• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መንገድ ሲዘጋ የኖረው ህወሃት/ኢህአዴግ መንገድ እየተዘጋበት ነው

December 18, 2015 10:31 am by Editor 2 Comments

ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞውን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬዉን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡ (የዜና ዘገባው ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ነው)

የተቃውሞው መነሻ  “ያለ ተገቢ የገንዘብ ክፍያ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል የመሬት ቅርምት ነዉ” የሚል መኾኑ ሲዘገብ ቆይቷል። የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹ ላይ በወሰዱት ርምጃ ቢያንስ አምስት ሰዎች እንደተገደሉ መንግሥት  አምኗል። የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች በበኩላቸው የተገደለዉ ሰዉ ቁጥር ስልሳ እንደሚደርስ ተናግረዋል፡፡ የጸጥታ አስከባሪዎች ሕይወት ማለፉም ተገልጿል።

የኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦቻችን ስለ ዛሬው  የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ ምንጮቻቸውን ጠቅሰው እንደዘገቡት፤በዛሬው ዕለት በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ በሱሉልታ፣ በሆሮ ጉድሩ፣ በነጆ፣ በጫንቃና በሌሎች ቦታዎች  ሰልፉ መቀጠሉንና በዚሕም የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በኢሉባቡር አልጌ ሳቺ ከተማ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ተቃውሟቸውን አሰምተው በሰላም መመለሳቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መታሰራቸውን አብዛኞቹ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በፌደራልና መከላከያ ፖሊስ ጥብቅ ጥበቃ ሥር መዋላቸውን ዘግበዋል፡፡thur

በሌላ በኩል ማርታ ከአዲስ አበባ ባጠናከረችው ዘገባ  “የተማሪዎቹ ተቃውሞ ወዲያዉ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ክልልን አዳረሰ፡፡” ሲል ይጀምራል፡፡ ገበሬዎችና ሌሎች ነዋሪዎችም በተቃውሞዉ ተማሪዎቹን ተቀላቀሉ። መንግሥት አንዳንዶቹ ተቃዋሚዎች አገሪቱን ለማናጋት የሚንቀሳቀሱ ናቸዉ በማለት ይከሳል። ለደህንነታቸዉ በመስጋት ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የክልሉ ነዋሪ፤ ወደ ክልሉ የተላኩ የጸጥታ ኃይሎች ሌሎች ሰዎች ተቃውሞውን እንዳይቀላቀሉ መንገዶችን ዘግቶ እየተቆጣጠረ እንደኾነ ተናግረዋል።

እንደ ነዋሪው ገለፃ “አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ገበሬዎች ናቸዉ። ከገጠር አካባቢዎች ነው ወደ ከተሞች የሚመጡት። የመከላከያ ኃይል ደግሞ ወደ እነዚህ ገጠሮች አምርቷል። ፖሊሶችም ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ቁጥጥር ስር እያዋሉ ነዉ።”

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ባደረጉት ግጭት አምስት  ሰዎች መሞታቸዉን አረጋግጫለሁ ብሏል፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል ይላሉ። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽል (Amnesty International)  ትላንት ዕረቡ ባወጣዉ መግለጫ መንግሥት ተቃውሞዉን በኃይል እያፈነ ነዉ ብሏል።

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለውን በመቃወም ባለፈዉ ዓመት ሚያዚያ ወርም እንዲሁ ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። ተቃውሞዉን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል ርምጃ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎችም ታስረዋል። ማስተር ፕላን የተባለዉ የዋና ከተማዋን ማለትም የአዲስ አበባን ድንበር የሚያሰፋ ንድፍ ነዉ። በዙሪያዋ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር ዜጎች “የታቀደው መዋቅር መሬታችንን ነጥቆን የባህል ቅርሶቻችንን የሚያወድም በመኾኑ ያሳስበናል” ይላሉ።

thuየኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ካለፈዉ ዓመት ተቃውሞ በኋላ ስለ ማስተር ፕላኑ ጉዳይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ሁለገብ ዉይይት ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር። ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እነዚያ ቃል የተገቡት ውይይቶች አልተደረጉም ይላሉ።

“ብዙ ጊዜ ውይይት እንዲደረግ ሞከርን፣ አናደርግም አሉ። ከዚያም ግልጽ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ሞከርን እሱንም እንቢ አሉ። መንገዱን ዘጉብን። አሁን እንግዲህ እዚህ ላይ ደረስን። የዚህ መንግሥት ሁኔታ ሕዝቡን አንገሽግሾታል። በተለይም ወጣቱ ይህ መንግሥት በሚያደርገው ነገር ኹሉ ተንገሽግሿል።”ሲሉ ይገልጻሉ፡:

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፤ “ማስተር ፕላኑ መሰረዝ አለበት፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትም ፈርሶ በሌላ መተካት አለበት” ይላሉ። መንግሥት በበኩሉ ማስተር ፕላኑ ሥራ ላይ አልዋለም ይላል፤ ተቃዋሚዎች ደግሞ ገበሬዎችን ማፈናቀል ከተጀመረ እንደቆየ ይገልጻሉ።

በኢትዮጵያ ብዙም ተቃውሞ አይካሄድም። ገዢዉ ፓርቲ እንደ አዉሮፓውያን አቆጣጠር በ1991 ዓ.ም ሥልጣን የያዘ ሲኾን ባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደ ምርጫ ሙሉውን የምክር ቤት መቀመጫ ተቆጣጥሯል። የጸጥታ ጥናቶች ተቋም ባልደረባ ሃሌሉያ ሉሌ ውጥረት እንደሰፈነ ይናገራል።

“ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተመለከትን ነዉ። የጸጥታ ኃይሎቹም ኾነ መንግሥት የተከሰተዉን ከፍተኛ ተቃውሞ የጠበቁ አይመስለኝም። በእኔ እምነት የክልሉ መንግሥትም እንዲህ ዓይነቱን ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ያለመኾኑን ሁኔታዉ አሳይቷል”ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ድምጽ እዚህ ላይ ያድምጡ፡፡

በሌላ በኩል ሳምንታት ያስቆጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ ሃሙስም ቀጥሎ ውሎዋል፡፡ በሰላማዊ ትግል አሠራር መሠረት በተለይ በሱሉልታና ሌሎች አካባቢዎች የታየው ስልት የትግሉን መስመር መያዝ እንደሚያሳይ ተጠቁሞዋል፡፡ ሱሉልታ ለአዲስ አበባ ከመቅረቡዋ አኩዋያ ነዋሪዎች የመኪና መንገዱን ዘግተው መዋላቸው ያደረሰው ተጽዕኖ በአገዛዙ በኩል ሄሊኮፕተር እስከማሰማራት ያደረሰ ሆኖዋል፡፡

የዘር ጽንፈኝነትን የሚቃወሙ ወገኖች ንቅናቄው ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ጥሪ እያደረጉ ሲሆን በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኩል ደግሞ ንቅናቄውን ለማኮላሸት የዘር ልዩነቶችን ማስፋትና ከተቻለም መጎዳዳት እንዲከሰት የማድረግ ሥራዎች ይሠራሉ የሚሉ ወገኖች ህዝቡ ይህንን ከመሰለ የዘርና የሃይማኖት ክፍፍል እንዲቆጠብን ያሳስባሉ፡፡

ሕዝባዊ ንቅናቄው ይህንን ያህል ሳምንታት መቆየት መቻሉ እጅግ አሳሳቢ ሲሆን በህወሃት/ኢህአዴግ በኩል የሚፈጸመው ግድያ አሁንም ቀጥሎ እስካሁን የሞቱት ከመቶ በላይ እንደሆኑ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ይነገራል፡፡ (ጎልጉል)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Oumar says

    December 18, 2015 12:33 pm at 12:33 pm

    Sheikh Hussein endalut ” endewetu yiqeralu.” Yaa mehonu new.

    Reply
  2. Adisu says

    December 18, 2015 03:29 pm at 3:29 pm

    All Ethiopian pease be together to be free to be unethiopian to be the owner of the country
    That is the only way to get your freedom you have ditrmination to be free.

    Reply

Leave a Reply to Adisu Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule