መግቢያ በዚህ ርእስ ይህችን ጦማር እንዳዘጋጅ የተገደድኩበት ምክንያት “የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ በመሆኔ ለቤተ ክርስቲያኔ እቆማለሁ፤ ጋዜጠኛ በመሆኔም ለህዝቤ እውነቱን አስጨብጣለሁ” እያሉ፤ ነገር ግን እንደሚሉት ሆነው የማይገኙ እንደ አቶ አዲሱ አበበ የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች በመካከላችን ስለተከሰቱ ነው። አቶ አዲሱ እንደሚሉት የክርስትና ሕይወትና የጋዜጠኝነት ሙያ የተዋሀዳቸው ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በታደልን ነበር። እንደነ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች ታስረው በመሰቃየት ላይ ሳሉ፤ በቂ ችሎታና ሙያ ሳይኖራቸው አቅጣጫ እየቀያየሩ በሚፈጽሙት ተደጋጋሚ በደል በአካባቢያችን ያሉትን አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ባልወረሩና ወያኔ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ አውታሮች ተሰልፈው የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያፈኑ ጋዜጠኞች ቁጥራቸው ባልበዛ … [Read more...] about ሰይፈ ነበልባል ክርስትና እና ጋዜጠኝነት ሲወሀዱ ወደ ሰይፈ ነበልባልነት ይለወጣሉ
Archives for January 2015
አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?
* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ ! * ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን! ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette ነው። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ፣ መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን? እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም! መዲና የተባለች እህት በጽዳት ላይ እያለች አይኗ ላይ ተፈናጥሮ የገባው መርዝ የአይን ብርሃኗን አሳጥቷት በከፋ … [Read more...] about አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?
ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!
“የራበው ሥራ ፈልጐ ማግኘት የማይችልና ልጆቹን ለማስተማር አቅም ያጣ ሰው ከባርነት ነፃ ነው ማለት አይቻልም፡፡” የሚለው የአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ. ጆንሰን ንግግር እውነትነት አሁን አሁን በጆሮዬ መደወሉ ራሴን እያስገረመኝ መጥቷል፡፡ የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገደማ ሰዎች፤ ስለኑሮ ውድነት ሲጽፍ ብዙዎቻችን እያነበብን ፈገግ ከማለት በቀር ብዙ ልባችን አልተነካም ነበር፡፡ ምናልባትም በጣም አልፎ አልፎ ከምናነባቸው መጣጥፎች ይልቅ መንግስት ስለ ልማት የሚነፋው ጥሩንባ አደናቁሮን ይሆናል፡፡ አሁን አሁን የመንግሥት መዝገበ ቃላት “ልማት” የሚለው ትርጓሜ ግራ እያጋባን መጥቶ ጭራሽ ወደ ብስጭት የተመነዘረብን ብዙ ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ መንግስት ልማት የሚለው ከእኛ አፍ “ቫት” እያለ የሚነጥቃትን ገንዘብ ሰብስቦ ለሌቦች ካጠገበ በኋላ፣ በፍርፋሪዋ የሚሠራትን መንገድና ጤና ጣቢያ … [Read more...] about ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!
የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .
በጠለምት፣ በበየዳ፣ በጃናሞራ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በአርማጨኾ ነዋሪው እየተባረረ፣ ሀብቱ እየተዘረፈ፣ ያንገራገረው እየተገደለ፤ ሰው በምሬትና በሰቀቀን ኑሮውን መግፋት አቅቶት አጣብቂኝ ላይ ገብቷል። ትናንት ቡያ ነበር ክልሉ። ትናንት በሀከር ነበር ክልሉ። ቀጥሎ ራስ ደጀንን ወደነሱ አካተቱት። ጠገዴን ጠቀለሉት። ገፍተው ስሜን አውራጃን በሙሉ ጠቀለሉ። ወገራ አውራጃን ሽራርፈው ወሰዱና ጎንደር አውራጃን ተጠጉ። አሁን ዘለው የጎንደር ከተማውን ገነት ተራራ፤ የትግራይ መሬት እያሉ ለትግራይ ልጆቻቸው እያሰተማሩ ነው። ጎንደር ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ እየተገፋ ነው። ይህ የመኖርና ያለመኖር፤ ውሎ የማደርና በወጡበት የመቅረት፤ ተገፍቶ ተገፍቶ የገደል ጫፍ ላይ የተንጠለጠለ ሕይወት ሕዝቡን ሰቅዞ ይዞታል። ይህ ጉዳይ የጎንደሬዎች ብቻ ጉዳይ አይደለም። አዎ! በዋግም ተመሳሳይ ተግባር እየተፈጸመ … [Read more...] about የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .
የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ስሌት
ኢኮኖሚያችን በድርብ አኻዝ እያደገ ነው! በአፍሪካ ፈጣን ኢኮኖሚ በማስመዝገብ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ እያደረግን ያለው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑ …፤ ህዳሴ፣ ልማት፣ ዕድገት፣ … “ሥራ ላይ ነን” … “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!” … [Read more...] about የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ስሌት
“እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ
ከቂሊንጦ እስር ቤት ከሚገኙት መካከል የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አብርሃ ደስታና የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ኦኬሎ አኳይ፣ ስለ እስራቸው ሁኔታ እንዲህ ይላሉ:: በቅድሚያ አብርሃ ደስታ:- "እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡ "ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን አለ፣ እሱም ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ እኔ አልታሰርኩም፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ እስር የአዕምሮ ነው፡፡ እኔ አዕምሮየ አልታሰረም፡፡ ነጻ ሰው ነኝ፤ ውስጤ በጣም ነጻነት አለው፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ "እኔ እስር ቤት እንድገኝ … [Read more...] about “እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ
እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!
የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሆይ፤ እትብታችሁ ስለተቀበረባት የምትወዷት ሀገራችሁ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ሃይማኖታችሁና ስለ ቤተ ክርስስቲያናችሁ ስታስቡ ሁሌም አስተዋይ፤ አርቆ አሳቢ፤ ብልህና ንቁ ሁኑ እንጂ ባማሩ ቃላት በመሳብም ሆነ ልብሰ ተክህኖና ግርማ ሞገስን በማየት የተንኮልና የሃሰት ሰለባ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፤ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች፤ ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነብቢያት ተጠንቀቁ” ተብሏልና (የማቴ. ወ. ም. ፯ ቁጥር ፩፭) በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ መንስኤው ማን እና ምንድን ነው ከተባለ ደግሞ እውነተኛው መልስ ሥጋዊ ጥቅምን በማስቀደም ለሥልጣን፤ ለንዋይና ለዝና ያደሩ ጥቂት ካህናት የፈጠሩት ችግር መሆኑ የተረጋገጠ … [Read more...] about እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!