
አቻምየለህ ታምሩ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ አዳነች ፍሰሃዬ ወልቃይትን አስመልክቶ ላነሳችው አመክንዮዎች የሰጠው ምላሽ:-
ይድረስ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሀዬ
በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ ካለሽበት ቦታ ይድረስሽ። በዛሬው እለት (ህዳር 28, 2016) «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት» በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ዶክተር ብርሀኑ መንግስቱን፣ ፕሮፌሰር አለማንተ ገብረሥላሴና ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያን ጋብዘሽ ስለወልቃይት ያቀረብሽውን ዝግጅት በጥሞና ተከታትየዋለሁ። ይህንን ግልጽ አስተያየት እንድጽፍልሽ የገፋፋኝ ምክንያት አንቺ አዘጋጅና አቅራቢ ሆነሽ ባሰናዳሽው በዚህ «የምሁራኖች» የውይይት መድረክ ላይ ይዘሽ የቀረብሽው የግል አቋምና የተሳሳተ ግንዛቤ አመክንዮ የሌለው መሆኑን በመታዘቤ በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዳደረገ ሰው ምናልባት የተሳሳትሽው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነሽ ከሆነ በሚል ስህተትሽን ታርሚ ዘንድ እርምት ለመስጠት ነው።
«ወልቃይት የትግራይ ነው» የሚለውን አቋምሽን ለማንበር ቢያንስ ሶስት ስህተት የሆኑ መነሻዎችን ጠቅሰሻል። የመጀመሪያው መነሻሽ «የወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ የቦታ ስሞች <የትግርኛ ስሞች> መሆናቸውን» ያነሳሽበት መከራከሪያሽ ነው። ሁለተኛው መከራከሪያሽ «ወልቃይቶች ትግርኛ ቋንቋ ስለሚናገሩ ወደ ትግራይ መካለል አለባቸው» ያልሽው ሲሆን ሶስተኛው ምክንያትሽ ደግሞ «የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮምቴ አባል የሆነው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ሎሎችም የወልቃይት ተወላጆች የሆኑ የኮሚቴው አባላት ከወያኔ ጋር ሆነው ደርግን መታገላቸው ትግሬ ያደርጋቸዋል» በማለት ያቀረብሽው ነው።
በመጀመሪያ «ወልቃይት የትግራይ ነው» እንድትይ ያስቻለሽን የቦታ ስያሜዎች አመክንዮሽን እንመልከት። ይህንን «አመክንዮ» የኒዮርኩ ገላውዲዮስ አርአያ ለኔ ግብረ መልስ በጻፈውና ትግራይ ኦንላይን ባሳተመው «Beyond Ethnocentric Ideology and Paradigm Shift for a Greater Ethiopian Unity» ጽሁፉ ላይ አንስቶት ነበር። እኔም ለዚህ ደካማ መከራከሪያ «Forceful Annexation, Violation of Human Rights and Silent genocide: A Quest for Identity and Geographic Restoration of Wolkait-Tegede, Gondar, Amhara, Ethiopia» በሚል በጻፍሁት ሰፊ አርቲክል በቂ መልስ ሰጥቸው ነበር። ለጊዜው አንቺ ባነሳሽው «መከራከሪያ» ላይ ያለኝ አስተያየት እንዲህ የሚል ነው።
በቅድሚያ አንቺና ገላውዲዮስ አርአያ የወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ የተወሰኑ የቦታ ስያሜዎች የትግርኛ ስሞች ናቸው የምትሏቸው የአካባቢ ስሞች የትግርኛ ስሞች ሳይሆኑ የግዕዝ ስያሜዎች መሆናቸው ግንዛቤ ይያዝ እላለሁ። ሲቀጥል ስሞቹን የትግርኛ ስሞች እንኳ አድርገን ብስወስድ ተመሳሳይ ስሞች በመላው ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ አሉና የናንተ መደምደሚያ ገዢ ሀሳብ አይደለም። የቦታ ስም የማንነት መገለጫ ከሆነ ኦጋዴን ያለው ቀብሪ ዳህር የትግራይ መሬት ሊሆን ነው ማለት ነው። የቦታ ስም የማንነት መገለጫ ከሆነ ኤርትራ ውስጥ ያሉ የትግርኛ የቦታ ስሞች ሁሉ የትግራይ ክልል አካል ሊሆኑ ነው ማለት ነው። በእውነቱ እንደዚህ አይነቱ መነሻ ውሀ የሚቋጥር መከራከሪያ አይደለም። እንደዚህ አይነት መከራከሪያ በየትኛውም ህልዮት ትርጉም ያለው ድምዳሜ ላይ አያደርስም።
ይህ የአንቺና የገላውዲዮስ መከራከሪያ በቀላሉ ፉርሽ የሚሆነው በወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌላቸው አካባቢዎች የግዕዝ፣ የአማርኛና የአረብኛ ስሞች መሆናቸውን ስናስታውስ ነው። ለምሳሌ የሚከተሉት የቦታ ስሞች በወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ውስጥ የሚገኙ የአረብኛ ስም ያላቸው ቦታዎች ናቸው። ሞይ ካድራ [ማይ ካድራ አላልሁም]፣ ቧኸር፣ ህለትግርሽ፣ ረውያን፣ አብደላፊ፣ በዋል፣ ኋጃ፣ ሎግዲ፣ ህለጂን፣ ሁመራ፣ ህለትሚማ፣ አደባይ፣ ሸሪፋ አህመድ፣ ሸሪፋ ጎላ፣ ኑጓራ፣ ገላዕዘራብ፣ ገላዕነሀር፣ መቻቺ፣ እምባራኪድ፣ አበጡር፣ መዋለድ፣ ወዘተ…ወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ የአረብኛ የቦታ ስሞች ናቸው። ከአረብኛ ስሞች በተጨማሪ በወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ፍየል ውሃ፣አወራ፣አፅመጥንት፣ 30አይን፣ ወፍ አርግፍ፣ ባናት፣ ወይ እናት [በወያኔ አውሮራ/ድቭዥን ተብሎ የተቀየረ]፣ ማክሰኞ ገብያ [በወያኔ ወደ ከተማ ንጉስ የተቀየረ]፣ አንድ አይቀዳሽ፣ ወዘተ… የአማርኛ ስም ያላቸው የቦታ ስያሜዎች ናቸው።
እና በአንቺና በገላውዲዮስ አርአያ «አመክንዮ» መሰረት ወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ውስጥ ያሉት እነ ሞይ ካድራ፣ ቧኸር፣ ህለትግርሽ፣ ረውያን ፣ በዋል፣ ኋጃ፣ ሎግዲ፣ ህለጂን፣ ሁመራ፣ ህለትሚማ፣ አደባይ፣ ሸሪፋ አህመድ፣ ሸሪፋ ጎላ፣ኑጓራ፣ ገላዕዘራብ፣ ገላዕነሀር፣ መቻቺ ፣ እምባራኪድ፣ አበጡርና መዋለድ፣ ወዘተ የአረብኛ ስሞች ስለሆኑ የሱዳን መሬቶች መሆን አለባቸው ማለት ነው? ስም የማንነት መገለጫ ከሆነ በወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ያሉት እነ ፍየል ውሃ፣ አወራ፣ አፅመጥንት፣ 30አይን፣ ወፍ አርግፍ፣ ባናት፣ ወይ እናት፣ ማክሰኞ ገብያ፣ አንድ አይቀዳሽ፣ ወዘተ… የመሳሰሉት የአማርኛ ስሞች ወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራን የአማራ አያደርጓቸውም ማለት ነው? ኦጋዴን ውስጥ ያለው ቀብሪ ዳህር ቃሉ ትግርኛ ስለሆነ የትግራይ መሆን አለበት ማለት ነው? በናንተ መከራከሪያ መሰረት አክሱምና ተምቤን የሚሉት ስሞች አገውኛ ስለሆኑ ግዛቶቹ የአገው ምድር አካል መሆነ አለባቸው ማለት ነው? እስቲ መልሽልኝ? እነዚህን አራት ጥያቄዎች እናንተ ወልቃይትን፣ ጠገዴንና ሁመራን ለትግራይ ለማድረግ በተነሳችሁበት በዚህ የመጀመሪያው አመክንዮ ማዕቀፍ ትይዩ መሰረታዊ የሎጂክ ህጎችን ሳትጥሺ ከፍ ብዬ ያነሳኳቸውን አራት ጥያቄዎች ከመሰሽልኝ የተነሳሽበትን ሀሳብና የደረስሽበትን ድምዳሜሽን አገዛሻለሁ።
ሌላው ያነሳሽው አመክንዮ አልባ መከራከሪያ «ወልቃይቶች ትግርኛ ስለሚናገሩ ወደ ትግራይ ክልል መካለል አለባቸው» በሚል የደረስሽበት ድምዳሜ ነው። እስቲ ልጠይቅሽ ጋዜጠኛ አዳነሽ፡- አንቺ አሜሪካን አገር ስትኖሪ እንግሊዝኛ አቀላጥፈሽ ትናገሪያለሽና እንግሊዛዊ ነሽ ማለት ነው? መለስ ዜናዊ አማርኛ ከመናገር አልፎ ቅኔ ሳይቀር ይቀኝበት ነበርና አማራ ነው ማለት ነው? አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አማርኛ ይናገራልና አማርኛ የሚናገረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አማራ ነው ማለት ነው? ሱዳን ድንበር አካባቢ የሚኖሩ የወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ሰዎች አረብኛ ይናገራሉ፤ አረብኛ ስለተናገሩ ሰዎቹ አረብ ወይንም ሱዳናዊ ናቸው ማለት ነው? ጎንደር ውስጥ ቅማንቶች አሉ። 42 ቀበሌዎችን ማዕከል ያደረገ ልዩ ወረዳ መስርተዋል። የልዩ ወረዳው የመስሪያ ቋንቋ ደግሞ አማርኛ ነው። እና ቅማንቶች አማርኛ ስለተናገሩ አማሮች ናቸው ማለት ነው? እኔ ትግርኛ እችላለሁ፤ ትግሬ ነኝ ማለት ነው? እስቲ ትግርኛ የቻለ ወልቃይቶች ሁሉ ትግሬ የሚሆኑ ከሆነ አማርኛ የሚናገሩ ወልቃይቶች ሁሉ አማራ የማይሆንበትን አመክንዮ አስረጅኝ?
«ወልቃይት የትግራይ ነው» ብለሽ ለመደምደም ያነሳሽው ሶስተኛውና የመጨረሻው መከራከሪያሽ ደግሞ የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮምቴ አባል የሆነው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ሌሎች የወልቃይት ተወላጆች የሆኑ የኮሚቴው አባላት ከወያኔ ጋር ሆነው ደርግን መታገላቸውን ነው። ይህ መከራከሪያ በውነቱ ውሃ ካለመቋጠሩም ባሻገር የወያኔን የትግል ታሪክ ላነበበ ሰው አስቂኝ ትርክት ነው። ውድ አዳነች፡- ህወሀት ውስጥኮ አይደለም የአማራ ተራ ወታደርና የኮሚሳር መሪ ይቅርና ከአስራ አንዱ የህወህት መስራቾች መካከልኮ አንዱ አማራ ነበር። ምናልባት ይህንን ታሪክ አታውቂው ይሆናል። መቀሌ በሚገኘው የህወሀት «ሰማዕታት» አዳራሽ ብትሄጂ ከህወሀት አስራ አንዱ መስራቾች መካከል ወረድ ብዬ ታሪኩን የምነግርሽን አማራ ስም ታገኝዋለሽ። አስገደ ገብረ ሥላሴም «ገሀዲ» ብለው በጻፉት መጽሀፋቸው አማራውን የህወሀት «ቼ ጎቬራ» አውስተውታል።
አብተው ታከለ
አማራው የህወሀት መስራች አብተው ታከለ ይባላል። አብተው የተወለደው በ1929 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ 774 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከተንጣለለችው ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ 118 ኪሎ ሜትር ርቀት ገባ ብላ በምትገኝው ድብ በሐር ውስጥ ነው። ድብ በሐር በደባርቅ ወረዳ የምትገኘው ከተማ ስትሆን ከአምስት ሺ በላይ ኗሪዎች እንደሚኖሩባት ከአስር አመት በፊት የተካሄደው የህዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት ያሳየል። የድብ በሐር ከተማ በርካታ ሰዎች በደርግ የግፍ አገዛዝ ከተወረወሩበት ሊማሊሞ ገደል ስር ትገኛለች። በህወሓት ታሪክ ውስጥም ጉልህ ስፍራ ሊይዝ የሚገባውን፤ ነገር ግን አመድ አፋሽ የሆነን አብተውንም አፍርታለች።
ስለአብተው የታገለለት፣ የደማለት፣ የቆሰለለት፣ የወጣለት፣ የወረደለት… ድርጅት ህወሀት ታሪኩን አልዘከረለትም። አብተው እድሜው ሲጎረምስ ከድብ በሐር በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው የሽሬ ከተማ ሄደ። ኑሮውን በዛው አደረገ። የሽሬ ከተማ ግምጃ ቤት ሀላፊ የሆኑትን የባላባራስ አፅባሀ ልጅ ወ/ሮ አለም አፅበሀንም አግብቶ ሶስት ጉልቻ መሰረተ። ባለንባራስ አፅበሀ የሌላኛው የህወሓት መስራች ስሁል አየለ [ገሠሠ] አጎት ናቸው። ይሄ ሁኔታም አብተው እና ስሁል እንዲቀራረቡ መንገዱን ከፈተላቸው። እናም ከእለታት አንድ ቀን «የትግራይ ህዝብን ከአማራ ጭቆና ለማላቀቅ እና ነፃይቱን ትግራይ ለመፍጠር» ድርጅት መመስረቱ አስፈላጊ እንደሆነ ተወያዩ፤ እንደ ዘመኑ ደንቆሮ ትውልድ አብተው ምንም እንኳ አማራ ቢሆንም፤ ‹‹የተጨቆነ ካለማ…›› ሲል ለመታገል መወሰኑን አስገደ ገብረ ሥላሴ በመጽሀፋቸው ያስነብቡናል። እናም አብተው ከሌሎች 10 የትግራይ ልጆች ጋር በመሆን ወደ ደደቢት በረሃ አመራ። አስራ አንድ ሆነው ስድስት አሮጌ መሳሪያ ታጥቀው ዱር ቤቴ አሉ። እናም በደደቢት በርሀ ህወሓትን አማራው አብተው ከአስር ትግሬዎች ጋር አብሮ መሰረተ።
እነዚህ አስራ አንድ የመጀመሪያው በረሃ የገቡና ህወሀትን የካቲት አስራ አንድ ቀን 1967 ዓ.ም. የመሰረቱ ታጋዮች በስም ስንዘረዝራቸው የሚከተሉት ናቸው፡- ስሁል አየለ [ገሰሰ]፣ አረጋዊ በርሀ፣ ስዩም መስፍን [አምባዬ]፣ ግደይ ዘርአፅዮን [ፋንታሁን]፣ አጋዚ ገሰሰ [ዘርኡ]፣ አስፋሐ ሐጎስ [ሙሉ]፣ ፀሀዬ ካሕሳይ [አረፈአይኔ]፣ ምስጋና ቡርሀ [ካሕሳይ]፣ ቀለበት ታዬ [ንጉሴ]፣ አስገደ ገ/ስላሴ [ወ/ሚካኤል] እና አብተው ታከለ [ሚካኤል] ይባላሉ። እነዚህ ሰዎች የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ መስራቾች ናቸው። ነገር ግን ከእነሡ አንዱ የትግራይ ተወላጅ አይደለም። አማራ ነው። ከፍ ብዬ እንዳልሁት አማራው አብተው ታከለ ነው። ደደቢት በረሃ አብረውት የገቡ ጓደኞቹ ትግሬዎች የትግል ስም አውጥተውለት ‹‹ሚካኤል›› ሲሉ ሰየሙት።
ሆኖም ግን ህወሓት የአብተውን መስዋትነት ካደው። ዘረኛው ወያኔ አብተው ታከለ አማራ ስለሆነ ከህወሓት መስራቾች ታሪክ ዝርዝር ውስጥ በመደለዝ መስዕዋትነቱን ነጠቀው። በእጅጉ የሚያስገርመው ትግራይ በቆመው የሰማዕታት ሀውልት ስር የአስሩ የህወሀት መስራቾች ስም እና ፎቶ አለ። የአብተው ታከለ ግን ስሙ አለ፣ ፎቶው ግን የለም። ይህ ሰው ፎቶ የለውም እንዳይባል ደርግ ከወደቀ በኋላም በህይወት ነበር። እስከ 2000ዓ.ም. በጎንደር ደባርቅ፣ ደብ በሐር ከተማ ከባለቤቱ ጋር ይኖር ነበር። የአራት ልጆችም አባት ነው። ከዚህ አለም ያለፈው በአንጀት ድርቀት ተሰቃይቶ ነው። አብተው ከስምንት አመት በፊት የሚንከባከበው አጥቶ ህይወቱ አለፈ። አማራው የህወሓት ቼ ጉቬራ የታገለለት ድርጅት ህወሀት አንድም ቀን ሳይጠይቀው ከዚህ አለም በሞት ተለየ። የሰራው ታሪክም የአማራ ብሄር ተወላጅ በመሆኑ ብቻ ተቀበሮ እንዲቀር የተፈረደበት- አማራው የህወሀት ቼ ጉቬራ።
ከህወሓት መስራቾች ውስጥ የተወሰኑት መጽሐፍ ፅፈዋል። ከአስገደ ገብረ ሥላሴ በስተቀር አረጋዊ በርሄ፣ ገብሩ አስራትም ሆነ ግደይ ዘራፅዮን በመጽሐፋቸውም ሆነ ቃለ ምልልስ በሚሰጡበት ጊዜ ስለአብተው አማራነት ነግረውን አያውቁም። የብአዴን መስራቾችም ስለዚህ ጉዳይ ሲያነሱ አልተሰሙም። ስለማያውቁ ነው እንዳይባል በደንብ ያውቃሉ። ምናልባት ህወሓት የጠላውን መጥላት፣ ህወሓት የወደደውን መውደድ የሚለው ያልተፃፈው የህወሓት ህግ አስሯቸው ሊሆን ይችላል።
አየሽ ጋዜጠኛ አዳነች፡- ከህወህት ጋር መታገል የግድ ትግሬ አያደርግም። የህወሀት መስራቹ አብተው ታከለ አማራ ነው፤ ግን ከህወሀት ጋር ታግሏል። አብተው ከህወሀት ጋር የታገለው ደርግን ለመጣል እንጂ ትግሬ ለመሆን ስላልነበረ ደርግ ከወደቀ በኋላ አብተው ወደ ትውልድ ስፍራው ድብ በሐር ተመልሶ አማራ ሆኖ ኖረ! መቼም ከህወሀት መስራቾቹ አንዱ አማራ መሆኑን ስትሰሚ ተራ ወታደር ሆነው የታገሉት እነ ኮሎኔል ደመቀም ሆነ ሌሎች የወልቃይት አማሮች በተራ ወታደርነትና በኮሚሳር መሪነት ከህወሀት ጋር ደርግን ለመጣል ስለታገሉ እነሱ «እኛ አማራ ነን» እያሉ ከህወሀት ጋር ስለታገላችሁ የግድ ትግሬ ሁኑ ማለት ነውር እንደሆነ የምትገነዘቢ ይመስለኛል። ስለዚህ ከወያኔ ጋር መታገል ትግሬ አያደርግምና እነኮሎኔል ደመቀ ከወያኔ ጋር ስለታገሉ «አማራ አይደሉም፤ ትግሬ ናቸው» ያልሽው መከራከሪያ ክብደት እንደማያነሳ ከህወሀት መስራቹ ከአብተው ታከለ የህይወት ታሪክ መረዳት የቻልሽ ይመስለኛል።
ከወያኔ ጋር መታገል የግድ ትግሬ እንደማያደርግ ሁለት ተጨማሪ ታሪካዊ አብነቶችን ልጨምር። በቅርቡ «The Eritrean Liberation Front: Social and Political Factors Shaping Its Emergence, Development and Demise, 1960-1981» በሚል ሚካኤል ወልደ ጊዮርጂስ ተድላ የጻፈውን የሁለተኛ ዲግሪ ቴሲስ እያነበብሁ ነበር። የሚገርምሽ ጀብሀ ውስጥ ተዋጊ የነበሩ የወልቃይት ልጆች ነበሩ። መቼም እነዚህ የወልቃይት ሰዎች ከጀብሀ ጋር ስለተዋጉ ኤርትራውያን ናቸው የሚል መከራከሪያ የምታነሽ አይመስለኝም። ሁለተኛው አብነት አንቺ የምታውቂው የማነ ጃማይካ ነው። የማነ ጃማይካ ወያኔን ሊሰልል በሻዕብያ ተልኮ ህወሀት ውስጥ ሰጥሞ የቀረ ወዶ ገብ ነው። የማነ ጃማይካ ከወያኔ ጋር ሆኖ ደርግን ስለተዋጋ የኢትዮጵያ ትግሬ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ እነ ኮሎኔል ደመቀም ከወያኔ ጋር ደርግን መዋጋታቸው መታየት ያለበት እንደ አማራው አብተው ታከለና እንደ ኤርትራዊው የማነ ጃማይካ ነው።
አዳነች:- ከፍ ብዬ ያነሳሁት አመክንዮ ሁሉ አንቺ ካነሳሻቸው መከራከሪያዎች አንጻር እንጂ ወልቃይት የአማራ መሆኑን የሚያስረዳ የታሪክ ማስረጃ አጥቼ አይደለም። እንዴውም ባለፈው ሰሞን ከአስራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እስከ ደርግ ስልጣን መጨረሻ ድረስ ወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ የማንና በየትኛው የአስተዳደር መዋቅር ስር እንደነበሩ የሚያሳዩ ከ40 በላይ የታሪክ ሰነዶችንና ከ15 በላይ ካርታዎችን ከጥንታዊ መጽሀፍቶች ሰብስቤ ባለ 52 ገጽ ጽሁፍ በኢንተርኔት ለቅቄያለሁ። የአርቲክሉ ርዕስ ከፍ ብዬ የጠቀስሁት ነው። ምናልባት ስለወልቃይት ያለሽ የተሳሳተ ግንዛቤ ከወገናዊነት ያልመነጨ ከሆነ የሰበሰብኋቸውን ከ700 ዓመታት በላይ የሚሸፍኑ የታሪክ ድርሳኖችና የካርታ ማስረጃዎች ብዙ ሳትወጪና ሳትደክሚ የኔን አርቲክል በመመልከት ብቻ ስለወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ታሪክ የጠራ አመለካከትና ግንዛቤ ይኖርሽ ዘንድ የጻፍሁትን ወረቀት እንድታነቢ በአክብሮች ጋብዝሻለሁ። ሰናይ ጊዜ! (መነጭ: Muluken Tesfaw ፌስቡክ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
ሠላም ጎልጉሎች! ባለኝ ጊዜ በዋናነትና በቅድሚያ ከምከታተለው የድረ ገጽ አምድ የመጀመሪያዎቹ ናችሁ። በእዉነቱ በጣም አድናቂያችሁ ነኝ። ይሄ ደግሞ የለበጣ እንዳይመስላችሁ። ብዙ ጊዜ ባላኝ ጊዜ ደረ ገጻችሁን እጎበኛለሁ። በእኔ ዕይታ አቀራረባችሁ ይማርከኛል። በተለይ የህዝብ አስተያየት መስጫ( Comment) ማስቀመጫ ቦታ ላይ ለሚሰጡ አስተያየቶች በአንዳንዶች ላይ ( አስፈላጊ ሆኖ ስታገኙት )የምትሰጡት መልስ እና ማብርሪያ ምን ያህል ሲሪዬስ (ቁምነገረኛ) እንደሆናችሁ አመላካች ነው። ማለትም ፕሮፌሽናል እና ስራችሁን የትርፍ ጊዜ ሥራ አድርጋችሁ እንደማታዩት ድርጊታችሁ ገላጭ ነው። እናም በርቱ ! ጎበዞች
ውድ Ezira
መመስገን ያስፈራል – ይህ የቀረበልን ደግሞ ከልብ የመነጨ እንደሆነ ስለምናምን ክብደቱ ታላቅ ይሆንብናል። ሆኖም እንደዚህ ዓይነት ምስጋና ከአንባቢ ማግኘት በሌላው መልኩ እጅግ ያደፋፍራል – ብዙ እንድንሠራ ያደርገናል።
እጅ ነስተናል!
ጎልጉል
Regarding the case in point it very impressive and convincing. I have heard that before the current ruling part took power the river Tekeze was the demarcating boundary between the two administration regions. Both ethnic groups have had good and healthy relationships and intermarry.
Both ethnicities had no problem during the feudal system and The Derge military dictatorship living side by side and together. If that was the case then, who and what brewed the problem now? I believe that is the fundamental question that needs to be addressed.
As a lay man, I always think why not the government leave the two ethnic groups alone and let them live like they were used to.
Some of my friends who have a thorough knowing about that particular region told me, land has never been a problem. There is a vast land that can accommodate large number of people. The problem is equality. People who were once equal and friendly have become unequal, dominant and unfriendly. That is the root cause, not only in that particular region buy also through out all regions. so many people believe that is exactly the reflection from the highest level of the ruling party and government structure down to the grass root level. When government intervenes in the every livelihood of communities that is a bad unlucky sign.
In a country where the government assign you a name without your preference and limit and lock you up
in one particular region, what is the option to be a free citizen? If I do not have the right to be what I want to be, If I can not move freely within my country, if I am denied to work and live where ever I want, what is the meaning and the purpose of my citizenship. I know the slaves had been denied such rights because they were not considered citizens and human beings.
Back to Wolkiet Tsegedea, I believe the people have every right to be what they want to be. If they are denied this right, they have every right to secure their right by any means possible. It is not about language, associations and locations, it is about God given natural rights.
The inferior breed of Tigres are, creatures without conscience. If these traitors could easily betray the country of their birth, its history, the rest of Ethiopians, do they deserve to be humans?
They fought along side Eritreans to help the latter secede. No sooner than their occupation of Ethiopia, they ransacked Tanna Beles project and plundered every movable item of the multi-billion dollar investment to take it Tigrai and Eritrea.
They decommissioned Ethiopia’s multi-ethnic armed forces and supplanted them with Tigres who comprise only 5% of Ethiopia’s population. The annexed vast swathes of territory from Gondar and Wollo as well as ceded another vast tract of land to Sudan.
They divided us along baseless linguistic lines and made sure that tens of thousands of innocent Amaras were massacred by their armed proxies. They carried documented genocide in Ogaden, Gambella aginest Anuaks, Konsos recently.
They rendered us land-locked and are busy evicting millions of Ethiopians from their ancestral lands to sell it to foreigners. They dismissed the country’s most qualified academics from the oldest university n the country. The fate of the Ethiopian Airlines’ irreplaceable staff was no different. This was done to cripple the country and destroy its institutional memory.
Has there ever been anything like this in history?
I do not know how the minds of these Tigres and their servants work. It is puzzling that they do seem to be oblivious of the simmering rage across Ethiopia which when it soon boils over, will undoubtedly consume them big time.