የሰው ልጅ፣ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ከታደለው ፀጋ ውስጥ አንዱ ስልጣኔ ናፋቂ መሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዝግመተ-እድገት ታሪክ የሚነግረን፣ አለም አሁን ለደረሰችበት የሀያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ስልጣኔ፣ መንስኤው ስልጣኔ ናፋቂ የሆነው የሰው ልጅ በየዘመኑ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤት መሆኑን ነው፡፡ የሰው ልጅ፣ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የማሰብ ፀጋ ስለቸረው ነው፡፡ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት” እንዲል ቃሉ፤ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ፤ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነ ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እነሆ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ … [Read more...] about ያለነፃነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይኖርም!
Archives for January 2015
“ስኳር ለባለካርድ ብቻ” – ምርጫ ቦርድ
የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ይሁን ባላንጣዎቻቸውን ወይም ከእርሳቸው የተለየ ሃሳብ የሚያመነጩትን “ስኳር ወዳድ”፣ “በስኳር የተታለለ”፣ … እያሉ ለእስር ሲዳርጉ የነበሩት አቶ መለስ፤ ሞት ሳይቀድማቸው በፊት ራሳቸው ያቋቋሙትና እርሳቸውን ደግሞ ደጋግሞ እያገላበጠ አንዴ ፕሬዚዳንት ሌላ ጊዜም ጠቅላይ እያደረገ ሲሾማቸው የኖረው “የምርጫ ቦርድ” ሕዝቡን በስኳር እየፈተነ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ “ስኳር” ቀምሰው ሳያውቁ ስለ ስኳር “አስከፊነት” ዘለግ ያለ መግለጫ በመስጠት ይታወቁ የነበሩት መለስ ለፓርቲያቸው መለያ “ንብ” መምረጣቸው በስኳር ላይ ያላቸውን ጥላቻ በትጋት ያሳየ እንደሆነ ታሪካቸው አሁንም ይመሰክራል፡፡ የሆነው ሆኖ ጓዶቻቸውን “በስኳር ወዳጅነት” ለእስር የዳረጉት መለስ እርሳቸው እየመላለሰ እንዲያነግሥ የመሠረቱት “የምርጫ ቦርድ” ሰሞኑን በ“አፍቅሮተ ስኳር” መጠመዱን ቢሰሙ ኖሮ ምን … [Read more...] about “ስኳር ለባለካርድ ብቻ” – ምርጫ ቦርድ
“አእምሮዬ አልዳነም!”
“በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተናገረ፡፡ አንድ ዓመት ከሁለት ወር (14 ወራት) ከሥራ ባልደረባው ዮሐን ፔርሶን ጋር ኢህአዴግ አስሮት የነበረው ጋዜጠኛ ሺብዬ ለጎልጉል የአውሮጳ ዘጋቢ ይህንን የተናገረው በዖጋዴን ክልል የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም መሰራጨቱን ተከትሎ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡ “በአካል ሰላም አለኝ፤ አእምሮዬ ግን አልዳነም፤ … [Read more...] about “አእምሮዬ አልዳነም!”
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
• “ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር “በነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ” ዘመቻው ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ትብብሩ ዛሬ ጥር 12/2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ “የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ አጋፋሪነት ሊቀጥል ይችላል” ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሆኖም የትግሉ አላማ ኢህአዴግን ማጋለጥ በመሆኑ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ትግሉን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ “ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ ጥሪ ስናደርግ የፖለቲካ ምህዳሩ ተስተካክሏል እያልን አይደለም፡፡ እኛ አሁንም እያነሳን ያለነው የትግል ጥያቄ … [Read more...] about የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
ምርጫ ቦርድ፣ ማጭበርበሩን ያቁም!
በሕወሓት አመራርና አጃቢዎች የተፈበረከው ምርጫ ቦርድ ባለፉት 20 አመታት ለ4 ጊዜ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ምርጫ አካሂዷል። ሁሉም ምርጫዎች ግን የዴሞክራሲ መስፈርትን የሚያሟሉ እንዳልነበሩ ዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ጭምር አረጋግጠዋል። በ2007 ዓ.ም የምርጫ ውድድርም ሕወሓቶች፣ በዚሁ አመት ሃቀኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ጭራሹን ላለማሳተፍ፣ ለአመታት ያህል የቤት ስራ እየሰሩ ቆይተዋል፡፡ ለዚሁ አላማ ግቡን ለመምታት አስቀድመው እጅግ ብዙ ብቁ ምሁራንን እና ወጣት የፖለቲካ አመራሮችን “ለስልጣናችን አስጊ ናቸው” በማላት በሀሰት ወንጅለው አስረው በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ። ብዙ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላት ላይም ስጋት ፈጥረዋል፤ ከትምህርትና ከስራም አፈናቅለዋል። ፓርቲዎችን ለመበታተን ብዙ ሰርጎ-ገቦችን በማስረፅ አለመተማመን በመፍጠር፣ እንዲከፋፈሉ ለማድረግ ብዙ ገንዘብ ረጭተዋል። ተቃናቃኝ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ፣ ማጭበርበሩን ያቁም!
የአምባገነኖች ፀሐይ ጠልቃለች!
በእኛ በኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ለ23 ዓመታት ተመዝኖ ቀሎብናል - ይህ የጥቂት ሽፍታዎች ቡድን! የመንግስትነት ስም ሊመጥነው የማይችል የውንብድናና የማፍያ ተግባር በ’መንግስትነት’ ሽፋን ሲራመድም ቆይቷል - ላለፉት ሁለት አስርታት፡፡ ዛሬ፡- ይህን በገሃድ የሚታይ ጥሬ-ሀቅ ያልተገነዘበ አንድም ኢትዮጵያዊ አይገኝ፡፡ ይህንን የጥቂቶች "የምዝበራ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ" ለመሸፈን እና የተለየ ልባስ/ጭንብል ለማልበስ፤ እነዚህ መዝባሪዎች አያሌ ፎቆቻቸውን ከህዝብ በመዘበሩት የህዝብ አንጡራ-ሃብት አማካይነት ህዝብን ባፈናቀሉበትና ከቀዬው-በነቀሉበት በዚያው ስፍራ ላይ ለማቆም ችለዋል፡፡ ፎቆቻቸውን ያነፁት የእነርሱ-ዝርፊያ የሃገር-‘ልማት’ እንዲባልና በዚህም ሰፊው-ህዝብ ተደናግሮ ይህንን በአገር ላይ የሚሠራ "ጥፋት" በበጐ ጐኑ እንዲመለከተው ለማድረግ ነው፡፡ ‘ልማት’ እና የዘር-ልዩነት ላይ … [Read more...] about የአምባገነኖች ፀሐይ ጠልቃለች!
ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ!
ታህሳስ 19 ቀን በቅዱስ ገብርኤል ስም የሚታሰበው በዓል፤ እግዚአብሔር ሥነ ባህርይን (ሞራልን) እንዲያከብር ቅዱስ ገብርኤልን የላከበት ቀን ነው። ማሳሰቢያ፦ በቅዱስ ገብርኤል ስም በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ህዝብን በመዝረፍ ላይ የሚገኙት ብዙዎቹ “ቅዱስ ገብርኤል ተከበረ እንጅ አከበረ ” የሚለውን ሰምተውት ስለማያውቁ፤ “ቅዱስ ገብርኤል አይከበር አለ ” እያሉ፤ አንብበው ከእውነቱ መድረስ የማይችሉትን አንዳንድ የዋሆችን ውዥንብር ውስጥ መክተታቸው አይቀርም። እኔ ኢትዮጵያን በመምራት ያሉ ፖለቲከኞችና በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን የሚከፍቱትን የአስመሳይ ነጋዴዎች ባህርይ፤ አባቶች ስለበዓሉ አላማና ምክንያት ካስተማሩኝ ጋራ ሳንጻጽረው፤ ቅዱስ ገብርኤል ካከበረበት ምክንያትና ዓላማ ጋራ ምንም ግንኙነት እንደሌለው ገለጽኩ እንጅ ቅዱስ ገብርኤልማ ክብር ይገባዋል … [Read more...] about ቅዱስ ገብርኤል ሥነ ባህርይን (ሞራልን) አከበረ!
ኢትዮጵያና የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ. ም.
ኢትዮጵያና የካቲት 11 ቀን 1967 በሚል ርእስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማቅረብ ተገቢ ነው ብዬ ተነሳሁ። የማቀርበውም ባጭሩ የሚከተሉትን በተመለከተ ይሆናል፤ የየካቲት 11 ቀን 1967 ዓላማ፤ ፖሊሲው፣ ለማን እና ለምን እንደተፈጠረ። ቅድመ የካቲት 1967 ዋናው አስኳሉ የተፈጠረው፣ ማሕበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) በ1965 አካባቢ በቀ. ኃ. ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ነው። በትምህርት ላይ የነበሩ የትግራይና የኤርትራ ተማሪዎች ተሰብስበው ያቋቋሙት ማህበር ነው። ይህ ማህበር እንደተፈጠረ የወሰድው አቋምና የሚከተለው ፖሊሲ፣ በረቀቀ መንገና ጥናት ጸረ ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት፣ ፍቅርና ስላም ለማፍረስ የወጠነ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ኹከትና ብጥበጥ እንዲፈጠር የወሰነ በባእዳን የተፈጠረ ማህበር ነው። ማገብት ገና በረሃ ሳይወጣ ያዘጋጀው ፖሊሲው፣ ኤርትራና … [Read more...] about ኢትዮጵያና የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ. ም.
እውነት ስድብ ሲሆን!
ይገርማል በአገሬ ይሰድባል አዳሜ የሴት ልጅ እያለ፣ እስኪ መልሱልኝ ያስረዳኝ የገባው የወንድ ልጅ አለ? (ኢዮብ ብርሃነ ፌስቡክ) … [Read more...] about እውነት ስድብ ሲሆን!
ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች!
ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጭት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን» እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል። ይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር … [Read more...] about ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች!