጨፈጨፈ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ደኑ ሲጨፈጨፍ የነበረው ሃዘን በቃል የሚገለጽ አልነበረም።timber log

ባገኘው ከፍተኛ የደን ምርት ጣውላ ማምረት የጀመረው ኩባንያ መጋዘን ገንብቶ የጣውላ ንግድ ውስጥ ገባ። አሁን ድረስ ንዴቱና የበደል ስሜቱ ያለቀቀቃቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የተካሄደባቸውን ግፍ “ዝርፊያ” እያሉ ነው የሚጠሩት።

ህግን ጠብቀው ኢህአዴግን ያሳሰቡት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በእስርና በድብደባ በማሰቃየት ኢንቨስትመንትን /ነዋሪዎቹ ዝርፊያ ነው የሚሉት/ በክልሉ ቀጣይ ማድረግ አይቻልም። አስቀድሞ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ኢህአዴግና ኩባንያው ጆሮ ሰጥተዋቸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለ አደጋ ሊፈጠር እንደማይችል አስተያየት ሰጡ አሉ።

92 ሚሊዮን ብር በላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እዳ ያለበት የእርሻ ድርጅት፣ ንብረቱ በእሳት ከወደመ በኋላ የተሸከመው እዳ አጀንዳ ሆኗል። የደረሰበት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉንና ኢህአዴግን ካሳ እንደሚጠይቅም ከወዲሁ ተሰምቷል። ዜናውን ያቀበሉ ክፍሎች “ህዝብ ላልተቀበለው ኢንቨስትመንት ካሳና የልማት ባንክ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው” የሚል ጥያቄ መነሳቱን አመልክተዋል።

ለአበባ እርሻ ላስቲክና ኬሚካል በማስያዝ ልማት ባንክን እያለቡ የተሰወሩ በርካታ ድርጅቶችና ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ሸሪኮቻቸው መኖራቸውን በማስታወስ በጋምቤላ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል የዜናው ምንጮች ጠቁመዋል። ካራቱሪ በኪሳራ መንገዳገዱን፣ ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በ”ውክልና” ለሳዑዲ አረቢያ ቀለብ እንዲያመርት የተከሉት ሳዑዲ ስታርና ሌሎች የህወሃት ሰዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ መበደራቸውን ገልጸዋል።

“ህዝብን ያለፈቃዱ በማፈናቀልና መሬቱን በመቀማት የሚከናወን ኢንቨስትመንት ሁሌም አደጋ ላይ መሆኑ አያጠራጥርም” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ገልጸዋል። “ኢንቨስትመንት እንኳን ደህና መጣህ በሚል ህዝብ ካልተቀበለው ዘረፋ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ድምጹን ሲያሰማ ጆሮ ያጣ ህዝብ ተቃውሞውን ገለጸ” በማለት በደረሰው ውድመት ባይደሰቱም ለውድመቱ ተጠያቂው ኢህአዴግና ከኢህአዴግ ጋር ተሻርኮ ዝርፊያ ያከናወነው ድርጅት እንደሆነ አመልክተዋል።

ካሩቱሪና ሳዑዲ ስታርን ጨምሮ ህዝብ ላይ በተፈጸመ ግፍ ሃብት ለማፍራትና ለመበልጸግ የሚያስቡ ትልቅ ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ ዝርፊያና ኢንቨስትመንትን ለይቶ መሔድ ካልቻለ ስጋቱ እየጨመረ ይሄዳልና ከስህተት በመመለስ ህዝብ በሚፈቅደው መልኩ ማስተናገድ ግድ ነው” ሲሉ አሁንም ጆሮ የለውም ለሚባለው ኢህአዴግ ማሳሰቢያ አዘል ምክር ለግሰዋል። ባለሃብት የሚባሉትም ከዚህ ታላቅና አሳዛኝ ውድመት ሊማሩና ህዝብ “እንኳን ደህና መጣችሁ እንዲላቸው ህዝብ ከሚቃወመው ዝርፊያና አሰራር ራሳቸውን ሊያገሉ ይገባል” ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ቃጠሎውን ማመናቸውን ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ያስታወቀ ሲሆን አጣሪ ኮሚቴ ተቃቁሞ አደጋውን ያደረሱት እነማን ናቸው የሚለው እየተመረመረ እንደሆነ ጠቁሟል። የክልሉ የጎልጉል ምንጮች በርካታ ሰዎች እሳት አስነስታችኋል በሚል መታሰራቸውና በፌዴራል አንጋቾች እየተመረመሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። እሳት ያስነሱትን ለማጋለጥ በሚል በየመንደሩ በሚደረግ ማዋከብ ነዋሪዎቹ መማረራቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው የእስረኞች ቁጥር ባይታወቅም ወደ ማዕከል የተላኩ በርካታ እንደሆኑም ገልጸዋል። በማያያዝም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኢህአዴግም ሆነ ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ህዝብን ማዳመጥ ሊቀድም እንደሚገባው ጠቁመዋል። (ፎቶ፡ ለማሳያነት ብቻ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ezra says

    October 28, 2013 03:00 pm at 3:00 pm

    very very good news, wow! golgul many many thanks Dear

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule