የአገር መከላከያ ሰራዊት “ርዝራዥ” ሲል የሚጠራውን ሃይል መደምሰሱን አስታወቀ። ሃይሉ የተደመሰሰው ድንበር አቋርጦ ወደ ሱዳን ለመሸሽ በሞከረበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል። ከተገደሉት በፍተሻ “የኦሮሞ ማንነት መታወቂያ ተሰርቶላቸው ነበር” ተብሏል።
የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ እነዚህ የጁንታው አባላት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የሌላ ክልል መታወቂያ በመያዝ ከሀገር ሊሸሹ ሲሉ ሰራዊቱ በደረገው ከፍተኛ ጥረት ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡
የዚህ ድርጊት ዋነኛ አላማ እነዚህን አባላት ወደ ሱዳን በማሸሽ ከዚያ ሆኖ ሀገር ውስጥ ያሉትን ተጣቂ ሀይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት ሀገር ለመበጥበጥ የታቀደ እንደነበር ሌ/ጄነራል ባጫ በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡
እርምጃ በተወሰደባቸው ሁሉም የጁንታው አባላት እጅ ላይ ይህ ሀሰተኛ መታወቂያ መገኘቱንም አስታውቀዋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በዜጎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት የኦሮሞና አማራ ብሄሮችን ህዝብ ለማጋጨት የሚሹ ሀይሎች የፈጸሙት መሆኑንም ጀነራሉ ገልጸዋል ። (ኢ.ፕ.ድ)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply