ከአዘጋጆቹ፤ በጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ ጀማሪነትና አቀናባሪነት ሲስተናገድ የነበረው “እኚህ ሰው ማናቸው?” የተሰኘው ዝግጅታችን እንደገና ተጀምሯል፡፡ ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ይቅርታ እየጠየቅን አሁን ግን በወዳጃችን ወለላዬ ብርቱ ትጋት ለመጀመር በመቻላችን ለወለላዬ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በዝግጅቱ ስትካፈሉ ለነበራችሁና መልሳችሁን ስትሰጡ ለነበራችሁ ሁሉ አሁንም ይህንኑ ማድረግ እንድትጀምሩ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በአገራችን ስማቸውን ተክለው ያለፉ በፎቶ አስደግፎ የግጥም ጥያቄ ማቅረብ ሲሆን ተሳታፊዎችም ምላሻችሁን በግጥም እንድትመልሱ ትደፋፈራላችሁ፡፡ ታሪክ በሥነቃል ታጅቦ ያዝናናል፤ ዝርዝር ጥናት ለማድረግ ለሚፈልግ ደግሞ ብርሃን ይፈነጥቃል፡፡ ለአሁኑ የእኚህን ሰው ፎቶ በግጥማዊ ጥያቄ አጅበን አቅርበናል፡፡ ከላይ እንዳልነው ቢቻል በግጥም ምላሻችሁን ከሥር … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳
Archives for February 2016
መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
* “የሟቾች ቁጥር እስከ መቶ ሊደርስ ይችላል” ነዋሪዎች * “የሞቱት 14 ሰዎች ናቸው” ኢህአዴግ ሰሞኑን በጋምቤላ በደረሰው የእርስበርስ ፍልሚያ እስከመቶ የሚጠጉ መሞታቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በበኩሉ የሞቱት 14 ብቻ ናቸው ይላል፡፡ ዘረኝነትንና ጠባብ ጎሰኝነትን ለኢትዮጵያ እንደ “ገጸ በረከት” ያመጡት መለስ በየቦታው የጫሩት እሣት ለፍርድ ሳያቀርባቸው ሾልከዋል፡፡ እሣቱ ግን አሁንም እየነደደ ነው፡፡ ጎልጉል ከአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ ባገኘው መረጃ መሠረት በግጭቱ የሞቱት እስከ መቶ እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ግጭቱ ከመነሻው በቀላሉ የተነሣ ቢሆንም ወዲያውኑ ወደከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ሥር የሰደደ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህንኑ ዜና ኢሳት ሲዘግብ የሟቾቹ ቁጥር ከመቶ እንደሚያልፍ ምንጮቹን ጥቅሶ … [Read more...] about መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
ሥልጣን የያዙ ሰሞን ሞት የቀደማቸው መለስ ሲጠየቁ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እመግባለሁ ወይም ሲመገብ አያለሁ የሚል የውሸት ተስፋ ሰጥተው ነበር፡፡ “የቀማኛ ኢኮኖሚ አቀንቃኝ” የነበሩት መለስ ለሥልጣናቸው ማራዘሚያ ጥቂቶችን በሃብት እንዲወጠሩ ሲያደርጉ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ቀርቶ በሶስት ቀን አንዴ የማይመገብ አድርገውት ተሰናብተዋል፡፡ “ሌጋሲያቸውን እንጠብቃለን፤ እናስጠብቃለን” የሚሉት ያሁኖቹ ዘራፊዎችና ተላላኪዎች አገር በሁለት አኃዝ አድጋለች፤ ኢኮኖሚው ዓለምን እያስደነቀ ነው፤ ህዳሴ ነው፤ ውዳሴ ነው፤ … በማለት በቁማቸው ይዋሻሉ፤ የጥቅም ተካፋዮቻቸውም ይህንኑ ይዘው በየቀኑ ሲያናፉ ይውላሉ፡፡ ህወሃት ስለዘረጋው የዘራፊ፤ የቀማኛ፤ የሌባ፤ ኢኮኖሚ ብዙ ሊባልበት ይቻላል፡፡ ሌብነቱን ደግሞ መለስ ራሳቸው መስክረው ነው የሞቱት፡፡ “ያስቸገረን የመንግሥት … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
“ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
"መንግሥት ስህተቱን ካመነ ኦሮምያ ውስጥ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑ አጥፊዎች በገለልተኛ አካል ተለይተው ይቀጡ” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጠይቀዋል። “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” ሲሉም ተችተዋል። “ቀደም ሲል የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በኦሮምያ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዋናው መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው” ማለታቸው ይታወቃል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ መለስካቸው አምሃ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር አለው፡፡ እዚህ ላይ ያዳምጡ። (ምንጭ: VOA) … [Read more...] about “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
አንቺን አስታዋሼ
መቼ ትመጫለሽ መቼ ልጠብቅሽ ወይ መቼ ላምጣልሽ መቼ ላቀብልሽ ሽሮና . . . ምናምን ስለተላከልሽ ሽሮውን ውሰጂው በርበሬውን ውሰጅ ቅቤውንም ውሰጅ . . . ሚጥሚጣ ተይልኝ እሱ ስለሆነ - አንቺን ሚያስታውሰኝ ............................. ምን ይሰራልሀል ብቻውን ሚጥሚጣ ትደፋው የለም ወይ እንጀራ ስታጣ … [Read more...] about አንቺን አስታዋሼ