• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”

March 9, 2013 03:18 am by Editor 10 Comments

“አማራ መሆን ወንጀል ነው? የሌሎች ብሔረሰብ አባላት በፈለጉበት ክልልና ስፍራ ይኖራሉ። አማራ ክልል ውስጥ ሰፊ መሬት ወስደው የሚኖሩ አሉ፤ የሚነካቸው የለም። አማራው እየተመረጠ ለስደት፣ ለመከራ፣ ለእንግልት ይዳረጋል? እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል? ክልሉን እንመራለን፣ የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የት ናቸው? ያሳዝናል፣ ለአማራው አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አማራው አለቀ …”  ሲል በስልክ ለጎልጉል አስተያየቱን ሰጠ። መናገር አይችልም፤ ሲቃ ልሳኑንን አንቆ ይዞታል።

ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ያነሳል። 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታ እየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው። በድንገት ገበያው ታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎች በቅጽበት ተረሸኑ። ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖች ድምጻቸውን አላሰሙም ነበር። አሁንም በተቆራረጠ አንደበት አስተያየቱን ቀጠለ።

በወቅቱ ፓዌ እንደነበር ያስታወሰው አስተያየት ሰጪ “አሰፋ ኢናቦ” ሲል ስም ጠራ። አሰፋ ኢናቦ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ ነበር። ድንገት በደረሰው ጭፍጨፋ የተበሳጩ ከመንደር አራት ስምንት ኪሎሜትር ርቆ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ አሰፋ ኢናቦን አስገድደው ወሰዱት። በመጨረሻም ሰፋሪውን እያሳዩ የበቀል ኃይላቸውን አሳረፉበት፤ ቦጫጨቁትና እዛው ተቀበረ። በስፍራው ስለተደረገው ሁሉ በቂ መረጃ ያለው መሆኑን የሚናገረው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው በቀትር በአደባባይ ህዝብ የጨፈጨፉትና ያስጨፈጨፉት አልታሰሩም። ህግ ፊት አልቀረቡም። ለይስሙላ ታስረዋል ተብለው ተለቀዋል።

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የሚኖሩት የሺናሻ ብሔረሰብ አባላት ሲሆኑ ቀደም ሲል ጀምሮ “አገሩ የናንተ ነው። ባለመብቶች እናንተ ናችሁ። ውሳኔው ሁሉ የራሳችሁ ነው” ስለተባሉ በክልሉ በአንድ ትምህርት ቤት የሚማሩ የአማራ ብሔር አባላት እኩል የትምህርት እድል እንደማያገኙ፣ እሱም የችግሩ ሰለባ እንደሆነ ያስረዳል። ነጻ ሚዲያ ቢኖር ግፉ በተዘረዘረ ነበር ሲል ቁጭቱን ይገልጻል።

አገሬውን “ሆን ብለው ክፋት እየጋቷቸው በየጊዜው አማራ ውጣ፣ አማራ ሂድ …” በማለት እንደሚፎክሩ ያስረዳው ቅሬታ አቅራቢ አስገራሚውና አስደንጋጩ ጉዳይ የአማራ ክልል “እመራዋለሁ” የሚለው አካል ለህዝቡ መከራከር አለመቻሉ ነው።

በጉራፈርዳ በክልሉ መንግስት ትዕዛዝ የከፋ ወንጀል ሲሰራ፣ አንደኛ ክፍል ለሚማር ህጻን “ክልሉን ልቀቅና ውጣ” የሚል ደብዳቤ ሲሰጥ ተቆጣጣሪና ተቆርቋሪ አለመኖሩ መጨረሻ የሌለው ግፍ አማራው ላይ እንዲካሄድ ስምምነት ያለ እንደሚያስመስል የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም።

ሰሞኑን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል አማራውን የማፈናቀል ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ሆነ እንጂ ችግሩ የቆየና ማዕከላዊ አገዛዙም ሆነ የክልሉ መስተዳድር ጠንቅቀው የሚያውቁት ጉዳይ እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ። የካቲት 28፤2005 (ማርች 7፤2013) የተላለፈው የአሜሪካን ሬዲዮ አማርኛ ክፍል ያነጋገራቸው የችግሩ ሰለባ አሁን ያለውን ችግር የሚገልጹት በተማጽኖ ነው።

በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡሎን ወረዳ የሰፈሩና ከ15 እስከ 20 ዓመት በረሃውን አልምተው፣ ወልደው ከብደውና ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከየካቲት19 እስከ 30 ቀን 2013 ዓም መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዝዘዋል። ለቪኦኤ የተማጽኖ ቃላቸውን ያስተላለፉት አቶ የሺህ ዋስ ትንሳኤ ድምጻቸው ያሰሙት ባህር ዳር “መንግስታቸው” ደጅ ቆመው ነው።

ባህር ዳር ሆነው “ሰሚ አጣን” በማለት ድምጻቸውን ያሰሙት አቶ የሺህ ዋስ “ለክልሉ መንግስት ለምን አመለከታችሁ በሚል ስለምንታሰር እባካችሁ ለፌደራሉ መንግስት አሳውቁልን” ሲሉ ተደምጠዋል። አገር ቤት የመንግስትም ሆነ “የግል” የሚባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ጆሮ የነሷቸው በሚመስል ኑዛዜ ያቀረቡት አቶ የሺህ ዋስ “ፈልሶ የመጣ፣ ውጣ አማራ” እየተባሉ የውጭ አገር ዜጋ እንኳን በማይጠራበት ሁኔታ ክብረ ነክ ስድብ እንደሚሰደቡ አመልክተዋል።

ከመንግስታችሁ ሸኚ አምጡ መባላቸውን፣ በርካቶች ሸኚ ለማምጣት ከብቶቻቸውን በርካሽ መሸጣቸውን፣ ሸኚም ካመጡ በኋላ ተቀባይነት አለማግኘቱን አቶ የሺህ ዋስ ያስረዳሉ። አያይዘውም ባፋጣኝ ክልሉን ለቀው ካልወጡ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ምን ሊከሰት እንደሚችል የዛቱባቸውን ተናግረዋል።

የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን (ፎቶ: ምንጩ ያልታወቀ)

ባስቸኳይ ክልሉን ለቀው ካልወጡ “የፌደራል ፖሊስ ደብድቦ ያስወጣሃል” የሚል ማስፈራሪያ የደረሳቸው መሆኑንን ያመለከቱት አቶ የሺህ ዋስ፣ የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ማግኘትና ማነጋገር አለመቻላቸውን ከክልሉ መንግስት መቀመጫ ባህር ዳር ሆነው መናገራቸው ጉዳዩን አወሳስቦታል። ለሰሚውም ግራ ሆኗል። ቪኦኤ እንዳለው የክልሉን ባለስልጣናትም አግኝቶ ማነጋገር አልተቻለም።

ለጊዜው የክልሉ መንግስት ማረፊያ እንዲያዘጋጅላቸው ወይም የሚሰፍሩበት ቦታ እስኪመቻችላቸው ከክልሉ ጋር በመነጋገር አደጋ ላይ ለሚገኙት ከአምስት ሺህ  በላይ ሰዎች መፍትሔ እንዲያፈላልግ የተጠየቀው የክልሉ መስተዳድርም ሆነ “የጭቁኑ አማራ ተወካይ ነኝ” የሚለው ብአዴን/ኢህአዴግ ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ያሉት ነገርም የለም።

የአማራ ክልል ለምና ሰፊ መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት፣ ሁመራንና ወልቃይት ገባውን ለትግራይ ክልል አሳልፎ በማስረከብ የሚታወቀውን ብአዴንን የሚመሩት አቶ ደመቀ መኮንን በአማራው ስም “ቅምጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር” ሆነው በውለታ መሾማቸው የሚታወስ ነው።

(ፎቶ፡ CSSP)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    March 9, 2013 12:12 pm at 12:12 pm

    hodam Demeke Mekonnen is servant of woyane ethnic fascists and does not represent his ethnic group (whether he be Agaw or Amhara) or his religion. Say no to woyane ethnic fascists and state terrorism in Ethiopia.

    Reply
  2. Adamu says

    March 12, 2013 03:18 pm at 3:18 pm

    በተደጋጋሚ ከአንድ አስተያየት ሰጭ በተለያዩ ብሎጎች የማነበው ነገር አለ፡፡ይህ አስተያየት ደግሞ ወያኔ/ሻእብያ የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀከት አስፈፃሚ ቅጥረኛና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ኢትዮጵያ ባንዳዎች ናቸው የሚል ነው፡፡ይህ አባባል አስካሁን ልቤ ውስጥ የተፃፈ ነገር ነው፡፡ወያኔ እንደ ደርግ ዝም ብሎ ተራ አምባገነን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በከፋ የባእዳን ቅጥረኛ ነው፡፡ብዙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች ወያኔን አምባገነን ወዘተ እያሉ ይጠራሉ ለእኔ በቅጡ የተዋጠልኝ እውነተኛ ድብቅ ማንነታቸው ግን ከላይ የተጠቀሰው የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀከት አስፈፃሚ ቅጥረኛ እየተባለ በተደጋጋሚ የተጠቀሰው አይነት አስተያየት ነው፡፡ይህ አይነት ዘር እየመረጡ ማፈናቀልና እረስ በርስ በከፋፍለህ ግዛው ስልት ማናከስ ደግሞ የለየለት ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ነው፡፡ከአምባገነንትና ከዲሞክራሲ ጋር ብዙም የሚገናኝ ነገር አይደለም፡፡ምክንያቱም ያለፉት ሰርዓቶች አምባገነን ነበሩ ነገር ግን ይህንን አይነት አይን ያወጣ የከፋ ጥፋትና ወንጀል በሀገር ላይ በህዝብ ላይ አልፈፀሙም፡፡ወያኔ መሬት ለባእዳን ሰዎች በዶላር እየቸበቸበ አማራውን ግን እያፈናቀለ ወደ ክልልህ ግባ ማለቱ ይህ ሃይል ለባእዳን ሃይሎች የቆመ የባእዳን ቅጥረኛ እንደሆነ በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡በዚህ አይነት አዲስ አበባ ውስጥ ፎቅ የገነቡና ኢኮኖሚውን የተቆጣጠሩና ሌላውም ክልል ውስጥ ሰፋፊ የመሬት እርሻ ያላቸው ሀብታም ትግሬዎች ለምን ወደ ክልላቸው አይሄዱም፡፡ወያኔ የሚሰራው ይህ አደገኛ መሰሪ ስራ ቆሜለታሁ ለሚለው ትግሪኛ ተናጋሪው ሳይቀር ወደፊት አደጋ ያዘለ ነገር ነው፡፡በእርግጥ ጥቂት የወያኔ የበላይ አለቆች የመጨረሻ ግባቸው ዶላር እየተሰጣቸው የባእዳን ሃይሎችን ፍላጎት ማስፈፀም ነው፡፡ከውጪ ባእዳን ሃይሎች የተሰጣቸው የመጨረሻ ግባቸው ደግሞ ሀዝብን እረስ በርስ አናክሰውና አፋጀተው ሲያበቁ ሀገሪቱን ማዳከምና በስተመጨረሻ መበጣጠስ ነው፡፡ይህንን መጥፎ አካሄድም አጠንክረው መያዛቸው ሲታይ ሰይጣናዊ ስራቸውን ልክ የቅድስና ተልእኮ አድረገው የቆጠሩትም ይመስላል፡፡ነገር ግን እንደተባለው እንደ ይሁዳ ከርስቶስን ለ30 ዲናር አሳልፎ እንደሸጠው ህዝብን ከመሬት እያፈናቀሉ ኢትዮጵያን ለዶላር ሸጠው ሲያበቁ የሰበሰቡትን የግፍ ሀብት በሰላምና በጤና ይበሉት ይሆንን ወይነስ እንደ አኬልዳማ የደም መሬት የሚገዛበት አሳዛኝ የውደቀት ፍፃሜ ይሆን ያሰኛል፡፡

    Reply
  3. ababu says

    March 12, 2013 05:17 pm at 5:17 pm

    aye demeke behizb dem tikelidaleh, nege megbiahin ewoke, ande ken ye hizb bisot yimetabachihual.

    Reply
  4. ababu says

    March 12, 2013 05:20 pm at 5:20 pm

    Amhara people have no real representative because most of them speak amharic and have either Tigrean origin or Eritrean origin. Most of the Amhara lands have been annexed to Tigray.

    Reply
  5. Senait says

    March 12, 2013 05:21 pm at 5:21 pm

    Very sad and I have no idea to which level shall we tolerate this fascists.

    Reply
  6. Gudu Kassa says

    March 13, 2013 12:53 am at 12:53 am

    we Ethiopian citizen who are members of any opposition parties should have to enforce the political and/or civic organization inwhich we are members’ to act againist the ethnic cleansin crime committed by TPLF tyranne regime againist the the Amhara ethinic group specifically & objectively and Ethiopian in general.

    Reply
    • Tazabi says

      March 21, 2013 06:35 pm at 6:35 pm

      Good point Ato Gudu Kassa,
      Take a look at Shengo for instance; it did not give press releas about the displacement of Amaras from Gura Ferda and other parts of Ethiopia. Shengo is not the only opposition party that ignores Amara issues, but for our dismay many of the opposition parties don’t give a damn about Amara. Take G7, do they have Amara in their leadership? The most imbaresing part in all of this sidelining Amara conspiracy is the part Amara himself play. It is the Amaras who gives life to all opposition parties. The majority members without leadership positions are Amara. Amaras are the one that funds the parties and organizations the most. When demonstrations and meetings called it is the Amaras that take part the most. BUT when it comes to defend Amara from the apartheid TPLF non of these opposition parties show solidarity. Amara must wake up and demand respect!

      Reply
  7. Save-Ethiopia says

    March 13, 2013 04:10 pm at 4:10 pm

    ኢትዮጵያ አፍሪካና መላው ታዳጊው አለም ይህንን አይነት መፈናቀልና ስደት እየፈጠረ ካለው ከግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ የጭቆናና የምዝበራ መዳፍ ስር ነፃ ሊወጣ የሚችለው እንደ ሁጎ ሻቬዝ አይነት ዳግማዊ ሁጎ ሻቬዝ ሲፈጠር ብቻ ነው፡፡ወያኔዎች እንደ ቅጥረኛ ተላላኪ አውቀውምትም ይሁን ሳያውቁት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በረቀቀና በተቀነባባረ መንገድ እያስፈፀሙ ያሉት የዚህን የአለቃቸውን የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ነው፡፡የቬንዝዋላው መሪ ሁጎ ሻቬዝ ደግሞ ይህንን የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በፅናት የታገለና ለድሃው የሀገሩ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላዩ የአለም ድሃ ህዝብ በፅናት የቆመ ሰው ነበር፡፡
    ኢትዮጵያውያን ዌብ ሳይቶች ለምን ስለ ሁጎ ሻቬዝ ሞት ትንፍሽ አትሉም እረ?
    ይህንን ያህል ዝም ያላችሁት ከወያኔ የጭቆናና የዝርፊያ መዳፍ ለመላቀቅ ይረዱናል ነፃ ያወጡናል ብላችሁ ተስፋ የምታደርጉት የአሜሪካና የምእራባውያን መንግስታት እንዳይቀየሙ ነውን ?
    ለማንኛውም ይኽ ሰው ማነው እረ ?
    የሚከተለውን በጥሞና ያንብቡት፡፡
    http://www.paulcraigroberts.org/2013/03/12/hugo-chavez-paul-craig-roberts-4/

    Reply
  8. ዱባለ says

    March 13, 2013 06:10 pm at 6:10 pm

    ይሄማ በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት እንደሚባለው ነገር አደራጋችሁት:: ለተፈናቀለው የጉራ ፈርዳ አማራ ህዝብ ግሎባል ካፒታሊዝምን መቃወም ምንም ፋይዳ አይሰጠውም:: ይሄኮ ጊዜ የሚስጥ ጉዳይ አይደለም:: በአስቸኳይ ወደ ተፈናቀለበት ቀዬው ተመልሶ ኑሮውን እንዲጀምርና ከልመና እንዲላቀቅ ለማድረግ እርምጃ እንዲወሰድ መታገል ሲገባ ግሎባል ካፒታሊዝም እያልን አንቀልድ!! መፍትሄው ዘርን ከዘር ከሚያናክስ ከወያኔ የአገዛዝ ፍልስፍና ኢትዮጵያን ማላቀቅ ነው:: ይሄው ችግር ደግሞ እዛው ፊታችን ስር ያለ አይኑን ያፈጠጠ ሆኖ እያለ የምን በአለም ዙርያ መዞር ያስፈልጋል:: ጠላት ያለው እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው::

    Reply
  9. Birhanu kebede says

    March 15, 2013 02:20 am at 2:20 am

    The innocent Amhara people have been kept down by the servant of TPLF who are Amhara by ethnic that do not represent the Amhara people. Demeke Mekonnen is one of those puppets and slaves who serves for TPLF. Beseferut kunna mesefer endale altegenezebe yihon Ato Demeke. Wake up Mr Demeke it is high time to refrain from taking any illegal action like torturing, harassing and abusing against Amhara.

    Reply

Leave a Reply to koster Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule