125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በሰፊው ታስቦ እንደሚውል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል።
125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዓሉ ሲከበር በወረዳዎች በመሰረተ ልማት ቦታዎች ላይ የጀግኖች ስም የሚሰየም እንደሚሆንና የመደመር የኪነጥበብ ትርኢቶች እደሚዘጋጁ የምሁራንና የህዝብ የውይይት መድረኮችም እንደሚካሄዱ
አድዋን ለአባይ በሚል መሪ ሀሳብም የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳልም ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሰው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ወቅት ገልጸዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት አከባበር መለያ አርማ (Logo) ይፋ አድርጓል፡፡
የአርማው መግለጫ፦
– ጋሻ ጎራዴና ጦር፦ አባቶቻችን ጠላትን የተዋጉባቸው የጦር መሳሪያዎች፤
– ሶስቱ ኮከቦች፦ የነበረው አሁን ያለውና የሚተካው ትውልድ፤
– አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነፀብራቅ፦ አሁን ያለው የዓድዋ ትሩፋት፤
– ከ1888-2013=125 ዓመት፦ ስሌት
– የኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ዓርማ፦ መሪ ቃል፤
– ጥቁር መደብ፦ የጥቁር ህዝቦች ድል፤
– ቀይ ፍሬም፦ በመስዋህትነት የሚጠበቅ ሉዓላዊነት መሆኑን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply