ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሃያ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በጌምድርና - ሰላሌን በመግዛት ጠቅላይ አዛዥ ሆነው - በጣሊያን ጦርነት በተንቤን ግንባር - ላይ ሌሎች የመሩ ልዑል (ራስ) ካሣ ኃይሉ - እኚህ ሰው ነበሩ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ ጥያቄ ብዙዎች ነበሩን - እጅግ ጀግና ሰዎች የህዝብ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩
Archives for February 2016
“ብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ባለቤት አገኘ”
በአቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራው ሰሞኑን በአሜሪካን ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በጠራውና "ለመተማመን እንነጋገር" የሚል መሪ መፈክር በያዘው ስብሰባ ላይ ለመገኘት እድሉ አጋጥሞኝ ነበር፡፡ ስብሰባው የጀመረው ከተባለበት ሰዓት "በባሕላችን መሠረት" አንድ ሰዓት ዘግይቶ ቢሆንም ስብሰባው ላይ የተካሄዱት ቁምነገራም ሀሳቦች የስብሰባውን አርፍዶ መጀመር አላስታወሰኝም። በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ከአውሮፓ ከአውስትራሊያና ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውያን አሁን ሀገራችን የምትገኝበት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ እንቅልፍ ያሳጣቸውና የበኩላችንን ማድረግ አለብን ብለው የቆረጡና ኢትዮጵያ የምንላት ሀገራችንን ከሞላ ጎደል የሚወክሉ ተሳታፊዎች ነበሩ። በርግጥም ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታና በውስጧ ያለውን ውስብስብ ችግር ያለምንም አድርባይነትና አስመሳይነት የሚታያቸውን መግለጽ የሚችሉ “ከዘረኝነት … [Read more...] about “ብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ባለቤት አገኘ”
“በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
ነሐሴ 21/2003 ከምሠራበት ቦታ በስልክ ተጠርቼ በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ ከሚጠራው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተወስጄ ከአንዲት ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከተወረወርኩ በኋላ በማግስቱ አራዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቀርቤ የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆብኝ ተፈቅዶላቸው፣ ያም ሲያልቅ እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተጠይቆ ተፈቅዶላቸው፣ የማይመለከቱኝን ጥያቄዎች ስጠየቅና ስመልስ ቆይቼ ጥቅምት 3/2004 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቤ የክስ ወረቀት ደርሶኝ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተልኬ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ዞን አንድ ቅጣት ቤት ተብላ በምትጠራው ቤት እገኛለሁ፡፡ የቀረበብኝ ክስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 241 የተመለከተውን በመተላለፍ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ሲሆን ዝርዝሩ፡- “የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦ.ነ.ግ./ … [Read more...] about “በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
የህወሃት ግፍ እና የሕዝብ ፍጹም ምሬት
በኦሮሚያ የተማሪዎች ተቃውሞ የተጀመረው በኖቬምበር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጊንጪ በመባል በምትታወቀው ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አነስተኛ ከተማ ሲሆን መንስዔውም የመንግስት ባለስልጣን አካላት በአካባቢው የሚገኘውን ደን ለኢንቨስትመንት ልማት በሚል ለመመንጠር በመሞከራቸው ነው፡፡ ተቃውሞው ወዲያው ወደ ሌሎች የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተስፋፋ ሲሆን የተቃውሞው ጥያቄም በመስፋት የአዲስ አበባ የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን በመባል የሚታወቀውን የአዲስ አበባ ማዘጋጃቤት ድንበር የማስፋፋት እቅድ ተቃውሞ ያካተተ ሆኗል፡፡ ተቃውሞው እስከ ዲሰምበር ወር ሲቀጥል ገበሬዎች እና ሌሎችም ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል፡፡ በርካታ ተቃውሞ አድራጊዎች እንዳስታወቁት መንግስት ተቃውሞውን በጉልበት ለማስቆም የፈጸመው ተግባር እና በዚህም … [Read more...] about የህወሃት ግፍ እና የሕዝብ ፍጹም ምሬት
ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም
ከኖቬምበር ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በስፋት እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ተቃውሞ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል በጉልበት እያፈነው እንደሚገኝ ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ አስታወቀ፡፡ ከ2016 ዓ.ም. መነሻ ጀምሮ በእየለቱ ሰዎች እንደሚገደሉ እና በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ ሂውማን ራይትስ ወች አስታውቋል፡፡ የወታደራዊ ሰራዊትን ያካተተው የጸጥታ ሃይል ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ቀጥታ በመተኮስ ገድሏል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው ያለምንም ክስ እንደታገቱ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት የተቃውሞው ድግግሞሽ የቀነሰ መስሎ ቢታይም አፈናው ግን ቀጥሏል፡፡ “ኦሮሚያን በበርካታ የጸጥታ ሃይሎች የማጥለቅለቅ እርምጃ የሚያመለክተው በተማሪዎች፣ ገበሬዎች እና ሌሎች ተቃዋሚዎች የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ ባለስልጣን አካላቱ በከፍተኛ ሁኔታ አለመፈለጋቸውን … [Read more...] about ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም
“ለአውሮጳውያን (ስለ ምርጫው ውጤት) ‘ሌክቸር’ አልፈልግም ብዬ ነግሬአቸኋለሁ”
በዑጋንዳ በተካሄደው ምርጫ አገሪቱን ለ30 ዓመት የመሩት ዮዌሪ ሙሰቪኒ ለአምስተኛ ጊዜ “አሸንፈዋል”፡፡ ተቀናቃኛቸው ምርጫው መጭበርበሩንና እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡ አውሮጳውያንና አሜሪካ ምርጫው ዓለምአቀፋዊ ሕግጋትን የጠበቀ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ሙሰቪኒ ዋናው ዓላማቸው እስካሁን ኢትዮጵያን ያላካተተውን የምስራቅ አፍሪካ ፌዴሬሽን መመሥረት እንደሆነና ስለምርጫው ከአውሮጳውያን “ሌክቸር” እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል፡፡ በምዕራባውያን ድለላና ድጋፍ በትጥቅ ትግል ወደ ሥልጣን የመጡት መለስ ዜናዊ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ፖል ካጋሜ እና ዮዌሪ ሙሰቪኒ “አዲስ የአፍሪካ መሪዎች ውልድ (ዘር)” በመባል በቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን እንዳልተሞካሹ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ፍጹም አምባገነኖች ሆነዋል፡፡ መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድማቸው ኖሮ ከሌሎቹ ጋር በመሆን ማቆሚያ የሌለውን ሥልጣናቸውን … [Read more...] about “ለአውሮጳውያን (ስለ ምርጫው ውጤት) ‘ሌክቸር’ አልፈልግም ብዬ ነግሬአቸኋለሁ”
ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም
ከአሜን ባሻገር በ19 ምዕራፎች የተቀነበበች246 ገጽ የሆነች ተነባቢ መፅሃፍ ነች። የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ እንደነገረን ከሆነ አብዛኛዎቹ ምእራፎች በመጽሄትም በጋዜጣም የወጡ ስለነበሩ አዲስ አይደሉም ብሏል። በመጽሄትና በጋዜጣ የሚወጡ መጣጥፎች ማጣቀሻ ዋቢ ስለማያክሉ ከጊዜ ብዛትም ጸሀፊውም ስለሚረሳቸው የይድረስ ይድረስ ነገር ሻጥ ሻጥ ይደረጋሉ። የበዕውቀቱ ከአሜን ባሻገር በዚህ ረገድ ጉልህ ጎደሎነት አሳይቷል። ከቤተ አማራ ፖለቲካ አቀንቃኞችንም ጋር እሰጥ አገባ ያስገባው ይሄ የመጽሃፉ ደካማ ጎን ለምንጭ ለዋቢ የሚሰጠው ግምትና ቦታ። በሁለተኛው እትም ይስተካከላሉ የሚል ግምት አለኝ። ስለ 19ኞቹ መጣጥፎች በዕውቀቱ በ13 ቃላት በሁለት አረፍተ ነገር ሲገልጽ “መጣጥፎቼ የእንጉርጉሮና የልግጫ ድብልቅ ናቸው። የሐሳብ አርአያዎቼ አንጎራጓሪ ሴቶች እንጂ ፕሮፌሽናል ፖለቲከኞች … [Read more...] about ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ቁልቁል የመንሸራተት አንድምታ!
በኢትዮጵያ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ማለት፤ የአገሪቱ የህግ ማስፈጸሚያ የመጨረሻው ችሎት ነው። ከዚህም በተጨማሪ፤ የአገሪቱ ፕሬዚዳንትም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲሁም የፓርላማ አባላት ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት፤ ቃለ መሃላ የሚያስፈጽመው የዚህ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መሆናቸው ይታወቃል። የህገ መንግስት ወይም የህግ ትርጉም የሚሰጠው የመጨረሻ አካል ነው - ጠቅላይ ፍርድ ቤት። ከዚህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በላይ ደግሞ፤ ፕሬዚዳንታቸው አለ። እስከቅርብ ግዜ ድረስ ፕሬዚዳንቱ አቶ ተገኔ ጌታነህ ነበር። እናም በቅርቡ “የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ፤ ስልጣኑን በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ” ሲባል፤ እንደማንኛውም ዜና ሰምተን ዝም የምንለው ሊሆን አይገባም። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ወይም ቃልአቀባዮች መግለጫ ባለመስጠታቸው የተፈጠረ ክፍተት አለ። ይህን ክፍተት … [Read more...] about የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ቁልቁል የመንሸራተት አንድምታ!
በአምቦ የ9 ዓመት ልጅ በህወሃት ነፍጥ አንጋቢዎች ተገድሏል
በአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ እንደገና ያገረሸው ተቃውሞ ከሦስት ወር በላይ አስቆጥሯል፡፡ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ አርሲ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በጋራ ሙለታ ግራዋ ወረዳ ዛሬም የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደነበር፤ ዛሬ በአምቦ የአዋሮ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጅ በጥይት መገደሉን የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል። በተጨማሪም እዚያው አምቦ ውስጥ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ላይ ቃጠሎ መነሣቱን፣ በተጨማሪም ምዕራብ አርሲ ውስጥ በሻሸመኔ ወረዳ አጄ በተባለች የገጠር ከተማ ውስጥ የሚገኝ እሥር ቤት ተሰብሮ እሥረኞች እንዲወጡ መደረጉን የሬዲዮው የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች … [Read more...] about በአምቦ የ9 ዓመት ልጅ በህወሃት ነፍጥ አንጋቢዎች ተገድሏል
Representatives of Diverse Ethiopians formed:
Executive Summary: On February 14, 2016, the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) announced the formation of the Ethiopian Council for Reconciliation and the Restorative of Justice (ECRRJ) at a public meeting held at the Sheraton Hotel in Silver Springs, Maryland. The Council’s formation was the outcome of a strategic planning retreat held over the course of three days previous to the meeting. Those attending the retreat were representatives of diverse Ethiopians. The ECRRJ is a … [Read more...] about Representatives of Diverse Ethiopians formed: