“ጋኔን ልክ ማስገባት የሚችለው … መንግሥት ነው” ጌታቸው ረዳ ታኅሳስ 6፤2008 ዓም “የታጠቁ ወንበዴዎች በየመንገዱ በየመንደሩ እየዞሩ ህዝብን የሚያሸብሩበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፤ ወደለየለት ሽፍትነት ተገብቶ ነው ያለው፡፡ እነዚህ ሰዎች የተላለፈላቸው መመሪያ ይሄ ነበር ወይስ አልነበረም ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ በሀገራችን ላይ ሁከት የጠራ ወገን፣ ጋኔል የጠራ ወገን ጋኔሉን ስለመቆጣጠሩ እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡ አሁን የጠሯቸው ሰዎች የጠሩትን ጋኔል ስለመቆጣጠራቸው እርግጠኛ አይደሉም፡፡ ይህንን ጋኔን ልክ ማስገባት የሚችለው የተደራጀ ህዝብና መንግስት ብቻ ነው፡፡” አፈቀላጤ ጌታቸው የካቲት 11፤2008ዓ.ም ይህንን አሉ: “እኔ ሁከት የጠሩ ወገኖች ነው (ጋኔን) ያልኩት። ሁከቱን ስለማይመልሱት ሕዝብና መንግሥት ይህንን ሁከት መመለስ ይገባቸዋል፤ በአጋጣሚ የእንግሊዝኛን አባባል ወደ … [Read more...] about ጋኔኑ ማነው?
Archives for February 2016
ለየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ሠማዕታት ቋሚ ጠበቃ መሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው
«ከታሪክ የማይማሩ ደግመው፣ ደጋግመው ለመሣሣት ይጋለጣሉ፤» የሚለው ብሂል ለዚህ ብሔራዊ በዓል መደብዘዝ አብይ ማጣቀሻ ነው። በደርግ የአገዛዝ ዘመን ይህ ዕለት ከብሔራዊ በዓልነት ደረጃ ወርዶ በመታሠቢያ ቀን ደረጃ እንዲከበር መደረጉ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነበር። በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ይብስ ስህተቱ ወደማይታረምበት ደረጃ ደርሷል። ይህንን ለማለት የሚያስደፍረው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ፋሽስት ኢጣሊያን ሲፋለሙ በሠማዕትነት ያለፉትን የአቡነ ጴጥሮስን፣ የደጃዝማጅ አፈወርቅ ወልደሰማዕትን እና ከሁሉም በላይ የማይጨው አርበኞቻችንን የመታሠቢያ ኃውልቶች አፍርሷል፣ ሌሎችንም ታሪካዊ ኃውልቶች አፍርሶ ድራሻቸውን ለማጥፋት እንቅስቃሴውን ቀጥሏል። ችግሩ የሰማዕታቱ መታሠቢያ የሆኑት ኃውልቶችን በማፍረስ ብቻ የሚገደብ አልሆነም፣ እንዲያውም ታሪካዊቱን አገር ኢትዮጵያን እስከመበታተን የሚደርስ ታላቅ … [Read more...] about ለየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ሠማዕታት ቋሚ ጠበቃ መሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው
የሰው ዘር ጭፍጨፋ በአዲስ አበባ
በየአመቱ የካቲት 12 ቀን ሲደርስ ከማስታውሳቸው የዚህች አገር ባለውለተኞች መካከል ተመስገን ገብሬ አንዱ ነው። ይህ ሰው ሀገሩ ኢትዮጵያ በፋሽስቶች እንዳትወረር ብዙ ትግል አካሂዷል። ከወረራው በኋላም በአርበኝነት ተሰማርቶ የፋሽስቶችን ግብአተ-መሬት ካፋጠኑ የኢትዮጵያ ታላላቅ ደራሲያን መካከል ከግንባር ቀደሞቹ አንዱ ነው። ተመስገን ገብሬ በ1901 ዓ.ም ጐጃም ደብረማርቆስ ከተማ ነው የተወለደ። ታህሳስ 15 ቀን 1941 ዓ.ም በ40 ዓመቱ አረፈ። በትምህርቱ እጅግ ጐበዝ የሚባል በመሆኑ ገና በ15 ዓመቱ የቅኔ መምህር ሆኖ ነበር። በቤተ-ክህነት ትምህርት በዚህ እድሜ የቅኔ መምህር የሆነ ሰው ከተመስገን ሌላ አልተገኘም ይባላል። ይህ ሰው በ1918 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ የዘመናዊ ትምህርቱን በስዊድሽ ሚስዮን ተከታትሎ ጨርሷል። በ1920ዎቹ ውስጥ ጣሊያን ኢትዮጵያን ከመውረሯ በፊት … [Read more...] about የሰው ዘር ጭፍጨፋ በአዲስ አበባ
የዘመነ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቅርምት
በዛሬው ርዕስ ሥር የማነሳው ጉዳይ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቅርምትን ይመለከታል። በርግጥ ይህን ርዕሰ ጉዳይ በቅርቡ ከተቋቋመው የ EDF (Ethiopian Dialogue Forum) ድርጅት ዓባላት ጋር በነበረን ቴሌ ኮንፈረስ ላይ ለውይይት አቅርቤው ነበር። ዛሬ ደግሞ በቀለም ቀንድ ጋዜጣ በኩል ከሃገር ቤት ወገኖቼ ጋር ለውይይት ይሆነን ዘንድ መረጥኩት። እንግዲህ በዓለም ላይ እጅግ ብዙዎቹ አገራት ወይ በባህል ወይም ደግሞ በሃይማኖት ብዙሃን ሆነው አንድ አገር መስርተው ይኖራሉ። አንዳንዶቹ ሃገራት እጅግ ብዙ ቋንቋና ባህል ያላቸው ቡድኖችን ይዘው በአንድ የፖለቲካ ጠገግ ውስጥ ይኖራሉ። ለምሳሌ ናይጀሪያ ወደ 250 ብሄሮችን ይዛ እነዚህ ብሄሮች በአንድ ፌደራል ሪፐብሊክ ናይጀሪያ የፖለቲካ ጠገግ ስር ተጠልለው ይኖራሉ። ኢንዶኔሽያን የመሰረቱ ቡድኖች ደግሞ ወደ 300 ቡድን ናቸው። … [Read more...] about የዘመነ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቅርምት
የእስራኤል ቀድሞው ጠ/ሚ/ር ወደ “ቃሊቲ” ወረዱ፤ የሃይማኖት መሪም ተከትለዋቸዋል
* “ማንም ከሕግ በላይ መሆን አይችልም” ታሳሪው ጠ/ሚ/ር የቀድሞ የእስራኤል ጠ/ሚ/ር ኤሁድ ኦልመርት ወደ እስር ቤት ወረዱ፡፡ በሃይማኖቱ ዓለም ታላቅ ዝነኝነትን የተጎናጸፉት ራባይ (ረቢ) ዮሺያሁ ፒንቶም ወደዚያው አምርተዋል፡፡ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የህወሃት/ኢህአዴግ “ሻኮችን” ማን ይንካቸው ሲሉ ጠይቀዋል? እስራኤልን ለሦስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት የሰባ ዓመቱ ኤሁድ ኦልመርት ከሙስና ጋር በተያያዘ የ19 ወራት እስር ተበይኖባቸው እስርቤት ወርደዋል፡፡ በአስተዳደር ዘመናቸው ከፍልስጤማውያን ጋር ስምምነት ለማድረግ ከፍተኛ እርምጃዎች ሲወስዱ የነበሩት ኦልመርት ወደ ወሳኝ ደረጃ ላይ ሲደርሱ በሥልጣን ላይ እንዳሉ በሙስና፣ ጉቦ፣ እና ሌሎች ገንዘብ ነክ ወንጀሎች መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡ በተለይም የአናፖሊስ ኮንፍራንስ በተባለው ስብሰባ በርካታ ውሳኔዎችን ለድርድር … [Read more...] about የእስራኤል ቀድሞው ጠ/ሚ/ር ወደ “ቃሊቲ” ወረዱ፤ የሃይማኖት መሪም ተከትለዋቸዋል
ሌ/ኮ ፍሥሐ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” በተሰኘው መፅሐፋቸው ስለ መኢሶን በተረኩት ላይ በጥቂቱ
ሌ/ኮ ፍሥሐ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” ብለው በኅዳር ወር 2008 ዓ/ም አንድ መጸሐፍ አሳትመው ለንባብ አቅርበዋል፡፡ ለዚህ አስተዋፆዋቸው ምሥጋናዬ እጅግ ከፍ ያለ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ስለመኢሶን እዚህና እዝያ የከታተቱት ውሀ የመይቁዋጥር ቢሆንም ቅሉ፣ ከመጸሐፉ ጠቃሚ መረጃዎችን አግኝቸበታለሁ፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሌ/ኮ ፍሥሐ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” በተሰኘው መፅሐፋቸው ስለ መኢሶን በተረኩት ላይ በጥቂቱ
የወቅቱን ሁኔታ የገመገመ የሸንጎ መግለጫ
እዚህ ላይ ይገኛል … [Read more...] about የወቅቱን ሁኔታ የገመገመ የሸንጎ መግለጫ
Responses to Some Criticisms Toward “The Danger of a Single Story…” Commentary
Feedbacks It has been a little more than a week since my commentary entitled “The Danger of a Single Story And What We Ethiopians Can Do About It” was posted on many Ethiopian Diaspora websites. Since then, a couple of friends encouraged me to take some follow up actions like arranging forums, panel discussions, and conducting interviews to continue the conversation. Even though I couldn’t promise to take the lead in implementing these tasks alone, I concurred with the idea and opened a Face … [Read more...] about Responses to Some Criticisms Toward “The Danger of a Single Story…” Commentary
ምግባረ ብልሹዎቹ “የመልካም አስተዳደር” ሰባኪዎች
“የኢትዮጵያ ፓርላማ” እየተባለ በሚጠራው የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ አነጋገር “እስከ እንጥሉ ስለገማው ኢህአዴግና የመንግሥት ሌቦች” ጉዳይ (በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አጠራር “መልካም አስተዳደር” ጉዳይ) ከቀናት በፊት ሪፖርት ቀርቦ ነበር፡፡ አዲስ ፎርቹን ከፎቶው ጋር አያይዞ ያተመው ዜና እንደሚያስረዳው እና ፎቶው በገሃድ እንደሚያሳየው በሪፖርቱ መ/ቤታቸው በአስተዳደር ብልሹነት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኙት የኢህአዴግ ሹመኞች አባተ ስጦታው (የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ) እና መድኀን ኪሮስ (የፍርድ ቤቶች ምክትል ፕሬዚዳንት) ከአፈጉባኤው አባዱላ ጋር በቃላት ሰይፍ “ሕዝባዊነታቸውን” ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ጋዜጣው ሹመኞቹን በጓደኞቻቸው ፊት “ሲያጉረመርሙ” ተሰሙ ቢልም፤ በርካታ ማኅበራዊ ሚዲያዎች “ዱላ ቀረሽ” ግብግብ ብለውታል፡፡ ጋዜጣው እንዳለው ከሆነ የአዲስ አበባ … [Read more...] about ምግባረ ብልሹዎቹ “የመልካም አስተዳደር” ሰባኪዎች
እትጌ ጣይቱ ቫለንታይን ፍቅርና አድዋ
ይህን የያዝነውን የየካቲት ወር እኔ የምኖርበት ቀዬ ምዕራባውያን የጥቁሮች ወር በማለት ወሩን በሙሉ የሀገሩን ጥቁር ገድል ሲዘክሩ በወሩ አጋማሽ አንዱን ቀን ደግሞ የ(ሮማው ቅዱስ) ቫለንታይን በአል፣ በቫለንታይን ማግስት ደግሞ የቤተሰብ ቀንም ብለው ስራ ዘግተው ያከብራሉ። ቫለንታይን አሁን አሁን የፍቅረኞች በአል ቢባልም ሲጀመር ሰማዕቱ ቅዱስ ቫለንታይን የንጉሱ ህግ ለከለከላቸው ጋብቻን በማፈጣጠም፣ ለተከለከሉ ክርስቲያኖች ቃለ-እግዚአብሔርን በማስማት፣ የታመሙትን በመፈወስ ነው ታሪክ የሚያውቀው፤ ፊታውራሪ ገበየሁ አባጎራውንም የአምባላጌውን ጀግና የአድዋውን ሰማዕት ታሪክ የሚያውቀው “የአድዋ ስላሴን ጠላት አረከሰው ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው” እየተባለ ሲወሳለት ነው። የሁለቱም ሰማዕትነት ደግሞ ከውትድርና፣ ከተገፉ፣ ነፃነታቸውን ከተገፈፉ ሰዎች ጋር መያያዙ ነው። ካለፉት አስርት … [Read more...] about እትጌ ጣይቱ ቫለንታይን ፍቅርና አድዋ