“ሥራ ፈላጊው” ገብረሕይወት አስማረ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሕገወጥ መልኩ ሲያዘዋውር ተያዘ።
“ገንዘቡ የተያዘው ሐምሌ 14/2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ገዳማ ከጠገዴ ወረዳ ሾርካ ንዑስ ወረዳ መፈተሻ ኬላ ላይ ነው” ብሏል ፖሊስ ለአብመድ በሰጠው መረጃ። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ምክትል ኮማንደር አስማማው ካሴ እንደገለጹት አቶ ገብረሕይወት አስማረ የተባለ ተጠርጣሪ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በቦርሳ ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥ ሥር ውሏል።
የተጠርጣሪው መታወቂያ “ሥራ ፈላጊ” የሚል መሆኑንም ነው ምክትል ኮማንደር አስማማው የተናገሩት፡፡ ግለሰቡም ከጎንደር ወደ ሁመራ ተጓዥ እንደነበር መናገሩም ተሰምቷል። ከ110 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በተጨማሪ የእንግሊዝ ፓውንድ መገኘቱንም ነው የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤቱ ያመለከቱት።
ከጎልጉል ዝግጅት ክፍል፥ መቶ አሥር ሺህ ዶላር በብር ሲመለስ በርከት ያሉ ሚሊዮኖች ይሆናል። ይህ ዓይነቱ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እጅግ ከመስፋፋቱ የተነሳ ይህ ሁሉ ገንዘብ የሚመጣው ከየት ነው? ዋንኛ አስተላላፊዎችስ እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። አገር በማፍረስ ዓላማ ላይ ትጋት እያደረጉ ያሉ በዚህ ዓይነቱ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ እንዳሉበት አጠያያቂ አይደለም፥ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው የሃሰት ዜና የዚህ ዓይነቱ ሤራ ውጤት መሆኑ አይጠረጠርም። በርግጥ ገንዘቡ መያዙ መልካም ሆኖ ሳለ ምንጩን ማድረቅ ግን በቅድሚያ የመንግሥት ኃላፊነት ነው። የሕዝቡንም የማያቋርጥ ድጋፍ ይጠይቃል።
©አብመድ
Gi Haile says
የግለሰቡን የግንኙነት መዋቅር በምርመራ መበጣጠስ አስፈላጊ ከዚህ ሰው ጋር የሚሰሩትን ሁሉ በቁጥጥር ስር መዋል ነው።