የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡ የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ … [Read more...] about አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ
Archives for January 2015
ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት
ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ ... ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡ ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ ቁራሽ ለሚሞላው ከርስ ራሳቸውንና ማንነታቸውን፣ ከዚያም አልፎ የትም የማይደበቁትን ኅሊናቸውን ያቆሸሹ፣ የአገር “እንግዴ ልጆች” ወይም “ውርጃዎች” ለህወሃት የማከሰምና የመግደል ሴራ ተላላኪ ሆነው የህዝብን ክብር ሰልበው ረክሰው ያረከሳሉ። ከዚህም በላይ … [Read more...] about ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት
የደቡብ አፍሪካዊያን ዕዳ!
የማንዴላ ልጆች ወገኖቹ ፤ የዋልንላቸው ውለታ ይህች አፍሪካ በነጻነት ፤ እንድታገኝ እፎይታ ጥረታችን ሁሉ ሰምሮ ፤ አገኙና ነጻነት በእኛ ቀን ሲዘነብል ፤ ብንሔድባቸው ስደት ከቅኝ ግዛት እስከ አፓርታይድ ፤ የረገጣቸው እያለ ወንድም ጓዱን ሐበሻ ፤ ስለ እሱ ዋጋ የከፈለ ከሀገር ይውጣ ብሎ ጮኸ ፤ ጎዳናው ላይ እያቃጠለ፡፡ ምን ነው ወገኔ ምን ነው? ፤ አእምሮም የለህ ማሰቢያ? ምን እንደሆነች አታውቅም? ፤ ውዷ የኔ ሀገር ኢትዮጵያ? በከፈልንላቹህ ዋጋ ፤ በእናንተ የተነሣ እንዲህ ሆና እንደቀረች ፤ በነጫጭ ጅቦች ተነክሳ? ታወክን ታመስን እንጅ ፤ በነጭ ሰይጣናት እከይ ወደ እናንተ የተመምነው ፤ መች አጥተን ነበር ሲሳይ ስለእናንተ ባደረግነው ፤ ከዲፕሎማሲው ማሳደም መሪዎችህን አሠልጥኖ ፤ በግንባር እስከ … [Read more...] about የደቡብ አፍሪካዊያን ዕዳ!
የፈረንሳዩ ቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ አሸባሪዎችና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት!
ከሰሞንኛው የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛዎች ወሬ እንዳዳመጣቹህት ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በሚታተም ቻርሊ ሄብዶ በተባለ ጋዜጣ ጥቅማችን ተነካብን ያሉ የመካከለኛው ምሥራቅ ተወላጆች በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች በተደረገላቸው ድጋፍ በጋዜጣው ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ባጠቃላይ 17 የሚሆኑ ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸውን ተከትሎ የምዕራቡ ዓለም መንግሥታትና ዜጎች በቁጣ በመነሣት አውግዘዋል ለጋዜጣውም ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል፡፡ የፈረንሳይ መንግሥትም ይሄንን ጥቃት በፈጸሙትና በደጋፊዎቻቸው ላይ እርምጃ ወስዷል እየወሰደም ነው፡፡ ይሄ ዓይነት ጥቃት ያሠጋናል የሚሉ ሀገራትም ተመሳሳይ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ እዚህ ሀገር ውስጥም የበሰለና ጥልቀት ያለው አይሁን እንጅ ኢ.ቴ.ቪ (ኢ.ቢ.ሲ) በልዩ ዝግጅት እና የሸገር ኤፍ.ኤም በሸገር ሸልፍ ዝግጅቱ … [Read more...] about የፈረንሳዩ ቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ አሸባሪዎችና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት!
አብዮት መንታ ነው
"የአብዮት ያለህ!"፥ አትበሉ ባ'ገሬ፣ በአብዮት መሃል፥ አብዮት አይጠሬ፣ ምስጋና ቢስ ትውልድ፥ ሆነነው ነው እንጂ፣ የግፈኛን ቀብር፥ የምናበጃጅ፣ የሚሞቱልንን፥ የደም ዋጋ ንቀን፣ በአብዮት መሃል፥ ካ'ብዮት ርቀን፣ በአርበኞች መሃል፥ ባ'ርበኝነት ስቀን... "ደሃ ህዝብ አስፈጁ"፥ ስንል ተሰምተናል፣ "አመሉ ሲታወቅ"፥ ብለን አድንቀናል፣ 'ያስፈጀው' ሲወገዝ፥ ፈጂውን ትተናል፣ አህያ እየፈራን፥ ዳውላ መ'ተናል። ልንገርህ ወገኔ፥ አብዮት ሁለት ነው፥ መንታ ነው ፍጥረቱ፣ እርግጥም አብዮት፥ ስም ያገኘበቱ፣ በዳዮችን ሲጥል፥ ስርአት ሲዘረጋ፣ ሙሉ ሥም ያገኛል፥ አቢዮት እዚህጋ። ነገር ግን ሲመታ፥ በበዳይ ፍላጻ፣ አቢዮት ተሽሮ፥ ይባላል አመጻ። "አብዮት የለም" አንበል፥ አብዮት አለን እኛ፣ ግዞት ቤቱ የሞላው፥ በአብዮተኛ። “There are … [Read more...] about አብዮት መንታ ነው
አንድነት በደጋፊዎቹ ላይ “አረመኔያዊ” ያለው ድብደባ መፈፀሙን ተናገረ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ሕጋዊ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሣተፉ በወጡ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ላይ በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ ሲል ከስሷል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ሕጋዊ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሣተፉ በወጡ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ላይ በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ ሲል ከስሷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞች የጠራቸው ሰላማዊ ሰልፎች ንግ በስኬት መጠናቀቃቸውን ገልጿል፡፡ ከፖሊስ ምላሽ አለማግኘቱን አዲስ አበባ ላይ የተጠናቀረው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ይናገራል፡፡ ለዝርዝሩ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያቀናበረውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡ የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ያጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ በሌላ በኩል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ … [Read more...] about አንድነት በደጋፊዎቹ ላይ “አረመኔያዊ” ያለው ድብደባ መፈፀሙን ተናገረ
Xenophobic attacks escalate as feeling of hatred sweeps South Africa
“In Russia, bread riots led to a revolution, here (in South Africa) they lead to xenophobia.” Nomalanga Mikize, on Twitter A nation in cantankerous mood and truculent society baying for blood. The air is thick with terror and despair of foreign nationals living and working in one of the world’s racially intolerant nations, South Africa. Collectively known as Makwerekwere-a derogatory term for black African immigrants and Onomatopoeia-for other non-nationals who speak unintelligibly, life in … [Read more...] about Xenophobic attacks escalate as feeling of hatred sweeps South Africa
ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ!
አቶ ኢሳይያስ እንዴት ነዎት ባያሌው? ሌሎቹ የሕዝባዊ ግንባር አመራሮችስ እንዴት ናቸው? ሕዝቡስ እንዴት ነው? አቤት! አቤት! አቤ……..ት! ለማንኛውም ድምፅዎን ማሰማትዎ መልካም ነው፡፡ በቅርቡ ለኢሳት የራዲዮና የቴሌቪዥን (የነጋሪተ-ወግና የምርዓየ-ኩነት) ጣቢያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ጣቢያው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያደርስልዎት ዘንድ ከኢሳት ጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቁን ማድረግዎን ሰማን፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልን! እግዚአብሔር ያክብርልን! ብለናል፡፡ ግን እንዲያው እውነት ለመናገር አቶ ኢሳይያስ ከአማርኛ ይልቅ እንግሊዝኛው ቀንቶዎት ቀርቦዎት ቀሎዎት ነው ከፊሉን ቃለ ምልልስ በእንግሊዝኛ ያደረጉት? በእርግጥ አባትዎ እንዳስጠነቀቁዎት ጠንቅቀው (perfectly) በማያውቁት ቋንቋ ያውም ቃለ መጠይቅን ያህል ነገር ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን እኮ አቶ ኢሳይያስ የእርስዎ አማርኛ ደኅና እና … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ!
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ (January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00-15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ። የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና … [Read more...] about ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። "ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።..." በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ "ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።..." ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች … [Read more...] about የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ