የመናገር፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ወዘተ መብቶች በሚከበሩባቸው አገራት በመጀመሪያ ደረጃ ፓርላማ የሚባል አካል ካላቸው ገዢው ፓርቲ የ99.6 በመቶ ወንበር አይዝም፤ በፓርላማው የተቀናቃኝ ፓርቲ አባልም አንድ ብቻ አይሆንም፡፡ ይህ ከሆነ ስብስቡ “ፓርላማ” ሳይሆን “የ… ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ” ነው የሚባለው፡፡ ከዚህ ሲያልፍ ረቂቅ ሕግጋትና ውሳኔዎች ሁሉ “በአክላሜሽን” ወይም በሙሉ ድምጽ ወይም “በእልልታ” አይደለም የሚጸድቁት፡፡ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላትም የአገርን ጉዳይ በተመለከተ “የሶስት ደቂቃ” የንግግር ገደብ አይጣልባቸውም፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በኔፓል ፓርላማ የደረሰው “የተከበሩ” የፓርላማ አባላት እንዲህም ያደርጋሉ እንዴ በማለት የሚያስጠይቅ ነው፡፡ ማክሰኞ ምሽት የአገሪቱን የተሻሻለ አዲስ የሕገመንግሥት ረቂቅ ለማጽደቅ የተሰበሰቡት የፓርላማ አባላት በጉዳዩ ላይ … [Read more...] about በኔፓል ፓርላማ “አንቀጽ 39 በእልልታ” አይጸድቅም!
Archives for January 2015
የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት እጅግ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሲል ፓርቲው ጥር 15/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ አቶ ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው ነበር ያለው ፓርቲው በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ግልጾአል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል አቶ ዘመነ አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ አረጋግጠናል ያለው መግለጫው የሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት … [Read more...] about የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
የሐመር አርብቶ አደሮችና የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃ
በጥር 7/2007 ሐሙስ ዕለት በሐመር ወረዳ በ"ላላ" ቀበሌ በሐመር ብሔረሰብ አርብቶ አደሮችና ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የደረሰዉ ጉዳት የሚከተለዉን ይመስላል፤ ሀ/ የሞቱ-- 1. ሻምበል ለማ አሸናፊ 2/ ወ/ር ሙሴ ማቱሳላ 3/ ወ/ር ደፋሩ ጦና 4/ ወ/ር ካሬ 5/ ወ/ር በኃይሉ 6/ ስሙ ለግዜዉ ያልታወቀ የልዩ ኃይል ባልደረባ 7/ ስሙዋ ለግዜዉ ያልታወቀ ሴት ባለሙያ 8/መምህር መሳይ ነሽ መርነህ ለ/ የቆሰሉ 1/ አቶ ቹሜሬ የረር /የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ ጸጥታና ደንብ ማስከበር ምክትል ሀላፊ 2/ ምክትል ሣጅን ጌታሁን ቶላ 3/ ወ/ር ተሰማ መሰረት 4/ ወ/ር ጌታቸዉ ጻንቃ 5/ ወ/ር ቱላ ኪያ 6/ ባሻ ወንድማገኝ ጨነቀ 7/ ወ/ር ሚልኪያስ ግራኝ 8/ ወ/ር ዘለቀ (አባታቸዉ ያልታወቀ) 9/ አቶ ደምሳሽ ሞላ (የዞኑ ሴቶችና ሕጻናት መምርያ … [Read more...] about የሐመር አርብቶ አደሮችና የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃ
“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”
የሰብዓዊ መብት ተመልካች የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ ያወጣል ተብሎ የተጠበቀውን ዘገባ ማምሻው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?” በሚል ርዕስ ባተመው ዜና ላይ ዘገባው እንደሚወጣ በተናገረው መሠረት ባለ 76 ገጽ ሪፖርቱ በሚዲያ አፈና ዙሪያ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃዎችን አውጥቷል፡፡ ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ አፈና፣ ማስፈራሪያ፣ ህይወት የማጥፋት ዛቻ፣ … ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በትንሹ 22 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ፤ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ አገር ጥለው መኮብለላቸውን በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ እንዲህ ያለው ገለልተኛ ሚዲያን የሚያፍን እና ከሜዳው የሚያስወጣ አሠራር ከወራት በኋላ ይካሄዳል ከሚባለው “ምርጫ” አኳያ የውድድሩን ሜዳ … [Read more...] about “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ!
ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደሆነ በሚነገርለት ካፍቴሪያ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ አይሏል ። ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እዚህ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰማርተው እያገለገሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ በወጣትነት እድሚያቸው የተቀጠሩ ናቸው። ታዲያ ለወጣትነት እድሜ ጉልበታቸው ሳይሰቱ ነገን በተስፋ በመናፈቅ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ አውዳአመታትን ሳይቀር ያለ እረፍት በስራ በማሳለፍ ኮሚኒቲውን አገልግለዋል። ሰራተኞቹ በተሰማሩበት የስራ መስክ በሚከፈላቸው ደሞዝ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ቤትሰብ አፍርተዋል ። እነዚህ ወገኖች እንደመነሻ በተቀጠሩበት አነስተኛ ደሞዝ ከግዜ ወደ ግዜ እየከበደ የመጣውን የስደት ዓለም ህይወት መቋቋም ተስኗቸው ገሚሱ በብስጨት በደረሰበት የጤና መታወክ ለህለፍት ሀይወት ሲዳረግ በስኳር በሽታ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ!
የካድሬ ብቻ
ኑሮ ተወደደ፣ ምሁር ከአገር ጠፋ እየተሰደደ፣ እውነትን የፃፈ ለሃቅ የቆመ ዘብጥያ ወረደ፣ በአገሬ ምድር ላይ ቁጥሩ የጨመረ ዋጋዉ የረከሰ፣ የካድሬ ብቻ ነው ሕዝብ እያስለቀሰ *ኢዮብ ብርሃነ … [Read more...] about የካድሬ ብቻ
ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?
* ኢህአዴግ አሸነፈ፤ ፋና መሰከረ! ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዘገባው ከዚህ በፊት ከወጡት ዘገባዎች ለየት ባለ መልኩ በፕሬስ ሚዲያው ላይ የተሰማሩትን ክፍሎች በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡ በተለምዶው በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና በብዙ መልኩ የሚነገር ሲሆን በዚህ ዘገባ ግን ኢህአዴግ … [Read more...] about ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?
Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia?
Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia? More Crackdowns Lock Out Opposition Groups from Political Participation “If we do not have a proper multiparty democracy, this country is going to end up like Somalia. This is imperative” he said. “It is up to the people to decide on how many seats should be given to the opposition and how many to the ruling party.” (Prime Minister Hailemariam Desalegn)[i] PRESS RELEASE. December 16, 2015. Washington, DC, The Solidarity … [Read more...] about Should Ethiopians Boycott the Upcoming Fake Election in Ethiopia?
ተመስገን ደሳለኝ
ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ አስራ አራት በአንክሮ ሲነበብ «... የገዢዎች ቁጣ ሲነሳብህ ችግር እንዳትነቃነቅ ካለህበት አገር ...» በሚለው የጸናህ የቆየህ በቃሉ ለካ! አንተ ኖረሃል ተሜ ባለውሉ በአንድ ብዕር ብቻ አላንዳች ፍራቻ ገዢን ያንበረከክ ዝምታን የሰበርክ ዕውነትን ያበሰርክ ተሜ ባለ ውሉ ተሜ ባለ ቃሉ ነጻነት ቃጭሉ የፍትህ አክሊሉ የታለ መሣሪያህ? የታለ ዝናርህ? የታለ ጦር ጋሻህ? እኮ! በምንህ ነው? እንደዚህ የፈሩህ! የጀግንነት ምስጢር ውስጡ ሲመረመር መግደል ብቻ ሳይሆን በጫካ መሽጎ ጽፎ የሚያጎርስም ቁጣውን ሰንጎ እንደሆነ ጎበዝ እንደሆነ ጀግና ትምህርት አስተማርከን አንተ ብቅ አልክና ተሜ ባለ ውሉ ተሜ ባለ ቃሉ ነጻነት ቃጭሉ የፍትህ … [Read more...] about ተመስገን ደሳለኝ
እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!!
በክፍል አንድ ጽሑፍ ውስጥ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሁሉ እነዚህ ከእውነት ይልቅ ሃሰትን፤ ክቅንነት ይልቅ ተንኮልና ጭካኔን የመረጡ ጥቂት ካህናት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመከፋፈልና አንዱን ከሌላው ጋር በአስተሳሰብ አለያይቶ ለማጋጨት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ከዚህም ውስጥ በዚሁ በቅርቡ በፌስ ቡክ ላይ በለቀቁት ጽሑፋቸው በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የደረሰው ችግር “ሰዎች ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ጠንቅቆ ባለመረዳትና የራሳቸው ትርጉም በመስጠት.....” የሚል ጠቅሰዋል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!! ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ጸሃፊውን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል: MaAyal@aol.com … [Read more...] about እውነትን ፈልጓት፤ ታገኟታላችሁም!!