• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”

August 10, 2013 04:12 am by Editor 3 Comments

”የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል” በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ።

በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ በየአቅጣጫው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ያለ ምንም ማጋነን ኢህአዴግ ደም አፍሷል፣ ህይወት ቀጥፏል፣ አስሯል፣ ገርፏል፣ ፈንክቷል፣ ጣጣው ለሌሎች የሚተርፍ አካሄድ በመከተሉ ችግሩን አወሳስቦታል። ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ርምጃ የሚወስደው “ከብዙ ትዕግስት” በኋላ መሆኑን “በመንግሥት ወግ” ቢገልጽም “የሚያምነው ያገኘ አይመስልም” የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል። እንደውም “ለየትኛዋ የሚወዳት አገር” በሚል ለፕሮፓጋንዳ አፉን በከፈተ ቁጥር ዘለፋ እየወረደበት ነው።

“ኢህአዴግ ጉልበት አልባ ተደረገ!”

ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ገለጻቸው ለሌላው ግራ የሚያጋባ አባባል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። ግን በነሱ እምነት ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል። አቅም አልባ ያደረገው “የድምጻችን ይሰማ” የትግል ስልት ነው። ኢህአዴግ ያለውና 4የሚታወቅበት መለያው የታጠቀው መሳሪያ፣ ወታደሩ፣ የፌደራል ሃይሉ፣ የክልል ፖሊስ፣ ፈጥኖ ደራሹ፣ የሰላምና መረጋጋቱ ፣ የስለላ ሃይሉ፣ የአጋዚ ጦሩ፣ የአንድ ለአምስት አወቃቀሩ … ከሁሉም በላይ ደግሞ ጉልበተኛነቱን የሚቆጣጠሩለት የአንድ ብሔር “ታማኝ” ሃይሎች መሆናቸው እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ።3

“ኢህአዴግ አለኝ የሚለውን ጉልበቱን መጠቀም ቢፈልግም መድረኩን ‘በተጠና’ የትግል ስልት በሚፈልገው ደረጃ ሊጠቀም አለመቻሉ በደጋፊዎቹና በራሱ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “የሙስሊሞች እንቅስቃሴ፣ የዕዝ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚያካሂዱት ትግል ኢህአዴግ ጉልበቱን እንዳይጠቀም ከልክሎታል። አሁን እየወሰደ ያለውና የወሰደው የሃይል ጥቃት ሊወስድ ከሚፈልገው ጋር ሲነጻጸር ሃይሉ ሽባ መደረጉን ያሳያል፤ ይህ ደግሞ የሰላማዊ ትግል ውበት ነው” ሲሉ ኢህአዴግ በገባው ጭንቅ መጠን ርምጃ ባለመውሰዱ እንደሚቆጭ ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር የሽብር፣ የማሸበርና የመግደል “ጠቢብ” ለሆነው ኢህአዴግ አሁንም ችግሩ የሚፈታው በሃይል፣ በባሰ ሃይል እንደሆነ ከማመን አላፈገፈገም ሲሉ ያብራራሉ።

ኢህአዴግ ነገሮችን እያባባሰ የሰላማዊ ትግሉን ወደ አመጽ ለማስቀየር ሃሳብ ቢኖረውም “የድምጻችን ይሰማ ህብረት አስቀድሞ መረጃ የማግኘትና በሰላማዊ ትግል ተክኖ መገኘት ኢህአዴግ ያሰበውን እንዳይፈጽም አድርጎታል” በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። እነዚህ ክፍሎች ኢህአዴግ “አክራሪነትን የሚሰብኩና የሚያቀነቅኑ አሉ” በማለት ለሚለፍፈው “እስካሁን የአክራሪ ሙስሊም እንቅስቃሴ ስለመታየቱ መረጃ የለም። ከተፈጠረም አክራሪነት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆነው ራሱ ኢህአዴግ ነው። ደም ማፍሰሱን አጠናክሮ በቀጠለና ዜጎችን ማሰሩ በገፋበት ቁጥር ለመሞት የሚዘጋጁ ዜጎች አገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል የወንድሞቻቸውን ጭፍጨፋ በመመልከት የመስዋዕትነቱ ተካፋይ ለመሆን ዓለምአቀፋዊ የሙስሊም ኅብረተሰብ ቁጣ ያስተባብርና ራሱን ችግር ላይ ይጥላል፤ ለአገርም መከራ ይሆናል፡፡”

በተቃራኒው አክራሪነት እየተስተዋለ የመጣው አሁን እንዳልሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “በአሁኑ ሰዓት አገራችን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ውህደት ቀደም ሲል እናቶቻችንና አባቶቻችን በየዋህነት ሲያደርጉት እንደነበር አይነት ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው” በማለት ይናገራሉ። በማያያዝም እንዲህ ያለው ስጋት በሰላማዊ ትግል ጉልበት አልባ የሆነውን ኢህአዴግ ሃይል እንዲያገኝና ይህንን ሃይል እንዲተማመን አድርጎታል ሲሉ ይከራከራሉ።

“ኢህአዴግ ሰክሯል”

ኢህአዴግ መስከሩን፣ አንጎሉ መዞሩንና የሚያደርገው እንደጠፋው የሚናገሩ ክፍሎች እንደሚሉት የኢድ ቀን ኢቲቪ ያሰራጨውን ዜና ቀላል ምሳሌ አድርገው ያቀርባሉ። የድምጻችን ይሰማ መነሻ ምክንያት የሆኑትን አዲሱን የመጅሊስ መሪ በቴሌቪዥን መስኮት አቅርቦ 2“ሙስሊሞች ላይ የወሰዳችሁትና የምትወስዱት ርምጃ የሚደገፍ ነው፣ ትክክል ነው” በማለት ያቀረበው ቃለ ምልልስ “ከስካርም በላይ አዙሪት ነው” ሲሉ የኢህአዴግን የበሽታ መጠን ይገልጻሉ። ሙስሊሙን አንኳን አሰራችሁት፣ ደበደባችሁት፣ ገደላችሁት በሚል ደረጃ “ደግ አደረጋችሁ፣ ርምጃችሁ ትክከል ነው” በማለት ዜና ማሰራጨቱ ኢህአዴግ በራሱ ሚዲያ በችግሩ ላይ እሳት ማርከፉን የሚያመላክት  ስለመሆኑ በማሳያነት ያቀርባሉ።

አንድ ጤና ያለው መንግስት የህዝብ ቁጣ ሳይለሳለስ፣ የቁጣውን መንስዔ አደባባይ በማቅረብ “ተጎዳን በሚሉ የህብረተሰብ፣ በተለይም የአንድ እምነት ተከታዮች ፊት ማዘፈን ኢህአዴግን የያዘውን የስካር የዞረ ድምር  (ሃንግኦቨር) የማሽተት ያህል ነው” የሚሉት ክፍሎች ኢህአዴግ ቢያንስ ለራሱ፣ ህወሃትና ቁንጮው ላይ ሆነው ሃብት ለሰበሰቡት ሲል እርቅ ሊወርድ የሚችልበትን መንገድ እንዲያስብበት ይመክራሉ። ጉዳዩንም በጥበብ እንዲይዘው ይመክራሉ።

መተማመን ድሮ ቀረ!!

በሙስሊም ወገኖች አወሊያ የተጀመረው የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ፣ የኢህአዴግ የጥያቄው አያያዝ ችግር ተዳምሮበት የእምነቱ ተከታዮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተቃውሞው እየተዳረሰ ይገኛል። የአገሪቱን ሙስሊሞች ከጫፍ እስከጫፍ በሚያስገርም የግንኙነት መረብ እያስተባበረ የሚነደው ሰላማዊ ቁጣ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ድጋፍ አለማግኘቱን ለኢህአዴግ ሃይል እንደሆነው የሚናገሩ ወገኖች “ይህንን አስመልክቶ በሚቀርበው መረጃ ግራ ተጋብተናል” ይላሉ።

“እንኳን የሌላውን ሃይማኖት የራሳቸውን ሃይማኖትና ስርዓት ማስጠበቅ ያቃታቸው የክርስትናው ሃይማኖት ተከታዮች፣ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ደገፉ ተብሎ ሲዘገብ ዘገባው ሚዛን የሚደፋ አይሆንም” በማለት የሚከራከሩ ክፍሎች “የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእምነታቸው ሊሰጡ የሚገባውን ክብር ከድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ መማር ከቻሉ ይህ ብቻ በራሱ ይበቃል” በማለት በተቃራኒ ወቀሳ ይሰነዝራሉ። እንደውም የራሳቸውን የእምነት ቤት ማጽዳት ባለመቻላቸው ሊወቀሱ እንደሚገባ መረጃ በማጣቀስ ይከራከራሉ።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ካለው የረዥም ጊዜ የተቀነባበረ ሴራና የምንገኝበት የጂኦ ፖለቲካ ካሸከመን ጣጣ ጋር በማዳመር “ሜዳዎች ሁሉ ሸራተን ሆነው አይዋቡም” የሚል አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች “መተማመን ድሮ ቀረ” ሲሉ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ዝምታ ይገልጹታል።

“ሙስሊሞች አብዛኞች በሆኑበት ቦታ ያለ ችግር ቢፈልጉ አክርረው፣ ቢፈልጉ አለዝበው እምነታቸውን ያራምዳሉ። አነስተኛ በሆኑባቸው አገራት ደግሞ ያለውን የአስተዳደር መሰረት የመጋራት ፈተና ይፈጥራሉ”  የሚሉት እነዚህ ክፍሎች “እነዚህ በሌሎች አገሮች የታዩ ተሞክሮዎች ከምዕራቡ መገናኛ ውስወሳ ጋር ተዳምረው በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ያስቀመጡት ጠባሳ ቀላል አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥም ይህ ችግር አለ” ባይ ናቸው። በሌላም በኩል በማህበራዊ ድረገጾች አርሲ አርባ ጉጉና ጅማ የተከናወነውን በማንሳት ሰሞኑንን ለመከራከር የሞከሩትን በመጥቀስ የፍርሃቻው ማሳይ አድርገው ያስቀምጡታል።

ፍጹም ሰላማዊ ትግል – ፍጹም የሚያስቀና ህብረት!!

መሰረታዊ የእምነትና አመራር ጥያቄ በማንሳት ትግላቸውን በተጠና መንገድ የሚያካሂዱት የ”ድምጻችን ይሰማ” የትግል መስመር አስገራሚ እየተባለ ነው። ህብረታቸውና በተዋረድ የሚያካሂዱት መናበብ አስደማሚ ሆኗል። አልፎ አልፎ ከሚሰራጩ ወፍ ዘራሽ5 መልዕክቶች በስተቀር መሪዎችን በመከተል የሚያሳዩት ትብብር የሚያስቀና እንደሆነ እየተነገረ ነው። ተመሳሳይ ዓላማ ይዘው እርስ በርስ የሚቧቀሱት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ከድምጻችን ይሰማ “የሰላማዊ ትግል” ቀመር ሊማሩና ይሁንታ ካገኙ ስልጠናም ሊወስዱ እንደሚገባ የሚናገሩ ተበራክተዋል።

እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የሙስሊም ወገኖች ጥያቄና ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ወደኋላ እንደማይሉ በመደጋገም ይፋ እያደረጉ ነው። ኢህአዴግ ከተካነበት ድርጅቶችን የመሰንጠቅና “የእባቡን አንገት ቁረጥ” ከሚለው የአምባገነኖች መርሁ አንጻር ድምጻችን ይሰማ ውስጥ ዘልቆ መግባት አለመቻሉ አስገራሚ የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ቅንጅት እንደ ሰደድ እሳት አገር አዳርሶ ኢህአዴግን ባስጨነቀ ማግስት “ሳሎኑ ተበርግዶ ኢህአዴግ ሲንቦጫረቅበት” የተመለከቱ፤ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የዘለቀውንና ከዕለት ወደ ዕለት በብቃትም ሆነ የኢህአዴግን መሠሪነት በመመከት እንዲሁም የተጠና የትግል ችሎታ በማሳየት ወደር ያልተገኘለትን የድምጻችን ይሰማ ትግል ከማድነቅ ወደኋላ አይሉም። ለሌሎች ሲመክሩም የመስመርና የትግል አስተላለፍ ለውጥ ለማድረግ አሁንም ጊዜው እንዳላለፈ ሊገነዘቡት ይገባል በማለት ለሌሎች የሰላማዊ ትግል ምንነት ላልገባቸውና የገባቸው መስሏቸው ተስፋ ለቆረጡ ይመክራሉ፡፡

ማስታወሻ

ይህ ሪፖርታዥ የተቀናበረው የዝግጅት ክፍላችን ካነጋገራቸው ወገኖችና በኢሜል ከተላኩ መልክዕክቶችና አስተያየቶች በመመርኮዝ ነው። ለንባብ እንዲያመች የአርታኢ ስራ ከመሰራቱ ውጪ ሙሉ ሃሳቡ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ያሰፈሯቸው ነው። አሁንም በዚህ ጽሁፍ ላይ የቀረቡትን ሃሳቦች በማስፋትም ሆነ በመቃወም የሚላኩ ጽሁፎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን። (ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከቢላል Tube Photos ድረገጽ ነው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, middle east

Reader Interactions

Comments

  1. anoolewako says

    August 10, 2013 05:08 am at 5:08 am

    Denk thehuf!! Ejeg maraki akerareb!! Tenkara melekt yeyaza thehuf!! Hulum leyanabew yemegaba!!

    uuuuuuuff!! Betam rakahu!!

    THANK U!!

    Reply
  2. ali mohamed says

    August 10, 2013 11:34 am at 11:34 am

    alhamedillilahh ethiopia hagerachin wete belyleww anunarr kegebban 30ametotchin askoternnn allahh yekterelenn mechemm bekerbb yezihh ayenotochin memamarr kadaberachehu bekkerebbe yemenewedaten ethiopiann enayalenn inshallahhh !!!!! lehulume etiopiwi manbbebbbyemigebbbaww amdachin newww alahh yechemerelachuu allahuakebberrrr!!!!!

    Reply
  3. Mario says

    August 12, 2013 07:24 am at 7:24 am

    When people have enough of oppression, suppression, subjugation, exploitation, etc etc, they can do the unthinkable. This brave man did the unthinkable and showed us the way how to resist and say no to all sorts of human abuse by woyane/TPLF.

    Yenesew Gebre, a teacher torched himself in public in protest against woyane/TPLF despotic and tyrannical rule. That was unheard of in Ethiopia. Who would have thought that?

    That un-named young man and Yenesew Gebre could be “enemies and terrorist” to woyane/TPLF, but they are our heroes without any doubt. Their sacrifice and bravery will not be wasted or in vain. There were/are thousands of Ethiopians like them to cary freedom torch and move forward.

    My question is this: Individuals like Yenesew Gebre and this brave young man showed us the way how to resist woyane/TPLF’s brutality. Have we really figured out in earnest the best way of bringing down this tyrannical regime that is eating us alive like a shark every single day?

    As much us woyane/TPLF love our division, we should love our collective fight against its brutality and tyrannical rule. We must hate what woyane/TPLF love and love what woyane/TPLF hate. That should be our motto and working formula.

    United we stand, divided we fall!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule