
ጀርመናዊው ገርድ ሙለር ቀጣዩ የUNIDO ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመርጠዋል
አርከበ ዑቅባይ ለተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት/UNIDO/ ዋና ዳይሬክተነት ሳይመረጥ ቀረ።
በኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ላይ የካበተ ልምድ እንዳላቸው የሚታመንባቸው፣ የጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆንና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የኃላፊነት ስራዎች ላይ ያገለገሉት አርከበ ከጀርመኑ ገርድ ሙለር እና ከቦልቪያው በርናንዶ ካልዛዲላ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ነበር።
ፉክክሩን አሸንፈው እንደሚመረጡ የብዙዎችን ቅድመ ግምት አግኝተው የነበረ ቢሆንም እንደታሰበው ሳይመረጡ ቀርተዋል።
የጀርመን የፌዴራል የምጣኔ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር ቀጣዩ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመርጠዋል።
ሙለር በዋና ዳይሬክተርነት የተመረጡት በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ቦርድ አማካኝነት ነው።
የቦርዱ ምርጫ የድርጀቱ ከፍተኛ አካል በሆነውና እንደፈረንጆቹ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 3/2021 በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ይጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።
አዲሱ ተመራጭ ጀርማናዊው የወቅቱ የኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር “ ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትን መምራት ይችላል በሚል፤ ለተጣለበኝ እምነት እጅጉን አመሰግናለሁኝ ”ብሏል።
ገርድ ሙለር “ዓለም አቀፍ ቀውሶችን ለማሸነፍ ጠንካራና ሁለንተናዊ ምላሽ ያስፈልጋል ። አሁን እያየነው ያለው ወረርሽኝ ለሁላችን የማንቂያ ደውል መሆኑን አምናለሁኝ።በኮቪድ-19 እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ለሚደረግ ውጊያ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሀገራት ታዳጊ ሀገራትን ለመደገፍ ከፍተኛ ቁርጠኝነትን ይጠይቃቸዋል።ተጨማሪ ፈጠራዎች እና ኢንቨስትመንቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂዎች እና የእውቀት ሽግግር እንፈልጋለን። ግባችን ፍትሃዊ ግሎባላይዜሽን ፣ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራ እና ለታዳጊ ሀገሮች የበለፀገ የወደፊት ዕይታ መፍጠር ነው” ሲሉም አክሏል።
የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት/UNIDO/ አጀንዳ 2030፣ የፓሪስ ስምምነት፣ የባዮሎጂካል ዳይቨርሲቲ ስምምነት፣ ዘላቂ ልማት ግቦችና ሌሎች ዓለም አቀፍ ፕሮገራሞች ከመፈጸም አኳያ የመሪነቱ ሚና ሊጫወት ይገባል እንዲሁም ይችላልም ነው ያሉት ገርድ ሙለር።
የበለጸጉ አካላት ለዚሁ ራዕይ እውን መሆን የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባቸውም ጭምር።
ሙለር እንደፈረንጆቹ ከ2013 አንሰቶ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትን ሲመሩ የቆዩቱን ቻይናዊው ሊ-ዮንግን የሚተኩም ነው የሚሆነው። (አል-አይን)
ለአርከበ አለመመረጥ ዕፎታን ይሰጣል በማለት አስተያየት የሚሰጡ አንዱ ምክንያት በማድረግ የሚያቀርቡት በብዙ ድጋፍ ለዓለም ጤና ጥበቃ ኃላፊነት የተመረጠው የቴድሮስ አድሃኖም አሁነኛ ሁኔታ ነው ይላሉ። ቴድሮስ እንዳይመረጥ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የበኩሉን አስተዋጽዖ ቢያደርግም ብዙዎች ግን በቅንነት ነገሩን በማየት ድጋፍ ሰጥተውት ነበር። ሆኖም አሁን ባለው ሥልጣን በመጠቀም በግልጽ የትህነግ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ ኢትዮጵያን አደጋ ውስጥ በሚጥል እኩይ ተግባር ተሰማርቷል። ቴድሮስ አድሃኖም በሌብነት፣ በወሲብ ጥቃት፣ በዘረኝነት፣ ወዘተ ከፍተኛ ክስ ቀርቦበት ዳግመኛ እንዳይመረጥ ዘመቻ ተከፍቶበታል። ጉዳዩ ተሳክቶ ካልተመረጠ የመጀመሪያው የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ስደተኛ ዳይሬክተር ይሆናል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
አሁን ስንት የሃገሪቱ አንገብጋቢ ጉዳይ እያለ ይህን ዜና ብላችሁ ትለጥፋላችሁ? ለእኔ ይህ ከወሬም የሚገባ አይደለም። ወያኔ ተያዘብኝ የሚለውን መሬት ለማስመለስ የአማራ አርሶ አድሮችን እያረደ፤ በሌላ መልኩ ምንም ሳይታሰብና ሳይጠበቅ የአማራ ልዪ ሃይልና የመከላከያ ሰራዊት በአላማጣና በኮረም እንዲሁም በማይጸብሪ ጠቅሎ በመውጣት ህዝቡን ለመከራና ለገዳይ አጋልጦ በፈረጠጠበት የሴራ ፓለቲካ ላይ ቆመን ስለ አንድ የቀድሞ የወያኔ ሰው መመረጥና አለመመረጥ መጣጥፍ ማቅረብ ወሬ የጠፋባችሁ ያስመስላችሁሃል።
አሁን የአልጄዚራ ተወካይ ከሁመራ ሆና በተቆራረጠ የስልክ መስመር የትግራይ የመከላከያ ሃይል እያለች የምትጠራው ከላይ የተጠቀሱትን ቦታዎችን እንደተቆጣጠረና አልፎ ተርፎም ማይካድራንና ሁመራን ለመያዝ እየተዘጋጀ መሆኑ ዘግባለች። ያው የእነርሱ ወሬ የሚደምቀው እኛ ስንጋደል በመሆኑ ደስ ያላትም ትመስላለች። ሌሎችም ሃገር በቀልና የውጭ ሚዲያዎች ይህኑ ወሬ አናፍሰውታል።
ዶ/ር አብይ አሜሪካ ስላስፈራራችውና የአውሮፓ ህብረት ስለጮኹበት ይህን ትዕዛዝ ሰቶ ከሆነ የራሱን ውድቀት ያፋጥናል። ከሊቢያው ጋዳፊ ሊማር ይገባው ነበር። ምዕራቡ ዓለም ምንም ዓይነት ትዕዛዛቸውን ተቀብለህ አሜን እሺ ብትልም ገፍትረው ገደል ከመክተት አይመለሱም። የአፍሪቃ ፓለቲካ ለእነርሱ ማላገጫ ነው። ዛሬ በሱዳንና በግብጽ የቀጥታና የእጅ አዙር ሴራ ፍዳዋን የምታየው ኢትዮጵያ የአሜሪካ እጅ በእነዚህ ሃገሮች ጀርባ እንዳለበት መገመት ቀላል ነው። ከ 20 ዓመት በህዋላ አፍጋንስታንን ለአክራሪዎች እንካችሁ ብለው ያስረከቡት አሜሪካኖች ለሰው ልጆች በጎነት አይገዳቸውም። በተደጋጋሚ እንዳልኩት ይህ ሃቅ አልዋጥለት ያለ ሁሉ የኋላ ታሪካቸውን ማየት በቂ ይሆናል። ለዛ ነው ከ 245 ዓመት የአሜሪካ ነጻነት በህዋላ ዛሬም በጥቁሮች ላይ ድብቅና ይፋዊ ሴራ በአሜሪካ ውስጥ የሚፈጽሙት። ወዬ ለአማራ ህዝብ። ወያኔ በማይካድራ ካደረገው የበለጠ ግፍ ይፈጽማል። ያኔ አሁን ለወያኔ ያላዘኑ ሚዲያዎች ሁሉ ዝም ጭጭ ነው የሚሉት። ውሻ በበላበት አይደል የሚጮኸው። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ በጣም ጅላ ጅል ነገር ነው። እንደ ገደል ማሚቶ የተነገረውን ብቻ የሚያስተጋባ። አሁን ደግሞ አልፎ ተርፎ የኦሮሚያ ልዪ ሃይል፤ የአማራ ልዪ ሃይል ወዘተ እያለ ሲቀባጥር መስማት ምንኛ ያበግናል። ባጭሩ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሸረቡት የሴራ ጅማሪ ለመሆኑ የሚጠቀሙባቸው ቃላቶች በግልጽ ያሳያሉ። እኔ እምለው የመከላከያ ሃይሉ ሮጦ ሮጦ የት ላይ ሊቆም ነው? የወያኔ አላማ እኮ ቤ/መንግስት መግባት ነው።
አሜሪካ ባለፉት ዘመናት በኢትዪጵያ ታሪክ ላይ ሶስት ጊዜ ተንኮልና ክህደት ፈጽማለች። የመጀመሪያው በጣሊያኑ ዳግመኛ ግጭት ሲሆን በሊግ ኦፍ ኔሽን ብዙ የፓለቲካ ጫና በማድረግ ጣሊያን እንዳትወረን ማድረግ ሲቻላት ከእንግሊዝና ከፈረንሳይ ጋር በመሻረክ በመርዝ ጋዝ እንድንጠቃ አድርጋለች። ሁለተኛ ንጉሱ በወታደር መንጋ ከስልጣን ሲሽቀነጠሩ በዙም ሳይቆይ በሱማሊያ በደረሰብን ወረራ የመሳሪያ ማዕቀብ በመጣሏ ደርግ ወዶም ሆነ ሳይወድ የሶቪዪቶች ጥገኛ እንዲሆን አድርጎታል። በሶስተኛ ደረጃ አንድ ጥይትና አንድ ሰው ብለው ያፋከሩት ኮ/ሌ መንግስቱ ወደ ሃራሬ እንዲፈረጥጡና ሰራዊቱ እንዲበተን ወያኔ በአዲስ አበባ ሻቢያ በአስመራ የሃገር መሪዎችን እንዲሆኑ ያደረጉት አሜሪካኖች ናቸው። አሁን የተያዘልን ድግስ ደግሞ ከበፊቶችም ሴራዎች የከፋ አራተኛ መሆኑ ነው። አሜሪካ ኢትዮጵያን እንደ የመንና እንደ ሶሪያ እንድትሆን ትፈልጋለች። እናስብ ወታደራዊ መኮንኖች ተሰብስበው በዚህ ዓመት የማንን ሃገር እናፍርስ የሚሉባት ምድር አሜሪካ ብቻ ናት። የጄ/ክላርክን ቃለ መጠየቅ ዪቱቭ ውስጥ ገብቶ መመልከት በቂ ነው። እንግዲህ ለመፍረስ ወረፋው የእኛ ሃገር ይመስላል። ቆይቶ ማየት ነው። በቃኝ!
“በኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ላይ የካበተ ልምድ እንዳላቸው የሚታመንባቸው፣ የጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆንና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የኃላፊነት ስራዎች ላይ ያገለገሉት አርከበ”
Really? Can you back that with facts or is it in your bird brain – golgool?
This is really good news and one can plausibly conclude that tplf’s sun is descending. The outgoing scoundrel, Arkebe’s comrade in crime, Adhanom’s selection for the WHO was purely political, the usual US ploy to benefit woyane.
የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያዊ መሪ ቢያገኝ ወያኔ የሳምንት ዕድሜም ባልኖረው ችግሩ አቢይን የመሰለ ከሀዲ የወያኔ አሽከርና ጸረ ኢትዮጵያ ዘረኛ የሚመራው ጦርነት መቼም አሽናፊ ሊሆን አይችልም፡፡ የሰሞኑን ሴራ ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ ሲጀመር ትግራይን ለምን ለቆ ወጣ? ቀጥሎስ አማራውን ለማስፈጀት ከአማራው ክልል ጦርን ማውጣት ምን አመጣው?? የጦርነቱን ዕቅድ ለወያኔ እያስተላለፈ ህዝብን ለፍጅት የሚዳርግ መንግስት ባለበት ሁኔታ ድልን መቀዳጀት ወይም ድልን ዘላቂ ማድረግ ዘበት ነው፡፡ በወያኔ ህገ መንግስት ወያኔን ማጥፋት ከቀልድም ቀልድ ነው፡፡ ችግሩ ህዝባችን በከረሜላ እንደሚታለል ህጻን ከሆነ ከረመ፡፡ ሆዳምና ቅጥረኛ “ምሁራን” በተለይም አማራ ነን ባዮች የሰሩትና እየሰሩ ያሉት ጸረ ሀገር በደል ታሪክ ይቅር የማይለው ነው፡፡ ትውልድ ሲተፋባቸው ይኖራል፡፡ ብርሃኑ፤ አንዳርጋቸው፤ ነአምን፤ አበበ ገላውና መሀይሙ ታማኝና መሰል የሻቢያ/አቢይ/ኦነግ ቅጥረኞችና በሀገርና ህዝብ ደም የሚነግዱ ማፊያ ሌቦች የፈጸሙተ እየፈጸሙ ያለውን በደል ለጊዜና ለታሪክ መተው ይሻላል፡፡ አሁን ደግሞ በተፈናቃይ ስም እርዳታ እንሰበስባለን ብለው ለአዲስ ዝርፊያ እየተዘጋጁ ነው፡፡ ጊዜው ሊረዝም ይችል ይሆን እንጂ ሁሉም የእጁን ያገኛል፡፡
I am sure you will delete the second entry too. If you are expecting to see only views you promote stop calling yourself a journalist. this is a work of a CADRE!!!