• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዳውድ ኢብሣ ከህወሓት ጋር በማበርና በሌሎች ምክንያቶች ከሥልጣን ተወገዱ

September 14, 2020 08:30 am by Editor 1 Comment

“ሕወሓት በኦሮሞ ህዝብና ታጋዮች ላይ ላደረሰው ጉዳት ይቅርታ ካልጠየቀ ከፓርቲው ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም” ሲል ኦነግ አስታወቀ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ ድርጅቱን ለ21 ዓመት የመሩትን አቶ ዳውድ ኢብሳን ከሊቀመንበርነት ማንሳቱን ይፋ አድርጓል።

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ አቶ ዳዉድ ኢብሳ በሊቀመንበርነት በቆዩባቸው 21 ዓመታት “የድርጅቱን ገንዘብና ሀብት ብቻቸውን ሲያዙበት ኖረዋል ፤ በድርጅቱ ውስጥ አድልዎ በመፍጠር የአካባቢያቸውን ሰዎችና ዘመዶች ቁልፍ የስራ መደቦች ላይ በመመደብ ጥቅማቸውን አስጠብቀዋል” ሲሉ ለአል ዐይን ኒውስ ተናግረዋል። ግንባሩ የሊቀመንበሩን መታገድ በተመለከተ መግለጫም አውጥቷል።

መግለጫው አቶ ዳውድን “በዚህ መሰል ኣካሄድ ከድርጅቱ ህገ ደንብና አሰራር ውጭ የራሳቸውን አምባገነንነት በድርጅቱ ላይ አነግሰዋለ” ያለ ሲሆን “አቶ ዳዉድ ኢብሳ 21 ዓመት በሊቀ መንበርነት በቆዩበት ጊዜ ድርጅቱ ፈራርሶ ከነበረበት ወረደ እንጂ እድገት አላሳየም” ብሏል። አቶ ዳውድ በአመራር ዘመናቸው የኦነግ ዋና አመራርና መዋቅሩ እንዲፈርስ ማድረጋቸውንና የጋራ አመራር የሚለው በሃሳብ እንጂ በተግባር ሊታይ እንዳልቻለ ፓርቲያቸው ገልጿል።

አሁን ላይ ኦነግ ዉስጥ የተማሩና ልምድ የቀሰሙ አባላት ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የገለጸው ግንባሩ ለዚህ ደግሞ “ተጠያቂው አቶ ዳዉድ ናቸው” ብሏል።

ግንባሩ ብዙ አመታት ባስቆጠረው የኦሮሞ ነጻነት ትግል ውስጥ ኦነግ ከተለያዩ ብሄርና ብሄረሰቦች ትግል ጋር የትግል አጋርነትና ወዳጅነት ለመፍጠር ጥረቶችእንዳደረገ ያነሳ ሲሆን ይህም የትግል አጋርነትና ወዳጅነት በእኩልነት፣ በመከባበርና በዲሞክራስያዊ መርህ ላይ መሆንን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ለታክቲክ ወይም ለግዜያዊ ጥቅም ተብሎ የሚደረግ ትብብር ዘለቄታዊ ጥቅም እንደማያስገኝ ያነሳው የግንባሩ መግለጫ በተለይም ሕወሓት በኦሮሞ ህዝብና በኦሮሞ ታጋዮች ላይ ላደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ይቅርታ ጠይቆ በኦሮሞ ህዝብ ቅቡልነት አስኪያገኝ ድረስ ኦነግ ከዚህ ድርጅት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ይሁንና አቶ ዳዉድ ኢብሳ ከአመራሩ ዕውቅና ውጪ የፋይናንስ ሰራተኛቸውን በቅርቡ መቀሌ በተካሄደው የህወሃት ስብሰባ ላይ አንዲሳተፍና ግንኙነት እንዲያደርግ መላኩ የግንባሩን ፖሊሲ የጣሰ ህገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ነው ፓርቲው የገለጸው። ኦነግ በኦሮሞና በትግራይ ህዝብ መካከል ያለው ወንድማዊና ዘላቂ ግንኙነት አንዲጠናከር እንደሚሰራም አስታውቋል።

ኦነግ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግና ያለውን ድክመት ለማረም እንደሚሰራ የገለጸው መግለጫው ፣ “አቶ ዳውድ ኢብሳ ከድርጅቱና ከሀገሪቱ የፓርቲ ህግና ደንብ ውጪ እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአቶ ዳውድን ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን አንዲከታተል” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በመሆኑም “አቶ ዳውድ የኦነግ ሊቀ መንበር የሚል ስም በመጠቀም ከቦርዱና ከተለያዩ አካላት ጋር ግንኙነት ለማድረግ የሚያደርጓቸው ጥረቶች በድርጅቱ ተቀባይነት የላቸውም” ይላል መግለጫው። ግንባሩ ጠቅላላ ጉባዔ አድርጎ አዲስ መሪ እስኪመረጥ ድረስ ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ የድርጅቱ ተወካይና መሪ እንዲሆኑ መወሰኑ በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።

“ከኦነግ ከፍተኛ አመራር ውስጥ ሊቀ መንበሩ ያሰማሯቸው ጥቂት ግለሰቦች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን መቀላቀላቸውና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት ከፍተኛ አመራር በማለት በትጥቅ ትግል ለመቀጠል መርጠዋል” ያለው የኦነግ መግለጫ “ጥቂት አባላት በስልክ ሠራዊቱን ለመገናኘት መሞከርና የሰላማዊ ትግሉን ስነ ምግባር ያለማክበር ድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል” ሲል ገልጿል።

ይህም በተለይም በወለጋና ጉጂ የሚኖረው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ወከባ፣ የሀገር ውስጥ ስደት፣ የህይወትና የንብረት ጉዳት በማስከተል የህዝቡን የመንቀሳቀስ ነጻነትና ሰላማዊ ኑሮ ማናጋቱን አስታውቋል።

በውጭ ያሉ ጥቂት የድርጅቱ አመራር አባላት የነበሩ ግለሰቦችም “ከትጥቅ ትግል ውጪ የሚያዋጣን የለም” በማለት ገንዘብ በማሰባሰብና በየጊዜው በማህበራዊ ሚዲያና በኦኤንኤን (ONN) ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ወጥተው በኦነግ ስም የሚያስተላልፉት መልዕክትና የሚያደርጉት ቅስቀሳዎችና ጥሪዎች ከድርጅቱ የትግል ስትራቴጂና ከሀገሪቷ ህግ ጋር የሚጣረሱ በመሆናቸው” በድርጅቱ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ በመግለጫው አካቷል።

“ከፊል የድርጅቱን የአመራር አባላት የትጥቅ ትግል ደጋፊዎች፣ ሌሎችን ደግሞ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የሚፈልጉና ከመንግስት ጋር ያበሩ በማለት የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ራሳቸውን ወደር የማይገኝለት የነጻነት ታጋይ አስመስለው በማቅረብ በድርጅቱ ውስጥ መከፋፈል አንዲኖር በሰፊው ዘመቻ አካሂደዋል” ብሏል ግንባሩ ባወጣው መግለጫ።

ከዚህ ቀደም አቶ ዳውድ በጊዜያዊነት ስለመታገዳቸው አል ዐይን አማርኛ መዘገቡ ይታወሳል። አሁን ድርጅቱ ስላሳለፈባቸው ዉሳኔ እንዲሁም በተያያዥነት ስላወጣው መግለጫ አቶ ዳውድ ኢብሳን ለማናገር በእጅ ስልካቸው ላይ ለመደወል ብንሞክርም ስልካቸው ባለመስራቱ አል ዐይን ሀሳባቸውን ማካተት አልቻለም። (ምንጭ፤ አል ዐይን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Politics

Reader Interactions

Comments

  1. GI Haile says

    September 14, 2020 03:27 pm at 3:27 pm

    ራዕይ የሌለው መሪ በሆሮሞ ደም ሐብት ያፈራ ለማንም ግድ የሌለው ሰው ነው። ፀረ ሆሮሞ እንጅ ለሆሮሞ ሕዝብም ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ደንታ የለውም። ዋናው ኣላማው ድርጅቱን ለራሱ በማድረግ ኣምባገነን ሆኖ ሆሮሞን ኣስፈጀ። መነሳት የተበረበት ከኣስር አመት በፊት ሆኖ ቢሆን ዛሬ ኢትዮጵያ ሆነ ሆሮምያ እንደዚህ ኣይነት ወንጀል በሆነግና በሸኔ ባልተሰራ ነበር። የተወሰደው እርምጃ ትክክለኛ ነው።

    Reply

Leave a Reply to GI Haile Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ October 30, 2023 10:27 am
  • የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ October 26, 2023 01:30 pm
  • ጥቅምት 15 ለምን? October 26, 2023 01:29 am
  • “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” October 26, 2023 12:57 am
  • “ውትድርና ሕይወቴ ነው” October 26, 2023 12:13 am
  • መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው October 20, 2023 05:07 pm
  • “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ October 20, 2023 04:47 pm
  • 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ October 18, 2023 04:29 pm
  • በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ October 18, 2023 04:00 pm
  • ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” October 13, 2023 10:04 pm
  • ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም October 10, 2023 01:51 pm
  • “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች October 10, 2023 09:07 am
  • እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ! October 7, 2023 06:47 am
  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule