አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን የሚሰጡት አስተያየትና ንግግር ህወሃት/ኢህአዴግ ያፈጠጠበትን ችግር ብቻ ሳይሆን እርሳቸውም በቋፍ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ያመላከተ እየሆነ ሄዷል፡፡ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በሙስና ላይ ዘመቻ እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ይናገሩ የነበሩት ኃይለማርያም እስካሁን የሚታይ ለውጥ ሳያመጡ ቀርተዋል፡፡ በቅርቡ ከምሁራን ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይም “የተለያየ አመለካከትን የማይቀበል ሥርዓት የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውደቁ አይቀርም” ማለታቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግሩን በቀጥታ ከኢህአዴግ ጋር እያያዙ በግልጽ መናገራቸው በሕይወታቸው ላይ አደጋ እስከሚያመጣ የደረሰ መሆኑ ለጎልጉል የደረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም የግል ጠባቂዎቻቸውና አጃቢዎቻቸው ላይ የተደረጉ ለውጦችን ከዚህም ጋር የሚያያይዙ ወገኖች ኃይለማርያም በእርግጥም በችግር ውስጥ እንዳሉ ጠቋሚ መሆናቸውን … [Read more...] about ኃይለማርያም ቋፍ ላይ የደረሱ ይመስላሉ!
News
የአዲስ አበባውና የአሜሪካው ኢህአዴግ ቢሮ አይተዋወቁም
በሳምንቱ አጋማሽ የተሰማውን ዜና ያደመጡ፣ ከቅርብ ሆነው የሚከታተሉና ለጉዳዩ የቀረቡ እንደሚሉት የአዲስ አበባው ኢህአዴግና አሜሪካ ያለው የኢህአዴግ ቢሮ የማይተዋወቁበት ደረጃ ደርሰዋል። ኢህአዴግ በደብዳቤ የተረከባቸውን ስደተኞች በብሔር መትሮ “ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም” በሚል ወደ አሜሪካ መመለሱ የእለት ጉርስና የዘመን መሻገሪያ ድርጎ የምትመድበውን አሜሪካንን አስቆጥቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። ኢህአዴግ እንደ “አሸባሪ” የፊጥኝ አስሮ ከፍሎሪዳ ጠቅላይ ግዛት ማያሚ እስር ቤት ወደ ኢትዮጵያ የወሰዳቸው ወገኖች ከአገራቸው የወጡበትን ጊዜ ሳይቆጥር አሜሪካ ለመድረስ ብቻ እስከ አስራ አራት ወራት ፈጅቶባቸዋል። ስደተኞቹ በብራዚል፣ በኮሎምቢያ ጫካ ፣ በፓናማ ወንዝ አሳብረው፣ በሜክሲኮና በድምሩ 16 የሚደርሱ አገራትን አልፈው ነበር አሜሪካ ጥገኝነት የጠየቁት። እነዚህ ወገኖች ህጉ … [Read more...] about የአዲስ አበባውና የአሜሪካው ኢህአዴግ ቢሮ አይተዋወቁም
የዕርቅ ሃሳብ ከውስጥም ከውጭም ትኩረት ስቧል
አሁን ኢትዮጵያ ለደረሰችበት አሳሳቢ ደረጃ ዋናውና ብቸኛው መፍትሔ ሰላማዊ ዕርቅ መሆኑ በአገር ውስጥና በውጪ ልዩ ትኩረት እየሳበ መሆኑ ተሰማ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢህአዴግ በራሱ ችግር በየጊዜው ከሕዝብ ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱን፣ ይህንን ቅራኔ መፍታት ካልቻል መንገዱ የውድቀት እንደሚሆን አስጠነቀቁ። ሕዝብ በአፉና በእጁ እየገፋን ነው አሉ። ለጎልጉል የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርቡ የተጀመረውን “የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ምክርቤት” ተከትሎ የዕርቅ ሃሳብ አሁን ኢትዮጵያ ላለችበት ሁኔታ አማራጭ የሌለው እንደሆነ እየተጠቆመ ነው፡፡ በተለይ በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ጉዳይ ተከታታዮችና ፖሊሲ አውጪዎች ዘንድ ጉዳዩ ድጋፋቸውን የሚሰጡበት እንደሆነ መረጃው አመልክቷል፡፡ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተመሠረተው ምክርቤት ድጋፍ እንደሚያስፈልገው በመጠቆም ስለምክር ቤቱ … [Read more...] about የዕርቅ ሃሳብ ከውስጥም ከውጭም ትኩረት ስቧል
ህወሃት – 9 ስደተኞችን ደብዳቤ ጽፎ ከአሜሪካ ወሰዳቸው
ከተለያዩ አገራት አሜሪካ ገብተው የስደት ማመልከቻ ያስገቡ 9 ኢትዮጵያውያንን ህወሃት ተረከቦ ወደ አገር ቤት እንደወሰዳቸው ታወቀ። አንዱ ራሱን ለማጥፋት ሞከሮ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ቢሄድም የጤናው ሁኔታ አልታወቀም። ድርጊቱን አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ከህወሃት ተግባር በላይ በራሳችን አዝኛለሁ” ሲሉ ወጣቶቹን ለማዳን ያደረጉት ጥረት መረጃው ዘግይቶ ስለደረሳቸው አለመሳካቱን አመለከቱ። “ለቤተሰቦቼ የት እንዳለሁ እንኳን ነግሬያቸው አላውቅም” ሲል የተናገረውን ወጣት ጨምሮ ህወሃት የተረከባቸው ኢትዮጵያዊያን ወግኖች አሜሪካ ለመድረስ እስከ 14 ወራት ፈጅቶባቸዋል። በብራዚል፣ በኮሎምቢያ ጫካ አቋርጠው፣ በፓናማ ወንዝ ተሻግረው፣ በሜክሲኮ አድርገው በአጠቃላይ እስከ 16 የሚደርሱ አገራትን አልፈው በተለያዩ መንገዶቸ አሜሪካ ደርሰው ጥገኝነት የጠየቁት ወገኖች ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ … [Read more...] about ህወሃት – 9 ስደተኞችን ደብዳቤ ጽፎ ከአሜሪካ ወሰዳቸው
ኦህዴድ ሳያገግም፤ ብአዴን ሊደገም?
ኢትዮጵያን በተገንጣይ ስም የሚመራው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት፣ የገጠመው ቀውስ እየተለጠጠበት ነው። ኦህዴድ አደረጃጀቱ ሊጠገን በማይችልበት ሁኔታ ተናግቶበታል። ይኽው ወረርሽኝ ወደ ሌሎች ገባር ድርጅቶች መስፋፋቱ የማይቀር ቢሆንም ብአዴን ውስጥ ቀውስ ስለመነሳቱ መረጃዎች ከቀድሞው በላይ ጎልተው እየወጡ ነው። በ1997 ምርጫ ኢህአዴግን ከውድቀት ጉድጓድ ያወጣው ኦህዴድ፣ ህወሃት በአንጃ ተቧድኖ ሲባላ የመለስን ወገኖች የታደገው ብአዴን አሁን ለህወሃት መከራ ሆነውበታል። አጋር የሚባሉት ድርጅቶችም ውስጥ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ የራሱ የህወሃት መገናኛዎች እየመሰከሩ ነው። የችግሩ አሳሳቢነት ቀላል ባለመሆኑ ኦሮሚያና ጋምቤላ ተሸንሽነው “በጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር” ሥር ወድቀዋል። ይህንኑ እውነት አሁንም የራሱ የህወሃት ልሳኖች አምነው ይፋ አድርገውታል። አንድ … [Read more...] about ኦህዴድ ሳያገግም፤ ብአዴን ሊደገም?
“የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?
ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተቃውሞና ዓመጽ የተወጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ በአስሩም ክፍለከተሞች የሚገኙ እስከ 600 የሚደርሱ የመሬት ባለሙያዎችን ካገደ በኋላ የአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ሞሳኞች ያላቸውን 85 አመራሮችና ሠራተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ “የመሬት ከበርቴውን” አባይ ጸሃዬንስ ማን ይደፍራቸው ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡ በአባይ ጸሃዬ “ልክ እናስገባለን” ተግባራዊ እንዲሆን የታሰበው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ከተስተጓጎለ በኋላ ህወሃት/ኢህአዴግ ማስተር ፕላኑን “ትቼዋለሁ” ቢልም የኦሮሞ ሕዝብ ያስነሳው ተቃውሞ ግን እስካሁን አልበረደም፡፡ “መልካም አስተዳደርን አሰፍናለሁ” በሚል ኢህአዴግ የሕዝቡን ቀልብ ለመሳብ ከላይ ታች እየተራወጠ ነው የሚሉ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት ኪራይ ሰብሳቢነት ለመዋጋት በሚል … [Read more...] about “የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?
“ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ታክሲ አሽከርካሪ
“ሁላችንም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክሥራ ውጪ እንሆናለን።’’ በዛሬው ዕለት የታክሲ ማቆም አድማ ካደረጉት የታክሲ አሽከርካሪዎች በከፊል፡፡ በአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ደንብን ለማስከበር ከአምስት ዓመት በፊት የወጣውና በከፊል ሲተገበር የነበረው ሕግ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ በመጀመሩ የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች በሙሉ በዛሬው ዕለት ሥራ የማቆም አድማ መተው ውለዋል፡፡ ፌደራሉ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ትናንት ባወጣው መግለጫ ትግበራው ለሦስት ወር መራዘሙን አስታውቋል፡፡አሽከርካሪዎቹ ደግሞ “ለሦስት ወር ማራዘም መፍትኄ አይደለም ዘላቂ መፍትሄ እንፈልጋለን” ይላሉ፡፡ አሽከርካሪዎችን የአዲስ አበባን ፖሊስ ኮሚሽንን ያነጋገረችው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘገባ … [Read more...] about “ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ታክሲ አሽከርካሪ
ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!
በኦሮሚያ የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኛነትና ዓመጽ ተከትሎ ስለጠፋው የሰው ህይወት እርግጠኛ አሃዝ የሚጠቅስ አልተገኘም። ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የአገር ውስጥ ቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚሉት የህወሃት አንጋቾች ከ200 በላይ ንጹሃንን ገድለዋል። በነጻ አውጪ ስም አገሪቱን እየመራ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት፣ አመጹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ ቆይቶ በስተመጨረሻ ችግሩን ቆንጥሮ አስመራ ልኮታል። ወታደርና ከባድ መሣሪያም ወደ ድንበር አስጠግቷል። መፍትሔው ጭፍን ብሔረተኝነት ሳይሆን ሁሉንም በሰብዓዊ ፍጡርነት ማየት ነው የሚሉ አካላት “ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልቡና ያለው ያስተውል” እያሉ ነው፤ ርምጃቸውንም ከጊዜ ጋር አዋዝተዋል። ህወሃት የትጥቅ ትግልን የራሱ “ንግድ ምልክት” አድርጎ መውሰዱ የማይዋጥላቸው “ለህወሃት ብቻ የትጥቅ … [Read more...] about ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!
በአዲስ አበባና አካባቢ የታክሲ ሥራ ማቆም ዓድማ እየተካሄደ ነው!
የካቲት 14 የጸደቀውን በተለይ ታክሲዎችን የሚመለከተው የአሽከርካሪዎች ሕግ በመቃወም ለሁለት ቀናት የተጠራው ዓድማ በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለከተሞች አድማው እየተካሄደ ከመሆኑ ባሻገር ዓድማውን በመጣስ ታክሲቸውን ሲያሽከረክሩ የነበሩ “አድርባይ ሹፌሮች” ላይ በተለይ በአውቶቡስ ተራ፣ በጦር ኃይሎች እና በፈረንሣይ ሌጋሲዮን አካባ የተገኙ ታክሲያቸው ላይ ጥቃት የደረሰ መሆኑን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አድማው ለሰኞ እና ማክሰኞ እንደተጠራ እሁድ የካቲት 20 ህወሃት/ኢህአዴግ በግሉ በከፈተው ፋና ብሮድካስቲንግ አማካኝነት በለቀቀው መረጃ ታክሲ ነጂዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ለሦስት ወራት ተራዝሟል ቢልም ዓድማው ግን ቀኑን ጠብቆ ተካሂዷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ወገኖች የሚሰማው መረጃ እንደሚጠቁመው ዓድማው ወደ … [Read more...] about በአዲስ አበባና አካባቢ የታክሲ ሥራ ማቆም ዓድማ እየተካሄደ ነው!
“ለአውሮጳውያን (ስለ ምርጫው ውጤት) ‘ሌክቸር’ አልፈልግም ብዬ ነግሬአቸኋለሁ”
በዑጋንዳ በተካሄደው ምርጫ አገሪቱን ለ30 ዓመት የመሩት ዮዌሪ ሙሰቪኒ ለአምስተኛ ጊዜ “አሸንፈዋል”፡፡ ተቀናቃኛቸው ምርጫው መጭበርበሩንና እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡ አውሮጳውያንና አሜሪካ ምርጫው ዓለምአቀፋዊ ሕግጋትን የጠበቀ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ሙሰቪኒ ዋናው ዓላማቸው እስካሁን ኢትዮጵያን ያላካተተውን የምስራቅ አፍሪካ ፌዴሬሽን መመሥረት እንደሆነና ስለምርጫው ከአውሮጳውያን “ሌክቸር” እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል፡፡ በምዕራባውያን ድለላና ድጋፍ በትጥቅ ትግል ወደ ሥልጣን የመጡት መለስ ዜናዊ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ፖል ካጋሜ እና ዮዌሪ ሙሰቪኒ “አዲስ የአፍሪካ መሪዎች ውልድ (ዘር)” በመባል በቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን እንዳልተሞካሹ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ፍጹም አምባገነኖች ሆነዋል፡፡ መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድማቸው ኖሮ ከሌሎቹ ጋር በመሆን ማቆሚያ የሌለውን ሥልጣናቸውን … [Read more...] about “ለአውሮጳውያን (ስለ ምርጫው ውጤት) ‘ሌክቸር’ አልፈልግም ብዬ ነግሬአቸኋለሁ”