• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጥልቅ ተሃድሶ “በመበስበስ” ጀመረ!

September 20, 2016 11:55 pm by Editor 9 Comments

የኢህአዴግ አካል የሆነው ኦህዴድ “ጥልቅ ተሃድሶውን” “በመበስበስ” መጀመሩን የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ያሰራጨው ዜና አመልክቷል፡፡ ዜናውን ተከትሎ “በጥልቀት የመታደሱ” ጉዳይ “በመበስበስ” መጀመሩ አመላካች ነው ተብሏል፡፡ በሌሎች ክልሎችም የመበስበስ መጠናቸው የጠለቀና ለህወሃት ከመታመን ውጪ ተስፋ በሌላቸው ታማኞች በመተካት ሹምሽር እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

የኦህዴድ ምክትል ሆነው የተሾሙት ጄኔራል፣ ዶክተር፣ አቶ፣ አሁን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ብቅ ያሉት የኦሮሞን ብሔር የማይወክሉ የትግራይ ተወላጅ እንዶኑ በስፋት የሚነገርላቸው ሻሸመኔ ያደጉት ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?” በሚል ርዕስ (July 6, 2013) ስለ ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” መጠነኛ ዘገባ ባቀረበበት ወቅት የሚከተለው ሪፖርት አድርጎ ነበር፤

“የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።

በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።

አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።

አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።”

ቀደም ሲል ከተዘረዘሩት የሥልጣን መጠሪያዎች ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” አሁን የኦህዴድ ሊቀመንበር ከሆኑት ለማ መገርሳ ጋር በአንድነት በማታው የትምህርት ክፍለጊዜ የዶ/ር መረራ ጉዲና ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ከዚህም በላይ ወርቅነህ ገበየሁ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር (የጄኔራል ማዕረግ በህወሃት ተሰጥቷቸው እንደ ሲቪል “አቶ” ተብለው) በሚሠሩበት ወቅት ለማ መገርሣ የኦሮሚያን ደኅንነት በመምራት አብረዋቸው ይሠሩ ነበር፡፡

ከህወሃት የተሰጣቸውን የሚኒስትርነት ሥራ ሳይለቁ፤ ከፓርቲና ደኅንነት ሥራቸውም ሳይነቃነቁ ትምህርት ተምረው “ዶክተር” ለመባል እንደበቁ የሚነገርላቸው ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ተማሩበት በተባለው የትምህርት ተቋም ስማቸው “ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን” ተብሎ ከነፎቷቸው ተመዝግቧል፡፡

ከግራ ወደቀኝ ፓስተር ገመቺስ ቡባ፣ ጌታቸው ረዳ፣ የኦሮሞዎች መገደል ትክክል ነው ያለ አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እና ለማ መገርሳ
ከግራ ወደቀኝ ፓስተር ገመቺስ ቡባ፣ ጌታቸው ረዳ፣ የኦሮሞዎች መገደል ትክክል ነው ያለ አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እና ለማ መገርሳ

በኢህአዴግ አሠራር የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት የሚሆኑት ዛሬ ፋና ይፋ ያደረጋቸው አዲሱ የኦህዴድ ሊቀመንበር (የኦሮሚያ ምክርቤት አፈጉባዔ) ለማ መገርሣ በደኅንነት ውስጥ ከፍተኛ ታማኝነት ያተረፉና በሚያቋቸው ሰዎችና የሥራ ባልደረቦች “ተንበርካኪ የመቀሌ ልጅ” እየተባሉ የሚጠሩ መሆናቸውን በቅርብ የሚያቋቸው ይመሰክራሉ፡፡

ተሰናባቾቹ ሙክታር ከዲርና አስቴር ማሞ ራሳቸውን ከኃላፊነት አንስተዋል በሚል በሁለቱ የደኅንነት ማሽኖች መተካታቸው ያፈነገጠውን ኦህዴድ ወደ ሃዲዱ ስለመመለሱ ማረጋገጫ አይሰጥም፡፡

በሼህ መሃመድ አላሙዲን ባልደረቦችና ታዛዦች አማካኝነት አባዱላን ገልብጠው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሙክታር ዛሬ ራሳቸውን ከሥልጣን አነሱ ቢባልም ከመሾማቸው ጊዜ ጀምሮ ካድሬው ሙሉ በሙሉ የሚቀበላቸው ሰው አልነበሩም፡፡

በጅማ ንጹሃን በታረዱነበት የህወሃት ወንጀል እጃቸው እንዳለበት በሥፋት የሚነገርላቸው ሙክታር እጅግ ውብ የሆኑት ባለቤታቸው ሚሊዮኔር መሆናቸው የኢህአዴግ ወፍጮ ሊቀረጥፋቸው ታሳቢ ካደረጋቸው መካከል የቅድሚያ ተሰላፊ እንደሚሆኑ ይነገራል፡፡

በባለቤታቸው የህወሃት አባል የሆኑት አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ azeb and asterሚኒስትር የሚል ረጅም ሥልጣን ከተሰጣቸው ጊዜ ጀምሮ ብቃት የላቸውም፣ ዓቅም ያንሳቸዋል፣ ለቦታው አይመጥኑም፣ ወዘተ በሚል ተቃውሞ በግምገማ ላይ ሲቀርብባቸው ህወሃት/ኢህአዴግ “ጥሪ አይቀበልም” ሲል ሰንብቷል፡፡ ይልቁንም ዕድገት እየሰጠ የኦህዴድ መሪ አድረጋቸው፡፡ በሰባራ ጋሪ “ሽምጥ እየጋለብኩኝ” ነው ሲል የነበረው ኦህዴድ ራሱ አንኮታኩቶ ያጠፋውን የመልካም አስተዳደር፤ መሠረታዊ የችግር ቁልፍ አድርጎ በመውሰድ የአስቴር ማሞን ከሥልጣን መውረድ በ11ኛው ሰዓት ላይ ተቀብሎታል፡፡

የአስቴር ማሞን ከኃላፊነት መነሳት የተቀበለው ህወሃት “በጥልቅ ተሃድሶ” ምሎ ጥልቅ ተሃድሶውን በግፍ ከሸተተው መጋዘኑ ውስጥ ታማኞቹ አውጥቶ በመሾም የመታደሱን ቁርጠኝነት አሳይቷል፡፡ በዚህ የሥልጣን ሹም ሽር የቀለዱ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት የኢህአዴግ የጥልቅ ተሃድሶ “ዳግም መበስበስ” ነው ብለውታል፡፡ አክለውም በመበስበስ የተጀመረው ይህ “ጥልቅ ተሃድሶ” ህወሃትን ወደ ትክክለኛ ጥልቅ ተወርውሮ የሚገባበትን ፍጥነት ቁልቁል የሚያዳልጥ አድርጎ ያፋጥነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. alem wagaye says

    September 21, 2016 09:22 am at 9:22 am

    ዘገባችሁ ይቀጥል ትግላችን ይቀጥላል

    Reply
  2. Cccc says

    September 21, 2016 08:39 pm at 8:39 pm

    ደም መፋሠሡ አልሳከ አለ?

    Reply
  3. Ethio says

    September 22, 2016 06:21 am at 6:21 am

    ይሄ ጽሁፍ ይቀጥላል? ወይስ »»ምክንያቱም ፣ ወርቅነህ ገበየሁ የፌደራሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በምርጫ 97 ወቅት ፣ በአጣሪ ኮሚሽን ለተረጋገጡ የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎት ቀጥተኛ በህይዎት ያለ ተጠያቂ ነው። ለእርሱ የ ህወሃት /ኢሃዴግ ህልውና ከራሱ የመኖር ያለመኖር ህልውና የተቆራኘ በመሆኑ ማንኛውንም አይነት ርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ አይልም። እኔ ራሴ personally የምምስክረው ብዙ ነገር አውቃለሁ። ሰውየው በደም የተጨማለቀ ነው ፣ ይህን አውሬ ማጋለጡ ይቀጥል

    Reply
    • Editor says

      September 22, 2016 07:18 am at 7:18 am

      ያለዎትን ምስክርነት በአድራሻችን ይላኩልን editor@goolgule.com

      ከምስጋና ጋር
      የጎልጉል አርታኢ

      Reply
  4. tibebe says

    September 23, 2016 08:33 pm at 8:33 pm

    Ye weyane wisht ayalkim

    Reply
  5. Mulugeta Andargie says

    September 26, 2016 03:49 am at 3:49 am

    ትናት የላኩትን አነሳችሁት:: ለምን? ውሸት አይታክታችሁም??

    Reply
    • Editor says

      September 26, 2016 06:47 am at 6:47 am

      እኛ ምንም የምናነሳውም የምናስቀምጠውም ነገር የለም:: ትላንት https://www.goolgule.com/lets-talk-to-save-our-country/ እና https://www.goolgule.com/workineh-gebeyehu-is-from-tigray/ ላይ ባተምናቸው ሁለት ጽሁፎች ላይ የተሳደብከው እንኳን እንዳለ ተለጥፏል:: ሌላም ምትሳደበው ካለ መጨመር ትችላለህ:: ለዚህ ምላሻችን ምላሽ አንፈልግም ይህንንም የጻፍነው ውሸትህን ሰው እንዲያይልህ ነው::

      Editor

      Reply
  6. Mulugeta Andargie says

    September 26, 2016 08:01 pm at 8:01 pm

    ውነት እንነጋገር!!!??? የናንተ አርበኛ የምትሏቸው ዘርፈው የወጡ ሌቦችን ነው የሰበሰባችሁት! ዳዊት መስፍን እነማናቸው?እርስ በርስ እኮ እንተዋወቃለን! ሁሉም ገመሬ ዝንጀሮ ሆኖ ተራራ ላይ ወጥቶ ቢጮህ ቤተ ሰብ ሰብሳቢ ሊሆን ነው?? ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን እኮ!እንተዋወቃለን! መሸዋወድ ይቅር! እናንተ ለዘራችሁ ስታስቡ:እኛስ አናስብም? ምላጭን ምላጭ አይቆርጠውም!ህዝብን አታታሉ!

    Reply
  7. Mulugeta Andargie says

    September 30, 2016 04:50 am at 4:50 am

    ጓዶች! እናንተኮ አታሚዎች ናችሁ! የሰበሰባችሁት: ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ፡መስፍን ወ/ማርያም:ጌታቸው ሃይሌ:ብርሃኑ ነጋ:አለማየሁ ገ/ማርያም:ዳዊት ከበደ:አበበ ገላው:የሙሉጌታ ሉሌ (ኢሳት ስብስቦች)+ መኢአድ + ሰማያዊ ፓርቲ + መረራ ጉዲና + ኣረጋዊ በርሀ= ሚስቶ:: እናንተ ናችሁኮ!! ሌላ አለ?? ከዚህ ውስጥ:ያኮረፈ:የተጎዳ:የደማ:ያጣ:የተቆጨ:የተወናበደ:የተንገዋለለ:የተጎለጎለ:ያረጀ:የዘረፈ:የቀማ:የገደለ:የጓጓ ቡድኖች ናችሁኮ!በዚያ ላይ:መደብራችሁ ጴንጤ!ዋቃ ፈታ!ዓርብ ሮብን የምትዳፈሩ!እንደ ደብተራ አነብናቢዎች:እንደ ጠንቋይ ዘያሪዎች!ፈደል ናፋቂዎች!የኮፒ ማሽን:ስልጡኖች!እንደ ታማኝ በየነ ፔስት አዋቂዎች!! እናንተ ናችሁ! ሌላ አለ??? ሚስቶ ናችሁ!የካፌ ተረበኞች! የቃላት ትግል ወዳዶች!ስልጣን ናፋቂዎች!እንደ ሳሙና ሞላጮች!አልምጦች!!!ጎድን! ጎድን! የሰሩትን አታውኩ!!!ለመሆኑ ልቃቂት ነ ወይስ አረም:የምትጎለጉሉት???

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am
  • በላይነህ ክንዴ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ኢትዮ 360ዎች ጠቆሙ July 31, 2023 01:54 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule