• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”

August 23, 2021 04:07 am by Editor 2 Comments

ቁጭ ብዬ ናሽናል ጂኦግራፊክ ስመለከት ጅቦች አየሁ። አንድ ጎረምሳ አንበሳ ይተናኮላሉ። አንበሳው እየገላመጠ መንጋጋውን እያጓራ ያሳያቸዋል። ራሱን ለመከላከል ብዙም ያልተጨነቀው አንበሳ እየተቆጣና እየተገላመጠ ሲራመድ ጅቦቹ የልብ ልብ ተሰማቸው። ጅቦች አንበሳን ሊበሉ ቋመጡ። በመካከሉ አንዱ ጅብ ዘልቆ ሲገባ አንበሳው ተወናጭፎ መቀመጫው አካባቢ ነከሰው። ይህኔ የተነከሰው ጅብ ጩኸቱን አምባረቀ።  

አንበሳው በጣም ተናዶ ጉልበቱን ማሳየት ሲጀምር ጅቦች አፈገፈጉ። ይህን ጊዜ የተነከሰውን ጅብ መቀመጫ የማየት ዕድል የገጠማቸው ጅቦች አንበሳውን ትተው “ወንድማቸውን” ያሳድዱ ጀመር። አባረው ያዙት። አንበሳው በነከሰው በኩል የሚፈሰውን ደም ተከትለው በደቦ በሉት። ጅብ ሌላው ጅብ ላይ ደም ካየ አይምርም። ደም ሲደማ ሆዱ እንደሚሞላ ስለሚያውቅ ማድማት ወይም በደማው በኩል ገብቶ መከተት፤ ደም ካለው ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወንድም፣እናት፣ አባት፣ የሚባል የጅብ ዓይነት የለም።  

ይህን እያየሁ ስለ 360 የሰማሁት መረጃ ተገናኘልኝ። 360 የአንድ መንጋ ስብሰብ ነው። በዚህ መንጋ ውስጥ አስር የሚጠጉ እንደየደረጃቸው የሚለይዩ ጅቦች አሉ። ዋናው ራሱን “እኔ ባለሙያ ነኝ” የሚለው ጅብ ኤርሚያስ ለገሰ ነው። የመተትና ድግምት ዓይነት ስሜት እንጂ ዕውቀት የማይታይበት ሁለተኛው ጅብ ሃብታሙ አያሌው ነው። የተቀሩት እነደየአቅሚቲ ለአካለ ሤራ ትንተና ያልደረሱ ፍልፈሎች ናቸው። እነሱን ከዚህ በኋላ አላነሳቸውም።  

ልክ ወገናቸው ላይ ደም ሲያዩ ተረባርበው እንደበሉት የጅብ መንጋዎች፣ 360 የሚባለው የመርዝ ማከፋፈያ የዩቲዩብ ክፍለ ጊዜ የተመሰረተው ኢትዮጵያ ለውጡን ተቋማዊ ለማድረግና ያለፈውን የሰላሳ ዓመታት ትብትብ ለመበጣጠስ ስትባዝን ነው። ይህ ቡድን ጀሌዎቹን ሰብስቦ ዘመቻውን የጀመረው ለውጡ ትህነግ የሚባለው ቡድን እየፈረሰና እያነተበው በመሄድ ላይ ሳለ እንደ ስሙ 360 ዲግሪ በመዞር ነው።  

ይህ የሤራ ተንታኝ ጀሌ ሰሞኑንን “ገቢ ቀነሰ” በሚል መበላላት ሊጀምር እንደሆነ ተሰምቷል። አንድ ሳይገባው ገንዘብ ያዋጣና ይረዳቸው የነበረ እንዳለው “የምናገኘው ገቢና ብዛታችን አልተመጣጠነም” በሚል የመለየት ጥያቄ ያነሱ አሉ። ዋናው ምክንያቱ አልጠግብ ባይነት ነው።  

አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እጃቸውን ለ360 የሚዘረጉ እጆች እየታጠፉ ነው። የባለቤቶቹ ዓላማና ፍላጎት የማይታወቅው የመረጃ ቴሌቪዥን ባለቤቶች ካልሆኑ በቀር አብዛኛው የሚታወቀው ድጋፍ ደርቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ “መረጃ ቲቪ” ብሎ ፍጹም የሆነ ሽብርና መርዝ ኢትዮጵያ ላይ እየረጩ ያሉት የሚዲያው ባለቤቶች ዛሬ ድረስ በያዙት አቋም መቀጠላቸው በበርካቶች ዘንድ አሳዛኝ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ዓላማቸው ምን እንደሆነ፣ ምን እንደሚፈልጉና እንዲህ ባለ አገርን የማፈራረስ ጉዳይ ውስጥ ለምን መግባት እንደፈለጉ ለመጠየቅና ዘመቻ ለመጀመር ዲሲ አካባቢ ያሉ ወገኖች እየመከሩ መሆኑ ተሰምቷል።

ወደተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ … የ360 ፊት አውራሪና የባልደራስ ምክትል ሊቀመንበር ኤርሚያስ ለገሰ “አሁንስ በቃኝ” ሲል የሰሙ እንደሚሉት እሱ፣ ሃብታሙና ብሩክ ለብቻቸው ሊወጡና ሌላ የሚዲያ ፕላትፎርም ሊዘረጉ ወይም ሌሎቹን በማሰናበት እንዳለ ሊቆጣጠሩት አስበዋል።  


ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”

ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ

የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ

ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ


ኤርሚያስ “እኔ ፕሮፌሽናል ነኝ፤ ሌላም ሥራ መሥራት እችላለሁ” የሚል የካድሬ ትምክህት ወጥሮት ሌሎችን ያጣጥላል። “አንድ ጽሁፍ ጽፋ ኢህአዴግ አስሮ ያጀገናት” እያለ በጀርባዋ የሚያጣጥላት ርዕዮት አለሙም ሆነ ሌሎች የሚያዘጋጁት ፕሮግራም ልክ እሱ በየዕለቱ እንደሚመራው የማራከሻ ፕሮግራም ያህል ገቢ ስለሌለው እኩል ጥቅም ሼር ማግኘት የለባቸውም ባይ ነው። ሃብታሙም በቤቱ ራሱን አዋቂ አድርጎ ይህንኑ ዓላማ አራማጅ ሆኗል።

ዲሲ አካባቢ በሰው ቤት ቤዝመንት (ምድር ቤት) ሆኖ የኢንተርኔት ኮኔክሽኑ እያስቸገረው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ እተነትናለሁ የሚለውን ሃብታሙ አያሌውን ኤርሚያስ የሚፈልገው ለጥቅሙ ነው። የኦርቶዶክሱንና በዚያ ጎራ ያለውን ሕዝብ ለመሳብ በኮሙኒስቱ በረከት ስምዖን ተጠፍጥፎ የተሠራው ኤርሚያስ የግድ ሃብታሙ ያስፈልገዋል። የራሱን አውቃለሁ ባይነት እያስጠበቀና ከዚህና እዚያ ያነበባቸውን በእንግሊዝኛ እየጠቃቀሰ “… ይህንን እኔ በሦስት ከፍዬ ነው የማየው … ከዚህ አራት መሠረታዊ ነጥቦችን ማውጣት ይቻላል …” እያለ ሤራ የሚተነትነው የሃብታሙን አቅመቢስነት በአደባባይ ሲያሰጣው ነው እንጂ የንቀቱን መጠን ሃብታሙም ሳይረዳው አልቀረም። እሱም በተገላቢጦሽ ለኅልውናው ኤርሚያስ ስለሚያስፈልገው አብሮ መጓዙ ግድ ሆኖበታል።

ስብሃት ነጋ ከተወሸቀበት ጉድጓድ በወጣበት ጊዜ ስብሃትን እንደሚያውቀው በስፋት ሲናገረው የነበረው ሃብታሙ እንዲያውም በአንድ ስብሰባ ላይ አስተያየት ሲሰጥ የሰማው ስብሃት ነጋ “እንዴ ይሄ የእኛ ልጅ አይደለም እንዴ?” ማለቱን በገሃድ ተናግሯል። እንደ ኤርምያስ የሤራ ትንተና ብቃት እንዳለው ለማስመስከር መከራውን የሚየው ሃብታሙ ከዚህ በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድምፅ ከብልጽግና ስብሰባ ሾልኮ ወጣ ተብሎ አንድ ቂሎ የተባለ ሚዲያ የፖሰተውን አለቅጥ ሲብጠለጥል ኤርሚያስ ግን በንቀት እያየው አንዳችም አልተናገረም ነበር። በኋላ ኦዲዮው ስህተት መሆኑን ያወጣው ሚዲያ ራሱ ይቅርታ ሲጠይቅ እነ ሃብታሙ ግን “ዐቢይ ባይለውም ሊለው የሚችል ነገር ነው” በማለት ነበር ሸምጥጠው የካዱት። ኤርሚያስ ግን ከሃብታሙ ጋር ከመቆም ይልቅ ከዚህ ራሱን ገለል ነበር ያደረገው።

ትህነግ ወደ መንበሩ እንዲመልስ መንግሥትን በፈጠራ፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በተለይም የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር በመቀንጨብ ለጥፋት ፖለቲካ በማዋል፣ ሲያካሂዱ የቆዩትን ዘመቻ፣ ‘እረኛውን ምታ’ የሚለውን የዲጂታል ወያኔ መሪ ቃል በማንገብ ሲታትርና እየታተረ ያለው 360 በመጨረሻ በጥቅም ምክንያት ተቧድኗል።  

ኤርሚያስ “አዲስ አበባ እሄዳለሁ፤ የዐቢይ አማካሪ እሆናለሁ” በማለት ብዙ ከተቦጠረቀና ለዚህም እንዲረዳው በማለት ለዶ/ር ዐቢይ ያለ የሌለውን አድናቆት ሲያወርድ ከቆየ በኋላ ሁሉም የእምቧይ ካብ ሲሆንበት ዐቢይን ማናናቅ ጀመረ። መገለባበጥ ብርቁ ያልሆነው የበረከት ልጅ “አዲስ አበባ ከኦሮሚያ መሬት እየነጠቀች ያለቅጥ እየሰፋች ነው” በማለት የኦሮሞ ጥናት ማኅበር ላይ በገሃድ ከተናገረ በኋላ እንደለመደው የባልደራስ የውጪ አስተባባሪና ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ በመግባት ለነእስክንድር የፖለቲካ ጉዞ ትልቅ ዕንቅፋት ፈጣሪ ሆነ።

መተቸትና ጉድፍን መንቀስ የጋዜጠኛነት ሥራ መሆኑ ቢታመንም፣ 360 በየቀኑ የባለሥልጣናት ንግግርና መግለጫ ላይ ተጣብቆ ሃሜት እየዘራ፣ ጥላቻና መለያየትን እያባባሰ፣ በተለይም አማራ ክልልን ለመናድ ከወቅቱ የትህነግ ተላላኪ ከሚባሉት ታምራት ላይኔ፣ ሻለቃ ዳዊትና ያሬድ ጥበቡ ጋር ሆነው የጀመሩት ዘመቻ በገሃድ አስፈርጇቸዋል። ርዕዮት ከሚባለው የታወረ የትህነግ ሚዲያ ጋር እንደ ኮሶ ተጣብተው በመናበብ መስራታቸው በርካታ ዜጎችን አሳዝኗል። በግልጽም “በቃችሁ” ያሉዋቸው እንዳሉም ተሰምቷል።  

በዚህና በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ኤርሚያስ ጭራሹኑ “ሌላ ሥራ እጀምራለሁ” ማለት የጀመረ ሲሆን፣ እንደ ጅቦቹ በከርስ ጉዳይ መከፈላቸው ግን የማይቀር እየሆነ መጥቷል። ሃብታሙና ኤርሚያስ የ360 ገቢ 50 ከመቶ እንደሚገባቸው ያቀረቡት ጥያቄ በሌላው የቡድኑ አባላት ዘንድ ተቀባይነት ስላጣ አማራጩ መበተንና ተቧድኖ መሥራት ሆኗል። ይሳካላቸው አይሳካላቸው አይታወቅም እንጂ ዕርቅ መውረድ አለበት የሚሉ ጥቂቶች እንዳሉም ተሰምቷል።

ደም እንደታየበትና በጅቦች እንደተበላው ጅብ፣ ኢትዮጵያ ዝላለች በሚል በከርሳቸው ተታለው አገራቸውን ለመብላት የተነሱት እነ ኤርሚያስ መጨረሻቸው እርስ በርስ መበላላት እንደሚሆን ይጠበቃል።  

አያሌው ለገሠ ነኝ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Right Column

Reader Interactions

Comments

  1. Belay Manaye says

    August 23, 2021 10:24 am at 10:24 am

    በየሱስ ስም! በአሁኑ ስዓት እውነታውን ይዘው መሬት ላይ የሚወርድ ወቅታዊ ጭብጥ ያለው መረጃ የሚያቀርቡት እነ ሃብታሙ ናቸው ወዳጄ። btw ሴራ ተንታኞች አይደሉም። ምን አይነት እርባና ቢስ ኮተት ነው የፃፍከው በጌታ!
    ህዝብ ሚከታተለውን ያውቃል ወዳጄ፣ ከመሃይማን ጎራ ወይም ከመሃይማን አለቃ ብልፅግና/ብአዴን ፍርፋሪ ተቀባይ ካልሆንክ 360ን መጥላት ህመም ነው፣ ታከመው!

    Reply
  2. ኢያሪኮ says

    September 4, 2021 12:39 am at 12:39 am

    አንተ አጋሰስ ካንተ አይነቱ አጨብጫቢ ጋር ሳይመሳሰሉ የሚተቹትን ሁሉ ችለው ፡ እውነቱን እየተናገሩ ያሉት ኤርሚ እና ሀብቴ ናቸው፡ አንተ መሰሎችህ ደሞ ባለስልጣናት እንዴት ይሰደባሉ እያልችሁ ባለጊዜ አጨብጭቡ ፡ አንተን ብሎ ጸሃፊ

    Reply

Leave a Reply to ኢያሪኮ Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule