• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው

August 2, 2013 09:58 am by Editor 5 Comments

አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር “… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል።

“ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችንም ይሁን ከሙስሊሙ ኅብረተሰብ በግፍ ለእስር የተዳረጉትን እንዲያስጎበኝ ለሚቀርብለት ጥያቄና በጸረ ሽብርና ህጉ ዙሪያ የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት ይጠበቃል።

ምክክሩን ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፣ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” በማለት የገለጹት ክሪስ ስሚዝ፣ ከባልደረባቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያመሩት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን አቋም ለመመርመር የሚያስችላትን ስራ ለመስራት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ከምክክሩ በፊትና በኋላ ክሪስ ስሚዝ በሰጡት ጠንካራ አስተያየት የተደናገጠው ኢህአዴግ አዲስ ዘመን በሚባለው ልሳኑ “አሜሪካ የኢትዮጵያ አጋርና ወዳጅ መሆንዋን አረጋገጠች” በማለት የሌሎች ተናጋሪዎችን  ወደጎን በመተው የአምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶን ብቻ አንድ ሃረግ ንግግር ቀንጭቦ ዘግቦ ነበር። በአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ባልተለመደ ሁኔታ የተብጠለጠለው ኢህአዴግ ወዳጆቹን ለማረጋጋት ያማሞቶን ጠቅሶ ያሰራጨው ዜና በወቅቱ በደጋፊዎቹ የፌስቡክ ገጽ ላይ በስፋት ተበትኖ ነበር።

Bass
እንደራሴ ኬረን ባስ

ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ መሆኗን ያመላክታል የተባለው የአዲስ አበባ ጉብኝት አስመልክቶ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኢህአዴግ የፖለተካውን ምህዳር በማጥበብ፣ በጸረ ሽብር ህጉ እያሳበበ የመናገርና የመሰብሰብ መብትን ማፈኑ፣ የነጻ ሚዲያና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማነቁ፣ በተለይም በእስር ቤት የሚሰቃዩ ወገኖችን በአካል በመገኘት በማነጋገር አቋም ለመውሰድ መታቀዱን አመልክተዋል። ይህም ከፖለቲካ እስረኞች ጀምሮ፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ጥያቄ ከፍ አድገው በማንሳታቸው ለእስር የተዳረጉትን ወዘተ የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡

“የሚሆነው እስከሚሆን መጠበቅ ነው” በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ አንድ ዲፕሎማት እንዳሉት ነሐሴ 10 ወይም 11 ቀን 2005 (ኦገስት 16 ወይም 17፤ 2013) ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩት ሁለቱ እንደራሴዎች፤ ለኢህአዴግ የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች እጅግ መሰረታዊ እንደሆኑ ይናገራሉ።

“ጉብኝቱ የሽርሽርና እንደተለመደው አይነት የሁለትዮሽ ስብሰባና ስምምነት ለማድረግ አይደለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም” ብለዋል። ሲያስረዱም “በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ኡደት፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም።”

“የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ህገደንብ” የሚል ስያሜ ያለው ህግ ኢትዮጵያን የሚመራው ኢህአዴግ ከአሜሪካ መንግስት ለሚፈልገው ማናቸውም ድጋፍ መሟላት የሚገባቸውን የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብት ግብአቶችን በቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነበር። ይህ ህግ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ አፍስሶ በአሜሪካን ጎትጓቾች (ሎቢዪስቶች) ዘመቻ ያካሄደበትና የወቅቱ የቡሽ አስተዳደር “እንዝላልነት” ታክሎበት ሊመክን ችሏል። ይህን ህግ እንደገና ለማጸደቅ እንደሚሰሩ በግልጽ የተናገሩት ስሚዝ፣ “አሁን ፖሊሲያችንን ዳግም የመፈተሽያ ጊዜ ላይ ነን። ቁም ነገሩ ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር መቆሙ ላይ ነው። ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር እንቆማለን” በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገው ነበር።

በዚህ ይሁን በሌላ ምክንያት የመለስ ምትክ የሆኑት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የስኳር ሚኒስትሩ አቶ አባይ ጸሐዬ ሰሞኑንን “የዲሞክራሲ ማበብ የህልውና ጉዳይ ነው” በማለት ለተለያዩ መገናኛዎች በየፊናቸው የተናገሩትን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በስፋት ዘግቦታል። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታው ከመለስ እጅ በተካሄደው ርክክብ መሰረት አፈናውን አጠናክሮ የቀጠለ ስለመሆኑ ከየአቅጣጫው የሚጎርፈው መረጃ ከወትሮው በተለየ ይፋ እየሆነ ነው።

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየመራ ያለው ህወሃት በራሳቸው በአሜሪካኖቹ ቋንቋ ‘አሸባሪን መዋጋት’ በሚል ሰበብ ምዕራባውያንን ሲያልባቸው ቢቆይም “ሽብርንና ሽብርተኛነትን የመታገል ትብብር ግን የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመርገጥ ፍቃድ ማግኛ አይደለም። የመብት ረገጣ ሽፋን ሊሆን አይገባም” ሲሉ በጀርመን ሬዲዮ የመረረ ንግግር ንግግር የተናገሩት እንደራሴ ስሚዝ “ዛሬ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ጊዜ ላይ ነች” በማለት ከሁለት ወር በፊት የተናገሩትን ከዳር ያደርሱት ይሆን የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ወቅት ተደርሷል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. mimi says

    August 3, 2013 08:26 am at 8:26 am

    menem lewet ayemetam

    Reply
  2. koster says

    August 3, 2013 11:16 am at 11:16 am

    Please say no to woyane ethnic fascists, ethnic cleansing and state terrorism in Ethiopia. http://vimeo.com/18242221
    http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html
    http://www.ethiomarket.com/effort/effort_companies.htm
    http://www.ecadforum.com/2012/12/19/from-ethnic-liberator-to-national-atrocities-the-tale-of-tplf

    Reply
  3. Teshale says

    August 4, 2013 04:01 am at 4:01 am

    ጎልጉሎች የምር እየጎለጎላችሁ ነው። ለወትሮው በሰል ላለ ትንተና ነበር ወደ ጎልጉል የማመራው። ይህ ዜናችሁ ግን ከትኩስነቱ በተጨማሪ ኢሳትን ለመሳሰሉ ተደማጭነት ላላቸው ዜና አቅራቢዎች ምንጭ ሆኗል። ስራችሁ ከብስለት በተጨማሪ ትኩስነትንም ያካተተ ማድረጋችሁ ተነባቢነታቸሁን ይጨምረዋልና በርቱበት እላለሁ። እግዜር ይባርካችሁ።

    Reply
  4. yohannes says

    August 4, 2013 06:16 am at 6:16 am

    yemihonewn metebeq new

    Reply
  5. simon says

    August 12, 2013 06:33 am at 6:33 am

    I like what it is gonna happen. But the question stays the same, why do u think america stands for our right, what is gonna be left for the future generation if they take everything by this means. It is because i can sniff it that ain’t end in peace. So i think it is better to get rid of this pain in the butt for our country, by our own people.However the exernal pressure supportted only if they are out side.

    Reply

Leave a Reply to simon Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule