• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢኮኖሚ አድማ!

September 6, 2016 11:07 pm by Editor Leave a Comment

በ#OromoProtests  አስተባባሪዎች በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት በኢኮኖሚ ላይ ያተኮረው የገበያ ማቆም አድማ እየተካሄደ ነው፡፡ በፎቶዎቹ ላይ እንደሚታዩት ከንጋት ጀምሮ የአምቦ አካባቢ ከተማ፣ ሻሸመኔ አዋሾ ክፍለ ከተማ፤ አሳሳ፣ ጉደርና ከተሞች ከነገበያቸው ባዶ ሆነዋል፡፡ ዓድማው በሌሎችም ከተሞች ላይ ሲካህይድ የዋለ ሲሆን በውጤቱም የህወሃትን የገቢ ኮሮጆ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳው ይገመታል፡፡

ከአስተባባሪዎቹ የተሰጠውና እስከ መስከረም 2 የሚዘልቀው ማሳሰቢያ እንዲህ ይነበባል፤

ማሳሰቢያ: የገበያ ማቆም አድማ በመላው ኦሮሚያ ነገ ጳግሜን 1 እንደሚጀምር አስቀድመን መግለጻችን ይታወቃል፡፡ ይህ አድማ እስከ መስከረም ሁለት ይቀጥላል። በዚህ አድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው። እቃዎችን ጭነው በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም አቀናጆች አስታውቀዋል። የመኪና ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ይህንኑ አውቀው ይህን የአድማ ወቅት በማክበር ለህዝብ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ እና ንብረታቸውንም ከውድመት እንዲያድኑ ደግመን እናሳስባለን። (ፎቶ፡ ከጃዋር መሐመድ፣ ከጸጋዬ አራርሳና ከሌላ ግለሰብ ፌስቡክ ገጽ የተገኙ)

በሌሎች ከተማዎች የመረጃ አለመድረስ እንዳለ የጠቆሙ አንድ አስተያየት ሰጪ ይህንን ብለዋል:

“በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልሎች ተቃውሞው በተሳካ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ደውዬ ያነጋገርኳቸው ሰዎች ገልፀውልኛል ነገር ግን አንዳንድ አከባቢዎች ጉዳዩን ካለመስማት ይሁን? ወይም ለጥሪው ምላሽ ለመስጠት አለመፈለግ? እንደወትሮው ሁሉ የእለት ተለት እንቅስቃሴያቸውን እየከወኑ ነው። ለምሳሌ ወለጋ ሲቡ ሲሬ ፣ ጅማ ፣ አሰላ፣ . . . በነዚህ ቦታዎች ላይ ሌላውን ማስተማር የሚችል ጥሩ መቀጣጫ እርምጃ መወሰድ አለበት። ዛሬ ጥዋት አንድ ባለ ሆቴል ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ገና በሩን ከፍቶ ሰዎች ማስተናገድ ሊጀምር ሲል ስልክ ደውለው ምን እንዳሉት ባላውቅም በሩን በሰከንዶች ፍጥነት ዘግቶ ከአከባቢው ጠፍቷል! ህዝብ ሲተባበር ሁሉም ይፈራዋል።”

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም ማለታቸውንና ላለፉት ሁለት ወራት ገቢዎች ቢሮ ግብር እንዳልሰበሰበ ሙሉቀን ተስፋው በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ አስታውቋል ከዚህ ጋር ተያይዞ የ#AmharaResistance አስተባባሪዎች ሕዝቡ ግብር አለመክፈሉን መቀጠል እንዳለበት ያሳስባሉ – እንዲህ ይነበባል:

“በጎንደር፣ በባህርዳር፤ በደብረ ማርቆስ እና ተጋድሎው እየተስፋፋባቸው ባሉ አካበቢዎች ያሉ ነጋዴዎች ግብር አንከፍል አሉ፡፡

“የመንግስት ባለስልጣናት የተጨማሪ እሴት ታክስ ለገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በየወሩ የገቢ ግብር ሪፖርት ማቅረብ የሚጠብቅባቸው ቢሆንም እስካሁን ላለፉት ሁለት ወራት የገቢ ግብር ያቀረበ ነጋዴ አልተገኝም፡፡

“በአሁኑ ስዓት አገልግሎቶት ሰጭዎች ባቆሙበት ስርዓት የመንግስት ፋይናንስ ላለፉት ሁለት ወራት በጎንደር በዚህ ወር ደግሞ በባህር ዳር ያሉ ነጋዴዎች ከመንግስት አካላት ግብር እንዲከፍሉ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለወንድሞቻችን ነፍስ መግደያ የጥይት መግዣ አናዋጣም፡፡ አሁን ላለው ስርዓትም እውቅና አንሰጥም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ላላፉት ሁለት ወራት ገቢዎች ምንም ግብር አልሰበሰበም!! የዐማራ ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም ማለቱን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው!!”

oromo cities

አምቦ
አምቦ
አዋሾ ክፍለከተማ ሻሸመኔ
አዋሾ ክፍለከተማ ሻሸመኔ
አዋሾ
አዋሾ
አሳሳ
አሳሳ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
አሳሳ ገበያ
ጉደር
ጉደር
ጉደር
ጉደር
ነቀምት
ነቀምት
ዶዶላ አርሲ
ዶዶላ አርሲ
አወዳይ
አወዳይ
አወዳይ
አወዳይ
አወዳይ
አወዳይ
አወዳይ
አወዳይ
ሻሸመኔ
ሻሸመኔ

city oromia

ሮቢ ባሌ
ሮቢ ባሌ
ቡራዩ
ቡራዩ
ቡራዩ
ቡራዩ

oromiacity1 oromiacity2 oromiacity3 shashenene o

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule