ትናንት ኣመሻሽ ላይ፤ ከYohanes Molla ጋር ተቀጣጥረን ተገናኘን ፡፡ካልዲስ ገብተን እኔ ኣንድ ፍንጃል ቡና ሳዝዝ ፤ ዮሀንስ ሲያቀብጠው ኣንድ ቡና እና የባራክ ኦባማን ጆሮ የሚያህል ቦምቦሊኖ ኣዘዘ፡፡ በመጨረሻ ኣስተናጋጂቱ የእዳችንን ደረሰኝ ኣምጥታ ጠረጴዛው መሀል ላይ ኣኖረችው ፡፡እሱ እኔ እስክከፍል ሲጠብቅ እኔ እሱ ይከፍላል ብየ ስጠብቅ ካብ ለካብ እየተያየን በጣም እረጅም ጊዜ ተጎለትን፡፡
በመካከሉ የኢትዮጵያን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ርእሰ ጉዳይ ጨርሰን “ፌንጣ ስንት እግር ኣላት? ስድስት ነው ኣራት?” በሚል ጉንጭ ኣልፋ ክርክር ተጠመድን፡፡ ወሬ ኣልቆብን ካጠገባችን ከተቀመጡ ተስተናጋጆች ወሬ እየተበደርን ስናወራ ቆየን፡፡ በመጨረሻ ካፌው ጭርር ብሎ ኣስተናጋጆች እንድንወጣላቸው እግራችን ስር መጥረጊያ ኣስገብተው ይጠርጉ ጀመር፡፡
ድንገት በብሄረሰቦች ላይ የሚነገረው ቀልድ እንዴት ኢ-ፍትሃዊነት እንደሆነ ኣንስቼ መከራከር ጀመርሁ፡፡በተለይም ጉራጌን እንደ ቋጣሪ ማየት መሰረት የለሽ መሆኑን ፤ እኔ የማውቃቸው ጉራጌ ጓደኞቼ ባጠቃላይ በጣም ለጋሶችና ኣባ መስጠቶች መሆናቸውን በመጥቀስ በስሜት ነድጄ ጠረጴዛ እየደበደብኩ ተናገርኩ፡፡ የሚቻል ከሆነ ጉራጌን እንደ ንፉግ የሚስሉ ኮሜድያን ባስቸኳይ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ኣሳሰብኩ፡፡
ወድያው ዮሀንስ ሞላ የኣባባሌን እውነተኝነት በተግባር ለማረጋገጥ ከኪሱ መቶ ብር መዥርጦ ሂሳቡን ዘጋው፡፡
ኣባቴ ከቅዱስ መጽሀፍ ኣንድ ምእራፍ ሳያነብ እንደማይተኛ እኔ ደግሞ ከ“ፍቅር እስከመቃብር” ኣንድ ኣንቀጽ ሳላነብ እንቅልፍ ኣይወስደኝም፡፡ከዮሀንስ ጋር ከተሰነባበትን በኋላ እቤቴ ገብቼ “ኣዲስ ኣበባ” የሚለውን ምእራፍ ገለጥሁ፡፡
ብዙዎቻችሁ እንደምታስታውሱት፤ በዛብህ ቦጋለ፤ ሰብለን ለመጥለፍ ያደረገው ሙከራ ከከሸፈበት በኋላ ከፊታውራሪ መሸሻ ቁጣ ሸሽቶ ኣዲስ ኣበባ ይገባል፡፡ እናም ሱልሉልታ ኣካባቢ ከሲራራ ነጋዴዎች ጋር ይወዳጃል፡፡ ኣንድ ቀን ከኒህ ወዳጆቹ ኣንዱ ከሆኑት ነጋድራስ ሁነኛው ጋር እያወራ ነው፡፡
“ኣዲስ ኣበባ የማውቀው ሰው የለኝም፡፡ ምን ማድረግ የሚሻለኝ ይመስልዎታል፡፡ እስኪ ይምከሩኝ ” ኣለ በዛብህ፡፡
“ገንዘብ ካለህ ኣትቸገርም፡፡ ገንዘብም የምታውቀው ሰውም ከሌለህ ነው ችግሩ! እስቲ ለማንኛውም ከኛ ጋር ጉለሌ ስፈርና ስራ እስክታገኝ የምትቆይበትን ስፍራ እንፈልጋለን” ኣሉ ነጋድራስ፡፡
“ገንዘብስ ከእናንተ ጋር ያገጣጠሙኝ ወዳጆች ኣዋጥተው የሰጡኝ ኣንድ መቶ ብር ኣለኝ“
”ኣንድ መቶ ብር ካለህማ፤ ማለፍያ ቤት ተከራይተህ፤ ማለፍያ ቀላቢ ቀጥረህ ብዙ ጊዜ ያቆይሃል . . . ገንዘብህ እንዳይጠፋብህ መጠንቀቅ ነው”(ፍቅር እስከመቃብር፤ ገጽ 434)ኣጀብ ነው!! ኣንድ ኢትዮጵያዊ በመቶ ብር ኣሪፍ ቤት ተከራይቶ ምግብ ኣብሳይ ሰራተኛ ቀጥሮ ለብዙ ጊዜ መኖር የሚችልበት ዘመን መኖሩን ሳስብ፤ በጊዜ መኪና ወደ ድሮ መመረሽ ያምረኛል፡፡ ኢትዮጵያ ከየት ወዴት የሚለውን ለማጥናት ኣቋራጩ መንገድ “መቶ ብር ከየት” ወዴት የሚለውን ማጥናት ኣይመስላችሁም?
በለው ! says
“የወር ገቢያችሁ ከሶስት (፫፻ብር)በታች የሆናችሁ የድሃ ድሃ ነዋሪዎች!? ፀረ ልማት…
***ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እንዲሁም የደሃ ድሃ ነዋሪዎች….ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች!!ድሮ የተረሳችሁ፣ የተጨቆናችሁ፣ በአድሃሪው መንግስት ኩንታል ጤፍ በአምስት ብር እየገዛችሁ፣ በመቶ ብር ኣሪፍ ቤት ተከራይቶ ምግብ ኣብሳይ ሰራተኛ ቀጥሮ ወለድ አበድሮ ሠንጋ ጥሎ ጎረቤት አብልቶ ቅርጫት እንቁላል በሽልንግ ገዝቶ እየበላ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ አፈርድሜ ያገባ የዋህና ጨዋ ድሃ ሕዝብ….ድህነትን ተረት ለማድረግ ብድርና ልመናን መዝራት ነው። ዕድሜ ለአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት እንቁላል ዕንቁ ሆነ! እናንት የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎች የድሮ መቶ ብር መቶ ብር አለ በለው!
Sanyii says
Typical racist jokes by a nagtegna (be’ewuketu) on Guraghe. Amaran bilhna asteway adrgo lelawun ye’Ethiopia bheroch feri, yewah, mogn, etc adrgo yemesal yalefebetn technic newu be’ewuketu yetetekemewu. That is why I advocate English as Federal Working Language to make the playing field level for all Ethiopian nations and nationalities. Otherwise, keeping Amharic as it is right now will continue putting others at a disadvantage, including the Tigres (it is only a matter of time and they will be cast aside when their influence dwindle or come to an end soon.) So, my advise for the Tigrean Elites is to exaclty that while they can influence better which is now. By the way making English Federal Working Language will also help Amharic speakers as they will not be treated as an enemy when they go to other Ethiopian regions. Because I strongly believe that it is the language that is causing all these divide and replacing it with a neutral language is the best solution! Chigru ende Metmku Yohannes yemisemagn’n atahu.