
የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ደግም ለተጀመረው ድርድር እንቅፋት መሆኑን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገለፁ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አምስተኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የሶስትዮሽ ድርድር የእስካሁን ውጤት ላይ እየሰጡት ባለው መግለጫ የግብፅ የእኔ ጥቅም ብቻ ይጠበቅ አቋም ድርድሩን እየተፈታተነ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፥ ግብፅ በድርድሩ በተለመደው ሁለት አካሄዷ ቀጥላበታለች ነው ያሉት። ግብፅ አንድ እግሯን ድርድሩ ላይ አንድ እግራን የፀጥታው ምክር ቤት አስቀምጣ መደራደርን መምረጧን በማንሳት።
በድርድሩ ግብፃውያኑ የፈለጉት እና የጠየቁት ሁሉ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ የሚሰጡት ግን የላቸውም ነው ያሉት።
ግብፅ የጋራ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ ውሃ መሙላት አትችልም የሚል ተቀባይነት የሌለው ሃሳብ ይዛ መቀጠሏም ተነግራል።
Leave a Reply