የህወሃቱ ታጋይ ጄ/ል ከበደ በ1988 ዓም የ31ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ ፓራ ኮማንዶ፣ የ1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሆኖ ሰርቷል። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በ31ኛ ክ/ጦር ምክትል ብርጌድ አዛዥ ሆኖ አገልግሏል። በ1992 ዓም 35ኛ ክ/ጦር ስትፈጠር የ35ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ ተሹሟል።
በ1997 ዓም ኮር የሚባለው አጀረጃጀት ፈርሶ ዕዝ የሚባል አደረጃጀት ሲቋቋም፣ ግለሰብ የ35ኛ ክ/ጦር ም/አዛዥ ቀጥሎም የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ሆኖ እስከ 2006 ዓ/ም ሠርቷል።
በ2006 ዓ/ም እነ ጄኔራል አበባው ታደሰን ለማስወጣት በተደረገው ግምገማ፣ ግለሰቡ የአበባው አሽከር ነህ ተብሎ ተፈርጇል። ይህን ተከትሎም ከክፍለ ጦር አዛዥነቱ ተነስቶ፣ የዕዙ ማሰልጠኛ ት/ት ቤት አዛዥ ሆኖ ተመድቧል።
የጡረታው ጊዜ ሲደርስ “ተጠቅሞ ይውጣ” ተባለና ወደ አብዬ በሚሊቴሪ “ኦብዘርቨርነት” ተላከ። በአማራና ኦሮሞያ የነጻነት ትግል ሲቀጣጠልና የህወሃት ህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ ህወሃት በጡረታ ልታስወጣው ያሰበችውን ሰው መልሳ፣ በ2010 ዓ/ም አጋማሽ ላይ የብ/ጄኔራልነት ማዕረግ ሰጥታ ለሌላ ተልዕኮ አጨችው። ከዚያም የ31ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አድርጋ ሾመችው።
ሰውዬው በጣም ጨካኝ ነው ይሉታል አብረውት የሰሩት ሰዎች ሲናገሩ። “በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት፣ ወደ ኤርትራ በጥልቀት ገብተን እያለ፣ ወደኋላ እንድንመለስ ስንታዘዝ፣ ሻዕብያም መረጃው ደርሶት ሰለነበር፣ ከፍተኛ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ማድረግ ጀመረ። በዚህ መሃል አዲስ ከመጡት ምልምል ወታደሮች መካከል አንድ ወጣት ተደናግጦ ራሱን አቆሰለ። ስለልጁ ድርጊት ለከበደ ሪፓርት ሲደረግለት፣ ‘አምጡት’ አለና፣ ሽጉጡን አውጥቶ ግንባሩን ብሎ ገደለው።”
በ2013 ዓ/ም ደግሞ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሲፈጸም፣ የእሱ ምክትል የነበረውን ኮ/ል ሻምበል በየነን (ባለከዘራውን) ለማስገደል አቅዶ፣ የክ/ጦሩ ም/አዛዥ እቅዱን ባለመቀበሉ፣ ከተማ ቀጥሮ በሽጉጥ ግንባሩን ብሎ ገደለው።
የብርጌድ አዛዥነቱን ተጠቅሞ ከኤርትራ ያዘረፈውን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ስኳርና ከብት፣ ሽራሮ ላይ ሽጦ አክሱም ላይ ፎቅ ሰርቶበታል። ከጭካኔውና ሌብነቱ በተጨማሪ በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል ዘረኛም ነው።
በለውጡ ማግስት አምባሳደር ስዩም መስፍን ከኮሎኔል ማዕረግ በላይ ያላቸውን ወታደራዊ አዛዦች በየሁለት ሳምንቱ እየሰበሰበ ግዳጅ ይሰጥ ነበር። ጄ/ል ከበደ ደግሞ ሽሬ ላይ ከፍተኛ መኮንኖችን እየሰበሰበ ከላይ ያመጣውን ተልኮ ወደታች በማውረድ ስራውን ይሰራ ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ሰራዊቱ በተደጋጋሚ ለበላይ አለቆች ቢያሳውቅም፣ ምላሽ በማጣቱ፣ የጥቅምት 24ቱ እልቂት ተከሰተ። ከዚህ እልቂት ጀርባ ካሉት ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ ይህ በተደጋጋሚ ታዳጊዎችን እያስጨፈጨፈ የሚፈረጥጠው ጄኔራል ነው።
ፋሲል የኔዓለም
Leave a Reply