• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ይገመታል!”

March 4, 2013 08:20 am by Editor 3 Comments

ኤርትራ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታና ወቅታዊው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ልዕልና መላላት ተከትሎ የፖለቲካ ጨዋታው ጦዟል። በበርካቶች ዘንድ ኢሳያስ እንዳበቃላቸው ተደርጎም እየተወሰደ ነው። ኤርትራ ውስጥ ለውጥ ከተካሄደ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለው አጓጊ ጉዳይ የሁሉንም ትኩረት የሳበ አጀንዳ ሆኗል። ኢሳያስ ያሉበት የ”ፖለቲካ ኮማ” ድብታ ውስጥ የከተታቸውም ጥቂት አይደሉም።

ኢሳያስን የደረሱበት የኮማ ጣጣ መቀመጫቸውን ኤርትራ ያደረጉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችና ወታደሮቻቸው የመጨረሻ እድል ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠራ መረጃ ባይሰጥም ሌላውና ዋናው የጡዘቱ አካል እንደሚሆን በርካቶች ይስማማሉ። በቅድሚያ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የሚጠቁሙም አሉ። ግን ምን አይነት ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት መፍትሄ የሚያቀርቡ የሉም። ዙሪያው ዝግ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤርትራ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የተቀመጡ የተቃዋሚ ድርጅት ወታደሮችና መሪዎቻቸውን አስመልክቶ ቅሬታ መሰንዘር ጀምሯል። በተለይም ኦነግ ኤርትራ ገብቶ ከመሸገበት ጊዜ አንስቶ ይሄ ነው የሚባል የትግል እድገትና ድርጅታዊ ግዝፈት ማሳየት ባለመቻሉ ኤርትራን ለቆ እንዲወጣ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ደጋፊዎች እየጠየቁ ነው።

“ትግሉ መካሄድ ያለበት አገር ቤት ውስጥ፣ ወገን መካከል ነው” የሚል አቋም የያዙ ደጋፊዎች በተለያዩ ድረገጾች ሃሳባቸውን እየሰነዘሩ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ መልኩ አንጋፋ የሚባሉት የኦነግ ሰዎች ከሰይፈ ነበልባል ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “የፈጀውን ጊዜ ቢፈጅም አገር ቤት ገብተን ትግላችንን እንቀጥል። የህዝብ አደራ አለብን” ሲሉ ተደምጠዋል። አደራውን ግን አላብራሩትም።

በሌላ በኩል ኢህአዴግ አንጋፋ ከሚባሉት የኦነግ ሰዎች ጋር በመደራደር የኦነግን የተወሰነ ክፍል ወደ አገር ቤት በማስገባት እርቅ ለማውረድ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ከእርሳቸው ጋር አብረው በሚሰሩ መልዕክተኞች አማካይነት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ከየአቅጣጫው ይሰማል። ቀደም ሲል ጀምሮ ሲፋዘዝና ሲግል የኖረው ኦነግንና ኢህአዴግን የማግባባት ስራ በኦነግ መከፋፈል ምክንያት እንደተፈለገው ውጤት እንዳላመጣ የሚገልጹ እንዳሉ ሁሉ ድርድሩን ኢህአዴግ ውስጥ ባለው የፖለቲካ አየር መሰረት ሆን ብሎ ቅኝቱን የማላላትና የማጥበቅ ስራ በመስራት ጊዜ እንደሚገዛበት የሚናገሩም አሉ።

የእርቅና የድርድር፣ ብሎም የኤርትራ መንግስት የፖለቲካ ጡዘት ማሸቀቡን በስፋት እየተወራ ባለበት አፍላ ወቅት ላይ ኢትዮጵያን ሪቪው በሚል ስያሜ የሚታወቀው ድረገጽ የአስመራ ታማኝ ምንጮቹ የነገሩኝ ነው በማለት ጄነራል ከማል ገልቹ በኤርትራ የቁም እስረኛ መደረጋቸውን ይፋ በማድረግ ያሰራጨውን ዜና ራሳቸው ከማል ገልቹ በኢሳት ሬዲዮ በኩል ቢያስተባብሉትም ኢትዮጵያን ሪቪው ግን የምንጮቹን ተዓማኒነት ደግሞ በመጥቀስ የጄኔራሉን ማስተባበያ ሊቀበለው አልቻለም።

ቀደም ሲል ጀምሮ በተቃዋሚዎች አያያዝና በአመራሮቻቸው ነጻ ሆኖ የመንቀሳቀስ ጉዳይ ላይ ሻዕቢያ ይታማል። አንዳንዶቹ የኦነግ አመራሮች ከአስመራ የመውጣትና ነጻ ሆነው የመንቀሳቀስ እድል የላቸውም። ኤርትራ ምድር ላይም ያረጁ አሉ። ይህንን ውሉ የጠፋበት የሻዕቢያ አቋም የሚቃወሙ ክፍሎች  “ሻዕቢያ ወገኖቻችንን መደራደሪያ ከማድረግ የዘለለ ዓላማ የለውም። ለዚህ ነው ለዓመታት ያለ አንዳች እድገትና ድርጅታዊ ውጤት ግዞተኛ ሆነው የቀሩት” በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። የጉልበት ስራ እንደሚያሰራቸው የሚገልጹም አሉ። ከኤርትራ በኩል ክብርን በሚነካ መልኩ የተቃዋሚ ድርጅቶችን አመራሮችና ወታደሮች የማሸማቀቅ ነገርም እንዳለ ይሰማል። ታስረው የሚማቅቁም ስለመኖራቸውም ይሰማል።

በየአቅጣጫው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጉዳይና የወደፊት እጣ ፈንታ መነጋገሪያ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ በሩን ዘግቶ ጉድጓድ እያማሰ እንደሆነ፣ ኢህአዴግ መለዮ ያለበሳቸው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ተቃዋሚዎችም ልዩነታቸውን በማጥበብ የመንግሥትነት ዝግጅት መጀመራቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን እስከወዲያኛው ለማሰናበት ኢህአዴግ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑንና ይኼው እንቅስቃሴ ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ አገሮች እንደሚደገፍ በተለይ ለዚህ ጉዳይ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል ተናግረዋል። እንቅስቃሴው ከራሳቸው ጥቅም አኳያ የቀጠናውን የጂኦ ፖለቲካ ጉዳይ የሚከታተሉ አገሮች ድጋፍ እንዳለበትም አልሸሸጉም።

በህወሃት ደረጃ ሻዕቢያን ማስወገድ እንደሚገባ አቋም ቢያዝም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተግባር እንዳልተገባ የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች፣ “ኢሳያስም የዋዛ አይደሉም። ይፋ ከሆነና ሚስጥር ተደርጎ ከተያዙ በርካታ ወጥመዶች በተደጋጋሚ አምልጠዋል። መረጃቸው ጠንካራና ለእርሳቸው ታማኝ በመሆኑ እስካሁን ለመቆየት ችለዋል” ሲሉ ድፍን መረጃ ሰጥተዋል።

አሁን ግን ሁኔታዎች መቀየራቸውን የሚያስታውሱት እነኚሁ ክፍሎች የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የመረጃና የመከላከያ አዛዦች ተሸርሽረዋል። እርሳቸውም ቢሆኑ የቀድሞው ሃይለኛነታቸው ክዷቸዋል። አሁን ያኮረፉና የሰለቻቸውን ባለስልጣኖቻቸውንና የጦር መሪዎች በማግባባት ስራ መጠመዳቸውን ነው የሚናገሩት። የህዝቡና ሰራዊቱ ምሬት ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ ህዝብ ኢሳያስን ወደ ማመንዠክ ደረጃ ማዳረሱን ይገልጻሉ። በራሪ ወረቀትና ፖስተር በመለጠፍ አዲስና ያልተለመደ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም ይናገራሉ።

ኢህአዴግ ኤርትራ ላይ አቋሙን ቢቀይር ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እንደሚሰጠው ስለሚያምን ኤርትራ ላይ በሚያራምደው ማናቸውም የአቋም ለውጥ ከውስጥ ተቃውሞ ይገጥመኛል የሚል ስጋት የለውም። ስለዚህ ኢህአዴግ ኢሳያስን በመጣል ኤርትራ ላይ የመንግስት ለውጥ ለማድረግ ትኩረቱ ኦፕሬሽኑ ላይ ብቻ እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ። አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት የኤርትራ ስደተኞች “በቅኚ አገዛዝ ረግጣ ይዛናለች” በሚሏት አገር ከባንክ ብድር ጀምሮ አስፈላጊው ሁሉ ተመቻችቶላቸው ስለሚኖሩ ኢህአዴግን ለመተባበር ቁርጠኞች እንደሆኑም ይነገራል። ጥር 22 ቀን 2005 ዓ ም አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ፊትለፊት በመቆም የአፍሪካ አገራት ኤርትራ ላይ አንድ አቋም እንዲይዙ መጠየቃቸው ለኢህአዴግ ከሚሰጠው ድጋፍ ትንሹና ቀላሉ መገለጫ አድርገው የሚወስዱ አሉ።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ኢሳያስን ያፈቅሩና ይወዱ የነበሩ በአብዛኛው አቋማቸውን ቀይረዋል። ኢሳያስ ላይ የሚነሳው ወቀሳና ትችት አደባባይ መውጣት ጀምሯል። በአገር የሚመሰለው ኤምባሲዎቻቸው ተበርግደው ተቃውሞ ተካሂዶባቸዋል። የማይደፈሩ የሚመስሉት ኢሳያስ ምስላቸው ከግድግዳ ወርዶ መሬት ሲከሰከስና ሲረጋገጥ ታይቷል። አገር ቤትም የተለያዩ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተካሄደ እንደሆነ ይሰማል። በጥር 21፣ 2013 ያኮረፉ ወታደሮች በብረት የተደገፈ ተቃውሞ አካሂደዋል። በዚህና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ኢህአዴግ ይህንን ወቅት ሊጠቀምበት ሩጫውን የማጠደፍና ለውጡ እንዲፋጠን የበኩሉን እየሰራ እንደሆነ  ሚስጥር አይደለም። ይልቁኑም ጊዜን የመግዛት ሩጫ ነው።

ምንጮቻችን አሁን ባላቸው መረጃ ኢህአዴግ ኢሳያስን ለማስወገድ የያዘው ዘመቻ ኢሳያስ ጥገናዊ ለውጥ ሳይጀምሩና ራሳቸውን በፈቃዳቸው በማግለል ከመጋረጃው ጀርባ ሳይሆኑ ለመቅደም ያሰበ ነው። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም በቅርቡ ፓርላማ ተገኝተው የመስሪያ ቤታቸውን የስድስት ወር ሪፖርት ሲያቀርቡ ኤርትራን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሚከተለውን ብለው ነበር።

“በኤርትራ ያለውን ሁኔታ በጥልቅ እየተከታተልነው እንደሆነ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። በተንታኞችና በመላምት ሳይሆን በተጨባጭ ያገኘነው መረጃዎች አሉ። ሁለት ዓበይት ነገሮች ይጠበቃሉ” ካሉ በኋላ ሁለቱን ጉዳዮች በመዘርዘር “ይህ በተጨባጭ መንግስት ባለው መረጃ መሰረት በተገኙ አንኳር ጭብጥ መነሻዎች መሰረት ክትትሉ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል። የኢትዮጵያን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ” ሲሉ ተናግረዋል። ስለላው ካሉት መረጃዎች መካከል “አንኳር” ተብለው የተጠቀሱት ጉዳዮች እነዚህ ናቸው።

ጥገናዊ ለውጥ በማካሄድ ስርዓቱን ማስቀጠልና የተነሱትን ተቃውሞዎች ለማላዘብ ሹም ሽር ማድረግ። በሹም ሽሩ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ራሳቸውን ከስልጣን እስከማግለል ይደርሳሉ። “አደገኛ” የሚባለውና ኢህአዴግም ስጋት አሳድሮብኛል በማለት የሚገልጸው። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይፋ እንዳደረጉት በለውጥ ስም ኤርትራ ውስጥ የሚፈጠረው ችግር በቀጠናው አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል የሚለው ትንበያ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው አንኳር ነጥብ ነው። ስለዚህ ኢህአዴግ እውቅና ያልሰጠው ለውጥ ወይም ኢህአዴግ የማይዘውረው አብዮት በኤርትራ እንዲከሰት አይፈለግም።

ኢህአዴግ በኤርትራ የሚካሄደውን የመንግስት ለውጥ ከማቀናበር ጀምሮ “ተተኪው ማን ነው?” በሚለው ዙሪያ ደፋ ቀና እያለ መሆኑን የጎልጉል መረጃ አቀባዮች አመልክተዋል። በዚሁ መነሻ መሰረት የኤርትራን ጉዳይ ብቻ የሚከታተል ንዑስ የደህንነት ክፍል በአገር ውስጥና በውጪ አገር እየተንቀሳቀሰ ነው፣ ከለውጡ በኋላ አቶ መለስ በህይወት እያሉ ለኤርትራ የደረሱላት የአስተዳደር ቅርጽ ተግባራዊ ለማድረግም ዝግጅት መጀመሩን እኚሁ ክፍሎች አብራርተዋል።

“ኤርትራ ውስጥ ለውጥ ይመጣል። ግን ህወሃት አጋፋሪ የሆነበት ለውጥ ከሚመጣ ከኢሳያስ ጋር ታፍኖ መኖር ይመረጣል፣ ምናልባትም እንደ አቶ መለስ እንገላገለውና ችግሮቹን ሊፈታ የሚችል ሃይል ከራሱ ከሻዕቢያ ውስጥ ሊፈጠር ይችል ይሆናል” የሚል አስተያየት የሚሰጠው በስዊድን የሚኖር የኤርትራ ተወላጅ ይህ አቋም የበርካታ ያገሩ ተወላጆች እንደሆነ ያስረዳል። ይህ መሰሉ አስተያየት የበርካቶች ቢሆንም ህወሃት አሁን ባለው አቅሙ ያሰበውን ለመፈጸም የሚያስችለውን ጉልበትና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ሊኖረው እንደሚችል ይናገራል። በስፋት ከሰጠው አስተያየቱ ውስጥ አስረግጦ የተናገረው ነጥብ “ኢህአዴግ ሃይልና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ቢኖረውም የኤርትራ ልጆች በህይወት እያሉ የትግራይ የበላይነት ኤርትራ ውስጥ አይታሰብም” የሚል ነው።

በየቀኑ ሰራዊቱን እየከዳ ወደ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚፈልሰው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጦር መፈርከሱን፣ በተቃራኒ ደግሞ የተቃዋሚዎቻቸው ሃይል መጠናከሩን የተረዱት ኢሳያስ በፕሬዚዳንት አልበሽር በኩል ድርድር እንደጠየቁ የጎልጉል የደቡብ ሱዳን ምንጭ ይገልጻል። ይህ የድርድር ጥያቄ ደቡብ ሱዳን ከያዘችው በተጨማሪ ነው።

ይኸው ምንጫችን ኢሳያስ ከበረሃው ትግል ጀምሮ ርምጃ የወሰዱባቸው፣ እስር ቤት በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍና እንዲሰቃዩ ያደረጓቸው ሰዎች ጉዳይ ይፋ እንዳይሆን በመጨነቃቸው ሰላማዊ ሽግግር በማድረግ ለለውጥ የተነሳውን ሃይል ማዳከም ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ እንደሆነ አመልክቷል። በማያያዝም ከኢትዮጵያ ጋር ጉዳዩን በሰላም መጨረስ ዋና አማራጭ በመሆኑ “የሰጥቶ መቀበል” ስምምነት ለማድረግ ፈቃደኘነቱ እንዳለ መረጃ እንዳለው አመልክቷል። ሰጥቶ መቀበሉ እጅግ ሰፊ ጥልቀት ያለው በመሆኑ የት ድረስ ሊሆን እንደሚችልና ምን ምን እንደሚያካትት ግን ማብራሪያ አላገኘም።

አኩራፊ የተባሉ ወታደሮች የኤርትራን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቆጣጥረው እንደነበር ከተሰማ በኋላ ኢሳያስ አፈወርቂ ጉዳዩን አቃለውና አጣጥለው አቅርበውታል። ፍጹም የተረጋጉ መስለው ተቃውሞውን ያጣጣሉት ኢሳያስ ባጽዕ (ምጽዋ) የተለቀቀችበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ግን እንደቀድሞው አልደሰኮሩም። ጉዳዩን ከሚከታተሉ ምንጮች እንደተደመጠው ከሆነ በዓሉ ላይ የተገኙት አቶ ኢሳያስ ብዙም ሳይቆዩ ባልተለመደ ሁኔታ ወደ አስመራ ተመልሰዋል። ይህ የተስፋ መቁረጥ ዋንኛ መገለጫ ተደርጎ ቢወሰድም በዋናነት ግን የመፈንቅለ መንግስት ፍርሃቻ ስላላ ኢሳያስ የንግስ ቤታቸውን እንደወትሮው ጥለው መሽከርከሩን አልወደዱትም።

ኢሳያስን ለማስወገድ የተቋቋመው ልዩ የደህንነት ክፍል በውጪ አገር ታዋቂ የኤርትራ ተወላጆችን በከፍተኛ ደረጃ እያግባባ ሲሆን በአገር ቤት ኢሳያስ ላይ ብረት ያነሱትን ሃይሎች በማደራጀት ላይ እንደሚገኝ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል ተናግረዋል። እንደነዚሁ ክፍሎች ገለጻ ኤርትራ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ይካሄዳል የሚል ግምታቸው ከፍተኛ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. addis mamo says

    March 4, 2013 04:41 pm at 4:41 pm

    I appreciate you

    Reply
  2. Milkias berhane says

    March 5, 2013 04:39 pm at 4:39 pm

    Ethiopia le eritrea tekawamiwoch genzeb kemestet yalef lela neger yemadreg akmum chilotawm yelewm b/c ertrawyan ethiopia mnachew endehonech bedenb yawkalu beterefe kelay yetexafew yante wey yemeriwochih kentu helm new

    Reply
  3. Milkias berhane says

    March 5, 2013 04:57 pm at 4:57 pm

    Eritrawyan AU ategeb selamawi self aderegu yalkew wedza man wesedachew? Bewdeta new begdeta? Self kalwetachihu weyewlachihu Eyale yasferaran man neber? Were agegnew teblo ayxafm

    Reply

Leave a Reply to addis mamo Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ August 11, 2022 03:04 pm
  • በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ግብጽ ለዓመታት የፈጸመችው ሤራ August 10, 2022 10:58 am
  • የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ August 8, 2022 09:45 am
  • “አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”          July 19, 2022 04:57 pm
  • ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው July 19, 2022 01:55 am
  • የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች! July 18, 2022 03:13 pm
  • ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች July 17, 2022 05:36 pm
  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule