• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግ የውጭ ምንዛሪ አሰሳ ሊያካሂድ ነው

January 7, 2013 11:06 am by Editor 3 Comments

ኢህአዴግ የተጭበረበረ የውጪ ምንዛሪ በማተምና በማሰራጨት ስራ የተሰማሩ እንዳሉ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖረውም ርምጃ እንደማይወስድ መደመጥ ከጀመረ ቆይቷል። በስራ ሽፋን የተጭበረበረ ዶላር የሚያትሙ የውጪ አገር ሰዎችን አስገብተው የሚሰሩት ለራሱ ለህወሃት የቀረቡ ሰዎች ዝርፊያ ስለማካሄዳቸው ፖሊስ ተደጋጋሚ መረጃ ቢደርሰውም ርምጃ ሲወስድ አይታይም በሚል የሚወቅሱት ጥቂት አይደሉም።

ቀደም ሲል የተጭበረበረ ዶላር የሚያስገቡ እንደነበሩ የሚገልጹት የጎልጉል የፖሊስ ምንጮች እነዚሁ ክፍሎች አቅማቸውን በማሳደግ የሐሰት (ፎርጂድ) ዶላር አገር ውስጥ ማተም ከጀመሩ ቆይተዋል። ከሩቅ ምስራቅና “ከትንሿ ታላቅ አገር” ህገወጥ ብር አታሚዎችን ከማሽን ጋር በማስገባት የአዲስ አበባን ሃብታሞች ሙጥጥ አድርገው ዘርፈው አድራሻ የቀየሩ አሉ። በዚህ ስራ ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የህትመት ሰዎችም እንደሚገኙበት ጥቆማ አለ።

የለፉበትንና በብድር ያገኙትን ገንዘብ በሚያምኗቸው ትልልቅ ሰዎች ደላላነት በተጭበረበረ ዶላር ቀይረው የከሰሩ ጉዳዩን ወደ ክስ እንዳይወስዱ ራሳቸው የህገወጥ ስራ ተባባሪ መሆናቸው ያግዳቸዋል። ህግ ፊት እንዳይሄዱ ህገወጥ መሆናቸው የያዛቸው እነዚህ ስግብግቦች ባዶ እጃቸውን አጨብጭበው ለመቀመጥ ተገደዋል። ኃይል ለመጠቀም እንዳይሞክሩ ደላላ ሆነው የሚቀርቡት “ትልቅ” የሚባሉት የዘመኑ ሰዎችና ባለጊዜዎች መከታና ደጀን ስላላቸው ቀላል አይሆንም።

አይ.ኤም.ኤፍ. በሚባል ምህጻረ ቃል የሚታወቁት የኤ.ዲ.ኤች. ዋናሥራአስኪያጅና ባለአክሲዮን አቶ አየለ ደበላ፣ የአያት የመኖሪያ ቤት ድርጅት ሊቀመንበርና ዋና ባለአክሲዮን አቶ አያሌው ተሰማ፣ ጃማይካና ሌሎች አራጣ አበዳሪዎቸ “አራጣ በማበደር በባንክ ስራ ገብታችኋል” ተብለው በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ በተመሳሳይ መንግስት የተጭበረበረ ዶላር በማምረት ዝርፊያ ላይ የተሰማሩትና በየስርቻው እየገቡ ዶላር የሚያስለቅሙት እነማን እንደሆኑ መረጃው እንደነበረው ባልደረባችን ከአዲስ አበባ ያሰባሰበው መረጃ ያመለክታል።

በዶላር ህገወጥ ንግድ ውስጥ በግንባር ቀደም ተዋናይ ከሆኑት መካከል “የክልል አስራ አምስት አባላት” የሚባሉት ቻይናዎች ይገኙበታል። ካልሲና የውስጥ ሱሪ ሳይቀር በየስርቻው ውስጥ በማምረት ቦምብ ተራን የተቆጣጠሩት የቻይና ዜጎች፣ በከፍተኛ ደረጃ በዶላር የጨለማ ገበያ ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከተማዋ ውስጥ ያለውን ዶላር በመሰብሰብ ወደ አገራቸው በቀጥታ በኤምባሲያቸው አማካይነት በመላክ ዶላሩ አገራቸው ሲደርስ በራሳቸው ገንዘብ ተመንዝሮ ለፈለጉት አገልግሎት እንደሚውልላቸው በቴሌ ከሚሰሩ የቻይና ዜጎች ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው ለጎልጉል ይገልጻሉ።

የቻይና ዜጎች የሚሰበስቡትን ብር ወደ ዶላር በመቀየር ወደ አገራቸው መላክ የመሃላ ያህል ተግተው የሚሰሩት ስራ እንደሆነ የሚገልጹት የቴሌ ምንጫችን፣ ዶላር በማቅረብ አብረዋቸው የሚሰሩት ራሳቸው የመንግስት ሰዎች መሆናቸው ያደባባይ ምስጢር እንደሆነ ይናገራሉ።

ይህ ሁሉ ጉድ ህጋዊ ሆኖ በሚከናወንበት ባሁኑ ወቅት፣ ራዲዮ ፋና ታህሳስ 25 ቀን 2005 ዓ ም ህግን በማንተራስ ባሰራጨው አስተያየት መሰል ዜና  “የውጭ ገንዘቦችን ለመዘርዘር ፈቃድ የተሰጣቸው ባንኮች ብቻ ሲሆኑ ፥ ከዚህ ውጭ ማንኛውም የውጭ ሀገር ገንዘብ ፈቃድ ሳይኖረው የገዛ፣ ከውጭ ሀገር ያስመጣ፣ ወደ ውጭ ሀገር የላከ ያስቀመጠ፣ የመነዘረ፣ የሸጠ ወይም ለሽያጭ ያቀረበ  ገንዘቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚወረስ ፥ እንዲሁም ከ10 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራትና ከ50 ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ በሀገሪቱ የወንጀል ህግ አንቀጽ 346 ተደንግጓል” በማለት ዋናዎቹን የውጪ ምንዛሪ ቀበኞች ወደ ጎን በመተው ልጥፍ ሱቆች ላይ ያነጣጠረ መረጃ አስተላልፏል።

በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ድርጊቱ ተስፋፍቶ እንደቀጠለ ፥ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ ፣ በጋንዲ ሆስፒታልና አካባቢው ፣ በአሜሪካን ግቢ፣ ቦሌ ሩዋንዳና በሌሎችም አካባቢዎች በመዘዋወር ይህንኑ ህገወጥ ዶላር ገበያ የተመለከተው የፋና ዘጋቢ የመንግስት ቤቶች፣ የኢትዮጵያ ሆቴል ሱቆች የሆኑና ለጫማ እና ለተዘጋጁ ልብሶች መሸጫ፣ የጽሁፍ አገልግሎት ለመስጠት  የተከፈቱና በዚያው አካባቢ የሚገኙ የግለሰብ ሱቆች፣ ለአነስተኛና ጥቃቅን ተብለው የተገነቡ በጋንዲ ሆስፒታል ፊት ለፊትና አጠገብ የሚገኙ  ሱቆች በዚህ ህገ ወጥ ተግባር እየተሳተፉ መሆናቸውን መታዘቡን ይገልጻል።

አንዳንዶቹ ሱቆች የታሸገ ውሃ፣ ሶፍት፣ ጥቂት የተዘጋጁ ልብሶችን ለሽፋን ያህል ደርድረው ቢታዩም  ዋና  ተግባራቸው ህገወጥ  የውጭ ምንዛሪ  ግብይት  መፈፀም ነው ። ከዚህም ባለፈም በርካታ ገንዘቦችን ወደ እነዚህ ስፍራዎች ይዘው የሚሄዱ ግለሰቦችን ፥ በዋጋ ሽያጭ ድርድሩ እንዳልተግባቡ በማስመሰል በሀሰተኛ የውጭ ገንዘቦች የሚቀይሩ እንዳሉና፣ ይህም አልፎ አልፎ እንደሚከሰት የድርጊቱ ሰለባ የሆኑ ተጠቃሚዎች መናገራቸውን ያመለከተው ዘጋቢ የተጭበረበሩ የውጪ ምንዛሪዎች /ፎርጂድ ገንዘቦች/ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ በሪፖርቱ አልገለጸም።

ዘጋቢው ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ብሩክ ዓለሙ፥ የውጭ ገንዘቦችን ስልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ መዘርዘርና መለወጥ ሀገርና ህዝብን ለጉዳት እንደሚዳርግና የንግድ ስርዓቱን በማዛባት የዋጋ ግሽበትን እንደሚያባብስ ሲገልጹ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አሳይ አምባዬ ችግሩን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የተደረገው ጥረት ዝቅተኛ የሚባል እንደሆነ ነው የተናገሩት።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ወንጀል ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ኢንስፔክተር አበራ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመከላከል እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግሩን ለመቅረፍ ጋንዲ ሆስፒታል አጠገብ የውጭ ምንዛሪ መስጫ ቢሮ ቢከፍትም፥ ህገ ወጥ ድርጊቱን ከጊዜ  ወደ ጊዜ ከመስፋፋት እንዳላገደው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጸጋዬ ደስታን የገለጸው ፋና ዘገባ ያስረዳል። ጋዜጠኛው በመጨረሻ “ህገ ወጥ ተግባሩን ለመከላከል ፖሊስ ያደረገው ጥረት ዝቅተኛ መሆኑንና በቀጣይም ለድርጊቱ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” ብሏል።

በዘገባው ደቃቃዎቹ የዶላር ማዘዋወሪያ ኪዎስኮች እንጂ በትላልቅ ሆቴል የሚካሄደውን ዝርፊያና ወንጀል አልነካውም። ዱባይና ናይሮቢ እየሄዱ የሚዳሩት “ደላላ ባለሀብቶች” በከፍተኛ የምንዛሪ አደን ላይ ሃይል በቅጥር አሰማርተው እንደሚሰሩ ፖሊስም፣ መንግስትም፣ አብሮ አረቄ የሚጋተው ደህንነቱም እንደሚያውቅ የጎልጉል ምንጮች ያብራራሉ።

ህገወጥ ተግባርን ተከታትሎ እልባት መስጠት አግባብ እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች “መንግስት የችግሩን ዋና መነሻና አስኳል ስፍራ የትና እነማን ጋር እንደሆነ ያውቃል፣ ነገሩን ከቆሰቆሰው “እጄን በእጄ” ስለሚሆንበት ህዝብን እያስለቀሰ ይኖራል። ይህ አካሄድ ራሱን ይደፋዋል” ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

በድንገት አሰሳ የማድረግ እቅድ የያዘው ኢህአዴግ ስለያዘው ኦፕሬሽን ዝርዝር መረጃ ባይሆንም “ቀደም ሲል በድንገት በተደረገ ወረራ ለከፍተኛ ኪሳራ የተዳረጉ የምንዛሪ ሰራተኞች እንደቀድሞው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ቢሯቸው ያስቀምጣሉ ተብሎ አይገመትም” የሚል የፖሊስ ትንተና መኖሩ ተሰምቷል። ይሁን እንጂ የተወሰኑ ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የመጠቀም አዝማሚያ አለ።

በውጪ ምንዛሬ እጥረት ዙሪያ ሙስና መኖሩ፣ አንድ ዶላር ለመውሰድ አንድ ብር ከሃያ ሳንቲም ጉቦ እንደሚሰጥ በመግለጽ ሪፖርተር ዜና ማውጣቱን ተከትሎ ብሄራዊ ባንክ በመላው የአገሪቱ ባንኮች ላይ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት መንግስት ከየስርቻው የሚለቅመው የውጪ ምንዛሪ አሁን ተፈጠረ ለሚባለው የምንዛሪ እጥረት መፍትሄ አይሆንም።

በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ በማጋዝ ላይ በተሰማሩ “ወኪል ባለሃብት አሽከሮቻቸው” ላይ ትኩረት ማድረግ፣ አቶ መለስ እንዳሉት “የመንግስት ሌቦች” ላይ ጨክኖ ርምጃ መውሰድ ዋና መፍትሄ እንደሆነ የሚጠቁሙት አስተያየት ሰጪዎች፣ መንግስት በራሱ ላይ ርምጃ ሲወስድ ታይቶም ተሰምቶም ስለማይታወቅ ችግሩ እንዳለ እንደሚቀጥልና ቀን ጠብቆ ግን መልሶ ኢህአዴግን ለህልውናው በሚያሰጋ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደሚጥለው አስታውቀዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    January 7, 2013 05:53 pm at 5:53 pm

    እኛ የሞቱ ጠ/ሚ እንዳሉት “ስኳር ልሶ የማያውቅ መላስ ስለጀመረ” ሳይሆን የዋጋ ግሽበትና ዕጥርት የመጣው የምግብ ውጤቶች በተለያ ዘዴና ምክንያት በተጭበረበረ ገንዘብ ሀገር አቋርጠው ጎረቤት ሀገር በርካሽ ስለሚሸጡ ነው። ድሃው ኢትዮጵያ ህዝብ የልጆቹን አንጀት በሻይና ቂጣ በጠዋት ሊጠብስበት እንጂ እንደ ጎረቤት ሀገር ኬክ ሠርቶ አልበላበትም! በተቀመጡት ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደስአለኝና በሦስት ም/ጠ ሚኒስትሮች በተጠናው ጥናት ደግሞ ጤፍ በልቶ የማያውቀው ብሔር ጤፍ መብላት በመጀመሩም የሚመጣ የዋጋ ግሽበትም ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። ምን አልባት ህንድ፣ቱርክ፣ዓረቦች እና ቻይና ጤፍ ሀገራችን አምርተው የሀገራቸውን ህዘብ መቀለብ ካልጀመሩ በስተቀር ? ?እኛ ሰማነው የኢትዮጵያ ህዝብ የአመጋገብ ሥርዓቱን አሻሻለ የሚሊኒየሙን ምርጥ ምግብ ሩዝ የራሱ ባሕላዊ ምግብ አደረገው ሲሉ የራሳቸው ምሁራን “በአይጋ ፎረም” ላይ ፅፈው ያስነበቡትን ኀይሌና አማካሪዎቻቸው ማንበብ አይችሉምን? ?
    ኀይለመልስ መቼም ያው የዩኒቨርሲቲ መምህርነታቸው ይሳላቸው ነበር አለቆቻቸውን ለማስደሰት ብለው ከሚኒስትሮቻቸውም ብቻ ሳይሆን ከከደጋፊዎቻቸውም መላተም ጀምረዋል የቡድን (የደቦ) ነገር ይሄው ነው፡፤እሳቸው እንደሚቀላምዱት ሳይሆን “የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ብሩክ ዓለሙ፥ የውጭ ገንዘቦችን ስልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ መዘርዘርና መለወጥ ሀገርና ህዝብን ለጉዳት እንደሚዳርግና የንግድ ስርዓቱን በማዛባት የዋጋ ግሽበትን እንደሚያባብስ ገልፀዋል፣”
    ሌሎችም እንደሚሉት”ደቃቃዎቹ የዶላር ማዘዋወሪያ ኪዎስኮች እንጂ በትላልቅ ሆቴል የሚካሄደውን ዝርፊያና ወንጀል አልነካውም። ዱባይና ናይሮቢ እየሄዱ የሚዳሩት “ደላላ ባለሀብቶች” በከፍተኛ የምንዛሪ አደን ላይ ሃይል በቅጥር አሰማርተው እንደሚሰሩ ፖሊስም፣ መንግስትም፣ አብሮ አረቄ የሚጋተውን ደህንነቱም እንደሚያውቅ ሊረዱ ሊያስተካክሉ ይገባል። መንግስት በራሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ታላቁን ‘ሞኖፖሊ’ እንደመናድ ስለሚቆጠር ሕዝብን እያናደዱ/እያነደዱ ሥርዓቱ እንዳለ እንደሚቀጥልና ቀን ጠብቆ በሕዘብ ‘እንቢኝ ባይነት!’ ግን መልሶ ኢህአዴግን ለህልውናው በሚያሰጋ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደሚጥለው ምንም የማይካድ የቅርብ ጊዜ ውጤትም ሊሆን ይገባል። የዋህንት፣ታጋሽነት፣ጨዋነት፣ታጋሽነት፣የኢትዮጵያን ልጆች በሀገራቸው ሊያዋርዳቸው አንገት ሊያስደፋቸው እንደሁለተኛም ዜጋ ሊያደርጋቸው አይገባም በለው!ሀገር የጋራ ነው! በቸር ይግጠመን ሰላም ለሁሉም ይሁን አሜን !!>>>>>>>

    Reply
  2. moged says

    January 8, 2013 06:49 pm at 6:49 pm

    A minority government cannot survive long!! It is a proven fact
    and if ever it survives with undemocratical and powerful means
    the end of such opperssive regime will be very tragic.

    Reply
  3. Germame Neway says

    January 18, 2013 10:30 am at 10:30 am

    The timeless lesson repeating itself by those who never learn that-Power corrupts and absolute power corrupts absolutely-is a manifest destiny of Woyne/TPLF gangster regime.

    The system of rule of law not of men/women is to temper the excesses of human greed and restrain ambtious rulers and deter corruption from polluting the body politics,economics and social behaviour.

    WOYANE/TPLE is a gangster group which held state power, has its own army, security and police through which it amassed/robbed.looted the national treasure and natural resources as private fiefdom. It has its own court to punish and jail even disappear the offenders of its command ,edict and power.

    It is typically A TOTALITARIAN POLICE STATE at this time of its 21 years in existence.

    The GODFATHER, like in the gangster organizations,the big boss of the lesser bosses, is the LAW and the LAW is the GODFATHER. Herr marshal Meles Zenawi was the LAW and the LAW is “Meles’ vision” EVEN AFTER HIS DEMISE.
    TODAY our beloved Ethiopia, the dear mother of humanity is being raped by this daylight robbery, looters and international gangster squads and collaborators/bandas etc… A centuary and half ago one great philosopher scribes more or less like this-
    -All philosophers before him has told and interpreted history..my task is not to do the same but how to change the human condition.-
    This is not verbatim or direct quote but the idea is what we should do about this gangster regime?
    The regime is day by day falling apart despite its outward and healthy looking facelift appearance of strength.It is a master of deception and falsehood. The trouble is like all gangsters it does believe its own decption and falshoodat its own peril. It is pathological and delusion of grandeur is its modes operandi. It is rotten from within. Do we have to wait until it implodes from its own overweight and political obesity causing a massive regime heart attack-the equivalent of massive stroke and cardiac arrest and taking its life and the Nation with it as Herr Grazziani Mengistu fled cowardly to exile leaving behind his handiwork for 17 years to gives us the mortals the dead weight of the state and 22 yrs of home work while he writes his “memoirs”? It is chilling even to think about it.
    LET US NOT ALLOW ONCE MORE HISTORY REPEAT IT SELF. LET US RISE UP IN UNITY TO THIS MOMENTUM HITORICAL OCCASION AND SAVE OUR BELOVED COUNTRY TO ALL OF US ETHIOPINS NEVER FOR THE FEW SELF APPOINTED!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule