• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

፸ ደረጃ

August 26, 2014 08:45 pm by Editor 2 Comments

ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ወይም “ቴዲ አፍሮ” በሰባ ደረጃ የተባለ(ች) ነጠላ ዘፈን ለቆልናል፡፡

“በሰባ ደረጃ”ን እኔ ስሰማው እልም ያለ የፍቅር ዘፈን ነው፡፡ ፍቅርን ልዩ በሆነ ቦታና ልዩ በሆነ ሥፍራ የሚያሳይ ዘፈን፡፡ በአማርኛ ዘፈን ባህል ውስጥ ቦታን ማስጎብኘት የተለመደ ነው፡፡ “የሐረር ልጅ ነች ወጣቷ/ጀጎል ነው ቤቷ” አይነት ዘፈን ሞልቶናል፡፡ አብዛኛው ያገራችን ዘፋኝ፣ ያስጎብኝነት ሚናም ደርቦ ሲጫወት ኖሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተፈቃሪዋ ሴት ሁሌም ከታሪካዊ ቦታ አጠገብ ለመወለድ ትገደዳለች፡፡

ቴዲ በዚህ ዜማው ባልተሄደበት መንገድ ሄዷል፡፡ ሲጀምር፣ እዚህ ግባ የማይባል፣ ለዓይን የማይሞላ ቦታ መረጠ፡፡ ብዙ ጊዜ፣ ታሪካዊ ቦታ ሲባል አክሱም፣ ላሊበላ፣ ፋሲል፣ ሶፍኡመር፣ ጀጎል እንላለን፡፡ ካሜራው በኒህ ቅርሶች ላይ አፍጥጦ ኖሯል፡፡ ታሪክ አክሱም ላይ ጀምሮ ጀጎል ላይ የተጠናቀቀ ይመስል፡፡

ብዙዎቻችን በሸገር ላይ አድልኦ ስንፈጽም ኖረናል፡፡ አዲስ አበባ ለአቅመ ቅርስ የምትበቃ ከተማ አትመስለንም፡፡ ሸገር ታሪክ ሲሠራባትና ሲሠራላት እንደኖረች አናውቅም፡፡ ወይም ለማወቅ አንፈልግም፡፡ ቴዲ ይህንን እይታ ቀየረው፡፡

ሁለተኛ፣

ከላይ የጠቀስኳቸው ቅርሶች የጌቶች መታሰቢያ ናቸው፡፡ የምድራዊና ሰማያዊ መሪዎችን የሚወክሉ ናቸው፡፡ የስም የለሹን፣ የተርታውን ሰው ኑሮ የሚያሳዩ ቅርሶች ግን ደምቀው አልወጡም፡፡ አይተን እንዳላየን፣ ቸል ብለናቸው ቆይተናል፡፡ ቴዲ ግን ማንም ሲወጣበትና ሲወርደበት ለኖረው አንድ መንገድ ዘፈነለት፡፡ መዝፈን ቢሉህ ዝም ብሎ መዝፈን ብቻ አይደለም፤ አንድ ውብ የሆነ የፍቅር ታሪክ 70 de rejaተረከበት፡፡ ነጠላ ዜማው ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሰባ ደረጃን በድሮ ዓይናችን አናየውም፡፡ አሪፍ ጥበብ ዓይን ገላጭ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

ሦስተናው ነጥብ፣

ዘፋኞች ልዩ ቦታን ሲያሳዩ ኖረዋል፡፡ ቴዲ ደግሞ አንድን ልዩ ዘመን ለማሳየት ሞክሯል፡፡ የቴዲን ዘፈን ስሰማ፣ በካሳሁን ግርማሞ ዘመን የኖረ አንድ ሮሚዎ ይታየኛል፡፡ ሸዋ ዳቦ ሳይቋቋም፣ ከአርመን ሱቅ ፉርኖ በሚሸመትበት ዘመን፣ ምኒባስ ሳይገባ፣ ሰዎች ሴቼንቶ የሚሳፈሩበት ዘመን፣ ከጄኔራሎች በላይ ሴቼንቶ ነጂዎች ስመጥር የነበሩበት ዘመን፣ ሴቶች የጥላቸውን ቁመት አይተው ሰአት ከመገመት ወጥተው፣ ክንዳቸው ላይ ሰአት ማሰር የጀመሩበት ዘመን – በዚያ ዘመን የኖረ አፍቃሪ ይታየኛል፡፡ አንድን ልዩ ዘመን በሲኒማና በልቦለድ ማሳየት የተለመድ ነው፡፡ በጣም አጭር ቆይታ ባለው ዘፈን ውስጥ ዘመንን ለማሳየት በመሞከር ግን ቴዲ ፋና -ወጊ ይመስለኛል፡፡

70 derejaዜመኛ ስላልሆንሁ ስለቴዲ ዜማ ምንም ማለት አልችልም፡፡ያም ሆኖ ፣ግጥሙ የተዋጣለት እንደሆነ መመስከር እችላለሁ፡፡ አንድ ቦታ ላይ “አንደ አርሚዴ ሜሪ” የሚል ሐረግ ሰምቻለሁ፡፡ ዜመኛው፣ ሜሪ አርምዴን፣ አርምዴ ሜሪ ብሎ መጥራት የገጣሚነት ነጻነቱ ይፈቅድለታል፡፡ ገጣሚ እንደ ህጻን ልጅ፣ እንደ እብድና እንደ ቅዱሳን ከቋንቋ ሕግ በላይ ነው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ፣ በሰዋስው ህግ አይታሠርም፡፡ እንዲያውም ሳይራቀቁ መግጠም፣ ፈሳሽ ውስጥ ሳይገቡ መስጠም አይታሰብም፡፡

በነገራችን ላይ በድሮ ዘመን በኢትዮጵያ የአባት ስም ከልጅ ስም ቀድሞ ይጻፍ ነበር፡፡ ቴዲን ትውፊትም ያግዘዋል ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ፣ በሚቀጥለው ጽሁፌ እናወጋለን፣ እስከዛ ድረስ ያንን ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም!

(ምንጭ: Bewketu Seyoum facebook. ፎቶዎቹን የወሰድነው ከቴዲ አፍሮ ፌስቡክ ገጽ ነው)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. rahel says

    August 26, 2014 09:56 pm at 9:56 pm

    Teddy nice music I like it or so smart

    Reply
  2. በለው ! says

    August 30, 2014 06:38 pm at 6:38 pm

    /////ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም! …አዎን የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ…በሁሉን አናጥፋው ዘመን “የማፍረስ አባዜ” ይህ ወጣት ከታሪክ…አስክታሪካዊ ቦታና የፍቅር ሠፈር ሸገርን አስጎበኘን…ክብረት ይስጥልን ብለናል!።መቼም በግጥምም (አማርኛን በአማርእኛ)በትርጓሜና በትችት የሚችለን የለም ግን ሁሉን ቻይ አምላክ ለሁሉ ማሰብ፣ ክህሎት፣ ድምፅን ሲለግስ አንዳንዶች ያልተወለዱበትን ያላደጉበትን ባሕላና ቋንቋ መስለው ለመገኘት ብዙ ይጥራሉ። ያም ቢሆን ከማን አንሼ ያ..ብሄርና ሰፈርና ህዝቡ የአኔም ነው እኔም ያገባኛል አዘምርለታለሁ እቀኝለታለሁ አውቄው እቀውቅና ይሰጠኛል ብለው ነው መልካም ነው በልዩነታችን ውበታችንን ማሳየት ሳይሆን አንድነታችን ኅብረታችን ጥንካሬአችን ነው ታፍረንም ተከብረን የኖርነው ለዚያም ነው!እንግዲህ ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፸ ደረጃን ወረደበት ! እናንት የቀበና፣ የሽሮ ሜዳም፣ የውቤ በረሃ፣ካዛንችስ፣ለገሃር አራት ኪሎ፣ሽሮ ሜዳ፣ ጃልሜዳ፣አፍንጮ በር፣ እሪ በከንቱ እያላችሁ ውረዱበት ! /////>>>ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም!ተቀበል በለው!

    Reply

Leave a Reply to በለው ! Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule