• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

160 ሰዎች የሞቱበት፣ 360 ሰዎች የተጎዱበት፣ ከ4.6 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት የወደመበት የነጃዋር ክስ የወንጀል እንጂ የፖለቲካ እንዳልሆነ ተጠቆመ

September 29, 2020 09:05 pm by Editor 1 Comment

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለውና ክስ ተመሥርቶባቸው የሚገኙ ግለሰቦች ፖለቲከኞች ቢሆኑም፣ የታሰሩት በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው አለመሆኑን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ሚዲያ ኃላፊዋ ቢልለኔ ሥዩም ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት፣ የጉዳዮች መገናኘት ካልሆነ በስተቀር፣ የታሰሩ ግለሰቦች ፖለቲከኞች ቢሆኑም ከፖለቲካ አመለካከትቸና እንቅስቃሴያቸው የታሰሩ እንዳልሆነ አብራርተዋል።

ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ገላን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጥይት ተመትቶ የተገደለው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ተከትሎ፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ከተከሰቱ አመፆችና ጥቃቶች ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ 2,000 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመሥረቱን፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ጌዲዮን (ዶ/ር) እና የውጭ ቋንቋዎችና የዲጂታል ሚዲያ ኃላፊዋ ቢልለኔ ሥዩም እንዳስታወቁት፣ ክስ የተመሠረተባቸው ግለሰቦች በነበረው አመፅና ጥቃት ውስጥ በተለያየ ደረጃ ተሳትፎ የነበራቸው ናቸው ብለዋል።

የድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ ተከትሎ ከ9,000 ሰዎች በላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ታስረው የነበረ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥም እንደ አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ እስክንድር ነጋና አቶ በቀለ ገርባን የመሳሰሉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም የሚዲያ ኃላፊዎች ይገኙበታል። ከእነዚህ ታሳሪዎች መካከል በተለያዩ ጊዜያት የተፈቱ ግለሰቦች እንደነበሩ ሲነገር ነበር።

የድምፃዊውን ግድያ ተከትሎ በነበሩ አመፆችና ጥቃቶች በአንዳንድ አካባቢዎች አናሳ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ለይቶ የማጥቃት ድርጊት እንደነበር ያስታወቁት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ጌዲዮን (ዶ/ር)፣ በዚህም ሳቢያ 160 ሰዎች እንደ ሞቱ፣ 360 ሰዎች ጉዳት እንደ ደረሰባቸው፣ እንዲሁም ከ4.6 ቢሊዮን ብር በላይ የንብረት ውድመት እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ወንጀሎች የተፈጸሙበት መጠንና ግዝፈት በራሱ ለምርመራውና ለክስ ሒደቱ ትልቅ ፈተና እንደሆነ ያስረዱት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ፣ መንግሥት አጥፊዎችን ወደ ሕግ እያቀረበ ነው ብለዋል።

ምንም እንኳን የሰዎችን ሕይወት መቅጠፋቸው አሳዛኝ መሆኑንና መንግሥትም በዚህ ሐዘን እንደሚሰማው የተናገሩት ቢልለኔ፣ እንዲህ ያሉ የአመፅ ክስቶችን ግን መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነት ለማስጠበቅ አቅም የለውም ለማለት አያስችልም ብለዋል። ይልቁንም ትኩረት ያላገኙና ያልተነገረላቸው በርካታ ተመሳሳይና የሽብር ጥቃቶችን መቀልበስ የተቻለ መሆኑ ከግምት ሊገባ ይገባል ሲሉ አክለዋል።

በዚህ ላይ ያከሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) እንዳሉት፣ መንግሥት ተመሳሳይም ሆነ ሌሎች ጥቃቶችን ከመቀልበስ ባለፈ፣ የተለያዩ አጥፊዎችን ወደ ሕግ እያቀረበ መሆኑ፣ ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ተመሳሳይ ጥቃቶችም ሆኑ ሙከራዎችን ለማስቀረት ይረዳል ብለዋል።

በተለይ አቶ ጃዋር መሐመድ በፍርድ ቤት መንግሥት እሳቸውንም ሆነ ሌሎች ፖለቲከኞችን ያሰረው ጥፋት ኖሮባቸው ሳይሆን፣ የፖለቲካ አመለካከታቸው የተለየ ስለሆነ መንግሥት የምርጫ ሜዳው ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ እንዳይኖር እያደረገ ነው ሲሉ ያቀረቡትን መከራከሪያ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌዲዮን (ዶ/ር)፣ “የጉዳዮችን መገናኘትና ምክንያትነት መረዳት መቻል ይኖርብናል፤” በማለት፣ እነዚህ የታሰሩ ግለሰቦች ፖለቲከኞች ቢሆኑም፣ የታሰሩት ግን በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው እንዳልሆነ መታወቅ ይኖርበታል ሲሉ ተከራክረዋል።

2013 ዓ.ም. ከቀደመው ዓመት ይልቅ በሰላምና መረጋጋት ረገድ የተሻለ እንደነበረ ያስታወሱት ቢልለኔ፣ በመተከልና በሌሎች ሥፍራዎች በንፁኃን ዜጎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶችን መንግሥት ያወግዛል ብለው፣ በመንግሥትና በክልል መንግሥታት የፀጥታ መዋቅሮች ጠንካራ ትብብር በማድረግ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት እንዳለ አስረድተዋል። (ብሩክ አብዱ፤ ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Left Column, News Tagged With: chilot, jawar massacre, tplf, ችሎት

Reader Interactions

Comments

  1. ZTSM says

    September 30, 2020 01:20 pm at 1:20 pm

    Those are criminals by any definition, and must be tried as such; they are not political prisoners. It is time individuals/groups like them be dealt with in the style of North Korea (historically countries like China, Vietnam, South Korea, Cambodia, etc) attained their peace by confronting their own versions of Ethiopia’s thugs in the languages the thugs understood: quick elimination by any means available to the states. Thus like Mohammed and Geleba should be eliminated out of sight and sound in the middle of the night?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule