• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?

October 4, 2014 04:08 am by Editor 2 Comments

ሰሞኑን ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ”ባንዲራ ቀን” በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ”ባንዲራ ክብር” ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤ የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል።

ባድመ ስትወረር “ደርግ ኢሰፓ” ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ “እናት አገር ጥሪ” ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል ኪዳን ይኸው “አታስፈልግም ጨርቅ ነህ” የተባለው መለያ ነበር። ሲፈልጉ የሚጥሉት፣ ሲጨንቃቸው የሚያነሱት መከረኛ ባንዲራ ዳግም አጀንዳ ሆኖ ሰሞኑንን ቀርቦልናል።

wedi1በአሜሪካ በሚገኘውና ኢህአዴግ “ኤምባሲ” በሚለው ቅጥር ግቢ ውስጥ ወዲ ወይኒ የሚባሉ ታጋይ የፈጸሙት ድርጊት ነው የባንዲራን ጉዳይ ዳግም አጀንዳ ያደረገው። የወዲ ወይኒ ገድለ ዜና አስገራሚ የሆነባቸው፣ ያሳዘናቸው፣ ያናደዳቸው፣ የተደፈርን ስሜት የፈጠረባቸው፣ ክስተቱን በመቃወም ኢህአዴግን በመወከል መግለጫ ያወጡ፣ እስከመቼ ኢህአዴግ “ሆደ ሰፊ ይሆናል” ብለው የጠየቁ፣ አሜሪካንን የወነጀሉ፣ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቁ፣ … በተለይም የሳይበር ሚዲያውን አጣበውት ከርመዋል። በሌላ በኩል ዜናውን እንደዜና ብቻ ወስደው ሚዲያ በዘነጋቸው ኢትዮጵያዊያን ላይ ለሚደርሰው ግፍ ያዘኑ ስፍር ቁጥር የላቸውም።

ዋሽንግተን በሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ውስጥ የመዋቅሩ “መሪ” ተብለው የተቀመጡትን ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንደመጡ የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ወዲ ወይኒ ጥይት ሲተኩሱ ተሰምቷል። ታይቷል። ተረጋግጧል! በኢትዮጵያ ስም የተሰቀለው የህወሃት/ኢህአዴግ ዓርማ ወርዷል! በዚሁ በፊልም ተደግፎ በቀረበው ዜናና የማህበራዊ ገጽ ዓምዶች ላይ ዋሽንግቶን ከተማ ከዋይት ሃውስ 4 ማይል ርቀት ላይ በሚገኘው የኢህአዴግ ግቢ ውስጥ ተሰቅሎ የነበረው “ጨርቅ” ወርዶ ተጥሏል። “የጨርቁ ፍቅር ያቃጠለው” የጽህፈት ቤቱ ሰራተኛ የተጣለውን “ጨርቅ” ሰብስቦ ወደ ቢሮ ሲያስገባም ከካሜራ እይታ አላመለጠም። እንግዲህ ይህንን እውነት ነው ለመካድና “ከዓይናችሁ ጆሯችሁን እምኑ” እየተባልን ያለነው።

በሌላ በኩል የህዝብ ቀልብ ለመሳብ “ባንዲራ ያዋረዱ” በሚል “ኢህአዴግ በፈቃዱ ያሰራውን ጨርቅ” አውርደው የጣሉትን ለመክሰስና ከሃዲ አድርጎ ለመሳል ተሞክሯል፤ ሙከራውም ቀጥሏል። ሁኔታውን የሚከታተሉ እንደሚሉት “ይህ የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው” በማለት የሚጠሩትን ጨርቅ “ይህ የእኔ ባንዲራ አይደለም” በማለት ቀዳደው የሚጥሉ ዜጎች በምን ሂሳብ ተቃውሞ ይሰነዘርባቸዋል የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው።

ህወሃት ትግራይን ነጻ ለማውጣት ትግል ጀምሮ፣ በወቅቱ ደርግ በነበረው የአመራር ጥበብ እጥረትና ሌሎች ተጽዕኖዎች ከአገዛዝ መንበር ተነስቶ ህወሃት/ኢህአዴግ አገር ገዢ ለመሆን ሲታደል የአገሪቱን ባንዲራ “ጨርቅ” ብሎ አዋርዶታል። የቀለብ መቋጠሪያው እራፊ አድርጎ ክብሩን ገፎታል። ባደባባይ አገርና ህዝብ እየተቃወመ በጠብ መንጃ ሃይል አስወግዶታል፤ አቃጥሎታል። ራሱ ባሰፋው ሌላ “ጨርቅ” ተክቶበታል። ይህ የሸፍጥ ታሪክና ተግባር የተረሳ ተደርጎ ዛሬ ህወሃት/ኢህአዴግ ደርሶ ለሠንደቅ ዓላማ ክብር ሰጪ ሆኖ ሙግት መግጠሙ ጥያቄውን የሚያነሱ ክፍሎች ተግባሩ “ያቅለሸልሻል” ባይ ናቸው።

“አገር የነሱ መፈንጫና ሃብት ማግበስበሻ የሆነችላቸው የድጋፍ ቀረርቶ ለማሰማት ቅድሚያ ቢይዙ፣ አገር የላችሁም፣ ባንዲራ አልባ ናችሁ፣ የተባልን የነሱ የሆነውን ጨርቅ አንፈልግም ብንል ምን ይገርማል?” የሚሉት ክፍሎች፣ “በሎንደን የኤርትራ ኤምባሲን ዘልቀው ለሰዓታት የተቆጣጠሩት አምባገነን በሚባሉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ዲፕሎማቶች” ጥይት አልተተኮሰባቸውም። ኢሳያስን አምባገነን በማለት የኤርትራን ህዝብ “ነጻ” አወጣለሁ የሚለው ህወሃት ግን በወዲ ወይኒ አማካይነት ህግ ባለበት አገር የህወሃትን ማንነት ባደባባይ አሳይቷል። “እዛው ህወሃት በሚነዳት አገር ውስጥ ቢሆን ኖሮ ስንቱን ይረሽን ነበር” ሲሉም የሚጠይቁ አሉ። እነዚህ ክፍሎች “አገር ቤት የተረሸኑትንና ታስረው የሚሰቃዩትን ቤት ይቁጠራቸው” ሲሉ ተደፈርን በሚል ስሜታቸውን የሚያንጸባርቁትን ወገኖች “ወዮልኝ ቀን ያጋደለ እለት” በሚል ምጸት ጥርሳቸውን ይነክሱባቸዋል።

ወዲ ወይኒ በጠራራ ጸሃይ፣ በካሜራ ታጅበው፣ እንደ ፊልም አክተር ሽጉጥ ወጥረው ሲያስፈራሩ፣ “ተኩስ፣ ግደለኝ፣ ተኩሰው” እያሉ ሲጠጉዋቸው የነበሩት ወገኖች ግርማ ብሩን እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። “የብሄር ብሄረሰብ መብት በገፍ ተሸክሜ ልገዛ መጣሁ” የሚለው ኢህአዴግ የወከላቸው አቶ ግርማ ሰዎቹን ወጥተው ለምን አያነጋግሩም? ችግራችሁ ምንድነው? ምን እንርዳችሁ? የማይሉበት ምክንያትስ ምንድነው? ይህ የእኛም አቋም meles sibhat embassyነው። ላደላቸው ኤምባሲ አገራቸው ነው። አምባሳደር መሪና ተከራካሪ ጠበቃቸው ነው። ለታደሉ ኤምባሲ በሄዱበት የባዕድ ምድር የሚሰበሰቡበት ቤታቸው ነው፤ ትንሽዋ አገራቸው ነው። መሪውም የቤቱ አስተዳዳሪ ነው። አገር በቤት፣ ህዝቦቿም በቤተሰብ ከተሰየሙ፣ የቤተሰቡ መሪና ረዳቶቹ ልጅና እንግዴ ልጅ ለይተው ላንዱ ወርቅ፣ ለሌላው ጥይት አያቀርቡም። በዚህ እሳቤ “የኢህአዴግ የመዋቅር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት” ብለን በጠራነው ቅጥር ውስጥ ወዲ ወይኒ የፈጸሙት ተግባር ከህወሃት ማንነት የተቀዳ ስለመሆኑ አንጠራጠርም።

በሰለጠነ አለም ውስጥ እንዳሻቸው እየበሉና እየጠጡ የሚኖሩ ሰዎች “ግደለኝ፣ ተኩስብኝ፣ ግደለኝ” በማለት ሞትን ለመጋፈጥ ሲወስኑ ምልክቱ “ብሶት ከልክ ማለፉን የሚያሳይ ነው” የሚሉ ክፍሎች “ይህ ድርጊት ነገ መልኩን ቀይሮ አገር ቤትም ሆነ ሌላ ቦታ ዋሽንግቶንን ጨምሮ ላለመከናወኑ ማረጋገጫ የለም” ይላሉ። ተበልቶና ተጠጥቶ በሚታደርበት አገር ውስጥ ዜጎች ሞትን ከናቁት፣ የኑሮ ጠኔ የሚለበልባቸው የበይ ተመልካቾች ያመረሩ ቀን አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዳሉት “የከፋ ቀውስ” ይከተላል። ህግና ስርዓት ባለበት አገር ጥይት እያንባረቁ አካኪ ዘራፍ ማለት፣ በዚያው ስሜት ተመልሶ “ተደፈርን” ብሎ መጮህ የሚያመለክተው “ከልክ ያለፈ ጥጋብ ተራራ ማከሉን ነው” ሲሉ በድርጊቱ የተበሳጩ ይናገራሉ።

የአገር ቤቱ አልበቃ ብሎ ህግና ስርዓት ባለበት አገር “በጫካ ማንነት አምባገነን ለመሆን መሞከር በጥጋብ መወጠር ያመጣው የትዕቢት ድምር ነው” በማለት አምርረው የሚናገሩት ክፍሎች “በጥጋብ የተወጠሩና ጥጋባቸው ያሳወራቸው ጥቂቶች፣ ርሃብ እንቅልፍ በነሳቸው፣ ግፍ ባንገፈገፋቸው፣ አገር ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያ ተስፋ ባስቆረጣቸው ህዝብ መካከል እንደሚኖሩ መዘንጋታቸው” የወደፊቱን ሲያስቡ ሃዘን እንደሚገባቸው ይጠቁማሉ።

ይህንኑ ከልክ ያለፈ ጥጋብ መተንፈስ እንዳለበት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ ለህወሃት አመራሮች በቅርቡ በላኩት ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፤ “ከእናንተ ጋር ሚቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት ማሰራችሁን አቁሙ! ኃይልን ወይም ጉልበትን በመጠቀም እስከመጨረሻው በሥልጣን አትቆዩም! በዓለም ታሪክ ያልተከሰ ስለሆነ እናንተ ልትከውኑት አትችሉም። እናንተ አለን ከምትሉት ጉልበት በብዙ እጥፍ የሚበልጥ የነበራቸውም ተንኮታኩተዋል። ስለዚህ ከትዕቢታችሁ ተንፍሱ፤ ትህትና አሳዩ፤ ከፍ ብላችሁ የተሰቀላችሁበት ከመሰላችሁ “ፎቅ” ውረዱ! ለለውጥ ያላችሁን ግልጽነት አሳዩ! ለዓመታት ሳታቋርጡ ስታወሩ የነበራችሁትን ውሸት አቁሙ፤ እውነትን መናገር ተለማመዱ። የሃሰትን መንገድ ሳይሆን ትክክለኛውን በመከተል በዜጎች መካከል መተማመን እንዲፈጠር የሚያስችል ሥራ ማከናወን ጀምሩ!”

“ውርደት ቀለቡ” የሚባለው ህወሃትና ሟቹ መሪው ተጠልተዋል። ጥላቻው ልክ አልፏል። መለስ ስድብና ርግማን ጠግበው እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩ። ከህልፈታቸው በፊት ውግዘትና ርግማንን ጠግበው የነበሩት መለስ “ሲሰው” ስብሃት ነጋ ስታርባክስ ቡና ሊጠጡ ገብተው ሃፍረትን በሲኒማ ተከናነቡ፣ “የህወሃት ቁስ” ከሚባሉት አንዱ ሬድዋን ሁሴን የልብስ ሱቅ ውስጥ ልጆችና ቤተሰባቸው አጥንት ስር ዘልቆ የሚገባ የውግዘት መርዝ ተጋቱ፣ አሁን ደግሞ ዋሽንግቶን የተተከለው ቅጥር ግቢያቸው ትዕቢታቸውን አሟሟው። እንደ እነዚህ ክፍሎች ገለጻ በስምምነትም ሆነ በግዴታ ወዲ ወይኒ 24 ሰዓት ሳይሞላ እንዳሻቸው መግደልና ማሰር ወደሚችሉባት የህወሃት ኢትዮጵያ መላካቸው አድሮ የህግ ጥያቄ ያስነሳል። ለዚሁ ይመስላል ህወሃቶች ግድያ ሊፈጽም የነበረው ሰው ትግሬ በመሆኑና የተነካውም ክብር የትግሬ ህወሃቶች በመሆኑ የስምምነት መግለጫ እንዲወጣ ይፈልጋሉ። አሜሪካ ይህንኑ እንድትፈጽም ጥረት ስለመኖሩ አቶ ግርማ ብሩ ፍንጭ መስጠታቸውን ያመለክታሉ።

ለኢህአዴግ ልሳን ቃላቸውን የሰጡት አቶ ግርማ፣ ከስቴት ዲፓርትመንትና ከሌሎች አካላት ጋር በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ተነጋግረናል” ሲሉ መናገራቸውን የሚጠቁሙ እንደሚሉት” ወዲ ወይኒ ወደ ህወሃት የግዛት አገር እንዲሄዱ የተደረገው ለፖሊስ የምርመራ ቃል ከሰጡ በኋላ በሁለትዮሽ ንግግር ነው። “ንግግሩ ምንም ይሁን ምን አሜሪካ ወንጀለኛውን የምትፈልግ ቢሆን “ኤምባሲ” ከሚባለው ቅጥር ግቢ ሲወጡ ፖሊስ ሊያስራቸው ይችል ነበር።

የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ጉዳዩ እንደተፈጸመ “ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዘ ጉዳይ በጥንቃቄ ይታያል” ማለታቸው አይዘነጋም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    October 4, 2014 09:46 am at 9:46 am

    TPLF fascists should understand that the anger of Ethiopians is boiling. It is not possible to loot and terrorize indefinately. If there are some wise people among these fascists or Tigrian collaborators should think twice and examine and understand the danger of what the home grown fascists are doing.

    Reply
  2. በለው ! says

    October 6, 2014 03:24 pm at 3:24 pm

    እንግዲህ ብሔር፫ በሔረሰቦች፪ እና ሕዝቦች፩ …ኢትዮጵያዊ፩ ትወልደ ኢትዮጰያዊ፪ ዲያስፐር፫.. አነስተኛና ጥቃቅን ኢንቨስትር፣ አውርቶ-አደር እያለ ሀገርና ሕዝብ ሲሸነሸን ቢቆይም መዘዙ አደገኛ ነው።ሰሞኑን በአርጥብ እነጀራ በርበሬና ሹሮ፣የሀገር ባሕል ልብስ ንግድ የተሳተፉ የሥርዓቱ ተደጋፎዎች ተንጫጩ ቤታችን ተደፈረ..የታጋይ ባንዲራችን ተነካ አሉ። ወዶ ገቦች ዙሪያውን ይጮሃሉ።
    “ግለሰቦች አንዲህ ያለ ቀሽም ስሕተት የሚሠሩት ከድንጋጤና የሚመጣውን ነገር በማሰብ ልክ ትምህርት ቤት እንደነገሩት ሊሰራ ሲፈልግ ነው። በጥላሁን ገሠሠ ሥም ቴሌቪዥን ጣቢያ አለኝ የሚለው መስፍን በዙ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዘላበደውን ማዳመጥ ስብእናን ሆድ እንዴት እደተቆጣጠረው ያሳያል።
    ሀ)ግለሰቡ አማሪካንን በማወደስ ጭራውን መቁላት ፈለገ፡
    ለ)ዚህ ጉዳይ በቅርብ አንደሚያውቅ ሆኖ ሊያስረዳ ፈለገ፤
    ሐ) በራሱም ላይ በተቃዋሚዎች የሚደርስብት ችግር እንዳላበት የክስ መዝገብ አቀረበ!
    መ)የተቃዋሚዎችን ጉዳይ በተለያዩ ግዜያት ለሚመለከታቸው ማሳወቁን አስረዳ!
    ሠ)በዚህ ጉዳይ ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ ከባላሥልጠናት ጋር መነጋጋሩን አወሳ!
    ረ)የጥያቄና መልሱ ሰብሳቡ መጥፎ ነገር በተቃዋሚዎች ላይ ብትናገር የእሱ የበላይነት ታየው!
    ሰ)በዚህ መልካም ድጋፉ ሀገሩ በእየዓመቱ ሲመላላስ ኢህአዴግ የሚያደርግለት አቀባባል ታየው!
    ሸ)በሙያው ፎቶግራፍ አንሺ..ወሬ አመላላሽነት አልፎ የግል ሚዲያ እንደሚኖረው ቋመጠ
    ቀ)በዲሲና አካባባው የሚያገኘው ዝናና ክብር የኤምባሲ እራት ግብዣ በዓይኑ ላይ መጣ!
    በ) አምባሳደሮች ልዩ የዲያስፐር አማካሪ እንደሚያደርጉትና የእራት ሳህን ሰብሳቢ ሲሆን ታየው
    ***እንግዲህ ፕሬዘዳንቱን ዋና ፀሐፊ..ኤምባሲውን የግል ቤት..ከዚያም አሜሪካንን ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ለማባረር ሁሉ ይቀሳፍታል…መንግስታችን ለአሜሪካ ኤምባሲ የሚያደርገው ጥበቃ መቀነስ አለበትም ሲሉ ይደመጣሉ.. የመሳሪያ ፍቃድ የሌለው ተገፋፍቶ መተኮሱ አግባብ ነው ሲል..አልተባረረም ግን አሜሪካንን አልፈልግም ብሎ አሁን የሳተውንና የባረቀበትን አነጣጥሮ ለመግደል በአጀብ ወደ ሀገሩ ተሸኝቷል የጀግና አቀባባል ይደረግለታል ይላሉ። ጉድ በይ አማሪካ!ግን ከአፍ ሲያመልጥ እራስ ሲመለጥ አይታወቅም አደለም?
    ***********************
    በእንቆቅልሽ በሥም ለበስ ቅኔ
    አሁን ገና መጣሽብኝ በዓይኔ
    አንድ ዓይን ያለው አይጫወት በአፈር
    አንድ ያለኝን ስጠኝ አልሽኝ ሀገር!?
    “በአፈር አታጫውችኝ ይታመማል ዓይኔ..
    አውቅልሽ ብዬ ባላውቅም እንቆቅልሽን ጨዋታ
    ሀገሬን ውዴን ሰጥቼ ባጣትስ የማታ ማታ!?
    አስቲ ሌላ እንዳላው መን አለኝ እና እኔ
    ሀገር ስጠን አልሺኝ አንዲህ እንደዋዛ
    ያውም እኔን ሀገር ሳይበሉ የሚያወዛ !
    የምን እንኦቀቅልሽ ምን አለሽ ከሀገሬ አስቲ ተናገሪ
    በይ ደስም አላልሽኝ ጨዋታ ቀይሪ።
    ***************
    ለዘፈኑ ባላቤት ለሀገሩ ክብር ስለሰጣት ምስጋናዬ ይድረሰው ። ብሔር በሀገር ላይ ነው። በብሔር በቋንቋ በጎሳ ላይ የቆመ የፖለቲካ ፓርቲና ሙስና ብቻ ነው። ሠላም ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ይሁን። አሜን!

    Reply

Leave a Reply to koster Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule