ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ግምባር ሲገዛ የኖረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የተከፈተውን የተማሪዎች ሰላማዊ ተቃውሞ “የሽብር ቡድን እንቅስቃሴ” በማለት በኢትዮጵያ ስም በተሰየመው የቴሌቪዥን ፕሮግራም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በ1997 ምርጫ ሽንፈት ለመቀበል ጥቂት የቀረው ህወሃት ሞት በወሰዳቸው መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ አማካኝነት የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ሥር ይሆናል በማለት በቀጥታ የህወሃት ታዛዥ በማድረግ በ197 ንጹኃን ዜጎች ላይ በአልሞ ተኳሾች ደረትና ግምባራቸውን በማለት እንደገደለ አሁንም “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” በማለት በተማሪና ነዋሪዎች ላይ ለመውሰድ ያቀደውን ፍጹም ኢሰብዓዊ እርምጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከህወሃት የጭከና ታሪክ አንጻር የመግለጫው ትርጉም ለመቀጣጫ እንዲሆን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የመግደያው ጊዜ … [Read more...] about “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” ህወሃት
News
ድሆች በደሃ ወገኖቻቸው ላይ ዘመቱ!!
“…. የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተገነባው በደሃ ልጆች ነው። እባካችሁን እንደናንተው የድሃ ልጆች ወገኖቻቹህን አትግደሉ። ተንደላቃችሁ የምትኖሩም ለዚህ ህዝብ ራሩለት። ለራሳችሁ ጥቅም ስትሉ ይህን ህዝብ አታስፈጁት…” ሲሉ አቶ በቀለ ገርባ ለኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊትና ለህወሃት ታማኝ አገልጋይ ሹመኞች ጥሪ አስተላለፉ። አሁን በተያዘው መንገድ ከተቀጠለ ለማንም አይበጅም ሲሉ በግልም ሆነ በጋራ ህዝብን የሚያከብር ታሪካዊ ውሳኔ እንዲወስኑ ተማጸኑ። አቶ ኦባንግ ሜቶና አርቲስት ታማኝ በየነ “የሞቱት ዜጎች ሞት የሁላችንም ሞት ነው” ሲሉ ሁሉም ያገባኛል በሚል ስሜት ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ። አቶ በቀለ በዲሰምበር ፩፫ ቀን ፳፩፮ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፣ መከላከያ ሰራዊት ማለት ህዝቡን ከአምባገነኖች የሚታደግ እንጂ የራሱን ህዝብ የሚገድል ባዕድ ሃይል … [Read more...] about ድሆች በደሃ ወገኖቻቸው ላይ ዘመቱ!!
ሰማያዊ እና ኦፌኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
ሰማያዊ ፓርቲና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በመስጠት፣ መንግስት የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመከታተል ለማጋለጥ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎችን በጋራ ለማካሄድ እንደተስማሙ ምክትል ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ከመድረክ ጋር እንዲሰራ በወሰነው መሰረት ዛሬ ከኦፌኮ ጋር በተደረገው ውይይት በሰማያዊ ፓርቲ በኩል ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጋሻው መርሻና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ መሃመድ … [Read more...] about ሰማያዊ እና ኦፌኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
“ኤርትራ የትግራይ ናት”
ኤርትራ የትግራይ አካል ናት የሚል አስተምህሮና የፖለቲካ ዝግጁነት ቅስቀሳ መጀመሩ ተሰማ። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ኤርትራ የትግራይ አካል ስለነበረች እንደገና መልሶ በመቀላቀል ታላቋን የአክሱም መንግስት ለመመሥረት የተያዘው አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ አስፈላጊው ሥራ እየተሰራ መሆኑንንም ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ እንደሆነ የሚጠቀሰው “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” የሚለው የህወሃት መፈክር ኤርትራን ከትግራይ በመቀላቀል የአክሱምን “ዳግም ልደት” (ህዳሴ) ለመተግበር የታቀደ ነው ተብሏል፡፡ አጀንዳው ባልታሰበ ወቅት ብቅ ያለው በመሃል አገርና በተለያዩ አካባቢዎች እየተነሳ ያለው ተቃውሞ መበራከቱ ያሳሰባቸው ለሚያነሱት የስጋት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው። የሻዕቢያን ተቃዋሚዎች በማደራጀት፣ በመደገፍና የስደት ፓርላማ በማቋቋም በህወሃት እየተካሄደ ያለው ሥራ የዚሁ ዕቅድ አካል … [Read more...] about “ኤርትራ የትግራይ ናት”
ጨለማው በረታ!! የትግራይ ተገንጣዮች ወስኑ!!
ወተት ሊገዛ የወጣ ልጅ በድንገት መሃል ግንባሩን በአልሞ ተኳሾች ይመታና ይወድቃል። ግማሹ ይሸሻል። አላስችል ያለው ርዳታ ለመስጠት ይሞክራል። በመካከል እናት የልጇን መውደቅ ትሰማለች። ጨርቋን ጥላ እያለቀሰች አስፋልት መሃል ተዘርሮ የወደቀው ልጇ ላይ ተጠመጠመች። በደም ተጨማልቃ እያነባች ህይወቱን ለመመለስ ፈለገች። ልጅ መሃል ግንባሩን ተወግቶ ነበርና ሕይወቱ አልፋለች። እናት አበደች። “እኔን፣ እኔ ልደፋ … …” አነባች። አስከሬኑን ለመውሰድ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተሰለፈች። ብዙዎች በተመሳሳይ አንብተዋል። በርካታ እስካሁንም እያነቡ ያሉ አሉ። ይህ የሆነው 1997 ዓም የህዝብ ድምጽ ከተሰረቀ በኋላ ህዝብ ለምን ድምጼ ተሰረቀ ብሎ ስለጠየቀ ነው። በገዳዮቹና ባስገዳዮቹ ዘንድ ይህ ልጅ “ጸረ ሰላም ኃይል” ነው። ይህንን አጭር መልዕክት ያስታወሱን አንድ የራስ ደስታ ሆስፒታል ሠራተኛ … [Read more...] about ጨለማው በረታ!! የትግራይ ተገንጣዮች ወስኑ!!
በሕዝባዊው ንቅናቄ ኢህአዴግ ሠግቷል
ለጎልጉል የእማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በላኩልን መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሣው ንቅናቄ ወደ ሲቪል ሠራተኞች ዘልቆ እንዳይገባ ስጋት ውስጥ የገባው ኢህአዴግ ሠራተኞችን ማባበልና ማንቃት ጀምሯል፡፡ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በሲቪል ሠራተኝነት የሚታወቁ ዜጎችን ኢህአዴግ በየቦታው መሰብሰብ ጀምሯል፡፡ እማኙ በላኩት መረጃ እንደገለጹት ለሁለት ቀን በሚካሄደው ስብሰባ በየወረዳው ለሚሰበሰቡ ሠራተኞች ቢያንስ ብር 300 አበል በመስጠት የማባበያ ስብሰባው እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በየወረዳው ካለው ሲቪል ሠራተኛ አንጻር ለአበል የታሰበው ብር በሚሊዮን ሊቆጠር እንደሚችል እማኙ ጨምረው አስረድተዋል፡፡ ዋናው አጀንዳ ሲቪል ሠራተኛው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ ተሳታፊ እንዳይሆን፤ እንዳይተባበር፤ ድጋፍ እንዳይሰጥ፤ … ሲሆን … [Read more...] about በሕዝባዊው ንቅናቄ ኢህአዴግ ሠግቷል
ተቃውሞ በዝምታ
* እስካሁን አምስት ሰዎች ሞተዋል ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ጋዜጠኝነት “አሸባሪነት” በመሆኑ መረጃ እንደልብ ባይገኝም ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የተማሪዎች ሰላማዊ የዝምታ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ እንደሚነገረው ዘገባ ከሆነ ስማቸውና የመኖሪያ ስፍራቸው የአንዳንዶቹም ከነፎቶዋቸው ይፋ የተደረገው መረጃ ላይ እንደሰፈረው የተማሪዎች ንቅናቄ ከተጀመረ እስካሁን የአምስት ወገኖች ህይወት በህወሃት ታጣቂዎች አልፏል፡፡ ዛሬ የተደረገው ተቃውሞ በበርካታ የተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ ሲሰማ በእንቅስቃሴው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በተለይ በአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ … [Read more...] about ተቃውሞ በዝምታ
ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
በመጪው ጥቂት ወራቶች ፈረንሳይ እስከ 160 የሚጠጉ መስጊዶችን ለመዝጋት መወሰኗ ተሰማ፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ ኢማም እንዳሉት በሥራ ላይ በዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ የእምነት ቦታዎች መዘጋት አለባቸው፡፡ በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ በፓሪስ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ጽንፈኛ አቋም አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት መስጊዶች መዘጋታቸውን የአገር አቀፍና የአካባቢ ኢማሞች ለመምረጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢማም ሃሰን ኤል-አላዊ ለአልጃዚራ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በቀጣይ ወራቶች በርካታ መስጊዶች እንደሚዘጉ አስረድተዋል፡፡ “ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋር በምናደርገው ውይይት እና ይፋ በሆኑት መረጃዎች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ታክፊሪ ንግግር የሚደረግባቸው ከ100 እስከ 160 መስጊዶች ይዘጋሉ” … [Read more...] about ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባርን በራሳቸው ልክ አሰፍተው፤ ተቃዋሚዎቻቸውን አስገድለው፤ ሌሎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርገው አገር በነጻ አውጪ ስም ለዓመታት የገዙት መለስ ሞተውም ሬሳቸውን እና በሕዝብ ደም የጨቀየውን “ሌጋሲያቸውን” ለመጠበቅ ዜጎች ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ፤ እምቢ ያሉ ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ለመለስ መዘከሪያ ቦታ ለማስቀቅ የተፈቀደበት ደብዳቤ ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በሰነድነት ደርሶናል፡፡ ደብዳቤው እንደሚያስዳው ሬሣ ለማክበር ሕያዋን እንዲገደሉ፤ እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሬሣ ሕያዋንን ለሞት ሲዳርግ! ህወሃት በኃይል በሚገዛት ኢትዮጵያ የማይሰማ ጉድ የለም፡፡ (ጎልጉል) … [Read more...] about የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው
ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ "የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም" የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት "በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት" በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ … [Read more...] about ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው